JW subtitle extractor

አምላክ ስም አለው?

Video Other languages Share text Share link Show times

አምላክ ስም አለው?
መጽሐፍ ቅዱስ የብዙ አማልክትን ስም ይጠቅሳል።
በጥንቷ እስራኤል አጠገብ የሚኖሩ ብሔራት ከሚያመልኳቸው አማልክት መካከል
አስታሮት፣ በኣልና ሞሎክ ይገኙበታል።
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የሚኖሩ ክርስቲያኖችም በዙሪያቸው
እንደ አርጤምስ፣ ሄርሜስ እና ዙስ ያሉ ጣዖታትን የሚያመልኩ ሰዎች ነበሩ፤
የእነዚህ አማልክት ስም ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል።
መጽሐፍ ቅዱስ “ብዙ ‘አማልክት’” እንዳሉ ይናገራል።
ይሁንና ስሙ በጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱሶች ውስጥ
በብዛት የተጠቀሰ አንድ አምላክ አለ።
የሌሎቹ አማልክት ስሞች በአንድነት ቢደመሩ እንኳ
የዚህን አምላክ ስም ያህል አይሆኑም።
የሌሎቹ አማልክት ስሞች
ዘመናዊ በሆኑ መጽሐፍ ቅዱሶች ውስጥ ዛሬም ድረስ ይገኛሉ።
ሆኖም አብዛኞቹ መጽሐፍ ቅዱሶች
ከእነዚህ ይበልጥ ብዙ ጊዜ የተጠቀሰውን አምላክ ስም አውጥተውታል።
የዚህ አምላክ ስም በጥንቶቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ
7,000 ጊዜ ያህል ተጠቅሷል።
ለመሆኑ ስሙ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የወጣው
ይህ አምላክ ማን ነው?
ብዙውን ጊዜ ብሉይ ኪዳን ተብሎ የሚጠራው
የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተጻፈው
በዕብራይስጥና በአረማይክ ቋንቋ ነው።
በዕብራይስጥ የአምላክን ስም የሚወክሉት ፊደላት አራት ናቸው።
የዕብራይስጥ ጽሑፍ የሚነበበው
ከቀኝ ወደ ግራ ነው።
እነዚህ አራት ፊደላት በአማርኛ ሲቀመጡ
የ ሐ ወ ሐ ይባላሉ።
በዕብራይስጥ የአምላክን ስም ለመጥራት
ያገለግሉ የነበሩት አናባቢ ፊደላት አይታወቁም፤
ሆኖም የአምላክን ስም የሚወክሉት አራት ፊደላት
በጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱሶች ውስጥ
በብዙ ቦታዎች ላይ ተጠቅሰዋል።
በሌሎች ብዙ ቦታዎች ላይም ተጽፈው ይገኛሉ።
በአማርኛ የተለመደው የአምላክ ስም አጠራር
ይሖዋ ሲሆን ሌላው አጠራር ደግሞ ያህዌ ነው።
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች
በመዝሙር 83 ቁጥር 18 እና በሌሎች ብዙ ቦታዎች ላይ
ከእነዚህ ስሞች አንዱን ይጠቀማሉ።
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች
ለምሳሌ አዲስ ዓለም ትርጉም
የአምላክን ስም መጀመሪያ በነበረባቸው ቦታዎች ላይ
መልሰው አስገብተውታል።
አምላክ ስሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
7,000 ጊዜ ያህል እንዲጠቀስ ማድረጉ
ይህን ስም እንድናውቀውና እንድንጠቀምበት
የሚፈልግ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።
አምላክ ለእስራኤላውያን ሕጉን በሰጠበት ጊዜ
“እስራኤል ሆይ ስማ፣ አምላካችን ይሖዋ አንድ ይሖዋ ነው”
ብሎ እንዲጽፍ ለሙሴ ነግሮት ነበር።
ኢየሱስ ከሕጉ ላይ ይህን መጥቀሱ
የአምላክን የግል ስም ያውቅና ይጠቀም እንደነበር ያሳያል።
ከመሞቱ በፊት ባቀረበው አንድ ጸሎት ላይ ይሖዋ አምላክን
“ስምህን አሳውቄአቸዋለሁ” ብሎት ነበር።
አንድ ሰው ብዙ የማዕረግ ስም ሊኖረው ይችላል።
ለምሳሌ
ባል፣
አባት፣
መሐንዲስ ተብሎ ሊጠራ ይችላል፤
የግል ስምም ይኖረዋል፣
ለምሳሌ ዮሐንስ ሊባል ይችላል።
አምላክም ተስማሚ የሆኑ ብዙ የማዕረግ ስሞች አሉት፤
ሁሉን ቻይ፣
ፈጣሪ፣
ጌታ ተብሎ ይጠራል።
በተጨማሪም ሌላ ማንኛውም አምላክ የማይጠራበት ልዩ የሆነ ስም አለው።
ይህ ስም ይሖዋ ነው።
ግን እንዲህ የሚል ጥያቄ ይፈጠርብህ ይሆናል፦
ፈጣሪያችን ምን ዓይነት አምላክ ነው?
አምላክ ያስብልሃል?
ከአምላክ ጋር መቀራረብ የምትችለው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህና ለሌሎች ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ መማር ትፈልጋለህ?
jw.orgን እንድትጎበኝ እንጋብዝሃለን።