JW subtitle extractor

የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው?

Video Other languages Share text Share link Show times

የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ 66 ትናንሽ መጻሕፍትን ይዟል።
ከ3,500 ዓመታት በፊት
ሙሴ የመጀመሪያዎቹን መጻሕፍት ጻፈ።
በቀጣዮቹ 1,600 ዓመታት ደግሞ
40 የሚያህሉ ሰዎች፣
ቀሪዎቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ጻፉ።
መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ከሆኑ
እንዴት “የአምላክ ቃል” ሊባል ይችላል?
ለምሳሌ ያህል፣
አንድ ሥራ አስኪያጅ ደብዳቤ መላክ ፈለገ እንበል።
ደብዳቤውን ወይም ኢ-ሜይሉን ለማጻፍ
ጸሐፊውን ሊጠቀም ይችላል።
ሥራ አስኪያጁ መላክ የሚፈልገውን መልእክት ለጸሐፊው ይነግረዋል፤
ከዚያም ጸሐፊው በተነገረው ነገር ላይ ተመሥርቶ ኢ-ሜይሉን ያዘጋጃል።
ኢ-ሜይሉን የሚጽፈው ጸሐፊው ቢሆንም
የመልእክቱ ባለቤት እሱ አይደለም።
በተመሳሳይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች
መልእክቱን በራሳቸው መንገድ የገለጹ ቢሆንም
የመልእክቱ ምንጭ እነሱ አይደሉም።
ታዲያ የመልእክቱ ባለቤት ማን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ “ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ
በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው” ይላል።
ይሖዋ አምላክ በመንፈሱ ተጠቅሞ
እንዲተላለፍ የፈለገውን መልእክት እንዲያውቁ አድርጓል።
ይህን ያደረገው እንዴት ነው?
ይሖዋ፣ ነቢዩ ዳንኤል ተኝቶ ሳለ
ሕልም እንዲያልም አድርጓል።
እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል ያሉ ሌሎች ጸሐፊዎችን ደግሞ
ነቅተው ባሉበት ወቅት አስገራሚ ራእዮችን አሳይቷቸዋል።
ይሖዋ በመላእክት አማካኝነት መልእክቱን ያስተላለፈበት ጊዜም አለ፤
ለምሳሌ ለሐዋርያው ዮሐንስ።
ሆኖም ይሖዋ በእነዚህ መንገዶች መልእክቱን ሊያስተላልፍ ይችላል?
በዛሬው ጊዜ፣ በጣም ርቀው ለሚገኙ ሰዎች መልእክት ማስተላለፍ ተችሏል።
በሕዋ ላይ ካሉ ተመራማሪዎች ጋርም እንኳ መነጋገር ይቻላል።
ሰዎች ይህን ማድረግ ከቻሉ
ፈጣሪ ከዚህ የበለጠ ማድረግ አይችልም?
የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ሰዎች ሳይሆኑ አፍቃሪ የሆነው ፈጣሪያችን ይሖዋ ነው፤
በመሆኑም ልንተማመንበት እንችላለን።
ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ያለብን ለምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን ከየት ማንበብ እንጀምር?
መጽሐፍ ቅዱስ ተቀይሮ ወይም ተበርዞ ይሆን?
መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህና ለሌሎች ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ መማር ትፈልጋለህ?
jw.orgን እንድትጎበኝ እንጋብዝሃለን።