JW subtitle extractor

ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?

Video Other languages Share text Share link Show times

በታሪክ ዘመናት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል።
የአንድ ሰው ይኸውም የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ግን
ከሁሉም የተለየ ነው።
ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?
የእሱ ሞት የሚያስገኘው ጥቅም አለ?
መልሱን ለማግኘት የሰው ዘር ታሪክ
ወደጀመረበት ጊዜ መመለስ ያስፈልገናል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ አዳምን ኃጢአት የሌለበት
ፍጹም ሰው አድርጎ እንደፈጠረው ይናገራል።
አዳም በኤደን ገነት ካሉት ዛፎች ሁሉ መብላት ይችል ነበር።
ከአንዱ ዛፍ ፍሬ ግን እንዳይበላ ታዝዞ ነበር።
ይህ ዛፍ መልካምና ክፉ የሆነውን የመወሰን መብት ያለው
አምላክ መሆኑን የሚያመለክት ነበር።
አዳም ይሖዋን እስከታዘዘ ድረስ
በገነት ውስጥ ለዘላለም መኖር ይችል ነበር።
ይሁንና አዳም አምላክ ላደረገለት መልካም ነገር
አድናቆት አልነበረውም።
በመሆኑም አምላክን ላለመታዘዝ መረጠ።
በዚህም የተነሳ
ለዘላለም የመኖር አጋጣሚውን አጣ።
ይህ ድርጊቱ ችግር ያስከተለው
በራሱ ላይ ብቻ አይደለም።
ዘሮቹ በሙሉ ከእሱ በወረሱት ኃጢአት ምክንያት
ለሞት ተዳርገዋል።
የሰው ልጆች በራሳቸው ጥረት
ከኃጢአትና ከሞት ባርነት መላቀቅ አይችሉም።
የሚታደጋቸው ያስፈልጋቸዋል።
በመሆኑም ይሖዋ ፍጹም ከሆኑ መንፈሳዊ ልጆቹ መካከል አንዱ፣
ሰው ሆኖ ወደ ምድር እንዲመጣ አደረገ።
ኢየሱስ ልክ እንደ አዳም ፍጹም ሰው ነበር።
አዳም ዓምፆአል፤
ኢየሱስ ግን እስከ መጨረሻው ታማኝ ሆኗል።
ይህም “በብዙ ሰዎች ምትክ
ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ [እንዲሰጥ]” አስችሎታል።
ይሁንና የአንድ ሰው መሞት
መላውን የሰው ዘር ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?
የአንድ ትልቅ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ
የድርጅቱን ገንዘብ አጭበርብሮ ወሰደ እንበል።
በዚህ ሰውዬ ድርጊት የተነሳ ድርጅቱ ከስሮ ተዘጋ።
ሠራተኞቹ ሥራቸውን አጡ፤
ወጪያቸውንም መሸፈን አቃታቸው።
በአንድ ሰው የተነሳ ብዙዎች ለችግር ተዳረጉ።
አንድ ደግና ለጋስ ሰው
ችግር ላይ የወደቁትን ሰዎች ሲያይ በጣም አዘነላቸው።
የፋብሪካውን ዕዳ በመክፈል
መልሶ ሥራ እንዲጀምር አደረገ።
በዚህ መንገድ ሠራተኞቹንና ቤተሰቦቻቸውን
ከወደቁበት ችግር ታደጋቸው።
አዳም እንደ አጭበርባሪው ሥራ አስኪያጅ ነው።
በአምላክ ላይ ሲያምፅ በኃጢአት ዕዳ ውስጥ የተዘፈቀ ሲሆን
ለልጆቹም ይህንኑ አውርሷል።
ኢየሱስ ደግሞ እንደዚያ ደግ ሰው ነው።
ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን በመክፈል
የኃጢአት ዕዳችንን የሸፈነልን ሲሆን
ሁላችንም የዘላለም ሕይወት ተስፋ እንዲኖረን አድርጓል።
ግን እንዲህ የሚል ጥያቄ ይፈጠርብህ ይሆናል፦
ኢየሱስ የሚባል ሰው ኖሮ ያውቃል?
ለመዳን በኢየሱስ ማመን ብቻውን በቂ ነው?
ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህና ለሌሎች ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ መማር ትፈልጋለህ?
jw.orgን እንድትጎበኝ እንጋብዝሃለን።