JW subtitle extractor

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

Video Other languages Share text Share link Show times

ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት
ከየትኛውም ርዕሰ ጉዳይ ይበልጥ ያስተማረው
ስለ አምላክ መንግሥት ነው።
ለበርካታ መቶ ዘመናት፣ የኢየሱስ ተከታዮች
ይህ መንግሥት እንዲመጣ ሲጸልዩ ኖረዋል።
ለመሆኑ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
የአምላክ መንግሥት
ከሰብዓዊ መንግሥታት ጋር ይመሳሰላል።
ማንኛውም መንግሥት
ገዢ፣
የመንግሥቱ መቀመጫ የሆነ ቦታ፣
የሚገዛበት ክልል፣
ሕጎች
እንዲሁም ዜጎች አሉት።
የሚያሳዝነው፣ አብዛኞቹ ሰብዓዊ መንግሥታት
የሕዝባቸውን ፍላጎት ከማሟላት ይልቅ
የራሳቸውን ጥቅም በማሳደድ ላይ አተኩረዋል።
የአምላክ መንግሥት ግን ፍጹም የሆነ ገዢ አለው፤
እሱም አምላክ ንጉሥ እንዲሆን የመረጠው ኢየሱስ ነው።
አምላክ ከኢየሱስ ጋር አብረው የሚገዙ
ሌሎች ሰዎችንም መርጧል።
ይህ መንግሥት የሚገዛው በሰማይ ሆኖ ነው።
ይህን መንግሥት ያቋቋመው አምላክ ራሱ ነው።
የግዛት ወሰኑ መላውን ምድር ያጠቃልላል፤
በመሆኑም በብሔርተኝነት ምክንያት
የሚመጡ ችግሮች ይቀራሉ ማለት ነው።
በተጨማሪም ሕጉን የሚታዘዝ ማንኛውም ሰው
የዚህ መንግሥት ዜጋ መሆን ይችላል።
ይህ መንግሥት ለዜጎቹ ምን ጥቅም ያስገኝላቸዋል?
ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ የፈጸማቸው ተአምራት
የአምላክ መንግሥት ሲመጣ ምን እንደሚያከናውን የሚያሳዩ ናቸው።
ኢየሱስ ማዕበልን ጸጥ ማድረግ መቻሉ
ንጉሥ በሚሆንበት ወቅት የተፈጥሮ ኃይሎችን እንደሚቆጣጠርና
አካባቢያዊ ችግሮችን እንደሚያስወግድ ያሳያል።
በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን በተአምር መመገቡ
የአምላክ መንግሥት
ረሃብን ከምድር ላይ እንደሚያስወግድ ያሳያል።
ኢየሱስ ሕመምተኞችን፣ አንካሶችን፣
መስማት የተሳናቸውንና ዓይነ ስውራንን መፈወሱ
በእሱ አገዛዝ ሥር የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ
ፍጹም ጤንነት እንደሚኖራቸው የሚያሳይ ማስረጃ ነው።
እንዲሁም የሞቱ ሰዎችን በማስነሳት
የአምላክ መንግሥት ሞትን ጭምር ድል እንደሚያደርግ አሳይቷል።
ግን እንዲህ የሚል ጥያቄ ይፈጠርብህ ይሆናል፦
የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛው መቼ ነው?
በአሁኑ ጊዜ፣ ለአምላክ መንግሥት ድጋፌን ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህና ለሌሎች ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ መማር ትፈልጋለህ?
jw.orgን እንድትጎበኝ እንጋብዝሃለን።