JW subtitle extractor

አምላክ ምድርን የፈጠረው ለምንድን ነው?

Video Other languages Share text Share link Show times

ምድራችን በሚያስደምሙ ውብ ነገሮች የተሞላች ናት።
ለመሆኑ አምላክ ምድርን እንዲህ
ውብ አድርጎ የፈጠራት ለምንድን ነው?
ከጠፈር ሆነን ብንመለከታት እንኳ
ከሌሎች ፕላኔቶች ልዩ ናት።
አምላክ ምድርን የፈጠራት
በቂ ውኃ እንዲኖራት አድርጎ ነው።
ከፀሐይ በትክክለኛው ርቀት ላይ ትገኛለች፤
በዛቢያዋ ላይ የምትሽከረከርበት
ፍጥነትም ቢሆን የተስተካከለ ነው።
በትክክለኛው መጠን እንድታጋድል
ደግሞ ጨረቃን ፈጥሮላታል፤
ይህም የወቅቶች መፈራረቅ እንዲኖር አስችሏል።
በተጨማሪም በምድር ላይ የሚኖሩ
የተለያዩ አስደናቂ ፍጥረታትን ፈጥሯል።
አምላክ ይህን ያህል ተጠቦ
ምድራችንን የፈጠረበት ዓላማ ምንድን ነው?
ለመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት ማለትም ለአዳምና ለሔዋን
ውብ የሆነ መኖሪያ ሊሰጣቸው ስለፈለገ ነው።
አምላክን እስከታዘዙ ድረስ እነሱም ሆኑ ልጆቻቸው ለዘላለም መኖርና
መላዋን ምድር ገነት ማድረግ ይችሉ ነበር።
አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ይህ ነበር።
የአምላክ ዓላማ ይህ ከሆነ
ምድራችን ገነት ያልሆነችው ለምንድን ነው?
የሚያሳዝነው፣ አዳምና ሔዋን አምላክን ላለመታዘዝ መረጡ።
በመሆኑም ከጊዜ በኋላ አርጅተው ሞቱ።
ገነት የነበረችው መኖሪያቸውም ጠፋች።
ይህ ሲባል ታዲያ አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ
ተለውጧል ማለት ነው?
አንድ አባት ለልጁ የሚያምር ቤት ሊሠራለት አሰበ እንበል።
ቤቱን ከሠራ በኋላ ለልጁ በስጦታ መልክ ይሰጠዋል።
ልጁ ግን አባቱ ለሰጠው ስጦታ አመስጋኝ ከመሆን ይልቅ
አላግባብ ስለያዘው ቤቱ ተበላሽቶ መጥፎ ሁኔታ ላይ ወደቀ።
በዚህ ጊዜ አንድ አፍቃሪ አባት ምን ያደርጋል?
እንደዚያ የለፋበትን ቤት ያፈርሰዋል?
በፍጹም፣ ቤቱን አድሶ አድናቂ ለሆነ ሌላ የቤተሰቡ አባል ይሰጠዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አዳም ለስጦታው አድናቆት ባያሳይም
አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ እንዳልተቀየረ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
አሁንም ቢሆን ዓላማው ያው ነው።
ገነት የሆነችውን ምድር ለአንተ ሊሰጥህ ይፈልጋል፤
የአምላክ ዓላማ በዚች ምድር ላይ ጤናማና
ደስተኛ ሆነህ ለዘላለም እንድትኖር ነው!
ግን እንዲህ የሚል ጥያቄ ይፈጠርብህ ይሆናል፦
አምላክ ምድርን እንደገና ገነት የሚያደርጋት እንዴት ነው?
ምድር ላይ ለዘላለም ለመኖር ምን ማድረግ ይጠበቅብሃል?
መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህና ለሌሎች ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ መማር ትፈልጋለህ?
jw.orgን እንድትጎበኝ እንጋብዝሃለን።