JW subtitle extractor

አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?

Video Other languages Share text Share link Show times

አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?
ይሖዋ አምላክ ሰዎችን የፈጠረው
መከራ እንዲደርስባቸው አስቦ አልነበረም።
እንዲያውም የመጀመሪያዎቹን ሰዎች የፈጠራቸው
ሕይወታቸው እጅግ አስደሳች እንዲሆን አድርጎ ነው።
ሆኖም ሰይጣን የተባለ ዓመፀኛ መልአክ
አምላክ ውሸታም እንደሆነ በመናገር
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በአምላክ ሥልጣን ላይ እንዲያምፁ አደረገ።
አዳምና ሔዋን አምላክን አንታዘዝም ሲሉ
ሰይጣንን ለመከተል መምረጣቸው ነበር።
አዳምና ሔዋን በይሖዋ ላይ ያመፁ ሲሆን
ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር በራሳቸው መወሰን ፈለጉ።
ታዲያ ሰይጣን እንደተናገረው
ሰዎች ያለ አምላክ እርዳታ ራሳቸውን በተሳካ መንገድ መምራት ይችሉ ይሆን?
ከእነዚህ ዓመፀኞች ጋር በተያያዘ ለተነሳው ወሳኝ ጥያቄ
መልስ ለማግኘት ጊዜ ያስፈልግ ነበር።
ይህን በምሳሌ ለማስረዳት፦
አንድ ዓመፀኛ ተማሪ አስተማሪው አንድን ስሌት የሠራበት መንገድ
ትክክል አይደለም ብሎ ተከራከረ እንበል።
እንዲያውም እሱ ከዚህ እጅግ በተሻለ መንገድ
ስሌቱን መሥራት እንደሚችል ተናገረ።
አንዳንድ ተማሪዎች ልጁ ትክክል እንደሆነ በማሰብ
እነሱም በአስተማሪው ላይ ዓመፁ።
ታዲያ አስተማሪው ምን ቢያደርግ ይሻላል?
ያመፀውን ልጅ ከክፍል ማባረር ይችላል።
ግን እንዲህ ቢያደርግ ሌሎቹ ተማሪዎች ምን ይሰማቸዋል?
መሳሳቱ እንዳይታወቅበት ሲል ልጁን እንዳባረረው ሊሰማቸውና
ለአስተማሪው ያላቸውን አክብሮት ሊያጡ ይችላሉ።
ሆኖም አስተማሪው ልጁ ስሌቱን በፈለገው መንገድ
በተማሪዎቹ ፊት እንዲሠራ ፈቀደለት እንበል።
ይህን ማድረጉ የማስተማር ብቃት ያለው ማን እንደሆነ
ሁሉም ተማሪዎች በግልጽ እንዲያዩ ያደርጋል።
ይሖዋም ያደረገው ነገር
ይህ አስተማሪ ካደረገው ነገር ጋር ይመሳሰላል።
ሰይጣን ይሖዋን ሲገዳደረው
በሚሊዮን የሚቆጠሩ መላእክት ይመለከቱ ነበር።
ይሖዋ ጉዳዩን የሚይዝበት መንገድ
በእነዚህ መላእክት ውሎ አድሮ ደግሞ
በሁሉም የሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።
ይሖዋ ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት
ሰይጣን ለተወሰነ ጊዜ ዓለምን እንዲገዛ ፈቀደለት።
የሰይጣን አገዛዝ
ይህ ነው የማይባል መከራና ችግር አስከትሏል።
የይሖዋ አገዛዝ ትክክለኛ መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ከተረጋገጠ በኋላ ግን
ይሖዋ የሰይጣን ዓመፅ ያስከተለውን ችግር በሙሉ ያስተካክላል።
በዚያ ጊዜ በምድር ላይ የሚኖሩት
በአምላክ መሥፈርቶች ለመመራት ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ይሆናሉ።
እስከዚያው ግን፣ መከራ ሲደርስብህ ምን ይረዳሃል?
መጽናኛ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህና ለሌሎች ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ መማር ትፈልጋለህ?
jw.orgን እንድትጎበኝ እንጋብዝሃለን።