JW subtitle extractor

አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች ይቀበላል?

Video Other languages Share text Share link Show times

ብዙ ሰዎች የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ብትሆን
ለውጥ እንደሌለው ይናገራሉ፤
ምክንያቱም ሁሉም ሃይማኖቶች ወደ አምላክ የሚያደርሱ
የተለያዩ መንገዶች እንደሆኑ ያምናሉ።
ሆኖም ይህ እውነት ነው?
አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች ይቀበላል?
መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት መንገዶች ብቻ እንዳሉ ይናገራል፦
አንዱ ሰፊና ብዙ ሰዎች የሚሄዱበት ሲሆን
ሌላው ደግሞ ጠባብና ጥቂቶች የሚሄዱበት ነው።
በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የሚኖራቸውና ሕይወት የሚያገኙት
በጠባቡ መንገድ ላይ የሚሄዱት ብቻ ናቸው።
ታዲያ በትክክለኛው መንገድ ላይ እየተጓዝን እንዳለን
ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
ወደ አንድ ቦታ ስትጓዝ መንገድ ጠፋብህ እንበል።
በመሆኑም ሰዎችን ለመጠየቅ ትወስናለህ።
አንደኛው ሰው ወደ ምሥራቅ ሂድ ይልሃል።
ሌላኛው ደግሞ ወደ ምዕራብ ሂድ ይልሃል።
በመጨረሻም አንድ ሰው
ካርታ በማሳየት
ትክክለኛው አቅጣጫ ወደ ሰሜን እንደሆነ ይነግርሃል።
ታዲያ የትኛውን ታምናለህ?
መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደ ካርታ፣
ወደ አምላክ የሚወስደውን ትክክለኛ መንገድ ይጠቁመናል።
ታዲያ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ
በርካታ ሐሳቦች የኖሩት ለምንድን ነው?
ለምሳሌ ብዙ ሃይማኖቶች ሰው ከሞተ በኋላ
ነፍሱ ወደ መንፈሳዊው ዓለም ሄዳ
ለዘላለም መኖሯን እንደምትቀጥል ያስተምራሉ።
ሌሎች ደግሞ ሌላ አካል ለብሰው
ዳግመኛ እንደሚወለዱ ያምናሉ።
ይህ እርስ በርሳቸው ከሚጋጩ
በርካታ ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ውስጥ አንዱ ብቻ ነው።
ታዲያ ሁሉም ሃይማኖቶች
እውነቱን ያስተምራሉ ሊባል ይችላል?
ካርታችን የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ
ሙታን ምንም እንደማያውቁ ያስተምራል።
ወደፊት አምላክ ከሞት የሚያስነሳቸው ሲሆን
ጻድቅ የሆኑ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ልናሳይ ከሚገባን ምግባር ጋር በተያያዘስ
ግልጽ የሆነ ትምህርት ይሰጥ ይሆን?
ሃይማኖተኞች ብንሆንም ምግባራችን አምላክን የማያስደስት ከሆነ
አምልኳችን ከንቱ ሊሆን ይችላል።
መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ሰዎች
“ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ ጥሩ ነገር የማይወዱ” እንደሆኑ ይናገራል።
እውነተኛዎቹ የአምላክ አገልጋዮች ግን ሰላማዊ እንደሆኑ፣
የታረመ ንግግር እንዳላቸውና
መልካም ምግባር እንደሚያሳዩ ይገልጻል።
መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው አምላክን የሚያስደስቱ
ብዙ ሃይማኖቶች እንዳሉ ሳይሆን
አንድ እምነት ብቻ እንዳለ ነው።
እውነተኛው ሃይማኖት ሰዎችን
ወደ አምላክና ወደ ዘላለም ሕይወት ይመራል።
ሆኖም ‘እውነተኛውን ሃይማኖት
ለይተህ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?’
አምላክን ለማስደሰት የግድ የአንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት አባል መሆን ያስፈልግሃል?
መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህና ስለ ሌሎች በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ምን እንደሚል ለማወቅ
jw.orgን ተመልከት።