JW subtitle extractor

ጄምስ ማንትስ፦ ‘በዓይነቱ ልዩ የሆነውን ዘመን’ እየተቋቋሙ ሌሎችን ማጽናናት

Video Other languages Share text Share link Show times

የዛሬው ንግግራችን ጭብጥ የተመሠረተው በ2 ቆሮንቶስ 1፡3-4 ላይ ነው።
“የምሕረት አባትና የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሆነው
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይወደስ፤
እኛ ከአምላክ በምናገኘው መጽናኛ
በማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ማጽናናት እንድንችል
እሱ በሚደርስብን መከራ ሁሉ ያጽናናናል።”
ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ ሁላችንም ማጽናኛ ያስፈልገናል።
ገና ጨቅላ እያለን ርቦን፣ ምቾት የነሳን ነገር ኖሮ
ወይም ወላጆቻችን እንዲያቅፉን ፈልገን
ለመጀመሪያ ጊዜ ያለቀስንበትን ወቅት ማናችንም አናስታውሰውም።
አሁን ግን ሁላችንም ማጽናኛ የፈልግንበትን ጊዜ እናስታውሳለን።
ብዙ ችግሮች ስለሚያጋጥሙን።
መዝሙር 90፡10 ከፍጽምና የራቀውን ሕይወታንን ጥሩ አድርጎ ይገልጸዋል።
“የዕድሜያችን ርዝማኔ 70 ዓመት ነው፤
ለየት ያለ ጥንካሬ ካለን ደግሞ 80 ዓመት ቢሆን ነው።
ይህም በችግርና በሐዘን የተሞላ ነው።
ፈጥኖ ይነጉዳል፤ እኛም እናልፋለን።”
የሚያሳዝኑን፣ የሚያስከፉን፣ የሚያሳምሙም የተለያዩ ሁኔታዎች በየጊዜው ያጋጥሙናል።
አንዳንዶቹ ችግሮች የጋራ ናቸው።
ፍጹም ስላልሆን ማናችንም ከእነሱ አናመልጥም።
ከሕመም፣
ከእርጅና
ወይም የምንወደውን ሰው በሞት ከማጣት።
አንዳንዶቹ ችግሮች ግን ሁሉንም ሰው የሚያጋጥሙ አይደሉም።
ጊዜና አጋጣሚ የሚያመጣቸው ናቸው።
ለምሳሌ አደጋዎች፣ የኢኮኖሚ ችግር፣
የትዳር መፍረስ፣
የተፈጥሮ አደጋዎች፣
የወንጀል ጥቃት፣
ሕዝባዊ ዓመጽና ጦርነት።
በተጨማሪም ከአምልኳችን ጋር በተያያዘ ማጽናኛ ሊያስፈልገን ይችላል።
በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤት ውስጥ መኖር
ስደት ወይም እስር ሊያጋጥመን ይችላል።
ወይም ደግሞ በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ቦታችን
ሰዎች ሊያሾፉብን ይችላሉ።
የቤተሰባችን አባል ወይም የቅርብ ጓደኛችን ይሖዋን ሊተውም ይችላል።
ንስሐ የገቡ ኃጢአተኞችም ወደ ጉባኤ ሲመለሱ ማጽናኛ ያስፈልጋቸዋል።
ያጋጠመን ሁኔታ የጋራ ችግር፣
ጊዜና አጋጣሚ ያመጣው ወይም ከእምነታችን ጋር የተያያዘ ይሆናል።
ሁላችንም ማጽናኛ ያስፈልገናል።
ችግሮቹ ዓለም አቀፋዊ ስለሆኑ።
አንደኛ ጴጥሮስ 5፡9 እንደሚለው
በዓለም ዙሪያ በመላው የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ያሉ ወን ድሞቻችን
ተመሳሳይ መከራ እየደረሰባቸው እንሆነ መገንዘብ አለብን።
ሆኖም ቁጥር 6 እና 7 ማጽናኛ የሚሰጠን ማን እንደሆነ ይነግረናል።
እንዲህ ይላል፦
“ስለዚህ በተገቢው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ
ከኃይለኛው የአምላክ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤
የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ፤
ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።”
ምንጊዜም ቢሆን የእውነተኛ መጽናኛ ምንጭ ይሖዋ ነው።
ሙሴ የሚያጋጥመው ሁኔታ ምንም ይሁን ምን
ይሖዋ እንደሚደግፈውና እንደሚያጽናናው እርግጠኛ ነበር።
በመሆኑም በእርግጠኝነት
ዘዳግም 33፡27 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ጽፏል፦
“አምላክ ከጥንት ጀምሮ መሸሸጊያ ነው፤
ዘላለማዊ ክንዶቹ ከበታችህ ናቸው” ብሏል
ስሜታችን ተደቁሶ ቀና ማለት ሲያቅተን
ይሖዋ እጆቹን ከሥራችን አስገብቶ
ቀስ ብሎ ያነሳናል።
በሁለት እግራችን እንድንቆም ያደርገናል።
ከይሖዋ የምናገኘው እንክብካቤና ማጽናኛ
በመዝሙር መጽሐፍ ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።
ለምሳሌ የመዝሙር 94፡19 ጸሐፊ
ለይሖዋ ያለውን አመስጋኝነት እንዲህ በማለት ገልጿል፦
“በጭንቀት በተዋጥኩ ጊዜ አጽናናኸኝ።
አጽናናኸኝ። ደግሞም አረጋጋኸኝ።”
ሮም 15፡4ም እንዲህ የሚል ማረጋገጫ ይሰጠናል።
“በምናሳየው ጽናትና ከቅዱሳን መጻሕፍት በምናገኘው መጽናኛ
ተስፋ ይኖረን ዘንድ ቀደም ብሎ የተጻፈው ነገር ሁሉ
ለእኛ ትምህርት እንዲሆን ተጽፏልና።”
የጭንቀታችን መንስዔ ምንም ይሁን ምን
ምንጊዜም የሚያጽናኑ ጥቅሶችን ማግኘት እንችላለን።
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት የሚለው መጽሐፍ
በውስጡ “ማጽናኛ” የሚል ርዕስ አለው።
ይሄ ጽሑፍ ተስፋ እንድንቆርጥ የሚያደርጉ ምክንያቶችን ብቻ ሳይሆን
በአምላክ ቃል ውስጥ ያሉ ምሳሌዎችንም ይጠቅሳል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት እነዚህ ሰዎች
እንደ እኛው ዓይነት ችግር እንዳጋጠማቸውና
ይሖዋ እንዴት እንደረዳቸው ይነግረናል።
ከይሖዋ ማጽናኛ ለማግኘት ማድረግ ያለብን ዋነኛው ነገር
እሱ እንዲረዳን መጠየቅ ነው።
መዝሙር 145 ላይ ንጉሥ ዳዊት
ይሖዋ ጸሎቱን ስለመለሰለት እንዲህ ብሎ ለማወደስ ተገፋፍቷል።
ቁጥር 18 እና 19ን አብረን እናንብብ።
ዳዊት እንዲህ ብሏል፦
“ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።
የሚፈሩትን ሰዎች ፍላጎት ያረካል፤
እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማል፤
ደግሞም ይታደጋቸዋል።”
አንድ አፍቃሪ ወላጅ እያለቀሰ የሚለምነውን ልጁን ለመርዳት እንደሚነሳሳው ሁሉ
አምላካችን ይሖዋም በርኅራኄ ተነሳስቶ
ለእርዳታ የምናቀርበውን ጩኸት ይሰማል።
አንደኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 1 እና 2 ላይ ያለው ታሪክ
ሐና የተባለች እስራኤላዊት ሴት ይሖዋ ልጅ ስላልሰጣት
መብላት እስኪያቅታት ደረስ በጣም ተጨንቃና ተመርራ እንደነበር ይነግረናል።
በጭንቀት የተዋጠችው ሐና በዚህ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዳ
ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ወደ ይሖዋ ጸለየች።
ይሖዋም ጸሎቷን ሰምቶ
ለዚህች ትሑት ሴት መልስ ሰጣት።
ከዚያም ሐና ተነስታ ሄደች።
ምግብም በላች።
ዳግመኛም በፊቷ ላይ ሐዘን አልታየም።
በተመመሳሳይም ይሖዋ እኛንም ያጽናናናል።
የልባችንን አውጥተን ጭንቀታችንን በጸሎት ከነገርነው።
የአምላክ ቃል 2 ቆሮንቶስ 1፡3-4 ላይ ያለውን
የዚህ ንግግር ጭብጥ የተመሠረተበትን ጥቅስ ጨምሮ
ስለ መጽናኛ የሚናገር ብዙ ሐሳብ ይዟል።
ጭብጡ የተመሠረተበትን ጥቅስ እባካችሁ አብረን እናንብበው።
ይህን ጥቅስ ደግመን ስናነበው
እኛ በግለሰብ ደረጃ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ተቋቁመን
ሌሎችን እንዴት በእነዚህ ቃላት ማጽናናት እንደምንችል ለማስተዋል ጥረት አድርጉ።
2 ቆሮንቶስ 1፡3-4 እንዲህ ይላል፦
“የምሕረት አባትና የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሆነው
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይወደስ፤
እኛ ከአምላክ በምናገኘው መጽናኛ
በማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ያሉትን ሰዎች
ማጽናናት እንድንችል እሱ በሚደርስብን መከራ ሁሉ ያጽናናናል።”
ከርኅራኄ የመነጨ ምሕረት ሌሎች የሚደርስባቸውን ሥቃይ አይቶ ማዘንን ያመለክታል።
ይሖዋ የአገልጋዮቹን ሥቃይ ሲመለከት
የሚሰማውን የመንሰፍሰፍ ስሜት ጥሩ አድርጎ ይገልጻል።
ጳውሎስ በመቀጠል ይሖዋን
“የመጽናናት ሁሉ አምላክ” ብሎታል።
ስለዚህ ይሖዋ የሁሉም መጽናኛ ምንጭ ነው።
ቁጥር 4 ይሖዋ የሚያጽናናበትን አንድ ልዩ መንገድ ይጠቁመናል።
ይህም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ናቸው።
ጥቅሱ ደግመን እናንብበው። እንዲህ ይላል፦
“እኛ ከአምላክ በምናገኘው መጽናኛ
በማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ያሉትን ሰዎች
ማጽናናት እንድንችል እሱ በሚደርስብን መከራ ሁሉ ያጽናናናል።”
ዝምድናቸውን አስተዋላችሁ?
እኛ ራሳችን ማጽናኛ ስናገኝ
ሌሎችንም ማጽናናት እንችላለን።
ይሖዋ እኛን ያጽናናናል።
እኛ ደግሞ በእሱ አምሳል የተፈጠርን ስለሆንን
በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ልክ እንደ እሱ ሌሎችን እናጽናናለን።
ስለዚህ ክርስቲያኖች በሁለት ቡድን የተከፈሉ አይደሉም።
ማጽናኛ የሚሰጡና
የሚቀበሉ ተብለው።
ከዚህ ይልቅ ሁላችንም ሌሎችን የማጽናናት ግዴታ አለብን።
እኛ ራሳችን እንኳ
ማጽናኛ የሚያስፈልገንም ቢሆን።
ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
ጳውሎስን እንደ ምሳሌ እንመልከት።
ጳውሎስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሮም ሲታሠር
የብርታት ምንጭ ለሆኑለት በርካት ወንድሞች
ልባዊ ምስጋና አቅርቧል።
ስላጽናኑት።
ቆላስይስ ምዕራፍ 4 ላይ አንዳንዶቹን በስም ጠቅሷቸዋል።
አርስጥሮኮስን፣
ቲኪቆስንና
ማርቆስን።
በዚህ ፕሮግራም ላይ ስለ እነዚህ ወንድሞች ተጨማሪ የምንማረው ነገር ይኖረናል።
ጳውሎስ እነዚህ ወንድሞች እሱን ለመጎብኘትና
በቃልም ሆነ በተግባር ለማጽናናት ላደረጉት ጥረት አመስጋኝ ነበር።
ግን ጳውሎስ ማጽናኛ ተቀባይ ብቻ አልነበረም።
ከዚህ ይልቅ እሱን ሊጎበኙ የመጡትን እምነታቸውን ለመገንባት
እንዲሁም ጉባኤዎችን ለማበረታታት ደብዳቤ በመጻፍ
ጊዜውን በሚገባ ተጠቅሞበታል።
በደቡብ አፍሪካ የምትኖር ክሎዲያን የተባለች እህታችን
ከባድ ቀዶ ጥገና ባደረገችበት ጊዜ የጳውሎስን ምሳሌ ተከትላለች።
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት
ያለችበት ሄዶ የሚጠይቃት ሰው አልነበረም።
ክሎዲያን ግን ስለ ራሷ ብቻ እያሰበች መቆዘም አልፈለገችም።
ከዚህ ይልቅ አምላክ ሌሎችን ማጽናናት እንድትችል እንዲረዳት ጠየቀችው።
ክሎዲያን ጥናቷን አቁማ የነበረች ሴት ጋር ደወለች።
ሴትዮዋ ጥናቷን ቀጠለች።
በኢንተርኔት አማካኝነትም ጉባኤ ላይ ትገኝ ጀመር።
በኋላም ክሎዲያን የሴትዮዋን ታናሽ እህት ማስጠናት ጀመረች።
እሷም ማጥናት የሚፈልጉ የአራት ሴቶች ስም ሰጠቻት።
ክሎዲያን ከሕመሟ ጋር እየታገለች ሌሎችን ለማጽናናት ጽኑ አቋም በመያዟ
በአጠቃላይ ከ16 ሴቶች ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መጀመር ችላለች።
አንድንድ ጊዜ ግን ተጨንቀው ማጽናኛ የሚፈልጉ ሰዎችም
ከሌሎች እርዳታ መቀበል ሊከብዳቸው ይችላል።
ለምሳሌ ሙሴ፣ እስራኤላውያንን አምላክ ከግብጽ ባርነት ነፃ እንደሚያወጣቸው ሲነግራቸው
ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሳ አላዳመጡትም።
በኋላ ላይ ግን ተቀብለውታል።
እስቲ ሌላ ምሳሌ ደግሞ እንመልከት።
የስሟ ትርጉም ደስታዬ የሆነው ናኦሚ
በእስራኤል በተከሰተው ረሃብ ምክንያት በባዕድ አገር ትኖር ነበር።
በኋላም ባሏንና ሁለት ልጆቿን በሞት ስላጣች ከፍተኛ ሐዘን ላይ ወደቀች።
ወደ እስራኤል በተመለሰች ጊዜ በቤተልሔም ያሉ ሴቶች
“ይህች ናኦሚ አይደለችም እንዴ?” ማለት ጀመሩ።
በዚህ ጊዜ ናኦሚ በሕይወቷ ውስጥ ለደረሰባት ነገር ሁሉ ይሖዋን ተጠያቂ በማድረግ
“ናኦሚ ብላችሁ አትጥሩኝ። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ
ሕይወቴን መራራ አድርጎታናል ማራ ብላችሁ ጥሩኝ ትል ነበር።”
ሆኖም ከይሖዋ ሕዝቦች ጋር ተቀራርባ የተደረገላትን
ፍቅራው እርዳታ በመቀበሏ
ምሬቷ
ወደ ደስታ ተቀየረ።
በሐዘን ስንዋጥ ከሌሎች ተለይተን
ከሌሎች ተለይተን ብቻችንን እንድንሆን
የሚገፋፋንን ስሜት መታገል ይኖርብናል።
ይህ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
ቢሆንም ከተሞክሮ እንደታየው
በዚህ ጊዜ ከሌሎች ጋር ለመሆን የምናደርገው ጥረት ይሖዋ
ወንድሞችና እህቶች በርኅራኄ ተነሳስተው
በሚናገሯቸው ቃላትና በሚደርጓቸው ነገሮች
እኛን ማጽናናት እንዲችል አጋጣሚ ይሰጠዋል።
በመከራ ወቅት ይሖዋ የሚሰጠን ማጽናኛ
እኛም ሌሎችን ችግር በሚያጋጥማቸው ጊዜ ቶሎ እንድንደርስላቸው ያሠለጥነናል።
ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።
ሌሎችን ለማጽናናት።
እርዳታ የሚያስፈልጋቸው እነማን እንደሆኑ ማስተዋልና
ትኩረት መስጠት አለብን።
አብዛኛውን ጊዜ
ችግሩ ግልጽ ነው።
ወንድማችን ሥራውን አጥቶ፣
አደጋ ደርሶበት
የቅርብ ጓደኛው አሊያም የቤተሰቡ አባል ሞቶ ይሆናል።
በሌላ ጊዜ ግን ችግሩ በግልጽ የሚታይ ላይሆን ይችላል።
ባሕርያቸው እንደተለወጠ አስተውለን ይሆናል።
ወይም ደግሞ ፊታቸው ላይ የምናነበው ነገር ችግር እንዳለ ይጠቁማል።
መጫን ባንፈልግም
በደግነት ቀርበን ስሜታቸን ለመረዳት ጥረት ማድረግ እንችላለን።
እንዲህ ያሉ ወንድሞች ስሜታቸውን አውጥተው ለመንገር ጊዜ ያስፈልጋቸው ይሆናል።
ስለዚህ ታጋሽ መሆን አለብን።
ማጽናና ለመስጠት የሚያስፈልገው ሁለተኛው ነገር
ማድረግ ያለብንን ነገር እንድናውቅ መጸለይ ነው።
ያስጨነቃቸውን ወይም የደቆሳቸውን ነገር ለማስወገድ ምንም ነገር ማድረግ አንችል ይሆናል።
ለምሳሌ ያህል፣ ለረጅም ዓመታት በሚስዮናዊነት ያገለገለ ወንድም
ሚስቱን በሞት ባጣ ጊዜ እንዲህ ብሏል፦
“ማዘኔን ማቆም ሳይሆን መጽናት ነው የምፈልገው።”
ምሳሌ 3፡27 ላይ ያለውን ምክር ተግባራዊ ማድረጋችን አስፈላጊ ነው።
እንዲህ ይላል፦
“ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል አቅም ካለህ
ለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትበል።”
ምን ማድረግ ወይም መናገር እንዳለብን ግራ ይገባን ይሆናል።
በዚህ ጊዜ ማጽናኛ የሚለው ግሪክኛ ቃል ባለው ትርጉም ላይ ማሰላሰላችን በጣም ይጠቅመናል።
የቃሉ ቀጥተኛ ፍቺ “ከጎኔ ሁን” ማለት ነው።
በሌላ አባባል ሦስተኛውን እርምጃ እንውሰድ።
ከጎናቸው መሆናችንን እናሳይ።
ብዙ መናገር እንደሚያስፈልገን አናስብ።
ወንድሞቻችን የሚፈልጉት የሚያስብላቸው ሰው እንዳለ ማወቅ ብቻ ነው።
አብረናቸው መሆናችን ብቻ ያጽናናቸዋል።
የሚያዋራቸው ሰው ብቻ ይሆናል የሚልጉት።
ይህ ከሆነ
ጥሩ አዳማጭ ሁኑ።
ጥቅስ የማንበብ አጋጣሚ ካገኛችሁ ከጥቅሱ ላይ
ስለ ሁኔታው ይሖዋ ምን እንደሚሰማው ለማጉላት ጥረት አድርጉ።
ሌሎችን ስናጽናና ብዙውን ጊዜ ለውጥ የሚያመጣው
የምንናገረው ወይም የምናደርገው ነገር ሳይሆን
ሥቃያቸውን መረዳታችንና ማዘናችን ነው።
ለምሳሌ በኮቪድ ወቅት በዋናው ቢሮ የምታገለግል አንዲት እህታችን
ሁለቱንም ወላጆቿን በሞት አጣች።
በጠና ከታመመች እናቷ ጋር ቀኑን ሙሉ ሆስፒታል ቆይታ ስትመጣ
ክፍሏ ውስጥ በፍራፍሬዎች የተሞላ ትልቅ ቅርጫት አየች።
አብረዋት የሚሠሩ ቤቴላውያን ነበሩ ያስቀመጡት።
እንዲህ ብላለች፦
“ቁም ነገሩ የፍራፍሬዎቹ ዓይነት
ወይም በሚያምር ሁኔታ መቀመጣቸው አልነበረም።
ስጦታው የወንድሞቼን ፍቅርና አሳቢነት የሚያሳይ መሆኑ ነው።
ያጽናናኝ ወንድሞችና እህቶቼ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጎኔ መሆናቸውን ማወቄ ነው።”
መጋቢት 2011 ላይ የመሬት መንቀጥቀጥና ሱናሚ ምሥራቅ ጃፓንን መትቷት ነበር።
በጃፓንና ሌሎች አገሮች የሚገኙ ወንድሞች አፋጣኝ ምላሽ ሰጥተዋል።
ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ
እኔና ባለቤቴ በዚያ አካባቢ የሚገኙ ብዙ ጉባኤዎችን ጎብኝተናል።
በኔፓል የሚገኙ ወንድሞች ለአንድ ጉባኤ የማጽናኛ መልእክት ልከው ነበር።
በሌላ ጉባኤ ደግሞ ወንድሞች በፊሊፒንስ በሚነገሩ ቋንቋዎች የተጻፉ መልእክቶች የያዘ ሰሌዳ አሳዩን።
ወንድሞች እንዲህ ብለዋል፦
“ጽሑፎቹን ማንበብ አንችልም። ምን እንደሚሉ ግን እናውቃለን።”
እነዚያ መልእክቶች አጫጭር ቢሆኑም ወንድሞቻችንን አጽናንተዋቸዋል።
እዚያው እያለን ሃያል የተባለ ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ ፊሊፒንስን አወደማት።
አውሎ ነፋሱን በተመለከተ የጃፓን ወንድሞች እንዲህ ብለዋል።
“አሁን በፊሊፒንስ ያሉ ወንድሞቻችንን ማጽናናት የእኛ ተራ ነው።”
ደግሞም የዚህ ሥርዓት መጥፊያ ይበልጥ እየቀረበ በሄደ መጠን
ማጽናኛ ይበልጥ ይበልጥ እያስፈለገን ይሄዳል።
የምሕረት አባት የሆነው አምላካችን የመጽናናትሁሉ አምላክም ስለሆነ
ሁላችንም በጣም አመስጋኞች ነን።
ይሖዋ በልግስና የጸሎት መብት ሰጥቶናል።
እንዲሁም በማጽናኛ የተሞላውን ቃሉንና
አፍቃሪ የሆነ ዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር ሰጥቶናል።
ከእነዚህ ዝግጅቶች በምንጠቀምበት ጊዜ ሁሉ
ማጽናኛ የሚያስፈልጋቸውን በንቃት መከታተላችንን አንርሳ።
ምን ዓይነት ተግባራዊ እርዳታ ልንሰጥ እንደምንችል እናስብ።
ያለንበትን አስጨናቂ ጊዜ እየተቋቋምንም
ሌሎችን ለማጽናናት አስፈላጊውን ሁሉ ማድረጋችንን እንቀጥል።