JW subtitle extractor

ለመንፈሳዊ ስብሰባዎች አድናቆት የነበራቸው ሰማያዊ ለባሾች

Video Other languages Share text Share link Show times

በ1960ዎቹ ደቡብ አፍሪካ በአጎራባች አገሮች በሚደረጉ
ወታደራዊ ግጭቶች ይበልጥ መሳተፍ ጀመረች።
መንግሥትም ብዙ ወጣት ወንድሞች
ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስገደድ ጀመረ።
ብዙዎች በገለልተኝነት አቋማቸው
ምክንያት እስር ቤት ተጣሉ።
መጀመሪያ ላይ ወንድሞች በወታደራዊ እስር ቤት ሲታሰሩ
የወታደር ዩኒፎርም እንዲለብሱ ይጠበቅባቸው ነበር።
እነሱ ግን ፈቃደኛ አልነበሩም።
ወንድሞች ልብሱ እስስራ ላይ ካሉ ወታደሮች ጋር
እንደሚያመሳስላቸው ስለተሰማቸው ላለመልበስ ወሰኑ።
በዚህ ምክንያት ሰማያዊ ቱታ ይለብሱ ስለነበር
“ሰማያዊ ለባሾቹ” ተባሉ።
ሁሉም ሰው ሰማያዊ ለባሾቹ የይሖዋ ምሥክሮች እንደሆኑ ያውቅ ነበር።
መጀመሪያ ላይ ወንድሞች ይታሰሩ የነበረው
ለየብቻቸው ስለነበር ለአምልኮ አንድ ላይ
መሰብሰብ በጣም አስቸጋሪ ሆኖባቸው ነበር።
በወቅቱ ከነበሩት ወንድሞች መካከል አንዱ ዴቪድ ካሪካስ ነው።
በቅርቡ ዴቭና እኔ በእስር ቤት ስላጋጠሙን ነገሮች ተጨዋውተን ነበር።
እስር ቤት በገባሁበት ወቅት እርስ በርስ እንዳናወራ ተከልክለን ነበር።
አብዛኛውን ጊዜ የምናሳልፈው ለየብቻችን ታስረን ነው።
ዓላማቸው ታማኝነታችን እንድናጓድል ማድረግ ነው።
የታሰርንበት ቦታ በሁለት ረድፍ 64 ክፍሎች ነበሩት።
እንደ መቀመጫ እንዲያገለግለን ከበሮቹ በላይ ባለው የብረት ፍርግርግ ላይ
አንሶላችንን ካሰርን በኋላ ጸጥ በሚልበት የሌሊቱ ክፍለ ጊዜ
እዚያ ላይ ተቀምጠን ስብሰባችንን እናደርጋለን።
በዚህ መንገድ የተለያዩ ስብሰባዎችን አድርገናል።
የሕዝብ ንግግርና ቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ጭምር።
ግን ሌሎች ድምፃችንን እንዳይሰሙ እንጠነቀቃለን።
እኔ እስር ቤት ከመግባቴ በፊት ወደ 10 ለሚጠጉ ዓመታት
እስር ላይ የቆዩ ወንድሞች ትልቅ እገዛ አድርገውልናል።
እነዚህ ወንድሞች ከእስር ቤት የወጡት ጠንካራ እምነት ይዘው ነው።
ደስተኞችም ነበሩ።
ይህን ማየታችን እንደ እኔ ላሉ በወጣትነታቸው
ለታሰሩ ወንድሞች በጣም የሚያበረታታ ነበር።
እኔ በታሰርኩበት ወቅት አንዳንድ ለውጦች ነበሩ።
የታሰርነው በተመሳሳይ ቦታ ቢሆንም።
ቅዳሜና እሁድ ጠባቂዎቹ የተወሰነ ነፃነት ይሰጡን ነበር።
ስለዚህ ወንበሮችን ወይም ባልዲዎችን አውጥተን
በቡድን ተቀምጠን አብዛኛዎቹን ስብሰባዎች እናደርግ ነበር።
መዝሙርም ጭምር እንዘምር ነበር።
አንዳንድ ወንድሞች የሙዚቃ መሣሪያዎችን ሠርተው ነበር።
ስለዚህ ጠባቂዎቹ የተለያዩ መዝሙሮችን ስንዘምር ስለሚሰሙን
ለእነሱ ይሄ እንግዳ ነገር አልነበረም።
እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ተጠንቅቀን ለወረዳና
ለአውራጃ ስብሰባዎች የሚያስፈልገንን ነገር እናስገባ ነበር።
ይገርማል።
ከዚያም ስብሰባዎቹን እናደርጋለን።
እዚህ ፎቶ ላይ እንደምታየው ወንድሞች
ጥንታዊ አልባሳትን ለብሰው ድራማ እየሠሩ ነው።
ጠባቂዎቹ የምናደርገውን እንዳያውቁ ድራማዎቹ የሚቀርቡት ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎቹን ሕያው ስለሚያደርጉላቸው ወንድሞች ድራማዎቹን ይወዷቸዋል።
ድራማ ስንሠራ እንዳንታይ በጣም እንጠነቀቅ ነበር።
ይገርማል። ይሖዋ መንፈሳዊ ምግብ እንዳያቀርብልን
የእስር ቤት ግንቦች እንኳ እንቅፋት አልሆኑበትም።
አዎ፣ ለስብሰባዎቻችን ትልቅ ቦታ ስለምንሰጥ
ባለሥልጣናቱ ፈቀዱም አልፈቀዱ መሰብሰባችንን ቀጥለናል።
የምናገኘው መንፈሳዊ ምግብ፣ በመከከላችን ያለው ፍቅርና
እርስ በርስ መደጋገፋችን ለጥንካሬያችን መሠረት ሆኗል።
ስለሆነም ወንድሞች ስብሰባዎቻችን እንዳይቋረጡ ጥረት ያደርጉ ነበር።
የመታሰቢያውን በዓል እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል።
እስር ቤት በገባሁበት ወቅት ባለ ሥልጣናቱን
“እባካችሁ የመታሰቢያውን በዓል እንድናከብር ፍቀዱልን”
ብለን ጠየቅናቸው።
እነሱ ግን አይቻልም አሉን።
ባይፈቅዱልንም ለማክበር ቆርጠን ነበር።
መጠየቃችንን ግን አላቆምንም።
በመጨረሻም የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ዕለት
በድንገት ከሰዓት ላይ ሁላችንም ከክፍላችን ወጥተን
ገላችንን እንድንታጠብ ፈቀዱልን።
ማክሰኞ ዕለት እንድንታጠብ ተፈቅዶልን አያውቅም።
ከዚያም “ለማታው ፕሮግራማችሁ ተዘጋጁ” አሉን።
ይገርማል።
ከዚያም ማታ አንድ ሰዓት ላይ እስር ቤቱ ውስጥ በሚገኝ
አንድ የጸሎት ቤት የጌታ ራትን አከበርን።
በዚያች ትንሽ የጸሎት ቤት ውስጥ 125 ሆነን ስንዘምር
ድምፃችን ያስገመግም ነበር።
ከመካከላችን ያላለቀሰ ሰው አልነበረም።
በዓሉን አክብረን ስንወጣ በስተምሥራቅ በኩል
በወታደራዊ መሥሪያ ቤቱ አናት ላይ
ወጥታ የነበረችውን ሙሉ ጨረቃ እስካሁን አስታውሳለሁ።
ይህ ለእኛ ትልቅ ድል ነበር።
ይሖዋ እስከፈቀደ ድረስ በዓሉን እንዳናከብር ማንም ሊያስቆመን አይችልም።
በሕይወቴ ፈጽሞ የማልረሳው የመታሰቢያ በዓል ነበር።
ለመገመት አያዳግትም።
እስር ቤት እንሰበሰብበት የነበረው መንገድ አንድ እውነት አስገንዝቦኛል።
አንድ ላይ የመሰብሰብ መብታችን
እኛ ለይሖዋ የምንሰጠው ሳይሆን እሱ እኛ የሰጠን ስጦታ ነው።
አዎ፣ ልክ ነህ።
ልዩ በሆነ መንገድ እስር በርስ እንድትቀራረብ ያደርግሃል።
አዎ፣ ልክ ነህ። ስብሰባዎች በጣም ያስፈልጉናል።
እምነታችንን ይበልጥ ያጠናክሩልናል።
በስብሰባዎች ላይ መገኘት በተለይ ከዚያን ጊዜ በኋላ
ከፍ አድርጌ የምመለከተው ስጦታ ነው።
ፈጽሞ ላለመቅረትና በአካል ለመገኘት
የቻልነውን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን።
ሌሎች እምነታቸውን ሲገልጹ መስማት እንዲሁም
አንተ ራስህ እምነትህን መግለጽህ በጣም ያበረታታሃል።
እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር ለመማር የተሰበሰብን ሰዎች አይደለንም።
ይህ መንፈሳዊ ቤተሰብ ነው።
ይሖዋ አንድ ላይ መሰብሰብና
እርስ በርስ መበረታታት እንዳለብን ያውቃል።
ጳውሎስ እንዳለው በተለይ
ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስናይ።