JW subtitle extractor

ዶምኒክ አሊሺያ፦ የአእምሮ ሕመም ቢኖርብኝም ተስፋ አግኝቻለሁ

Video Other languages Share text Share link Show times

አስተዳደጌ ጥሩ ነበር።
አፍቃሪ ወላጆች ነበሩኝ።
ግን ሁልጊዜ የሆነ የጎደለኝ ነገር እዳለ ይሰማኝ ነበር።
ደስተኛ አልነበርኩም።
ከልጅነቴ ጀምሮ ሙዚቃ በጣም እወዳለሁ።
ሃይማኖታዊ መዝሙሮች መዘመር ጀመርኩ።
ብዙ የሙዚቃ ወድድሮች ላይም ተካፍያለሁ።
ሙዚቃ ስጫት ልዩ ሰው እንደሆንኩ ይሰማኛል።
ስለዚህ በሙዚቃ ሥራዬ ዝነኛ ካልሆንኩ
በሕይወቴ መቼም ደስተኛ መሆን አልሆንም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ።
ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ሁልጊዜ በሐዘን መዋጥ ጀመርኩ።
የሥነ ልቦና ባለሙያ ጋር ሄጄ ስለመረመር
የመንፈስ ጭንቀት እንዳለብኝ ተነገረኝ።
ከሁሉ አብልጬ የምወደው ነገር ሙዚቃ ብቻ ሆነ።
ከመንፈስ ጭንቀት ጋር እየታገልኩም ሙዚቃ መማሬን ቀጠልኩ።
አስተማሪዬ ወደ ቪክቶሪያ የሥነ ጥበብ ኮሌጅ ገብቼ እንድማር አበረታታኝ።
በአነስተኛ ቲያትሮች ውስጥ
የኦፔራ ሙዚቃ መጫወት ያስደስተኝ ነበር።
በኋላም በኦፔራ የሙዚቃ ዲፕሎማዬን አገኘሁ።
እዚህም ላይ ደርሼ እንኳን
አሁንም የጎደለኝ ነገር እንዳለ ይሰማኝ ነበር።
ምንጊዜም የማስበው ዝነኛ ከሆንኩ ደስተኛ እሆናለሁ ብዬ ነበር።
በዚያን ወቅት ለኦፔራ አውስትራሊያ ተወዳደርኩና ፈተናውን አለፍኩ።
ኦፔራ አውስትራሊያ በጣም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር ነው።
በዚህም ብዙ የዓለም አገራትን ዞሬያለሁ።
ለምሳሌ ስዊዘርላንድ፣ ግሪክና ሆንግ ኮንግ ሄጃለሁ።
ከዚያም ... የሚባል በሽታ እንዳለብኝ ታወቀ።
... እንድንጨነቅና የምናስበውን ነገር መቆጣጠር
እንዲከብደን የሚያደርግ የአእምሮ ሕመም ነው።
በትክክል ማሰብ ይከብደኛል።
መዝፈን እወዳለሁ።
ግን ደስተኛ የሚያደርገኝን ነገር አሁንም እየፈለግኩ ነበር።
ምን እንደሆነ ግን አላውቅም።
ተስፋ ወደ መቁረጥ ደረስኩ።
ኦፔራውንና የምወዳቸውን ነገሮችን በሙሉ ማድረግ አቆምኩ።
የምበላና የምጠጣው ለመኖር ያህል ብቻ ነበር።
የሕይወት ዓላማም ሆነ
ለራሴ ጥሩ ግምት አልነበረኝም።
ለ10 ዓመታት ያህል ምንም ሳላደርግ እንዲሁም ቁጭ አልኩኝ።
በእነዚያ ዓመታት ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች
ጽሑፎችን ወደ ቤታችን ያመጡልን ነበር።
እኔም ጽሑፎቹን ማንበብ ጀመርኩ።
ጽሑፎቹን ማንበቤ ለውጥ ማምጣት ጀመረ።
ልጅ እያለሁ አባቴ መጽሐፍ ቅዱስን ያጠና እንደነበር ትዝ ይለኛል።
ለዘላለም መኖር እንደምንችልና
ይሖዋ ደግሞ የሚወደን አምላካችን መሆኑን መማሬ
የሚያስፈልገኝ እውቀት መሆኑን በወቅቱ ባልገነዘብም
የጎደለኝ ግን ይህ እውቀት ነበር።
ከዚያም አንድ ቀን የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ።
ቁጭ ብዬ እያነበብኩ ነበር።
እናም ራሴን እንዲህ አልኩት፦
‘ዶሚኒክ ወደ ስብሰባ መሄድ አለብህ።’
አዳራሹ የት እንዳለ ባውቅም መሄድ ግን ከበደኝ።
ስለዚህ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ።
‘በሽታዬ የአንተ ወዳጅ እንዳልሆን እንዲያግደኝ አትፍቀድ’ አልኩት።
ብዙም ሳይቆይ ቁርጥ ውሳኔ አደረግኩ።
ወደ ስብሰባ ለመሄድ ወሰንኩ።
ልክ እዚያ ስደርስ
‘እስካሁን የት ነበርኩ? ለምን አመነታሁ?’ አልኩ።
እዚያ መሆኔ አረጋጋኝ።
ሁኔታዬም እየተሻሻለ ሄደ።
በ2020 ተጠመቅኩ።
ይህ በሕይወቴ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ልዩ ቀን ነበር።
ከዚህ በፊት የጎደለኝ ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነበርኩ።
የጎደለኝ እውነት ነበር።
ይሖዋ ነበር።
አሁን የኦ... በሽታዬን መቆጣጠር ችያለሁ።
አንዳንድ ቀን ጭንቀት ሲሰማኝ
ብዙ የሚወዱኝ ወንድሞችና እህቶች እንዳሉ
ጉባኤው ከጎኔ እንዳለ
ከሁሉም በላይ ደግሞ የይሖዋን ፍቅር ሳስብ
ከዚያ ስሜት ውስጥ ቶሎ እንድወጣ ይረዳኛል።
በስብከቱ ሥራ የበለጠ ስካፈል ስለ ሌሎች የማስበው ብዙ፣
ስለ ራሴ ችግሮች የማስበው ደግሞ ትንሽ ይሆናል።
የምወስዳቸው መድኃኒቶችና የሕክምና ምክር አገልግሎቱ ረድቶኛል።
መድኃኒቶቹ ዘና እንድል ያደርጉኛል።
ሊያደርጉ የሚችሉት ይህን ብቻ ነው።
እንደ ተስፋ ያሉትን ነገሮች ሊያሟሉልህ አይችሉም።
ሕክምና የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣ ተስፋ አይሰጥህም።
አሁን ያገኘሁትን ደስታና እርካታ አገኛለሁ ብዬ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም።
ይሖዋን ቀደም ብዬ ለምኜው ቢሆን ኖር ይህን ያህል አልሠቃይም ነበር።
አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ በሙዚቃ እየተደሰትኩ ነው።