JW subtitle extractor

JW ብሮድካስቲንግ—ታኅሣሥ 2025፦ 158ኛው የጊልያድ ምረቃ

Video Other languages Share text Share link Show times

ወንድሞች፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!
ያለፈው መስከረም 13, 2025
የ158ኛው ክፍል የጊልያድ ተማሪዎች
ከአምስት ወር ጥልቅ ጥናት በኋላ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
የምረቃ ቀን ብዙ ስሜቶችን የምታስተናግዱበት ቀን ነው።
እፎይታ - ኮርሱን በተሳካ ሁኔታ ስለጨረሳችሁ።
ደስታ - ከወዳጅ ዘመድ ጋር ጊዜ ስለምታሳልፉ።
ምናልባት፣ ምናልባት ደግሞ ጭንቀት - ምን ይመጣ ይሆን ብላችሁ።
እስቲ ለተማሪዎቹ የተሰጡትን አበረታች ንግግሮች አብረን እናዳምጥ።
እነዚህን የሚያበረታቱ ንግግሮች እንደምትወዷቸው እርግጠኞች ነን።
እዚህ ያላችሁ ሁላችሁንም
ለ158ኛው ክፍል የጊልያድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት
የምረቃ ፕሮግራም እንኳን ደህና መጣችሁ
ብዬ ስቀበላችሁ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል!
የ158ኛው የጊልያድ ክፍል 52 ተማሪዎች
ቀጥሎ የሚቀርበውን ንግግር ትኩረት ሰጥታችሁ እንድታዳምጡ እጋብዛችኋለሁ።
ጭብጡ “የምድር ጨው መሆናችሁን ቀጥሉ” የሚል ነው።
እባካችሁ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን አውጡና ማቴዎስ 5:13ን አብረን እናንብብ።
የጥቅሱ የመጀመሪያ ክፍል ላይ
ኢየሱስ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ” ብሏል።
ኢየሱስ ይህን ሐሳብ የተናገረው “የተራራው ስብከት” ተብሎ በሚጠራው ንግግሩ ላይ ነው።
በወቅቱ ኢየሱስ ከተናገረው ከዚህ ሐሳብ በርካታ ሰዎች የተጠቀሙ ቢሆንም
እነዚህን ቃላት በቀጥታ የተናገረው ግን እነማንን አስቦ ነው?
ደቀ መዛሙርቱን አስቦ ነው።
በተለይ በዋነኝነት በቅርቡ ለመረጣቸውና
ምናልባትም በተራራ ስብከቱ ወቅት አብረውት ተቀምጠው ለነበሩት አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ነው።
እነዚህ የተመረጡት አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት
ለጉባኤው አመራር በመስጠትና ምሳሌ በመሆን ረገድ ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል።
ስለዚህ “የምድር ጨው ናችሁ” የሚለው አባባል ለሁሉም ሰው የሚጠቅም ቢሆንም
በዋነኝነት የተነገረው ለሐዋርያቱ ነው።
ለእናንተ ውድ ተማሪዎችም
እነዚህ ቃላት እንዴት እንደሚጠቅሟችሁ በዚህ ንግግር ላይ እያየን እንሄዳለን።
የሚገርመው እዚህ ላይ ኢየሱስ የንጽጽር ዘይቤን ተጠቅሞ አልተናገረም።
ማለትም “እናንተ እንደ ምድር ጨው ናችሁ” አላለም።
ከዚህ ይልቅ ኢየሱስ ያለው “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ” ነው።
ኢየሱስ ከጨው ጋር እያመሳሰላቸው ሳይሆን ጨው እንደሆኑ እየነገራቸው ነው።
ለደቀ መዛሙርቱ ይህን ያላቸው ምን ማለት ፈልጎ ነው?
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ በሰዎች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለመግለጽ
ጨው በነገሮች ላይ የሚያመጣውን ለውጥ እየጠቀሰ ነው።
ግን የትኞቹን ባሕርያት አስቦ ነው?
ስለ ጨው ባሕርይ በአእምሮው አስቦ ሊሆኑ የሚችሉ ሦስት ነገሮችን
እስቲ አብረን እንመልከት።
እናንተ ውድ ተማሪዎችም በእነዚህ ሦስት ገጽታዎች
“ጨው” የሆናችሁበትን መንገድ እያየን እንሄዳለን።
እባካችሁ ቆላስይስ ምዕራፍ 4ን አውጡ።
ኢየሱስ አስቦት ሊሆን የሚችለው
ጨው ያለውን አንደኛውን ባሕርይ
ቁጥር 6 ላይ እናያለን።
“ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ
ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ
ምንጊዜም በጨው የተቀመመ ያህል ለዛ ያለው ይሁን።”
ጥቅሱ ስለ የትኛው የጨው ባሕርይ እየተናገረ ነው?
የማጣፈጥ ባሕርይ ነው አይደል?
ምግብ የማጣፈጥ ባሕሪውን።
ጨው ከሌለው የምንበላው ነገር አይጣፍጥም።
እንዲጣፍጠን ጨው መጨመር አለበት።
እናንተም ቢሆን እንዲህ ያለው የጨው ባሕርይ እንዳላችሁ አልጠራጠርም።
በንግግራችሁና በምታሳዩት ጠባይ ይታያል።
በተለይ ደግሞ እዚህ ጊልያድ ያገኛችሁትን ሥልጠና ተጠቅማችሁ
ተመድባችሁ ወደምትሄዱበት ጉባኤም ይሁን
በቤቴል ለምታገኟቸው ወንድሞችና እህቶች
ንግግራችሁ ደግነት የተሞላበትና ሌሎችን የሚያንጽ እንደሚሆን እንተማመናለን።
መቼም የምትናገሯቸውን ቃላቶች በሚጥሚጣ አትቀምሙም አይደል?
ጥቅሱ “በሚጥሚጣ ቀምሙ” አላለም።
ወይም በቁንዶ በርበሬ፣
በጣም በሚያቃጥል ቃሪያ፣
በበርበሬም አላለም።
ያለው በጨው ነው፤
ማቃጠል ሳይሆን ማጣፈጥ በሚችል።
እኛም ንግግራችንን በጨው መቀመም ይኖርብናል።
እናንተም በጉባኤ ውስጥ መልስ ስትሰጡ፣
ከወንድሞች ጋር ስትጨዋወቱ
ወይም ንግግር ስታቀርቡ እንደዚሁ አድርጉ።
በቤቴልም ሆነ በምትመደቡት ጉባኤ ላሉ
ወንድሞችና እህቶች ጨው መሆን ትችላላችሁ።
ሁለተኛውን የጨው ባሕርይ ደግሞ እስቲ እንመልከት።
ሕዝቅኤል 16:4 እንደሚጠቁመን (ጥቅሱን አናነበውም)
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን አንድ አዲስ የተወለደን ጨቅላ ሕፃን ሰውነቱን
በጨው ማሸት የተለመደ ነበር፣ በዚያ ዘመን።
ግን የዚህን ጨቅላ ሕፃን ልጅ ሰውነት በጨው የሚያሹት ለምንድን ነው?
ጥቅሙ ምንድን ነው?
ይህን የሚያደርጉበት አንዱ ምክንያት
ጨው ጀርምን የመግደልና
ኢንፌክሽን እንዳይኖር የመከላከል ባሕርይ ስላለው ነው።
ዛሬም ቢሆን ሰዎች ጉሮሯቸውን ሲያማቸው
እዚያ አካባቢ ያለን ጀርም ለመግደልና ሕመሙን ለማስታገሥ
ውኃ በጨው አድርገው ይጉመጠመጣሉ።
ብዙ ሰዎች አትክልት ከመመገባቸው በፊት
ንጹሕና ከጀርም ነፃ ለማድረግ ጨው ባለው ውኃ ያጥቡታል።
ስለዚህ ጨው ባክቴሪያንና ሌሎች በሽታ አምጪ ተሕዋስያንን ለመግደል ያገለግላል።
እናንተ ተማሪዎችም መቼም ከዚህ በፊት ራሳችሁን
እንደ ጀርም ገዳይ
ወይም እንደ ባክቴሪያ ገዳይ ቆጥራችሁ አታውቁም።
ሆኖም መንፈሳዊን ጀርም መግደል ትችላላችሁ።
እስቲ አንድ ምሳሌ እንመልከት።
በተመደባችሁበት ጉባኤ ወይም ቤቴል ስለ አንድ ሰው ሐሜት ሲነገር ሰማችሁ።
ይህ በምሳሌያዊ ሁኔታ ጀርም ማለት እኮ ነው።
ይህን ጀርም ወዲያውኑ ትገድሉታላችሁ።
የወሬውን አቅጣጫ ታስቀይራላችሁ።
ለወንድማችሁ ጥብቅና ትቆማላችሁ።
ይህንን ጀርም በሆነ መንገድ ትገድሉታላችሁ።
ምናልባት አንድ ሰው ስለ አንድ ሽማግሌ እንዲህ ሲል ሰማችሁ፦
“ይህ ወንድም ክፍል ሲያቀርብ ሁልጊዜ ሰዓት ያሳልፋል።”
ከዚያ እናንተ እንዲህ ማለት ትችላላችሁ፦
“እኔ እንጃ፣ እንዲህ ተሰምቶኝ አያውቅም።
ግን ደግነቱን፣ አፍቃሪነቱን፣
ጥሩ እረኛ በመሆን
ጉባኤውን ለመርዳት የሚያደርገውን ጥረት ስመለከት በጣም ነው የምደሰተው።”
ጀርሙን ገደላችሁት ማለት ነው።
መንፈሳዊ ፀረ ጀርም ናችሁ የተባለው ለዚህ ነው።
በክልላችሁም ይህን ታደርጋላችሁ።
የሥላሴን ጀርም ትገድላላችሁ።
ሌሎች የሐሰት ትምህርቶችንም።
የገሃነም እሳት፣ የማትሞት ነፍስ አለች እንደሚሉ ያሉ ትምህርቶችን ትገድላላችሁ።
ኢየሱስ አስቦት ሊሆን ስለሚችለው ሦስተኛው የጨው ባሕርይ እንመልከት።
ዘሌዋውያን ምዕራፍ 2ን አውጡ።
ቁጥር 13ን እናንብብ።
ዘሌዋውያን 2:13
እንዲህ ይላል፦ “የምታቀርበው የእህል መባ በሙሉ
በጨው መቀመም አለበት።
የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው
ከእህል መባህ ላይ አይጥፋ።
ከማንኛውም መባህ ጋር ጨው አብረህ ታቀርባለህ።”
በሙሴ ሕግ ማንኛውም መሥዋዕት
በመሠዊያው ላይ ለይሖዋ መሥዋዕት ሆኖ ከመቅረቡ በፊት
በጨው እንዲቀመም ያዝዝ ነበር።
ስለዚህ የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊዎች እንዳሉት፣
መሠዊያው አቅራቢያ ለዚሁ ዓላማ ሲባል
ትልቅ መጠን ያለው የጨው ቁልል ይቀመጥ ነበር።
በቤተ መቅደሱ አካባቢ
በዚያ ዘመን “የጨው አዳራሽ” ተብሎ የሚጠራ
ጨው የሚከማችበት ትልቅ ክፍል ነበር።
የይሖዋን መሥፈርት ለመጠበቅ የተደረገ ዝግጅት ነው።
ሆኖም “ይሖዋ ይህን ዝግጅት ያደረገው ለምንድን ነው?” የሚል ጥያቄ ይነሳል።
አንድ መጠበቂያ ይህን ሲያብራራ
“እንዲህ ይደረግ የነበረው
መሥዋዕት ሆነው ለቀረቡት ነገሮች
ጣዕም ለመጨመር ተብሎ ሳይሆን
ጨው ከብክለት ወይም ከብልሽት ነፃ መሆንን
ስለሚያመለክት ሊሆን ይችላል” ይላል።
ልክ ነው አይደል?
ጨው ሦስተኛ ባሕሪው ምግብ እንዳይበላሽ ማድረጉ ነው።
ምግብ ሳይበላሽ፣ ሳይመረዝ የማቆየት ባሕርይ አለው።
ምንም ዓይነት ማቀዝቀዣ በሌለበት
ጨውን በመጠቀም ብቻ
ሥጋን ለብዙ ጊዜ ሳይበላሽ ማቆየት እንችላለን።
እናንተም በምትመደቡበት ቦታ የምታገኟቸውን ወንድሞችና እህቶች
በመንፈሳዊ ሳይበላሹ እንዲቆዩ መርዳት ትችላላችሁ።
ይህን በማድረግ እንደሚሳካላችሁ አንጠራጠርም።
ለምሳሌ አንድ ሰው ማስጠናት ጀመራችሁ።
ሰውየው ስለሚያጨስ ሳንባው፣ ልቡ በዚህ የተነሳ ችግር እያጋጠመው ነው።
ወይም ዕፅ የሚወስድ ይሆንና አእምሮው እየተጎዳ ነው።
የሚጠጣ ከሆነ ደግሞ ጉበቱ ችግር ላይ ነው።
ግለሰቡ የፆታ ብልግና የሚፈጽም ከሆነ ደግሞ
ለአባለዘር በሽታዎች የተጋለጠ ነው።
ይህን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ስታስጠኑት
በይሖዋ እርዳታ ከእነዚህ መጥፎ ልማዶቹ ይላቀቃል።
በምሳሌያዊ ሁኔታ እንደ ጨው ትሆኑለታላችሁ።
እንዲያውም ይህ ሁኔታ ብዙውን ጊዜ የመበላሸቱ ሂደት እንዳይቀጥል ማስቆም ብቻ ሳይሆን
ሰውየውን እንደ አዲስ እንዲታደስም ይረዳዋል።
አእምሮውና የሰውነት አካላቱ ይታደሳል።
ደግሞም ስታስጠኑት
ከይሖዋ ጋር ወዳጅነት እንዲመሠርት እየረዳችሁት ነው።
ደግሞም እኮ እንዲህ ማድረጋችሁ ሕይወቱ
ለዘላለም ተጠብቆ እንዲቆይ ያስችላል።
በዚህ መንገድ በአገልግሎት ላይ ለሰዎች እንደ ጨው ትሆናላችሁ።
በቤቴል ደግሞ
አንድ ሰው መንፈሳዊ አደጋ ሊያስከትልበት የሚችል እርምጃ ቢወስድ
“እናንተ መንፈሳዊ ብቃት ያላችሁ”
በገርነት መንፈስ ታስተካክሉታላችሁ።
በዚህ መንገድ፣ ሊጠፋ ይችል የነበረን ሕይወት ታድናላችሁ።
እነዚህ እንደ ጨው ሆናችሁ ማገልገል የምትችሉባቸው
ጥቂት ምሳሌዎች ብቻ ናቸው።
ጨው ያሉትን አስደናቂ ገጽታዎችም አይተናል።
እንዳየነው፣ ጨው ምግብ ያጣፍጣል፤
ጀርም ይከላከላል፤
ምግብ እንዳይበላሽ ያደርጋል።
ኢየሱስ የጠቀሰው ምሳሌ ትልቅ ትርጉም አለው።
ደግሞም ይህን ሲል አድናቆቱን መግለጹ ነው።
ውድ ተማሪዎች፣ እኛም ይህን ስንላችሁ
ለእናንተ ያለንን አድናቆት መግለጻችን ነው።
“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ።”
ግን እዚህ ላይ ኢየሱስ
የአድናቆት ቃላት ብቻ አይደለም የተናገረው።
ማቴዎስ ምዕራፍ 5 ላይ ኢየሱስ
ማስጠንቀቂያም ሰጥቷል።
ማቴዎስ 5:13ን እናውጣና ሙሉውን ጥቅስ እስቲ እናንብበው።
ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦
“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤
ሆኖም ጨው የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ
ጨውነቱን እንዴት መልሶ ሊያገኝ ይችላል?
ከዚህ በኋላ ወደ ውጭ ተጥሎ
በሰው ከመረገጥ በቀር
ለምንም ነገር አያገለግልም።”
ደግሞም ጨው በተለያዩ ነገሮች ሊበከል እንደሚችል ግልጽ ነው።
ለምሳሌ ከሆነ ነገር ጋር ሊቀላቀልና ያለውን ኃይል ሊያጣ ይችላል።
ጨው በተለያየ ምክንያት የጨውነት ጣዕሙን ሊያጣ ይችላል።
ይህ ለእኛም ይሠራል።
በመንፈሳዊ ጨው እንደሆንን መቀጠል ይኖርብናል።
የጨው ባሕሪያችንን ማጣት የለብንም።
ለዚህ ምን ይረዳችኋል?
በእነዚህ አምስት ወራት የተማራችኋቸውን ነገሮች ተግባራዊ ካደረጋችሁ
ምንጊዜም ቢሆን
የጨውነት ጣዕማችሁን ይዛችሁ ትቀጥላላችሁ።
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ
በጣም ተወዳጅ እየሆነ የመጣውን
“የትውውቅ መድረክ” የተባለውን ፕሮግራም እንከታተል።
“የትውውቅ መድረክ” ፕሮግራማችንን
ወንድም ጆኤል ኬሊ ይመራልናል።
ወንድም ጆኤል ኬሊ በጣም ከምንወዳቸው የጊልያድ አስተማሪዎች አንዱ ነው።
“የትውውቅ መድረክ” የተባለውን ፕሮግራም ሲመራ
ሁላችንም በትኩረት እንከታተለው።
ለትውውቅ መድረክ ፕሮግራማችን እንኳን ደህና መጣችሁ!
ኢሳይያስ 64:8 ላይ
ይሖዋ ራሱን እንደ ሸክላ ሠሪ አድርጎ ገልጿል።
እኛ ደግሞ እንደ ሸክላ ተደርገን ተገልጸናል።
እኛ የሰው ልጆች ፍጹማን ባንሆንም እንኳ
ይሖዋ አምላክ ሊቀርጸን ፈቃደኛ ነው።
እኛ በእሱ ለመቀረጽ ፈቃደኛ እስከሆንን ድረስ
ይሖዋ ዓላማውን ለመፈጸም የሚፈልገውን ሁሉ እንድንሆን ያደርጋል።
በዚህ ፕሮግራማችን ላይ የአምስት ተማሪዎችን ተሞክሮ እንሰማለን፤
ይሖዋ እንዴት እንደሚቀርጸንም እናያለን።
ተሞክሯቸውን ስትሰሙ የይሖዋን ባሕርያት ለማስተዋልና
መንፈሳዊ ጉዟቸውን ያቃናላቸው እንዴት እንደሆነ ለማስተዋል ሞክሩ።
በመጀመሪያ ከብሪታንያ ቅርንጫፍ ቢሮ የመጡትን ማርክና ሜሊሳን እንተዋወቅ።
ወደ ትውውቅ መድረካችን ስለመጣችሁ በጣም ደስ ብሎናል።
እናመሰግናለን።
የመጣችሁት ከብሪታንያ ቅርንጫፍ ቢሮ ነው።
ሁለታሁም እንግሊዛዊ ናችሁ?
እኔ የመጣሁት በሰሜን እንግሊዝ ካለው የማንቺስተር አካባቢ ነው።
እኔ ግን ከአሜሪካ ነው የመጣሁት፤ ከዲትሮይት፣ ሚቺጋን።
ግን አትላንቲክን የሚያህል ትልቅ ውቅያኖስ በመካከላችሁ እያለ እንዴት ተገናኛችሁ?
የተገናኘነው በ1998 ሜሊሳ በምትኖርበት አካባቢ በተደረገ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ልዑክ ሆኜ ሄጄ ነው።
የተጋባነው ግን ትንሽ ቆየት ብለን ከሰባት ዓመታት በኋላ ነው።
ጥሩ። ግን በወጣትነታችሁ መንፈሳዊ እንቅስቃሴያችሁ ምን ይመስል ነበር?
ወላጆቼ አፍቃሪዎች ናቸው።
የልጅነት ሕይወቴም ደስ የሚል ነበር።
በመንፈሳዊ ሁኔታ ግን ጥሩ ጎዳና ላይ አልነበርኩም።
ከልጅነቴ ጀምሮ ፋሽን ዲዛይነር የመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ነበረኝ።
ሕይወቴ ሙሉ በሙሉ ያተኮረው እዚያ ላይ ነበር።
ኮሌጅ ገብቼ አራት ዓመት ተማርኩ፤ ከዚያም በፋሽን ዲዛይን ዲግሪ አገኘሁ።
ወዲያው በዚህ የሥራ መስክ ተሰማራሁ።
በዚህም የተነሳ ይሖዋን ለማገልገል የሚረዱ ጥሩ ባሕርያትን ማዳበር አልቻልኩም።
ገንዘብ ማካበት በጣም እፈልግ ነበር።
አብሬያቸው ጊዜ የማሳልፋቸው ሰዎችም ጥሩ ሰዎች አልነበሩም።
የጓደኛ ምርጫዬም ቢሆን ጥበብ የተንጸባረቀበት አልነበረም።
መንፈሳዊ ግብም አልነበረኝም።
ማርክ፣ አንተስ?
የሚያሳዝነው እኔም በመንፈሳዊ ጥሩ ጎዳና ላይ አልነበርኩም።
እውነትን ያስተማረችኝ እናቴ ናት።
ከዚያ በ13 ዓመቴ ተጠመቅኩ።
ወዲያው ግን ሁለት ዓይነት ሕይወት መምራት ጀመርኩ።
ከዕለት ወደ ዕለት በዚህ ዓይነት ሕይወት ይበልጥ እየተጠላለፍኩ መጣሁ።
ይህን አደርግ የነበረው ጥሩ ምሳሌ የሚሆን ቤተሰብና
ይሖዋን በታማኝነት የሚያገለግሉ ወዳጆች እያሉኝም ነው።
ሁለት ዓይነት ሕይወት እየመራሁ እንዳለሁ ማንም ሰው አያውቅም ነበር።
ምን ዓይነት ሰው እንደሆንኩ፣ ከእነማን ጋር ጊዜ እንደማሳልፍ በትክክል የሚያውቀው ይሖዋ ብቻ ነበር።
እናመሰግናችኋለን።
እንዲህ ያለውን ነገር በግልጽ ማውራት ቀላል እንዳልሆነ ይገባናል።
ግን ለውጥ እንድታደርጉ የረዳችሁ ምንድን ነው?
የሚገርምህ፣ አባቴ የይሖዋ ምሥክር አልነበረም።
ግን ጥሩ ባልና ጥሩ አባት በመሆን ረገድ ግሩም ምሳሌ ሆኖልኛል።
ስለዚህ ከሜሊሳ ጋር መጠናናት ስንጀምር በተቻለኝ መጠን ጥሩ ባል መሆን ፈልጌ ነበር።
እንጠናና የነበረው በርቀት ቢሆንም ወዲያውኑ በየሳምንቱ መጽሐፍ ቅዱስን አብረን ማጥናት ጀመርን።
በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በትክክለኛ ዓላማ ተነሳስቼ መንፈሳዊ ነገር ማድረግ ጀመርኩ።
ቀስ በቀስ፣ ከይሖዋ ጋር ያለኝ ዝምድና እንደ አዲስ ሲጠናከር ተሰማኝ።
ከዚያ በፊት በነበሩት ዓመታት ይሖዋን ምን ያህል እንዳሳዘንኩት የገባኝ ያኔ ነው።
እኔም ብሆን ወዲያው እንደተጋባን የአቅኚነት አገልግሎት ጀመርኩ።
ከዚያ ግን፣ ድሮ ባደረግኳቸው ውሳኔዎች የተነሳ በጥፋተኝነት ስሜት እሠቃይ ጀመር።
ከማርክ ጋር አወራንበትና ሽማግሌዎችን አናገርን።
እንዲህ ማድረጋችን ጠቅሞናል።
ምክንያቱም በመንፈሳዊ ማገገም ችለናል።
በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ በጥልቀት ማጥናት
ንጹሕ ሕሊናና ጥሩ መንፈሳዊነት እንዲኖረን ይረዳናል።
እሺ። ከዚያስ ምን ሆነ?
ከዚያማ ይሖዋን ስታገለግል ሊሰማህ የሚገባው ስሜት ተሰማን።
በሁሉም የአገልግሎት ዘርፎች ለመካፈል ራሳችንን አቀረብን።
ለጊልያድ አመለከትን፤ ያኔ እንደ አቅኚነት ነበር የምታመለክተው።
ይህ ብቻ ግን አይደለም።
LDC ውስጥ ለመሥራት፣ ቤቴል ለመግባት አመለከትን።
የሚያሳዝነው ግን እነዚህን ሁሉ ማመልከቻዎች ብንሞላም ለአንዱም እንኳ አልተጠራንም።
ከጊዜ በኋላ ወዳጆቻችን ሰባኪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉበት በኒካራጓ ማገልገል እንደምንችል ጠቆሙን።
ስለዚህ ወደዚያ ሄድን።
ኒካራጓ ማገልገል ምን ይመስል ነበር?
ቆይ ይሄን ፎቶ ላሳይህ።
ይሄን ፎቶ የተነሳነው አገልግሎት ላይ እያለን ነው።
አገልግሎት በጣም አሪፍ ነው።
ሰዎቹ በቀላሉ የሚቀረቡ ናቸው።
ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ነበሩን።
በዚያ ያሳለፍናቸው ዓመታት በጣም አስደሳች ነበሩ።
እንደምታየው፣ አብዛኛውን ጊዜ የምንንቀሳቀሰው በብስክሌት ነው።
ያስታውቃል።
የምንሄደው በእግራችን ከሆነ ደግሞ ወንድሞችና እህቶች በቤታቸው በኩል ስናልፍ እንድንገባ ግድ ይሉናል።
ከእነሱም ብዙ ነገር ነው የተማርነው።
ያላቸው ነገር ጥቂት ቢሆንም በጣም እንግዳ ተቀባዮች ናቸው።
ፎቶውን ሳይ በጣም ነው የገረመኝ።
በሁለታችሁም ፊት ላይ ደስታ ይነበባል።
ሰባኪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉበት ቦታ ማገልገል የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥማችኋል።
እናመሰግናለን።
እሺ፣ ከኒካራጓ በኋላ
የሆነ ወቅት ላይ ወደ እንግሊዝ ቤቴል መጣችሁ።
ቤቴል ውስጥ የምትሠሩት የት ነበር?
እስቲ ስለ እሱ ትንሽ አጫውቱን።
እኔ የምሠራው ሕግ ክፍል ውስጥ ነው።
ሥራዬ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን የቪዛ ጉዳይ መከታተል ነው።
ሥራው በጣም ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል።
ወይም የተለያዩ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ።
ግን የይሖዋን እጅ ለማየት ስለሚያስችለኝ ሥራውን እወደዋለሁ።
በጣም ደስ ይላል።
ማርክ፣ አንተስ?
እኔ የምሠራው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ውስጥ ነው።
ከምናከናውናቸው ሥራዎች አንዱ
ለመገናኛ ብዙኃን፣ ለመንግሥት ባለሥልጣናትና
ለትምህርት ተቋማት ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ትክክለኛ መረጃ መስጠት ነው።
መቼም ከባድ ሥራ ይመስለኛል።
አዎ፣ ልክ ነህ።
የሚገርምህ፣ ወንድሞች ይህን ሥራ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰጡኝ በጣም ተጨንቄ ነበር።
እንዲያውም አንዴ ትዝ ይለኛል፣
በጣም ከመጨነቄ የተነሳ
እንቅልፍ እንኳ እንቢ ብሎኝ ነበር።
ከዚያ ተነስቼ ወደ ሳሎን ሄድኩና
ዘፀአት ምዕራፍ 3ና 4ን አነበብኩ።
ሙሴ በሕዝብ ግንኙነት ክፍል ውስጥ ሥራ የተሰጠው ያኔ እንደነበር አሰብኩ።
ምክንያቱም ትልቅ ሥልጣን የነበረውን ፈርዖንን ማነጋገር ነበረበት።
ሙሴ የተሰጠውን ሥራ ለማከናወን
ብቃት እንደሌለው በተናገረ ቁጥር
ይሖዋ ለሙሴ መሆን የሚፈልገውን ሁሉ እንደሚሆንለት
ያረጋግጥለት ነበር።
እኔም ከወንድሞች ጋር እዚህ ክፍል ውስጥ ስሠራ
ይህን የማየት አጋጣሚ አግኝቻለሁ።
አንድን ነገር ማድረግ እንደማንችል በሚሰማን ጊዜ ሁሉ ይሖዋ ያን ማድረግ እንድንችል ይረዳን ነበር።
ይህ ደግሞ እምነቴን በጣም አጠናክሮልኛል።
ይሖዋ እንዴት እንደተጠቀመባችሁ ማየት እምነት ያጠናክራል።
ከልጅነታችሁ አንስቶ ስላደረጋችሁት መንፈሳዊ ጉዞና አሁን ስለደረሳችሁበት ቦታ እያሰብኩ ነበር።
በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ወቅት ስለ ይሖዋ የተማራችሁት ነገር አለ?
እኔ ይሖዋ በትዕግሥት እንደያዘኝ ተምሬያለሁ።
በራሴ መንገድ አስደሳች ሕይወት መምራትና
አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እፈልግ ነበር።
ደግሞም እንድሞክረው ፈቅዶልኛል።
በራሴ መንገድ መሄዴ የተወሰነ ደስታ ቢያስገኝልኝም
የይሖዋን መንገድ መከተሌ ወደ እሱ ለመቅረብ የሚያስችሉ ባሕርያትን ለማዳበርና
ይበልጥ ደስተኛ ሕይወት ለመምራት አስችሎኛል።
ይሖዋን ሳገለግል የተማርኳቸው ክህሎቶችና ከተመደብኩበት ሥራ እያገኘሁት ያለሁት ደስታ
በራሴ መንገድ መሄዴን ብቀጥል ኖሮ ላገኘው የምችለው ዓይነት አይደለም።
ይሖዋ ይህን በሕይወቴ ቀምሼ እንዳይ አጋጣሚ ስለሰጠኝ በጣም አመስጋኝ ነኝ።
“የራስሽ ጉዳይ” ብሎ እንዲሁ እንድባዝን አልተወኝም።
ልክ ነሽ።
ማርክ፣ አንተስ?
እኔ በዋነኝነት የይሖዋን ምሕረት አይቻለሁ።
አሁን ላይ መለስ ብዬ ሳስበው፣
ፍርሃት የሚያስፈልገኝን መንፈሳዊ እርዳታ እንዳልጠይቅ እንቅፋት ሆኖብኝ ነበር።
ይሖዋ እንደ እኔ ላሉ ሰዎች የሚሰማውን ስሜት አልተገነዘብኩም ነበር።
ግን አንድ ጓደኛዬ አንድ ጥቅስ አሳየኝ።
ከፈቀድክልኝ፣ ለእናንተም ባሳያችሁ ደስ ይለኛል።
እሺ።
ጥቅሱ ያለው ኢሳይያስ 28 ላይ ነው።
ከቁጥር 24 እስከ 29 ያለውን ሐሳብ በጣም እወደዋለሁ።
ግን ቁጥር 24ን ብቻ ላንብበው።
እንዲህ ይላል፦
“ገበሬ ዘር ከመዝራቱ በፊት ቀኑን ሙሉ ሲያርስ ይውላል?”
እዚህ ላይ የአንድ ገበሬን ምሳሌ ይጠቅሳል።
ገበሬው ዝም ብሎ ሲያርስ አይኖርም።
ከዚህ ይልቅ ወደፊት ዘሩ አድጎ ሲመገበው በሚያገኘው ደስታ ላይ ትኩረት ያደርጋል።
ይሖዋ ከእኔ ጋር በተያያዘም ያደረገው እንደዚሁ ነው።
በዋነኝነት ያተኮረው እኔን በመገሠጽ ወይም በመቅጣት ላይ አልነበረም።
ከዚህ ይልቅ በደግነት፣ ደስተኛና ንጹሕ ሆኜ
እሱን ማገልገል ወደምችልበት መንገድ መርቶኛል።
አሁን ሁለታችንም፣ ይሖዋ ስታገለግል ሊሰማህ የሚገባው ዓይነት ስሜት እየተሰማን ነው።
ያካፈልከን ተሞክሮ ጥቅሱን ሕያው የሚያደርግ ነው።
አሁን ማርክ ካነሳው ጋር በተያያዘ፣
ክፍል ውስጥ ስንወያይ አንድ ጥቅስ ተጠቅሶ ነበር።
ዕብራውያን 9:14።
ይህ ጥቅስ፣ ይሖዋ ሕሊናችንን ካነጻን በኋላ
ለእሱ ቅዱስ አገልግሎት እንድናቀርብለት እንደሚፈቅድ ይናገራል።
በእኛም ሕይወት ይህን ተመልክተናል።
ቅዱስ አገልግሎት ማቅረብ ማለት ስህተት ከሠራን በኋላም
ተመልሰን ይሖዋን ማገልገላችንን መቀጠል ማለት ነው።
መሽመድመድ የለብንም።
እናንተም ያደረጋችሁን ይህንን ነው።
ይሖዋ እየተጠቀመባችሁና እየረዳችሁ እንደሆነ አይተናል።
ለተሞክሯችሁ እናመሰግናለን።
እኛም እናመሰግናለን።
ቀጣይዋ እንግዳችን ከምሥራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ ነው የመጣችው።
እህታችን ዋንጂኩ ዋይቺጎ ናት።
እሺ ዋንጂኩ፣ የመጣሽው ከኬንያ እንደሆነ እናውቃለን።
እዚያ ያሉ ጓደኞችሽ ሺኮ ብለው እንደሚጠሩሽ ሰምቻለሁ።
ልክ ነኝ?
አዎ፣ ልክ ነህ።
አንተም ሺኮ በለኝ።
እሺ ሺኮ።
እስቲ ታሪክሽን አጫውቺን።
እናቴ እውነትን የሰማችው ትንሽ ልጅ እያለሁ ነው።
ስለዚህ እውነት ውስጥ ነው ያደግኩት።
አባቴ ግን የይሖዋ ምሥክር አይደለም።
በዋነኝነት እንድናተኩር የሚፈልገው ትምህርት ላይ ነው።
እኔም ሕግ ማጥናት እፈልግ ነበር።
የሕግ ትምህርት?
አዎ።
ምስኪኖችን መርዳትና ፍትሕ እንዲያገኙ መርዳት እፈልግ ነበር።
‘ሳድግ እንዲህ ነው የማደርገው’ ብዬ አስብ ነበር።
የሕግ ትምህርት መከታተል ጊዜ እንደሚወስድ ግልጽ ነው።
ታዲያ ይሄ ከይሖዋ ጋር ያለሽን ግንኙነት አልነካብሽም?
እንዴ፣ በደንብ ነክቶብኛል።
ትምህርት ቤት እያለሁ ዋነኛ ትኩረቴ
ጥሩ ውጤት ማግኘትና የወደፊት ሕይወቴን ማስተካከል ነበር።
ስለዚህ መንፈሳዊነቴን ሙሉ በሙሉ ተውኩት።
ታዲያ ለውጥ እንድታደርጊ የረዳሽ ምንድን ነው?
ልክ ትምህርቴን እንደጨረስኩ አካባቢ አንድ ቤት ተከራየሁ።
እንደ አጋጣሚ ሆኖ ቤቱ ከስብሰባ አዳራሽ አጠገብ ነበር።
አስታውሳለሁ፣ አንድ ቀን ከሥራ ወጥቼ ወደ ቤት እየሄድኩ ነበር።
በጣም ነበር የደከመኝ።
ከዚያ የተወሰኑ ወንድሞች ወደ ስብሰባ አዳራሹ ሲሄዱ አየሁ።
እንዲህ ብዬ አሰብኩ፦ “እኔም እኮ ማድረግ ያለብኝ ልክ እንደዚህ ነው።
አሁን መገኘት ያለብኝ እዚህ ቦታ ነው።”
ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ስብሰባ ላይ ተገኘሁ።
ይገርማል። በዚህ ጊዜ ብዙኃኑን መከተል ጠቃሚ ሆኖ ተገኝቷል።
ልክ ነህ።
ምክንያቱም ወደ ስብሰባ አዳራሽ ወስደውሻል።
ትክክል።
እሺ፣ ወደ ስብሰባ አዳራሹ ስትሄጂ ምን ተሰማሽ?
ወንድሞችና እህቶች እንዴት ተቀበሉሽ?
የሄድኩበት ጉባኤ በጣም ሞቅ ያለና አፍቃሪ ጉባኤ ነው።
ሞቅ አድርገው ተቀበሉኝ።
ፍቅር አሳዩኝ።
በቃ ቤቴ እንዳለሁ ተሰማኝ።
መንፈሳዊ ሕይወቴን ታድገውልኛል።
በጣም ደስ ይላል።
ታዲያ ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዴት ገባሽ?
እስቲ አጫውቺን፤ ሂደቱ ምን ይመስል ነበር?
መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት አንብቤ ለመጨረስ ግብ አወጣሁ።
ይህን እንደ ፕሮጀክት ነበር የያዝኩት።
ቢሮ የምገባው በማለዳ ነው።
ስለዚህ ዎችታወር ላይብረሪን አወረድኩና ከሥራ በፊት ለቀኑ የተመደበውን ክፍል ማንበብ ጀመርኩ።
ከዚያ ባነበብኩት ላይ ምርምር አደርጋለሁ።
በዚያ ዓመት ሙሉውን እንደዚያ አደረግኩ።
ከዚያ ይህን ልማዴን ገፋሁበት።
ጥልቀት ያለው ምርምር ነው ያደረግሽው።
ልክ ነው።
አጀማመሩ እንዲህ ነበር ማለት ነው።
ሌላስ የረዳሽ ነገር ምንድን ነው?
ያኔ ከአንዳንድ አቅኚዎች ጋር አገልግሎት እወጣ ነበር።
ከዚያም አብረውኝ ከሚያገለግሉት አቅኚዎች አንዷ (የምቀርባት ጓደኛዬ ናት)
አዘውትራ “አንድ ቀን አቅኚ መሆንሽ አይቀርም” ትለኝ ነበር።
ያኔ ሙሉ ቀን ስለምሠራ በዚያ ሁኔታ ውስጥ አቅኚ መሆን እችላለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር።
ውትወታዋን ግን አላቆመችም አይደል?
በፍጹም። ልታቆም አልቻለችም።
የኋላ ኋላ ግን እሷ እንዳለችው አቅኚነት ጀመርኩ።
በአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤትም ተካፈልኩ።
ኧረ?
ይኸው ፎቷችን።
እሺ። አዎ፣ የአቅኚ መጽሐፍ ይዘሽ የተነሳሽው ነው።
እሷስ ማን ነች?
ይህችማ ስትወተውተኝ ነበር ያልኩህ እህት ናት።
በዚህ የአቅኚዎች ትምህርት ቤት ላይ አብረን ነው የተካፈልነው።
ግን እሷ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው።
ውትወታዋ ከንቱ አልቀረም ማለት ነው።
ትክክል።
ትምህርት ቤቱም በጣም አሪፍ ነው።
የይሖዋ ስጦታ ነው።
አሁንም ጥሩ ጓደኞች ትመስሉኛላችሁ።
አዎ፣ ልክ ነው።
ከዚያም ቤቴል መጀመሪያ በተመላላሽነት፣ ከዚያም ሙሉ በሙሉ ገብተሽ ማገልገል ጀመርሽ።
ቤቴል ውስጥ ምን ነበር የምትሠሪው?
ሕግ ክፍል ውስጥ ነው የምሠራው።
ቆይ እስቲ፣ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ።
ከዚህ በፊት በዓለም ውስጥ
ይህንኑ የሕግ ሥራ ስትሠሪ ቆይተሻል።
አሁን ደግሞ ይህንኑ ሥራ ለይሖዋ እየሠራሽ ነው፤
በእሱ ድርጅት ውስጥ ማለት ነው።
ስታወዳድሪያቸው እንዴት ታስቀምጫቸዋለሽ?
ፈጽሞ አይወዳደሩም።
በዓለም ውስጥ ስትሠራ ዋናው ነገር ገንዘብ ማግኘት
ወይም በዘርፉ ታዋቂ መሆን ነው።
ለይሖዋ ስትሠራ ግን የምታገለግለው ወንድሞችህን ነው።
ገና ሳታውቃቸው ትወዳቸዋለህ።
ስታውቃቸው ደግሞ ይበልጥ ትወዳቸዋለህ።
እምነትህ በእጅጉ ይጠናከራል።
በቃ ልታወዳድረው አትችልም።
እርካታ፣ ደስታ ይሰጥሃል።
ከሁሉ የተሻለ ሕይወት ነው።
ሺኮ፣ ይህን ልዩ ተሞክሮ ስላካፈልሽን እናመሰግንሻለን።
የከፈልሽውም ትልቅ መሥዋዕትነት ነው።
ማርክና ሜሊሳ፣ እናንተንም እናመሰግናለን።
ይሖዋ እንዴት እንደተጠቀመባችሁና እንደቀረጻችሁ መመልከት
እምነት የሚያጠናክር ነው።
በጣም እናመሰግናችኋለን።
ቀጣዩ እንግዳችን የመጣው ከዶሚኒካን ሪፑብሊክ ነው።
ወንድም ቲቶ አብሪዮን ሞቅ አድርገን እንቀበለው።
እሺ ቲቶ፣ እንኳን ደህና መጣህ።
አመሰግናለሁ።
እስቲ ስለ ራስህ ንገረን።
እውነት ቤት ውስጥ ነው ያደግከው?
አዎ፣ እናቴ የይሖዋ ምሥክር ናት።
አባቴ ግን አይደለም።
እርግጥ አባቴ እውነት ሕይወታችንን እንዴት እንደለወጠው ስላየ ይደግፈን ነበር።
እናቴ ይሖዋን በጣም በጣም ነው የምትወደው።
ለአገልግሎት ያላትም ፍቅር ልዩ ነው።
እኛ ልጆቿንም ለይሖዋና ለአገልግሎት ፍቅር እንዲኖረን አስተምራናለች።
ስለዚህ አቅኚ መሆን ያን ያህል አልከበደኝም።
በኋላም በ2010 በአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ተማርኩ።
እንዴ? MTS ሄዳሃል?
አዎ ሄጃለሁ።
ከዚያ በኋላስ የት ተመደብክ?
ልዩ አቅኚ ሆኜ እንዳገለግል ደሴቲቱ መሃል ተመደብኩ።
በጣም ደስ የሚል ጊዜ ነው ያሳለፍኩት።
እንዲያውም አንድ ፎቶ ላሳይህ።
እሺ፣ ደስ ይለኛል።
እዚህ ፎቶ ላይ የምታየው ወንድም ሆሴ ነው።
ያለነው እልም ያለ ጫካ ውስጥ ነው።
አሁን ሆሴ ልዩ አቅኚ ሆኖ እያገለገለ ነው።
ያኔ ግን ገና ያልተጠመቀ አስፋፊ ነበር።
ከኋላችን ራቅ ብላ ያለችውን ትንሽ ቤት አየሃት?
መስማት የተሳናቸውን ሰዎች ለማግኘት እንዲህ ወዳሉ ቤቶች እንሄዳለን።
ግን እዚህ ቤት ውስጥ ያሉ ወላጆች የሚናገሩት የሄይቲ ክሪዮል ነው።
አንዳንዶቹ ልጆች ደግሞ ስፓንኛ ይናገራሉ።
ግን አንዱ ትንሽ ልጅ ጨርሶ አይናገርም።
ከእሱ ጋር ለመግባባት ምልክት ቋንቋ መጠቀም ነበረብን።
በዚህ ቤት ውስጥ ለመስበክ ሦስት የተለያዩ ቋንቋዎች መጠቀም አስፈልጎናል።
ምልክት ቋንቋ ትችላለህ ማለት ነው?
አዎ፣ እህቴ መስማት ስለማትችል ቤተሰባችን በሙሉ የምልክት ቋንቋ ተምሯል።
በዚያ ነው የቻልኩት።
በጣም ደስ ይላል።
ወደተመደብክበት ቦታ ስትደርስ አገልግሎትህን ከየት ጀመርክ?
መስማት የማይችሉ ሰዎችን ለማግኘት
ወደ እያንዳንዱ ቤት ሄድክ?
መስማት የማይችሉ ሰዎችን መፈለግ የጀመርነው
በአካባቢው ካሉ ወንድሞች ጋር ሆነን ነው።
መጀመሪያ ወደ ሦስት ቦታዎች ሄድን፤
ወደ ፖሊስ ጣቢያ፣
ወደ ወታደራዊ ካምፕና
ወደ ከንቲባዋ ቢሮ።
ቀጥታ ወደ ላይ ነው የሄድከው።
አዎ፣ እንደዚያ ነው ያደረግነው።
ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ?
በጣም ጥሩ ውጤት ነው ያገኘነው።
በዚያ ከተማ ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች ባላቸው መልካም ምግባር የተነሳ
ቀድሞውንም ጥሩ ስም አትርፈው ነበር።
ግን የይሖዋ ምሥክሮች መስማት ለማይችሉ ሰዎችም ትኩረት መስጠታቸው ልባቸውን ነክቶታል።
በወቅቱ ያደረግነው ጉብኝት ስኬታማ ነበር።
እኔ እንኳ በዚያኑ ዕለት ሦስት ተመላልሶዎች አግኝቻለሁ።
ከንቲባዋ ቢሮ ውስጥ የሚሠሩ ሦስት መስማት የማይችሉ ሰዎች ነበሩ፤
እነሱን ማስጠናት ጀመርኩ።
ስለዚህ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ጥናቶችህን የሰጠችህ ከንቲባዋ ናት ማለት ነው።
ልክ ነህ።
ታዲያ እድገት አደረጉ?
አዎ፣ በተለይ ሁለቱ ትዝ ይሉኛል።
ሳይጋቡ አብረው ነበር የሚኖሩት።
ስለ ይሖዋ ሲማሩ ግን በእሱ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ፈለጉ።
ስለዚህ ተጋቡ።
ከይሖዋ ጋር ጥሩ ዝምድና መሠረቱ።
እንዲያውም አሁን እነዚህ ባልና ሚስት
በዚያ አካባቢ ያሉ መስማት የማይችሉ ሰዎችን
ስለ ይሖዋ እያስተማሩ ነው።
በጣም የሚያበረታታ ነው።
በምልክት ቋንቋ የሚደረገው የስብከት እንቅስቃሴ
በጣም እያደገ ነው።
ይህ ብቻ ሳይሆን ዶሚኒካን ሪፑብሊክ ውስጥ
በስፓንኛና በሌሎች ቋንቋዎች የሚደረገው የስብከት እንቅስቃሴም
እድገት እያሳየ እንደሆነ እናውቃለን።
ልክ ነህ።
እስቲ አንድ ቪዲዮ እንመልከት።
በዚያ ያለውን እድገት የሚያሳይ ነው።
በሂስፓኒዮላ ደሴት ላይ ሁለት አገሮች ይገኛሉ።
ዶሚኒካን ሪፑብሊክና ሄይቲ።
በሁለቱም አገራት የይሖዋ ሕዝቦች ጠንካራ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል።
በዶሚኒካን ሪፑብሊክ ምሥራቹ የሄይቲ ክሪዮልን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች በስፋት እየተሰበከ ነው።
በርካታ የሄይቲ ተወላጆች አገራቸው ውስጥ ብዙ ችግሮች ስላሉ
የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ ዶሚኒካን ሪፑብሊክ ይመጣሉ።
ከሄይቲ የመጡ ሰዎች አምላክ እንዳለ ቢያምኑም
በችግራቸው ጊዜ እንዳልረዳቸው ይነግሩናል።
ይህን መስማት በጣም ያሳዝናል።
ግን ይሄ እነሱን ለመርዳት ልዩ አጋጣሚ ይከፍትልናል።
ቀረብ ብለን እናነጋግራቸዋለን፤ እናዳምጣቸዋለን።
ተመልሰን ስንሄድ ደግሞ በጣም የሚያስፈልጋቸውን ተስፋውን እናካፍላቸዋለን።
ስለ እነሱ የሚያስብ አምላክ እንዳለ የሚያሳዩ ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እናሳያቸዋለን።
ከቤት ወደ ቤት ስንሄድ ሰዎች የሚቀበሉን በፈገግታ ነው።
ሁሌም ወደ ቤት እንድንገባ ይጋብዙናል።
በእያንዳንዱ ቤት እየገባን ረጅም ሰዓት ስለምንቆይ
ሁለት ወይም ሦስት ሰዓት አገልግለን እንኳ
ማንኳኳት የምንችለው የተወሰኑ ቤቶችን ብቻ ነው።
ከእነሱ ጋር ውይይት መጀመር በጣም ቀላል ነው።
የምንወያይበትን ርዕስ የሚያነሱት እንኳ እነሱ ራሳቸው ናቸው።
“እንዴት ናችሁ?
ቤተሰብ ደህና ነው?”
እንደሚሉት ያሉ ቀላል ጥያቄዎች እንኳ
ጥሩ ውይይት ለመጀመር በር ይከፍታሉ።
ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች ሲማሩ
ቀስ በቀስ በሕይወታቸው ላይ ለውጥ ማድረግ ይጀምራሉ።
ይህ ደግሞ በቃላት ሊገለጽ የማይችል እርካታ ያስገኝልሃል።
በአንድ ወቅት ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል
ብቸኛ ልጇን በሞት ያጣች አንዲት ሴት አገኘን።
ለደረሰባት መከራ ተጠያቂው ይሖዋ አምላክ እንዳልሆነ ስታውቅ
በጣም ተገረመች።
ብዙም ሳይቆይ ከዚህ ድቅድቅ መንፈሳዊ ጨለማ ላወጣት ለይሖዋ
አመስጋኝነቷን መግለጽ የምትችልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ
እሱን ማገልገል እንደሆነ ተሰማት።
አሁን በጣም የምንወዳት እህታችን ሆናለች።
በጣም ደስተኛ ነች።
ምክንያቱም ሕይወቷ ትርጉም ያለው ሆኗል።
አንድ ሰው ተጠምቆ ከውኃ ውስጥ ሲወጣ ማየት
በጣም የሚያስደስት ነገር ነው።
እርግጥ እዚያ እንዲደርሱ የረዳቸው ይሖዋ ነው።
ግን ሕይወታቸው እንዲለወጥ
ትንሽም ቢሆን አስተዋጽኦ ማበርከት
በጣም ትልቅ መብት ነው።
የጉባኤያችን አስፋፊዎች ቁጥር 30 ያህል ብቻ ቢሆንም
አማካይ የተሰብሳቢዎች ቁጥር 70 ነው።
ለመታሰቢያው በዓል ደግሞ በየዓመቱ ከ300 በላይ ሰዎች ይገኛሉ።
የአስፋፊውን አሥር እጥፍ ያህል ማለት ነው።
አሁን ይሖዋ ይህን ያህል የታገሠው ለምን እንደሆነ ገብቶኛል።
መሠራት ያለበት ገና ብዙ ሥራ አለ።
በመላዋ አገሪቱ ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።
ሰዎች እውነትን ለመስማት ፈቃደኛ ናቸው።
ኢየሱስ በዮሐንስ ምዕራፍ 4 ላይ እንዳለው
መንፈሳዊው የመከር ሥራ ሰፊና አጣዳፊ ነው።
ሠራተኞቹ ግን ደስተኞች ናቸው።
እኛም በዚህ ዓለም አቀፍ የመከር ሥራ ላይ ከሚሳተፉት ሁሉ ጋር በአንድነት ደስ ይለናል።
ይሖዋ በመስኩ ላይ የሚከናወነውን ሥራ እየባረከና
ሰዎችን ወደ ራሱ እየሳበ እንደሆነ ማየት የሚያስደስት ነው።
እስቲ አሁን ደግሞ ስለ ቤቴል ሥራህ ንገረን።
ቤቴል ሥራህ ምንድን ነው?
አሁን የምሠራው በጤና እንክብካቤ ክፍል ውስጥ ነው።
በቅርንጫፍ ቢሯችን ሥር ላሉ የልዩ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ድጋፍ እንሰጣለን።
ለሚስዮናውያን፣ ለልዩ አቅኚዎችና ለወረዳ የበላይ ተመልካቾች፤
በዶሚኒካን ቅርንጫፍ ቢሮ ሥር ላሉት ማለት ነው።
ግን በሄይቲ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን
ያሉበት ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ እነሱንም እንረዳለን።
የሄይቲን ቅርንጫፍ ቢሮ?
አዎ።
ስለዚህ በሄይቲ ያሉ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች
ዶሚኒካን ሪፑብሊክ መጥተው የሕክምና አገልግሎት ያገኛሉ።
ታዲያ ስለ እነሱ ምን ያስተዋልከው ነገር አለ?
ያለባቸው ኃላፊነት በጣም እንደሚያስጨንቃቸው እናውቃለን።
ስለዚህ እኛ ጋ ሲመጡ ትንሽ ዘና እንዲሉ፣
እንዲያርፉ ለማድረግ እንጥራለን።
እርግጥ፣ የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና እርዳታም እንሰጣቸዋለን።
ያላቸው አመለካከት ግን በጣም ያስገርማል።
ለምሳሌ አንድ ባልና ሚስት ትዝ ይሉኛል።
ምርመራ ካደረጉ በኋላ ውጤቱ ከባድ የጤና ችግር እንዳለባቸው እንደሚያሳይ ነገርናቸው።
ስለ በሽታውና ስለሚወስዱት ሕክምና ካስረዳናቸው በኋላ
የመጀመሪያ ጥያቄያቸው “ሕክምናውን ቶሎ መጀመር እንችላለን?” የሚል ነበር።
ሐኪሙ ራሱ በጣም ተገርሞ
“ለምን?” ብሎ ጠየቃቸው።
የሰጡት መልስ ያስገርማል።
እንዲህ አሉት፦
“በሄይቲ ያሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የእኛ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
ሕክምናችንን ቶሎ ጨርሰን አብረናቸው ማገልገል እንፈልጋለን።
ቶሎ ተመልሰን ልንረዳቸው እንፈልጋለን።”
የሚገርም ነው።
እነሱ ራሳቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚያሳስባቸው የወንድሞቻቸው ጉዳይ ነበር።
እንዴት ያለ አስገራሚ ፍቅር ነው ያሳዩት!
ስለነገርከን እናመሰግናለን።
የተሰጠህ ሥራ ከሄይቲ ቅርንጫፍ ቢሮ ጋር እንደሚያገናኝህ እናውቃለን።
ግን ይሄ ብቻ አይመስለኝም።
እንዲያውም ባለፉት አምስት ወራት አብሮህ አንድ ክፍል ይኖር የነበረው ከሄይቲ የመጣ ወንድም ነው አይደል?
አዎ።
ልክ ነህ።
እንድናናግረው ትፈቅድልናለህ?
ችግር የለም።
ስለዚህ ከሄይቲ ቅርንጫፍ ቢሮ የመጣውን ወንድም ፍራንክሊን ኤሚን እንተዋወቅ።
ወንድም ፍራንክሊን፣ ወደ ፕሮግራሙ እንኳን ደህና መጣህ!
አመሰግናለሁ።
እስቲ ስለ ራስህ አጫውተን።
በእውነት ቤት ውስጥ ነው ያደግከው?
ያደግኩት እውነት ቤት ውስጥ ነው።
እናታችን ብቻዋን ነው ያሳደገችን።
አራት ወንድሞችና እህቶች አሉኝ።
እኔ የመጨረሻ ልጅ ነኝ።
እናቴ ታታሪ ናት።
በይሖዋ ላይ ያላት እምነትም ጠንካራ ነው።
ይህ በእኔ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድሯል።
አንዳንድ ጊዜ በቀጣዩ ቀን ምን እንደምትመግበን እንኳ አታውቅም ነበር።
ያም ቢሆን በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት ነበራት።
ብዙ ጊዜ ስትጸልይና ሁሉን ነገር ለእሱ ስትተወው አይ ነበር።
ይሖዋም የሚያስፈልገንን ይሰጠን ነበር።
እናቴ የተወችልኝ ግሩም ምሳሌ
ይሖዋ እውን ሆኖ እንዲታየኝና
እምነት እንዳዳብር ረድቶኛል።
የእሷ ምሳሌነት ጥሩ ሥልጠና እንደሆነህ ግልጽ ነው።
ሌላስ ምን ሥልጠና አግኝተሃል?
በ2010 የአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ገብቻለሁ።
እንዴ፣ በ2010?
ቲቶ፣ ከአንተ ጋር ማለት ነው?
አዎ፣ በደሴቲቱ የተለያየ ክፍል ቢሆንም በተመሳሳይ ጊዜ ነው።
የሚገርምህ የተጠመቅነውም በተመሳሳይ ሳምንት ነው።
በተመሳሳይ ሳምንት?
በ1997።
ልክ ነው።
ይገርማል። የተለያየ ቦታ እየኖራችሁ አንድ ዓይነት ሕይወት ነው የመራችሁት።
አዎ፣ ልክ ነህ።
ግን በሄይቲ ከፍተኛ የምድር ነውጥ የተከሰተው ጥር 2010 ላይ ነው።
የምድር ነውጡ ከባድ ውድመት አስከትሏል።
የብዙ ሰዎችንም ሕይወት ቀጥፏል።
ታዲያ ያኔም ትምህርቱ ቀጠለ?
አይ፣ በትምህርት ቤቱ ፕሮግራም ላይ ለውጥ ማድረግ አስፈልጓል።
ጠዋት ጠዋት በተለመደው መንገድ እንማራለን።
ከሰዓት ግን ሁላችንም የአደጋ ጊዜ እርዳታ በመስጠቱ ሥራ እንካፈላለን።
እንዲያውም ይህን የሚያሳይ አንድ ፎቶ አምጥቻለሁ።
እ፣ እሺ።
እነማን ናቸው እነዚህ?
አብረውኝ የተማሩት ናቸው።
ለወንድሞችና ለእህቶች የተላኩ የእርዳታ ቁሳቁሶችን
በከሰዓቱ ክፍለ ጊዜ ከመኪና ላይ እያወረዱ ነው።
በጣም የሚገርም ነው።
ስለዚህ ጠዋት ጠዋት ክፍል ውስጥ ኢየሱስ ስለተወው ምሳሌ ትማራላችሁ፤
ከሰዓት ከሰዓት ደግሞ ያንን በሥራ ላይ ታውላላችሁ።
ልክ ነው፣ እንደዚያ ነበር።
በጣም ደስ ይላል።
ከMTS በኋላስ የት ተመደብክ?
አንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ ልዩ አቅኚ ሆኜ ተመደብኩ።
በዚያ ያሳለፍኩት ጊዜ አስደሳች ነበር።
ምክንያቱም ይሖዋ ሥራውን ሲባርከው ተመልክቻለሁ።
ሰዎች ይሖዋን እንዲያውቁትና እንዲያገለግሉት የመርዳትም ልዩ መብት አግኝቻለሁ።
የሄይቲ ሰዎች መንፈሳዊ ፍላጎት አላቸው፤ ለምሥራቹም ጥሩ ምላሽ ሰጥተዋል።
ግን ሕዝባዊ ዓመፁ በስብከቱ ሥራ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል?
በሄይቲ የተነሳው ሕዝባዊ ዓመፅ
በዚያ ያሉ ወንድሞችና እህቶች ቅንዓት እንዲቀዘቅዝ አላደረገም።
እርግጥ፣ የተወሰኑ ወንድሞችና እህቶች ከአገሪቱ ሸሽተው ስለሄዱ
ባለፉት ዓመታት የአስፋፊዎች ቁጥር ቀንሷል።
የስብከቱ ሥራችን ግን በተለያዩ መንገዶች ጭማሪ አሳይቷል።
ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል፣
ከ2021 ጋር ሲነጻጸር
በ2024 የአገልግሎት ዓመት
የጥናቶች ቁጥር 18 በመቶ ጨምሯል።
የሚገርመው እነዚህ ዓመታት ሕዝባዊ ዓመፁ በጣም የተባባሰባቸው ዓመታት ናቸው።
የረዳት አቅኚዎች ቁጥር
በአራት እጥፍ ጨምሯል።
የተጠማቂዎች ቁጥርም
ከበፊቱ በእጥፍ ጨምሯል።
እነዚህ ሁሉ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም ይሖዋ ሥራውን መባረኩን እንደቀጠለ ያሳያሉ።
ይሄን መስማት ያስደስታል።
ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት
ሕዝባዊ ዓመፁ እየተባባሰ እንደሆነ ነግረኸናል።
ሁኔታው ከባድ እንደሆነ ግልጽ ነው።
ወንድሞች ላይ ምን ተጽዕኖ እያሳደረ ነው?
ብዙ ወንድሞችና እህቶች
ከመኖሪያቸው በተደጋጋሚ ተፈናቅለዋል።
አንዳንዶቹ የያዙት የአደጋ ጊዜ ቦርሳቸውን ወይም የለበሱትን ልብስ ብቻ ነው።
ሸሽተው ከሄዱበትም ቦታ ከጥቂት ሳምንታት ወይም ከጥቂት ወራት በኋላ እንደገና ይፈናቀላሉ።
እነዚህ ሁሉ ነገሮች እያሉም
ወንድሞቻችን ውስጣዊ ሰላማቸውን፣
ደስታቸውን አላጡም።
ይሄ ደግሞ በጣም ያስገርመኛል።
ለምሳሌ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ
300 የሚያህሉ ወንድሞችና እህቶች
ይኖሩበት ከነበረው አንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ለመሸሽ ተገደው ነበር።
የሚገርመው በዚያው ሳምንት
የቅርንጫፍ ኮሚቴው ሁለት የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባላት
ወደዚያ ሄደው ወንድሞችን እንዲያበረታቱ ዝግጅት አደረገ።
ልዩ ስብሰባም ተዘጋጀ።
በዚያ ወቅት የተነሳ አንድ ፎቶ ይዣለሁ።
ፎቶው ላይ የሚታየው ምንድን ነው?
በዚያ ልዩ ስብሰባ ላይ የተገኙ ወንድሞችና እህቶች ናቸው።
እንደምታየው ወንድሞችና እህቶች ዝንጥ ብለው ነው የመጡት።
የቅርንጫፍ ኮሚቴው አባላትም ባዩት ነገር በጣም ተገርመዋል።
ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው የመጡ ወንድሞችና እህቶች
አዳራሹን ሙልት አድርገውት ነበር።
የሚያስገርመው ደግሞ፣ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው የመጡት ገና በቅርቡ ቢሆንም
ደስተኛና አንድ ላይ ሆነው ይሖዋን ለማምለክ ዝግጁ ነበሩ።
በጣም የሚገርም ነው።
እነዚህ ወንድሞች ሕይወታቸውን ለማትረፍ እየሸሹ ቢሆንም
ይሖዋን ለማምለክ ወደ ስብሰባ አዳራሹ መጥተዋል።
ግሩም ምሳሌ ናቸው።
ይሖዋ ኃይል እንደሰጣቸው በግልጽ ማየት ይቻላል።
ይሖዋ ድርጅቱንና አመራር የሚሰጡ ወንድሞችን የሚጠቀምበት መንገድም ያስገርማል።
እስቲ አንድ ቪዲዮ እንይ።
በሄይቲ የሚያገለግል አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካች
በዚያ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል ይገልጽልናል።
ሄይቲ የምትገኘው በሂስፓኒዮላ ደሴት ምዕራባዊ ክፍል ላይ ነው።
በሄይቲ የይሖዋ ሕዝቦች የተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል።
ሆኖም ደፋሮችና ትሑት ናቸው፤
በይሖዋም ይታመናሉ።
የእነሱ የእምነት ምሳሌ ሁላችንንም የሚያበረታታ ነው።
ከኮቪድ-19 በኋላ በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በምናደርገው የወረዳ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እየተዘጋጀን ነበር።
አንዳንድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሚኖሩት
ሕዝባዊ ዓመፅና አለመረጋጋት ባለበት ቦታ ነው።
ስለዚህ ቤታቸውን ትተው
ወደ ስብሰባው ቦታ መምጣት
ከባድ ይሆንባቸዋል።
ይህን ማድረግ ከፍተኛ ድፍረት ይጠይቃል።
ወደ ስብሰባው ቦታ ስንደርስ በዚያ
በርካታ ወንድሞችና እህቶችን አየን።
ሁሉም በጣም ተደስተው ነበር።
ይተቃቀፋሉ፤
አንዳቸው ለሌላው አስገራሚ ተሞክሮዎችን ይናገራሉ።
አንድ ላይ ሆነው እንዲህ ያለ ትልቅ ስብሰባ ላይ ከተገናኙ በጣም ረጅም ጊዜ ሆኗቸው ነበር።
በእርግጥም ትልቅ መንፈሳዊ ድግስ ነበር።
በዚያ ስብሰባ ላይ የቀረቡት ንግግሮች በሙሉ በጣም የሚያበረታቱ ነበሩ።
ቀጥሎ ላጋጠመን አስቸጋሪ ሁኔታ አዘጋጅተውናል።
የሚያሳዝነው ቀጣዩን የወረዳ ስብሰባ
በአካል ያደረግነው ከሁለት ዓመታት በኋላ ነው።
ምክንያቱም በአገሪቱ ውስጥ ሕዝባዊ ዓመፅና አለመረጋጋት ነግሦ ነበር።
ወንድሞች በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም
ከይሖዋ ጋር ተቀራርበውና
ለእሱ ታማኝ ሆነው መቀጠላቸውን ማየቴ አስደስቶኛል።
ሽማግሌዎች ድርጅቱ የሰጣቸውን መመሪያ
በፍጥነት ተግባራዊ በማድረግ ትልቅ ትሕትና አሳይተዋል።
አንድ መመሪያ ሲደርሳቸው መመሪያውን ወዲያውኑ ተግባራዊ ለማድረግ
ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።
በተለይ ደግሞ በሕዝባዊ ዓመፁ ምክንያት
ችግር ያጋጠማቸውን ወንድሞችና እህቶች የሚመለከቱ መመሪያዎች ሲሰጧቸው
በፍጥነት ተግባራዊ ያደርጉ ነበር።
በወንድሞቻችን መካከል ያለውን ፍቅር ስንመለከት
የቀድሞ ፍቅራቸውን እንዳላጡ፣
ይዘውት እንደቀጠሉ እንገነዘባለን።
እርስ በርሳቸው ይደጋገፋሉ።
ይህ ብቻ ግን አይደለም።
ወንድሞቻችን ያሉበት ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም
ከይሖዋ ጋር ያላቸው ዝምድና ይበልጥ ተጠናክሯል።
ደግሞም በይሖዋ ላይ ያላቸው እምነት ይበልጥ እንደጨመረና
ከይሖዋ ድርጅት የሚያገኙትን መመሪያ ለመታዘዝ
ከምንጊዜውም ይበልጥ ፈቃደኞች እንደሆኑ ተመልክተናል።
በእርግጥም እነዚህ ወንድሞችና እህቶች
እጅግ አስገራሚ ጽናት አሳይተዋል።
እኔና ባለቤቴ ከዚህ ትልቅ ትምህርት አግኝተናል።
ማድረግ የምንችለው ከሁሉ የተሻለ ነገር
ይሖዋ እንዲመራን መፍቀድ ነው።
ይሖዋ እንደማይጥለን ሙሉ በሙሉ እርግጠኞች ነን።
ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን
ይሖዋ እኛን መንከባከቡን አያቋርጥም።
ስለዚህ ያለንበት ሁኔታ ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን
በይሖዋ ላይ መተማመን እንችላለን።
አንድ ደሴት ላይ ያሉ ሁለት አገራት።
በሁለቱም አገራት ይሖዋን በታማኝነት የሚያገለግሉ ሕዝቦች አሉ።
ከሂስፓኒዮላ ደሴት የሰማናቸው ተሞክሮዎች
ይሖዋ ከሕዝቡ ጋር እንደሆነ ያረጋግጣሉ።
እንዲሁም ምንም ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ቢያጋጥመን
መጽናት እንደምንችል ያረጋግጣሉ።
ልብ የሚነካ ታሪክ ነው።
በሄይቲ ያሉ ወንድሞቻችን
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ ብቻ ሳይሆን
ቆላስይስ 1:11 እንደሚለው
‘ሁሉን ነገር በደስታ እየተቋቋሙ’ ነው።
ይህ ይሖዋ መንፈሱን እንደሰጣቸው ያሳያል።
እየደገፋቸውና የሚያስፈልጋቸውን ኃይል እየሰጣቸው ነው።
ሁለታችሁንም እናመሰግናችኋለን።
ታማኝነታችሁና በዶሚኒካን ሪፑብሊክና በሄይቲ ለሚገኙ ወንድሞቻችን ያሳያችሁት ፍቅር የሚደነቅ ነው።
አሁን የሰማናቸው ተሞክሮዎች
እንዲሁ የአምስት ሰዎች ታሪኮች ብቻ አይደሉም።
ስለ ይሖዋም የሚነግሩን ነገር አለ።
አገልጋዮቹ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟቸው
ኃይሉን እነሱን ለመርዳት እንዴት እንደተጠቀመበት አይተናል።
በስብከቱ ሥራ አማካኝነት ሰዎችን ወደ ራሱ የሚስበው እንዴት እንደሆነም አይተናል።
በተጨማሪም ይሖዋ አፍቃሪ፣ ታጋሽና መሐሪ ሸክላ ሠሪያችን እንደሆነ ተመልክተናል።
ሰዎችን እሱ በሚፈልገው መንገድ ይቀርጻቸዋል።
እርግጥ ሁላችንም ፍጽምና የጎደለን ነን።
የራሳችን የአቅም ገደቦችም አሉብን።
ግን ለመቀረጽ ፈቃደኞች ከሆንን
ይሖዋ ዓላማውን ለመፈጸም
መሆን የሚያስፈልገንን ሁሉ እንድንሆን ያደርገናል።
ታዲያ ይሖዋ እናንተን ምን እንድትሆኑ ያደርጋችሁ ይሆን?
በቀጣዩ ፕሮግራም እስክንገናኝ ሁላችሁም ደህና ሁኑ!
ወንድም ጆኤልንና የጊልያድ ተማሪዎቹን በጣም እናመሰግናለን።
ፕሮግራሙን በጣም ወደነዋል።
እናመሰግናለን።
ይህ አስደሳች ፕሮግራም አሁንም እንደቀጠለ ነው።
በፕሮግራማችን መሠረት ቀጥሎ የሚቀርብልን
የዚህ ፕሮግራም ዋነኛ ንግግር ነው።
ንግግሩን የሚያቀርብልን የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጆዲ ጄድሊ ነው።
ርዕሱ ሦስት ቃላት ብቻ ነው የያዘው፦
“ሞገስ
ማግኘታችሁን
ቀጥሉ”
እባክህ ወንድም ጄድሊ።
ውድ ተማሪዎች
አሁን ልትመረቁ ነው።
እዚህ ጊልያድ ባገኛችሁት ትምህርት ልባችሁ
በአድናቆት እንደተሞላ ምንም ጥያቄ የለውም።
ያደረጋችሁት ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
ይሖዋን ከበፊቱ ይበልጥ እንድታውቁት እና
እንድትወዱት ስላስቻላችሁ በጣም ደስተኞች እንደሆናችሁ
እርግጠኛ ነኝ።
እንዲያውም ትምህርቱን ምን ያህል እንደወደዳችሁት
ከተናገራችሁት ማየት ችለናል።
ከቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች ዲፓርትመንትና
ከአስተማሪዎቻችሁ መመሪያና ድጋፍ አግኝታችኋል።
ከቤቴል ዲፓርትመንቶች ባገኛችሁት ድጋፍም ተጠቅማችኋል።
እዚህ በቆያችሁበት ጊዜ ሁሉ
በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ወንድሞቻችሁ ረድተዋችኋል።
ግን ይህን ያደረጉት ለምንድን ነው?
ለምንድን ነው የረዷችሁ?
ስለሚወዷችሁና
ከትምህርቱ የተሟላ ጥቅም እንድታገኙ ስለፈለጉ ነው።
አዎ፣ ሁላችሁም ብዙ ሥልጠና አግኝታችኋል።
ግን ለምን?
ሥልጠና የተሰጣችሁ ወንድሞቻችሁን እንድታጸኑና
እንድታጠናክሩ ነው።
ሰይጣን ከዘጠኝ ሚልዮን በላይ ሰዎች
በመንፈሳዊ ገነት ውስጥ እየተደሰቱ መሆናቸውን
መቀበል አይፈልግም።
በየጊዜው ደግሞ ይህ ቁጥር እየጨመረ ነው።
አሁንም ብዙ ሰዎች እንዲመጡ እንፈልጋለን።
እዚህ ጊልያድ ያገኛችሁት ሥልጠና
እንድትጸኑና እንድትጠነክሩ አድርጓችኋል።
አሁን ደግሞ ከጊልያድ ባገኛችሁት ትምህርትና
ከይሖዋ ጋር የመሠረታችሁትን ዝምድና ተጠቅማችሁ
ወንድሞችን ማጠናከርና ማጽናት ይኖርባችኋል።
ይህን የምታደርጉት እንዴት ነው?
እናንተም ሁሉም የይሖዋ አምላክ አገልጋዮች
የሚያደርጉትን በማድረግ ነው።
በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችንና
በአገልግሎታችን የሰማዩ አባታችን ይሖዋን
ለመምሰል እንጥራለን።
ይህን ጊልያድ ከመምጣታችሁ በፊትም ታደርጉት ነበር።
ከተመረቃችሁ በኋላ ደግሞ
ይህን ይበልጥ እንደምታደርጉ
ምንም ጥያቄ የለውም።
በዚህ ረገድ ስኬታማ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
ሌሎችን ለማጽናትና ለማጠናከር የሚያስችሉንን
አንዳንድ መንገዶች እስቲ እንመልከት።
ምሳሌ ምዕራፍ 13ን እናውጣና
የቁጥር 15ን የመጀመሪያውን ክፍል
አብረን እንመልከት።
ቁጥር 15
“ጥልቅ ማስተዋል ሞገስ ያስገኛል።”
ይህ ጥቅስ ምን ሐሳብ ያስተላልፋል?
እስቲ በጥልቀት እንመልከተው።
ማናችንም ብንሆን ሌሎች ሞገስ ሲያሳዩን
እንደሰታለን።
በተለይ ደግሞ ይሖዋ በምናደርገው ነገር
እውቅና ሲሰጠን፣
ሞገሱን ሲያሳየንና ሲባርከን እንደሰታለን።
ይሖዋም ቢሆን ሞገሱን ሊያሳየን ይፈልጋል።
ይሖዋ ሞገሱን ለማሳየት
ሁሉንም አጋጣሚዎች ይጠቀማል።
አይዟችሁ! ለእናንተም ያሳያችኋል።
ለሁሉም አገልጋዮቹ።
ወደዚህ ከመምጣታችሁም በፊት
ይሖዋ ይህን ሲያደርግ ተመልክታችኋል።
ይሖዋ ከዚህ ቀደም ሞገሱን ያሳያችሁ
መንፈሳዊ ሰው ስለሆናችሁ እንደሆነ ግልጽ ነው።
ተመርቃችሁ ስትሄዱም
ጥልቅ ማስተዋል ያላችሁ እንድትሆኑና
የይሖዋ ሞገስ እንዳይለያችሁ እንመኛለን።
ግን መጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ማስተዋል ሲል
ምን ማለቱ ነው?
አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንደሚገልጸው፦
ጥልቅ ማስተዋል ተብሎ የተተረጎመው ሐረግ
‘አርቆ አሳቢነት፣ ጥሩ የማመዛዘን ችሎታና
ብስለት የተሞላበት አስተሳሰብ ማንጸባረቅን
ያመለክታል’ ብሏል።
ሌላ የማመሣከሪያ ጽሑፍ ደግሞ፦
‘ከአንድ ሁኔታ በስተ ጀርባ
ያለውን ሁኔታ መመልከት’
ሲል ገልጾታል።
ይህም ስለ አንድ ነገር
ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ማግኘትንና
አንድ ሰው ጥበበኛና
ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችለውን
የእውቀት ዓይነት ያመለክታል።
ጥልቅ ማስተዋል ሲባል
ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ ማዳበርና
ከአንድ ሁኔታ በስተ ጀርባ ያለውን
መመልከት
ማለት ነው።
ስለዚህ ጥልቅ ማስተዋል
ለመረዳት የሚከብድ ሐሳብ አይደለም።
ታዲያ ‘ጥልቅ ማስተዋል ይኑራችሁ’
የተባልነው ለምንድን ነው?
ጥልቅ ማስተዋል እንዳለን ማሳየት
ሁልጊዜ ቀላል ስላልሆነ ነው።
በተመደብንበት ቦታ የተለያዩ ሰዎችና
ሁኔታዎች ያጋጥሙናል።
ከዚህ በተጨማሪም የተለያየ አስተዳደግ፣
አስተሳሰብና ባሕል ያለን
ፍጹማን ያልሆንን ሰዎች ነን።
በተመደብንበት ቦታ ደግሞ
ከእኛ የተለየ ሥራ ከሚሠሩ ዲፓርትመንቶች ጋር
መሥራት ይጠበቅብን ይሆናል።
ከዚህም ሌላ እኛ
ወይም አብሮን የሚሠራው ወንድም
እንቅልፍ የሚነሳ ሁኔታ አጋጥሞን ይሆናል።
ይህ በራሱ ደግሞ ማስተዋል እንዲጎድለን ያደርጋል።
እስቲ ስለ ሙሴ እናስብ።
ሙሴ ታማኝና መንፈሳዊ ሰው ነበር።
በጥቅሉ ሲታይ ሕይወቱን ሙሉ
የይሖዋ ሞገስ አልተለየውም።
ሆኖም እስራኤላውያን በቃዴስ አቅራቢያ
በመሪባ ሙሴን ውኃ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁት
ያኔም የይሖዋ ሞገስ ነበረው?
ሕዝቡ ስላስጨነቀው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ነበር።
ዓለቱን ሲመታው ውኃ ወጥቷል።
የሚያሳዝነው ግን በዚያ ቀን ማስተዋል አላሳየም።
ለይሖዋ ክብር አልሰጠም።
ሕዝቡን በተገቢው መንገድ አልያዘም።
ሕዝቡን ማጠናከርም ሆነ ማጽናት አልቻለም።
ይህ ዘገባ አንድ ነገር ያስተምረናል።
በአብዛኛው የሕይወታችን ክፍል
የይሖዋን ሞገስና በረከት አግኝተን ይሆናል።
ግን ደግሞ አንድን ሁኔታ
ወይም አንድን ጉዳይ በተመለከተ
የይሖዋን ሞገስ ልናጣ እንችላለን።
ሙሴ የነበረውን መብት በዚያው ቀን አላጣም።
ሕዝቡን መምራቱን ቀጥሏል።
ማስተዋል የጎደለው ተግባር በመፈጸሙ ግን
እርማት የተሰጠው ሲሆን
ተስፋይቱ ምድር የመግባት መብቱንም አጥቷል።
አዎ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን
ማስተዋል ማሳየት በጣም አስፈላጊ ነው።
በመጀመሪያ ግን ጥልቅ ማስተዋል ለማሳየት
ማድረግ ያለብን ምንድን ነው?
መዝሙር 32
ቁጥር 8ን እናንብብ።
መዝሙር 32 ቁጥር 8
ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦
“ጥልቅ ማስተዋል እሰጥሃለሁ፤
“ልትሄድበት የሚገባውንም መንገድ አስተምርሃለሁ።
ዓይኔን በአንተ ላይ አድርጌ እመክርሃለሁ።”
ስለዚህ በመጀመሪያ የጥልቅ ማስተዋል ምንጭ
ይሖዋ መሆኑን መገንዘብ አለብን።
መመሪያ የሚሰጠንም እሱ ነው።
ይህን የሚያደርገው በመጽሐፍ ቅዱስ፣
በቅዱስ መንፈሱ፣ በድርጅቱና
በወንድሞቻችን አማካኝነት ነው።
በዚህ መንገድ አመለካከታችንን
ይሖዋ ነገሮችን ከሚያከናውንበት መንገድ ጋር
ማስማማት እንችላለን።
ይህ ደግሞ አንድን ጉዳይ
በጥሩ መንገድ እንድንይዝ ያደርገናል።
የይሖዋን ባሕርያት እንድናንጸባርቅም ይረዳናል።
ይህን እያደረጋችሁ ነው።
እስካሁን በሕይወታችሁ የይሖዋን ሞገስ አግኝታችኋል።
ስለዚህ ጥልቅ ማስተዋልንና
የይሖዋን ሞገስ ማግኘታችሁን ቀጥሉ።
እንዲህ ስታደርጉ ወንድሞቻችሁን ማጠናከርና
ማጽናት ትችላላችሁ።
እስቲ ጥልቅ ማስተዋልንና
የይሖዋን ሞገስ እንድናገኝ
የሚረዱንን ነገሮች እንመልከት።
በጉባኤያችን ውስጥ የሚገኙ
ወንድሞችና እህቶች እንዲጠናከሩና
እንዲጸኑ መርዳት እንፈልጋለን።
ሽማግሌ የሆናችሁ ወንድሞች
አንዲት እህት ጉባኤ ላይ አዘውትራ እንደማትገኝ
አስተዋላችሁ እንበል።
ልትረዷት ፈለጋችሁ።
ስለዚህ ከአንድ ወንድም ጋር ልታበረታቷት ሄዳችሁ።
በጉብኝቱ ወቅት
ጉባኤው እሷን ምን ያህል እንደናፈቃት ነገራችኋት።
የመሰብሰብን አስፈላጊነት የሚያጎሉ
ጥቅሶችንም አነበባችሁ።
አብራችሁም ጸለያችሁ።
ከነበራችሁ መረጃ፣
ካያችሁት ነገር ተነስታችሁ
እረኝነት ማድረጋችሁ ጥሩ ነው።
ግን ጥልቅ ማስተዋል አሳይታችኋል?
እንደዚያ ማለት አይቻልም።
ሐሳባችሁ እኮ ጥሩ ነበር።
ታዲያ አላሳያችሁም ያልነው ለምንድን ነው?
ለምን እንደቀረች አልጠየቃችኋትም።
ባሏ ተቃዋሚ ስለሆነ
የጉባኤ ቀን መኪና እንዳትወስድ ከልክሏታል።
ጉባኤ ለመምጣት መኪና ያስፈልጋታል።
ቤቷ ለስብሰባ አዳራሹ ቅርብ አይደለም።
ማስቸገር ስላልፈለገች ደግሞ እርዳታ አልጠየቀችም።
የጥልቅ ማስተዋልን ፍቺ አስታወሳችሁ?
ስለ አንድ ጉዳይ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ማግኘት።
ከዚያ ውሳኔ ማድረግ።
በጉባኤ ስለመገኘት ምክር ከመስጠት ይልቅ
የሚያስፈልጋት ማበረታቻ ነው።
ጉባኤ ውሰዱኝ ብሎ መጠየቅ
ማስቸገር እንዳልሆነ፣
ወንድሞችም ይህን በማድረጋቸው
ደስተኛ እንደሚሆኑ ብትነግሯት የተሻለ ነበር።
ግልጽ የሆነ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር
እንደሰጣችኋት ይሰማችሁ ይሆናል።
የእህታችን ችግር ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልተቀረፈም።
አሁንም መኪና ያስፈልጋታል።
ይሄኔ እንዲያውም ተጎድታ ይሆናል።
ወንድሞችን ለማጠናከር ማስተዋል ያስፈልገናል።
ከጉባኤ የቀረችበትን ዋናውን ምክንያት ማወቅ
የሚችሉት እንዴት ነበር?
ጥቂት ጊዜ ሰጥቶ በማዳመጥ፣
አሳቢነት በማሳየት።
ጊዜ ሰጥተን በማዳመጥ
የችግሩን መንስኤ ለማወቅ መጣር በጣም አስፈላጊ ነው።
ይህን ስናደርግ ጥልቅ ማስተዋል እናሳያለን።
እናንተ እህቶችስ?
ጥልቅ ማስተዋል በማሳየት
ጉባኤውን ማጽናት የምትችሉት እንዴት ነው?
ጉባኤውን በማጠናከርና በማጽናት ረገድ
እህቶች ትልቅ ሚና አላቸው።
በጉባኤ ውስጥ ካሉት አስፋፊዎች
አብዛኞቹ እህቶች ናቸው።
ስለዚህ መጠናከር የሚያስፈልገው
ብዙ ሰው አለ።
እናንተ እህቶች አንዳንድ ጊዜ
ከወንድሞች የበለጠ ማገዝ ትችሉ ይሆናል።
ቲቶ ሞዕራፍ 2ን እናውጣና
ቁጥር 3ን እናንብብ።
የመጀመሪያው ክፍል እንዲህ ይላል፦
‘በተመሳሳይም አረጋውያን ሴቶች ቅዱሳን ሁኑ።’
እህቶች ሁላችሁም ይሖዋንና
ድርጅቱን የምታከብሩ፣
ጎልማሳና መንፈሳዊ ሰው ናችሁ።
እዚህ ላይ ግን
ሁላችሁም በዕድሜ ገፍታችኋል
እያልኳችሁ አይደለም።
መቼም በአብዛኛው ባሕል
የሴቶች ዕድሜ አይጠየቅም።
ግን በምትመደቡባቸው ጉባኤዎች ውስጥ
በዕድሜ ከእናንተ የሚያንሱ
ወጣት እህቶች ይኖራሉ።
ታዲያ የምትረዷቸው እንዴት ነው?
ቁጥር 4ን እንየው፦
‘ወጣት ሴቶችን በመምከር’ ይላል።
እናንተ እህቶች ማለት ነው።
ስለዚህ አንዲት መንፈሳዊ እህት
በጉባኤ ውስጥ ያሉትን ወጣት እህቶች
በማጠናከርና በማጽናት ረገድ
ትልቅ ሚና አላት።
አንድ ምሳሌ እንይ፦
ይሖዋን ከማያመልኩ ወላጆቿ ጋር የምትኖር
አንዲት ወጣት እህት
በጉባኤያችሁ አለች እንበል።
ጥሩ እንቅስቃሴ የምታደርግ እህት ናት።
ሆኖም አንዳንዴ በምትለብሳቸው ልብሶች ረገድ
ልከኝነት ይጎድላታል።
ጥልቅ ማስተዋል ማለት
ከአንድ ነገር በስተ ጀርባ
ያለውን መመልከት መቻል እንደሆነ አስታውሱ።
የእህት ሁኔታ ያሳሰባቸው አንዳንድ እህቶች
ስለ ሁኔታው ይበልጥ ለማወቅ ጥረት አደረጉ።
የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑት ወላጆቿ
ለጉባኤና ለአገልግሎት የሚሆን ልብስ
እንድትገዛ ገንዘብ አይሰጧትም።
ሁኔታዋን የተረዱ እህቶች
ገንዘብ አዋጡና
እህታችንን ገበያ ይዘዋት ወጡ።
ደግሞ ገበያ መሄድ
የጥልቅ ማስተዋል መገለጫ ነው ብሏል እንዳትሉ።
በዚህ ሁኔታ ግን ጥልቅ ማስተዋል ነው።
በሁለቱም ምሳሌዎች ላይ
አንድ ሰው በስብሰባዎች ላይ ስለመገኘትም ሆነ
ስለ አለባበስና ስለ አጋጌጥ
ምክር ያስፈልጋቸዋል ብሎ ሊያስብ ይችላል።
ግን ከአንድ ነገር በስተ ጀርባ
ያለውን እውነታ ማየታችን
ጥልቅ ማስተዋል እንዲኖረን ያስችላል።
አንድን ጉዳይ በተሟላ መንገድ ለመያዝ ይህን ማድረግ አለብን።
መጀመሪያ ላይ የጠቀስናትን እህት
ወንድሞች ለብዙ ዓመታት ጉባኤ አመላልሰዋታል።
ከጊዜ በኋላም ባለቤቷ ለእውነት ፍላጎት አሳየ።
ወጣቷ እህት ደግሞ
ቤተሰቦቿ ወደ እውነት መጥተዋል።
ከዚህ ምን እንማራለን?
ጊዜ ወስደን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን
ጥልቅ ማስተዋልና አሳቢነት በማሳየት
ስናበረታታቸው የይሖዋን ሞገስ እናገኛለን።
ጥልቅ ማስተዋል ማሳየትን
ከባድ የሚያደርግ ሌላም ነገር አለ።
ለሥራችን ያለን አመለካከት።
አንዳንድ ጊዜ
በሥራችን ላይ በጣም ከማተኮራችን የተነሳ
ሥራችን በሌሎች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ አይታየንም።
ሁላችንም በግለሰብም ይሁን
በዲፓርትመንት ደረጃ
ሥራችንን ለማከናወን ጠንክረን እንሠራለን።
ይህን ማድረጋችን ጥሩ ነው።
ምክንያቱም በትጋት መሥራት
የአምልኳችን ክፍል ነው።
ሆኖም አንዳንዴ
በራሳችን ሥራ ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ
ቆም ብለን ከጀርባ ያለውን ትልቁን ምስል
ለማስተዋል እንሞክር።
እስቲ የጥልቅ ማስተዋልን ትርጉም
መለስ ብለን እንይ።
ስለ አንድ ነገር
ግልጽ የሆን ግንዛቤ ለማግኘትና
አንድን ሰው ጥበበኛና ስኬታማ
እንዲሆን የሚያስችል የእውቀት ዓይነት ነው።
ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ማግኘት።
ይህን ማድረግ ሁሌ ቀላል አይደለም።
ግን አስታውሱ፤
ብዙ ከተሰጠው ሁሉ
ብዙ ይጠበቅበታል።
ስለዚህ ሥራችንን በአግባቡ ማጠናቀቃችን ብቻ
ስኬታማ አያደርገንም።
ሥራችንን ለማጠናቀቅ መጣራችን አስፈላጊ ነው።
ግን ስኬታማ መሆን የምንችለው
ሌላ ሰው ወይም ሌላ ዲፓርትመንትም
ሥራውን እንዲያጠናቅቅ ስንረዳ ነው።
ይህ ደግሞ ሌሎችን ለማጠናከርና
ለማጽናት ይረዳል።
ስለ አንድ ነገር ጥልቅ ግንዛቤ ማግኘታችን፣
ጥልቅ ማስተዋል ማሳየታችንና
ከሌሎች ጋር በአንድነት ወይም ተባብረን መሥራታችን
ስኬታማ ያደርገናል።
ታዲያ ጥልቅ ማስተዋል ለማሳየትና
ከወንድሞቻችን ጋር ተባብረን ለመሥራት
ምን ይረዳናል?
እባካችሁ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን አውጡና
ፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2
ቁጥር 3ና 4ን
አብረን እናንብብ።
ፊልጵስዩስ 2:3, 4
“ሌሎች ከእናንተ እንደሚበልጡ በትሕትና አስቡ እንጂ
“በጠበኝነት መንፈስ ወይም
“በትምክህተኝነት ምንም ነገር አታድርጉ፤
“ስለ ራሳችሁ ፍላጎት ብቻ ከማሰብ ይልቅ
እያንዳንዳችሁ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎትም ትኩረት ስጡ።”
እዚህ ላይ የተጠቀሰው ፍላጎት የሚያመለክተው
መንፈሳዊ ፍላጎትን ነው።
ታዲያ ስለ ሌሎች መንፈሳዊ ፍላጎት እንድናስብ
የሚረዳን ምንድን ነው?
ትሕትና ነው።
ሌሎች ለሚሠሩት ሥራ ትኩረት መስጠት።
እንዲያውም ይሖዋ የመከረን
ሌሎች ሰዎች የሚሠሩትን ሥራ
ወይም ሌሎች ዲፓርትመንቶች የሚያከናውኑትን ሥራ
ከእኛ የተሻለ ወይም እንደሚበልጥ
አድርገን እንድንመለከተው ነው።
ደስ የሚለው፣ እነሱን እንዲህ ያስባሉ።
ሥራችንን በአግባቡ አከናውነናል እንበል።
ግን ሥራችንን ያከናወንነው
በሌሎች ዲፓርትመንቶች ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድረን ከሆነ
የይሖዋን ሞገስ አግኝተናል ማለት እንችላለን?
የሠራነው የይሖዋን ሥራ ነው።
ግን የሌሎችን ሥራ የምናስተጓጉል ከሆነ
ያስተጓጎልነው የማንን ሥራ ነው?
የይሖዋን።
ልናስብበት ይገባል።
ሙሴ በመሪባ ውኃ ማውጣት ችሎ ነበር።
የይሖዋን ሞገስ ግን አላገኘም።
ምን እንማራለን?
እንዳንድ ጊዜ እኛ የምንሠራው ሥራ
ከሌሎች ይበልጥ አስፈላጊ፣
ከበድ ያለና አጣዳፊ እንደሆነ እናስብ ይሆናል።
ሌሎች የሚያከናውኑት ሥራ ግን
ቀላል እንደሆነ ይሰማን ይሆናል።
እኛ የምንላቸውን ብቻ
ማድረግ እንዳለባቸው ይሰማን ይሆናል።
ሆኖም ትሕትና ከሌሎች ጋር በመተባበርና
በስምምነት እንድንሠራ ይረዳናል።
ለችግሮች የጋራ መፍትሔ ፈልጉ።
ጥልቅ ማስተዋል ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ
መጠቀምን እንደሚጨምር አይተናል።
ብዙዎች የማመዛዘን ችሎታ ይጎድላቸዋል።
እኛ ግን እንደ እነሱ መሆን የለብንም።
ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ ካለን
ግልጽ የሆነ የሐሳብ ግንኙነት በማድረግ
አለመግባባቶችን መቀነስ እንችላለን።
ለምሳሌ “እሳት ማጥፊያ መሣሪያ
እፈልጋለሁ” አላችሁ እንበል።
እሳት ማጥፊያውን የፈለጋችሁት ግን
መሣሪያው ጊዜ ስላለፈበት ለመቀየር ይሁን
ወይም እሳት ስለተነሳ
ለሌሎች ግልጽ አይደለም።
የማመዛዘን ችሎታ ያለው ሰው ግን
‘እሳት ተነስቷል’ ብሎ
በግልጽ ለሌሎች ይናገራል።
ግልጽ ግንዛቤ አስፈላጊ ነው።
ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት
የጥልቅ ማስተዋል መገለጫ ነው።
የሌሎች ሥራ አስፈላጊ እንደሆነ መገንዘባችንና
እነሱ ከእኛ የተሻሉ እንደሆኑ
በትሕትና መቀበላችን ስኬታማ ያደርገናል።
ይህንን በማድረግና
ሌሎች ለሚሠሩት ሥራ ትኩረት በመስጠት
ተባብረንና ተስማምተን መሥራት እንችላለን።
አንድን ሥራ በተመለከተ
ሌሎች የእኛን ውሳኔ ዝም ብለው
እንዲቀበሉ ከመጠበቅ ይልቅ
በጋራ ማቀዱ የተሻለ ነው።
ይህም አንድነታችንን ያጠናክራል።
አንድነት መኖሩ እንድንጸና ያደርገናል።
ይሖዋ ሞገሱን የሚያሳየን ያኔ ነው።
መዝሙር 133:1 እንዲህ ይላል፦
“ወንድሞች በአንድነት አብረው ቢኖሩ
“ምንኛ መልካም ነው!
ምንኛስ ደስ ያሰኛል!”
አንድ ነገር እንጨምር።
ለመጽናት የሚረዳ።
ከለውጥ ጋር መላመድ።
የምንኖርበትና የምናገለግልበት ቦታ
ሲለወጥ።
የአገልግሎት ምድባችንና
የምንሠራበት መንገድ ሲለወጥ።
ወይም የምንሠራበት መሣሪያ ሲቀየር።
ለውጥ ፍርሃትና ጭንቀት ሊፈጥርብን ይችላል።
ያጋጥማል።
ሁላችሁም ከአንዳንድ ለውጦች ጋር መላመድ
ጠይቆባችኋል።
ታዲያ እናንተ ራሳችሁ በለውጥ ውስጥ ሆናችሁ
ሌሎችን ማጽናት የምትችሉት እንዴት ነው?
እስቲ መጀመሪያ ከወንድሞች ጋር እንነጋገር።
የአንድን ወንድም ወይም የአንዲትን እህት
ሁኔታ የሚለውጡ ውሳኔዎችን በማድረግ
ትሳተፉ ይሆናል።
ይህ ከባድ ኃላፊነት እንደሆነ
ምንጊዜም አስታውሱ።
ውሳኔያችሁ የይሖዋን ሞገስ
እንደሚያስገኝ አረጋግጡ።
ለውጦች ሲኖሩ ጥልቅ ማስተዋል
ሌሎችን ለማጽናት እንድትችሉ ይረዳችኋል።
እንዴት?
እባካችሁ ኢሳይያስ መጸሐፍን አውጡና
ምዕራፍ 60 ቁጥር 17ን አብረን እናንብብ።
“በመዳብ ፋንታ ወርቅ፣
“በብረት ፋንታ ብር፣
“በእንጨት ፋንታ መዳብ፣
በድንጋዮችም ፋንታ ብረት አመጣለሁ።”
እዚህ ላይ ልብ በሉ፦
“ሰላምንም የበላይ ተመልካቾችሽ፣
ጽድቅንም አሠሪዎችሽ አድርጌ እሾማለሁ።”
ጥቅሱ ምን እያለ እንደሆነ እናውቃለን።
ይሖዋ ለውጥ እንደሚያመጣ እየተናገረ ነው።
ዛሬም ይህን ለውጥ እያየን ነው።
በየሳምንቱ ማለት ይቻላል ለውጥ አለ።
ለውጡን እያመጣ ያለው ይሖዋ ነው።
ይህም ጥሩ ነው።
መዳብ ጥሩ የማዕድን ዓይነት ነው።
ወርቅ ግን የበለጠ ነው።
ይሖዋ ይህን ለውጥ ሲያመጣ ማየት
ያስደስተናል።
ሆኖም እንደዚህ ዓይነት ለውጦች
በሕይወታችን ላይ ሲከሰቱ ያስጨንቁናል።
ግን ከለውጡ ጋር አብረን መሄድ እንችላለን።
ሊያጋጥሙን የሚችሉ
አንዳንድ ለውጦችን እስቲ እናስብ።
በጥቂት ሰዎች ብዙ ማተም የሚችል
አዲስ የማተሚያ መሣሪያ ቢገባ
የሥራ ምድብ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል
ምንም ጥያቄ የለውም።
ግን ለውጡን እንዴት እንቀበል?
ጥቅሱ ስለበላይ ተመልካቾች
ምንድን ነው ያለው?
‘ሰላምንና ጽድቅን የበላይ ተመልካቾችሽና
አሠሪዎችሽ አድርጌ እሾማለሁ።’
ምን እያላችሁ ነው?
ሌሎች ለውጡን በጥሩ መንገድ እንዲቀበሉ
እናንተ ወንድሞች ማገዝ ትችላላችሁ።
ስለ ጽድቅ እንዲሁም ይሖዋ አገልጋዮቹን ስለሚይዝበትና
ስለሚንከባከብበት መንገድ ምን እንማራለን?
ዕብራውያን 6:10ን እናንብበው።
ዕብራውያን ምዕራፍ 6 ቁጥር 10፦
“አምላክ ቅዱሳንን በማገልገልም ሆነ
“ወደፊትም ማገልገላችሁን በመቀጠል
“የምታከናውኑትን ሥራ እንዲሁም ለስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር በመርሳት
ፍትሕ አያዛባም።”
የሚገርም ሐሳብ ነው አይደል?
ይሖዋ አንድ ሰው የሠራውን ሥራ ቢረሳ
ፍትሕ እንደማዛባት ይቆጥረዋል።
ግን እኛ በተደረገው ለውጥ የተነሳ
ሥራችን እንደተረሳ ሊሰማን ይችላል።
ለውጦች ቢኖሩም ወንድሞቻችንን ግን
ፈጽሞ አንረሳቸውም።
ጽድቅ ማድረግ የምንፈልግ ከሆነ
ከመዳብ ወደ ወርቅ የመሰሉ ለውጦች
ወይም ማስተካከያዎች ሲኖሩ
ወንድሞቻችንንም ሆነ የሠሩትን ሥራ
መቼም ቢሆን አንረሳም።
ማስተካከያዎችን ስናደርግ
ርኅራኄ ማሳየት ይኖርብናል።
አንድ የበላይ ተመልካች
የዓይን መከለያ እንደተደረገለት ፈረስ
ሙሉ ትኩረቱ ሥራው ላይ ብቻ አይሆንም።
ወንድሞችን ማጽናት የምንችለው
ስናውቃቸው ነው።
ስለዚህ ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፦
‘ወንድሞቼንና እህቶቼን ጠጋ ብዬ
ስለ ቤተሰባቸው፣
ስላጋጠሟቸው ተፈታታኝ ሁኔታዎች፣
ስለሚሰማቸው ስሜትና
ምን ሐሳብ እንዳላቸው እጠይቃቸዋለሁ?’
እንዲህ ስታደርጉ
እውነተኛ ስሜታቸውን መረዳት ትችላላችሁ።
እርዳታ የሚያስፈልጋቸው
እነማን እንደሆኑ ግልጽ ይሆንላችኋል።
አንዳንዶች አልተደሰቱም ማለት
ለውጥ አይኖርም ማለት አይደልም።
ይሖዋ ማስተካከያዎች እንደሚደረጉ ተናግሯል።
ያም ቢሆን ያከናወኑትን ሥራም ሆነ
ያሳዩትን ፍቅር ፈጽሞ አይረሳም።
እኛም ሥራቸውንና ፍቅራቸውን
መቼም አንረሳም።
ራሳቸውን ከለውጡ ጋር እንዲያስማሙ
እንረዳቸዋለን።
ይህንን ስናደርግ
የይሖዋን ሞገስ እናገኛለን።
እናንተ እህቶችም የምታበረክቱት እርዳታ አለ።
ለውጡ እናንተንም የሚነካ ቢሆንም እንኳ
አዎንታዊ አመለካከታችሁና
የምታደርጉት ድጋፍ
ሌሎች ለውጡን እንዲቀበሉት ሊያደርጋቸው ይችላል።
ለውጥ እንዳለና ወንድሞች ለምን ለውጡን እንዳደረጉት ሲገባችሁ
እነዚህን ለውጦች በተሻለ መንገድ
ለመተግበር የሚያስችሉ
ገንቢ ሐሳቦችን ማካፈል ትችላላችሁ።
ጥልቅ ማስተዋል በማሳየት
የይሖዋን ሞገስ ማግኘት የምንችልባቸው
አንዳንድ መንገዶች እነዚህ ናቸው።
ይህን ስናደርግ ሌሎችን ማጽናት እንችላለን።
ጊዜ ወስዳችሁ አዳምጡ፣
አሳቢነትም አሳዩ።
የሌሎች ሥራ ከእናንተ ሥራ ይበልጥ
አስፈላጊ እንደሆነ በትሕትና አስቡ።
ይህም በመካከላችን የአንድነትና
የትብብር መንፈስ እንዲሰፍን ያደርጋል።
ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ
ወንድሞችንና እህቶችን ደግፉ።
ጥልቅ ማስተዋል ይሖዋን ስናገለግል
ስኬታማ እንድንሆን ያደርገናል።
ሁላችሁም በምድባችሁ
ስኬታማ እንድትሆኑ እንመኛለን።
በዚህ ዘመን ይሖዋ
ታላላቅ ነገሮችን እያከናወነ ነው።
ሁላችንም በዚህ አስደናቂ
መንፈሳዊ ገነት ውስጥ
አምላካችንን የማገልገል ውድ መብት አለን።
ሁሉም ሰው በዚህ ገነት ውስጥ እንዲቆይ እንፈልጋለን።
ሌሎችም ወደዚህ መንፈሳዊ ገነት እንዲመጡ እንጋብዛለን።
እናንተ የ158ኛው ክፍል
የጊልያድ ተመራቂዎች
በዚህ ትምህርት ቤት
ብዙ ሥልጠና ስታገኙ ቆይታችኋል።
ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ለመርዳት
የሚያስችላችሁን ይህንን ውድ አጋጣሚ
እንድትጠቀሙበት እናሳስባችኋለን።
እንወዳችኋለን!
ጥልቅ ማስተዋል ማሳየታችሁንና
የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት ጥረት ማድረጋችሁን
እንደምትቀጥሉ ሙሉ በሙሉ እንተማመንባችኋልን።
አሁን ደግሞ የዚህ ፕሮግራም አጓጊ ወደሆነው ክፍል እንሸጋገራለን።
እንደምታዩት እዚህ ጠረጴዛው ላይ ፖስታዎች ተቀምጠዋል።
እርግጥ እነዚህ ፖስታዎች ተራ ፖስታዎች አይደሉም።
የውድ ተማሪዎቻችን ዲፕሎማ የያዙ ናቸው።
እነዚህ ተማሪዎች ዲፕሎማቸውን ከተቀበሉ በኋላ
እንደ ቀድሞው “ተማሪዎች” አንላቸውም።
“ተመራቂዎች” ነው የምንላቸው።
“የጊልያድ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች”
እያንዳንዱ ተማሪ እዚህ መጥቶ ዲፕሎማውን ይቀበላል።
ዲፕሎማዎቹን በመስጠት ደግሞ ወንድም ዴቪድ ሼፈር ያግዘናል።
ወንድም ቲቶ አብሪዮ ወደ ዶሚኒካን ሪፑብሊክ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ፍራንክሊን ኤሚ ወደ ሄይቲ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ራንዲ አላቶሬ በዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግል ተመድቧል።
ወንድም ማክዴልና እህት ብሪጅት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ጄሽ አሩላፓ በስሪ ላንካ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግል ተመድቧል።
ወንድም ቻድ እና እህት ሊያ ወደ ማይክሮኔዥያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ሚርዛ ቡንዳቪትዛ ወደ ክሮኤሽያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ክርስቲያን እና እህት ጁልያና ወደ ፔሩ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ቲም እና እህት ብሪትኒ ወደ ኮንጎ ኪንሻሳ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ሮቢን ዳልማን ወደ ማዕከላዊ አውሮፓ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ግሪጎሪ ፍራንሷ በሞዛምቢክ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግል ተመድቧል።
ወንድም ኤሪክ ጎላምፕ ወደ ፓላንድ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ማርክ እና እህት ሜሊሳ በጃፓን ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።
ወንድም ዳንኤል እና እህት ስቴፊ ወደ ፓራጓይ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ኒክ እና እህት ካረን ወደ ፓፑዋ ኒው ጊኒ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ኒኮስ ካሳዶኒስ ወደ ግሪክ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ኤርኔስቶ እና እህት አንፓሮ ወደ ቺሊ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ሩበን ማቱሽ ወደ ቺሊ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ዴቭ እና እህት ሉደቪን ወደ ካሜሩን ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ሎያሊቲ ሙሶና ወደ ዚምባብዌ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም አልበርት ሙዛሜ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ጂያንማሬ ኒንዳይዛቫ ወደ ሩዋንዳ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ቺኩንዱ ኒንጃይዋ ወደ ማላዊ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ኤድጋር ኦርቴጋ ወደ ስፔን ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ኢማኑኤል እና እህት ሰኒ ወደ ቡልጋሪያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ካርሎስ እና እህት ሊያ ወደ ቬኔዙዌላ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ሴናድ እና እህት ማርቲና ወደ ክሮኤሽያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ክዊሲ እና እህት ኬይሻ ወደ ትሪኒዳድና ቶባጎ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
እህት አኪን ሽሪናር ወደ ቱርክዬ ቅርንጫፍ ቢሮ ትመለሳለች።
ወንድም ዴቪድ ሴኬ ወደ ሃንጋሪ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ኒልራ እና እህት ሲንዲ ወደ ምያንማር ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ፔፒን ፋንደርፌን በኮንጎ ኪንሻሳ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግል ተመድቧል።
እህት ዋንጂኩ ዋይሺኮ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ ትመለሳለች።
ወንድም ቤንያ እና እህት ጊፍቲ ወደ ላይቤሪያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
በጣም አስደሳች ነበር!
እኔ ቀላሉ ሥራ ነው የደረሰኝ።
በጊልያድ ምረቃ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ሊቀ መንበር የሆንኩበት ጊዜ ትዝ ይለኛል፤
ከአምስት ዓመት በፊት ነበር፤
148ኛው ክፍል ላይ።
ልክ ወረርሽኙ ከመጀመሩ በፊት።
ያኔ ትዝ ይለኛል፣ መጨባበጥ አንችልም ነበር።
መመሪያውን ለማክበር ሰላም የምንባባለው በክርናችን ነበር።
አሁን ግን እጃቸውን ጨብጠን
“እንኳን ደስ ያላችሁ” ለመባባል በመብቃታችን በጣም ደስ ብሎናል።
ባገኙት ስኬት ተደስተናል።
አሁን ተማሪዎቹን አንድ ላይ ሆነው እንመልከት።
ውድ ተማሪዎች፣ ሁላችንም ኮርተንባችኋል።
ያገኛችሁት ስኬት እንድንኮራባችሁ አድርጎናል።
በዚሁ እንደምትቀጥሉም እንተማመናለን።
አሁን ደግሞ ወንድም ሴናድ ፒዋሎዌጅ
(ትክክል የጠራሁት ይመስለኛል፤
በነገራችን ላይ ቅድም ወንድም ሼፈር ያገዘኝ ለዚህ ነው።)
ለማንኛውም ሴናድ ፒዋሎዌጅ የተማሪዎቹን ደብዳቤ ያነብልናል።
ውድ የበላይ አካል ወንድሞች፣
በጊልያድ ትምህርት ቤት የመማር አስደናቂ አጋጣሚ ስለተሰጠን
ከልብ እናመሰግናችኋለን።
ያሳያችሁን ታማኝ ፍቅር የእያንዳንዳችንን ልብ በጥልቅ ነክቶታል።
ከይሖዋ የምናገኘው ትምህርት እጅግ የላቀ እንደሚሆን ጠብቀን ነበር።
ሆኖም ኤፌሶን 3:20 እንደሚለው
እዚህ ስንመጣ ያገኘነው ካሰብነው ሁሉ እጅግ የላቀ ነገር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን ስንማር የይሖዋና የኢየሱስ ባሕርያት ይበልጥ ግልጽ ሆነውልናል።
ይሖዋና ኢየሱስ ለሰው ልጆች ምን ያህል እንደሚያስቡ ስንገነዘብ
ልባችን በጥልቅ ተነክቷል።
ለእኛ ያላቸውን ፍቅር ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም።
ለሌሎች ፍቅር በማሳየት ረገድ እነሱን እንኮርጃለን።
ከይሖዋ መማር እጅግ በጣም ትልቅ ስጦታ ነው።
አስተማሪዎቻችንም ልክ እንደ አንድ አፍቃሪ አባት
የይሖዋን ቃል በመጠቀም
እያንዳንዳችንን ለቀጣዩ ምድባችን በሚገባ አዘጋጅተውናል።
እናንተ የበላይ አካል አባላትም
ውድ ጊዜያችሁን መሥዋዕት አድርጋችሁ የሰጣችሁን ትምህርቶች
መንፈሳዊነታችን ይበልጥ እንዲጨምር አድርጓል።
ለእኛ በግለሰብ ደረጃ ለሰጣችሁን ትኩረትና
በትጋት ለምታከናውኑት ሥራ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።
በተጨማሪም ከቀረቡልን ንግግሮች፣
ከበላይ አካሉ ረዳቶችና ሌሎች ተጋባዥ አስተማሪዎች
በእጅጉ ተጠቅመናል።
እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአንድ ላይ ተዳምረው
እንደ አስደሳች ጣዕመ ዜማ ሆነውልናል።
ይህ ጣዕመ ዜማ ለዘላለም መሰማቱን ይቀጥላል።
መማሪያ ክፍል መጥተው ንግግር ባያቀርቡልንም
የዩናይትድ ስቴትስ ቤቴል ቤተሰብ አባላት ካሳዩን
ፍቅር፣ ልግስናና የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ትልቅ ትምህርት አግኝተናል።
ያደረጋችሁልን ነገር ሁሉ የይሖዋ ዓይነት ባሕርይ እንዳላችሁ የሚያሳይ ነው።
ምሳሌነታችሁ እኛም የይሖዋ ሕዝቦችን ሞቅ ባለ ስሜት ለመቀበልና
እነሱን ለመውደድ የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ አነሳስቶናል።
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስናስብ
ራሳችንን መዝሙር 116:12 ላይ ያለውን ጥያቄ ለመጠየቅ ያነሳሳናል፦
“ላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ?”
እርግጥ ጥያቄውም እንደሚጠቁመው
የይሖዋን ውለታ ሙሉ በሙሉ መመለስ አንችልም።
ግን እኛም ልክ እንደ ርብቃ ዓይነት መልስ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን፦
“አዎ፣ እሄዳለሁ” እንላለን።
እንደ ቤተሰብ ስለተቀራረብን መለያየቱ ቀላል አይሆንልንም።
እንደዚያም ሆኖ የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ፣
የተማርነውን በሥራ ላይ ለማዋልና
በሚጠበቅብን መንገድ ለመኖር ዝግጁዎች ነን።
ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ፣
የ158ኛው ክፍል የጊልያድ ተማሪዎች።
በጣም ግሩም ደብዳቤ ነው።
ደብዳቤው የተማሪዎቹን ስሜት በሚገባ ያንጸባርቃል።
አብራችሁን አምስት ወር ስለቆያችሁ ደስ እንዳላችሁ ነግራችሁናል፤
እኛም በጣም ደስ ብሎናል።
ስሜቱ የጋራ ነው።
አንዳችን በአንዳችን እምነት ተበረታተናል።
እስቲ አሁን ደግሞ ቅድም ወዳነሳነው ወደ ማቴዎስ 5:13 እንመለስ።
እዚያ ላይ ኢየሱስ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ” ብሏል።
እኛም ለእናንተ ይህንኑ እንላችኋለን።
ቅድም ጨው ስላሉት የተለያዩ ባሕርያት ተነጋግረናል።
ለምሳሌ ጣዕም ይሰጣል፤
የተለያዩ ጀርሞችን ይገድላል፤
እንዲሁም ምግብ ሳይበላሽ እንዲቆይ ያደርጋል።
እስቲ አሁን ደግሞ አንድ ሌላ ባሕርይ እንጨምር፤
ጨው ስላለው ዋጋ።
ጨው በጣም ውድ ነገር ነው።
ጠለቅ ብሎ ማስተዋል የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦
“በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ጨው ሁልጊዜ በቀላሉ የሚገኝ ነገር አልነበረም።
በጨው ምክንያት ጦርነቶችና ዓመፆች ተቀስቅሰዋል።
በጥንቷ ቻይና ከወርቅ ቀጥሎ ውዱ ነገር ጨው ነበር።
ሰዎች ለጨው ብለው ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ለባርነት ይሸጡ ነበር።
የቄሳር ወታደሮች የሚቀበሉትን ገንዘብ ጨው ይገዙበት ነበር።
የገዙበትን ጨው በአጠቃላይ ሳላሪየም ብለው ይጠሩት ነበር።
ደመወዝ ተብሎ የተተረጎመው ሳለሪ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የመጣው ከዚህ ነው።”
ኢየሱስ በነበረበት ዘመን
ጨው እንደ ልብ ይገኝ የነበረ ቢሆንም ኢየሱስ ይህን ታሪክ ያውቃል፤
ጨው እንደ ውድ ነገር ይታይ እንደነበር ኢየሱስ በሚገባ ያውቃል።
በኢየሱስ ዘመን ጨው በሙት ባሕር አቅራቢያ ከነበሩት ኮረብቶችና
የሙት ባሕር ውኃን በማትነን ይገኝ ነበር።
ከእነዚህ ቦታዎች በጣም ብዙ መጠን ያለው ጨው ይገኝ ነበር።
ስለዚህ ኢየሱስ እሱ በነበረበት ዘመን ጨው እንደ ልብ ይገኝ የነበረ ቢሆንም
ጨው በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ የነበረውን ቦታ ያውቅ ነበር።
በተጨማሪም ኢየሱስ በዚያን ወቅት ጨው
ለተለያዩ ዓላማዎች እንደሚያገለግል ያውቃል፤
ዛሬ ለተለያዩ ዓላማዎች እንደምንጠቀምበት።
ይህ ብቻ ግን አይደለም።
ኢየሱስ በእያንዳንዳችን ሰውነት ውስጥ
226 ግራም ወይም 0.23 ኪሎ ግራም ጨው እንደሚገኝ በሚገባ ያውቃል።
የተዋጣለት ሠራተኛ ሆኖ ከአባቱ ጋር ሁሉን ነገር ስለሠራ
(የሰው ልጆችን ጭምር ማለት ነው)
ውስጣችን ምን እንዳለ በሚገባ ያውቃል።
ይህ ጨው ከሌለ ልንሞት እንችላለን።
እንዲያውም መጠኑ ቢቀንስ ወይም የሰውነታችን የጨው መጠን ቢዛባ
ማቅለሽለሽ፣ ብዥታ፣ የጡንቻ መኮማተር፣ መንቀጥቀጥ፣ የአንጎል ዕጢ፣ ራስን መሳት፣
ሌላው ቀርቶ በአንዳንድ ሁኔታዎች ሞት ሊያስከትል ይችላል።
ስለዚህ ኢየሱስ የተዋጣለት ሠራተኛ ሆኖ ከይሖዋ ጋር
የሰው ልጆችን ጨምሮ ሁሉን ነገር ስለሠራ ይህን ያውቃል።
በመሆኑም ትልቅ ቦታ እንደሚሰጣቸው በመናገር እያደነቃቸው ነበር።
እኛም እንዲህ ልንላችሁ እንፈልጋለን፦
እንወዳችኋለን፤
እናደንቃችኋለን፤
ትልቅ ቦታ እንሰጣችኋለን።
እስካሁን ላደረጋችሁት ነገር ሁሉ እናመሰግናችኋለን።
ወደፊትም ብዙ ነገር እንደምታከናውኑ እንተማመንባችኋለን።
ከመደምደማችን በፊት በዘኁልቁ ምዕራፍ 6 ላይ ያለውን ጸሎት ልንጋብዛችሁ እንፈልጋለን፦
“ይሖዋ ይባርክህ፤
ደግሞም ይጠብቅህ።
ይሖዋ ፊቱን ያብራልህ፤
ሞገሱንም ያሳይህ።
ይሖዋ ፊቱን ወደ አንተ ይመልስ፤
ሰላምም ይስጥህ።”
ይህ ጸሎታችን ነው፤
ለእያንዳንዳችሁ ለ158ኛ የጊልያድ ክፍል 52 ተመራቂዎች በሙሉ።
ተመራቂዎቹ በተመደቡባቸው ቦታዎች ሁሉ በረከት እንደሚሆኑ እርግጠኞች ነን።
በቅርቡ ደግሞ በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ለተመራቂዎቹ የቀረቡ ንግግሮች
jw.org እና JW ላይብረሪ አፕሊኬሽን ላይ ይወጣሉ።
ከመለያየታችን በፊት በዚምባብዌ ስለሚገኙ ወንድሞቻችን ጥቂት እንበላችሁ።
ዚምባብዌ የባሕር በር የሌላት አገር ስትሆን ሦስት የአየር ንብረቶች አሏት።
አንደኛ፣ ወይናደጋ - ተራራ ላይ ያሉ ሜዳማ ቦታዎች።
ሁለተኛ፣ ቆላ - ዛምቤዚ ሸለቆ ውስጥ ያሉ ቦታዎች።
ሦስተኛ፣ ደጋ - በስተ ምሥራቅ ያሉት ተራራማ አካባቢዎች።
በአገሪቱ ውስጥ 16 የሚያህሉ የሥራ ቋንቋዎች አሉ።
በቆሎ በመላ አገሪቱ የሚበቅል ሲሆን የአገሪቱ ሰዎችም በደንብ ይጠቀሙበታል።
ይቀቅሉታል፤ ይጠብሱታል፤
አልፎ ተርፎም ሜ የተባለ ባሕላዊ መጠጥ ይሠሩበታል።
ከባሕላዊ ምግባቸው አንዱ ሳድዛ ነው።
ነጩን በቆሎ ይወቅጡትና ገንፎ እስኪሆን ድረስ ቀስ ብለው ያበስሉታል።
ሳድዛ የሚበላው በእጅ ነው።
ሳድዛ ከተለያዩ ነገሮች ጋር የሚበላ ሲሆን
ከበሬ ሰኮና ከተሠራ ወጥ፣ ከተጠበሰ ሥጋና የኦቾሎኒ ስጎ ከፈሰሰበት አትክልት ጋር ይቀርባል።
ምሥራቹ ወደ ዚምባብዌ የደረሰው በ1900 አካባቢ ነው።
ከማላዊና ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ስደተኛ ሠራተኞች
ጽሑፎቻችንን ይዘው መግባት ጀመሩ።
ከዚያም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ተቋቋመ።
በ1924 የመጀመሪያው አስፋፊ ናይሳን ሙክሩንዳ ተጠመቀ።
ብዙም ሳይቆይ መንግሥት የተለያየ ዘር ያላቸው ሰው አንድ ላይ በመሰብሰባቸው ምክንያት
ሥራችንን መቃወም ጀመረ።
በ1940 ሁሉም ጽሑፎቻችን ታገዱ።
ብዙ ወንድሞቻችን ታስረዋል፤ ፍርድ ቤትም ቆመዋል።
ያም ቢሆን በአቋማቸው ጸንተዋል።
ከዚያም ከስድስት ዓመት በኋላ እገዳው ተነሳ።
በ1970 በአገሪቱ ጦርነት እስኪፈነዳ ድረስ የመንግሥቱ መልእክት መስፋፋቱን ቀጠለ።
ጦርነቱ ሲጀመር በርካታ ወንድሞቻችን በገለልተኝነት አቋማቸው ምክንያት ወህኒ ቤት ተጣሉ።
ይህ መጽሐፍ ቅዱስ እስር ቤት ውስጥ የገቡ ወንድሞች ሲቀባበሉት የነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
ደስ የሚለው፣ ላለፉት አሥርተ ዓመታት በዚያ ያሉ ጉባኤዎች ሰላም አግኝተዋል።
አሁን 50,000 የሚያህሉ አስፋፊዎች ከ103,000 በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እየመሩ ነው።
ከእነዚህ ጉባኤዎች አንዱ በዋና ከተማዋ በሃራሬ የሚገኘው የዋተርፎልስ ጉባኤ ነው።
የጉባኤው አስፋፊዎች በአገሪቱ ለመጀመሪይ ጊዜ በተሠራው አዳራሽ ውስጥ ይሰበሰባሉ።
አስፋፊዎቹ 200 ጥናቶች ይመራሉ።
በዚያ ያሉ ወንድሞችና እህቶች ለሁላችንም ሰላምታ ልከውልናል።
በሾና ቋንቋ “እንዴት ናችሁ?
ሁላችሁንም እንወዳችኋለን” ማለት ነው።
እኛም ለሁላችሁም ሰላምታችንን ልከንላችኋል።
ይህ ከይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት የሚተላለፍላችሁ
JW ብሮድካስቲንግ ነው።