JW subtitle extractor

JW ብሮድካስቲንግ—ሚያዝያ 2026

Video Other languages Share text Share link Show times

ለJW ብሮድካስቲንግ ፕሮግራም እንኳን ደህና መጣችሁ!
በዚህ ወር ፕሮግራማችን ላይ
ራሳችንን በይሖዋ ዓይን ማየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።
የሚክያስ መጽሐፍን በጥልቀት በመመርመር
ስለ ሐቀኝነትና ልክን ስለማወቅ ጥሩ ትምህርት እናገኛለን።
የምናደርጋቸው ትንሽ የሚባሉ የደግነት ድርጊቶች እንኳ
በሰዎች ላይ የሚያሳድሩትን ከፍተኛ ተጽዕኖም እናያለን።
ይህ JW ብሮድካስቲንግ ነው።
አንዲት እህታችን እንዲህ ስትል ጽፋለች።
እናንተም እንደ እሷ ዓይነት ስሜት ተሰምቷችሁ ያውቅ ይሆናል።
“ለይሖዋ ያለኝ ፍቅር ወይም
“እሱን ለማገልገል የማደርገው ጥረት
ምንም ያህል ቢሆን ምንጊዜም በቂ እንዳልሆነ ይሰማኛል።”
የሚያሳዝነው አንዳንድ ጊዜ ፍጹም ያልሆነው ልባችን
ልፋታችን ሁሉ ከንቱ እንደሆነና
መቼም ቢሆን ይሖዋን ማስደሰት እንደማንችል ይነግረን ይሆናል።
ወይም ደግሞ ይሖዋ ይቅር ባይ አምላክ እንደሆነ ብናውቅም
ከዚህ በፊት በተናገርነው ወይም ባደረግነው ነገር
የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማናል።
የተሳሳተ ነገር ተናግረን
ወይም ኃጢአት ሠርተን ይሆናል።
ከዓመታት በፊት።
እነዚህን ነገሮች እያሰብን የምንብሰለሰል ከሆነ
ተስፋ ልንቆርጥ
ወይም በጭንቀት ልንዋጥ እንችላለን።
አብዛኞቻችን እንዲህ ዓይነቱ ስሜት
የሆነ ወቅት ላይ ተሰምቶን ይሆናል።
እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?
በመጀመሪያ ሐዋርያው ዮሐንስ
በይሖዋ ቅዱስ መንፈስ ተመርቶ
በ1 ዮሐንስ 3:19, 20 ላይ የጻፈውን እንመልከት።
ንግግራችንም የተመሠረተው በዚህ ጥቅስ ላይ ነው።
የንግግራችን ጭብጥ
አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው የሚል ነው።
አንደኛ ዮሐንስ 3:19, 20 እንዲህ ይላል፦
“ከእውነት ወገን መሆናችንን በዚህ እናውቃለን፤
“ልባችንም በፊቱ እንዲረጋጋ እናደርጋለን፤
“ይህን የምናደርገው ልባችን እኛን በሚኮንንበት ነገር ሁሉ ነው፤
“ምክንያቱም አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው፤
ደግሞም ሁሉንም ነገር ያውቃል።”
ጥቅሱ ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ ምን እንዳለ ልብ በሉ።
“ልባችንም!”
“ልባችንም በፊቱ እንዲረጋጋ እናደርጋለን።”
እንዲሁም “ልባችን እኛን በሚኮንንበት ነገር ሁሉ”
ስለዚህ ጥቅሱ ላይ እንደምናነበው
ሐዋርያው ዮሐንስም እንኳን ስለራሱ
አሉታዊ ስሜት ተሰምቶት ሊሆን ይችላል።
ግን ዮሐንስ ይሖዋ
በጥሩ ጎናችን ላይ እንደሚያተኩር
እርግጠኞች እንድንሆን የሚያደርገንን ምክንያት ነግሮናል።
ዮሐንስ ጥቅሱ መጀመሪያ ላይ
“ከእውነት ወገን መሆናችንን በዚህ እናውቃለን” ብሏል።
እውነትን እንዴት እንደሰማችሁ
ቆም ብላችሁ አስቡ።
በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን እውነት ሰማን።
ከዚያም አመንበት።
በኢየሱስ ክርስቶስና
እሱ ባስተማራቸው ትምህርቶች አመንን።
ዓለምንና የሐሰት ትምህርቶቹን
እርግፍ አድርገን ተውን።
ትክክል የሆነውን በማድረግና
ወንድሞቻችንን በመውደድ
ኢየሱስን ለመምሰል ጥረት አደረግን።
ስለዚህ ከእውነት ወገን መሆናችንን አሳየን።
ይህ እውነት ነው፣ የእናንተንም ሆነ የእኔን ሕይወት የለወጠው!
ይህ መሆኑ በራሱ የእሱ ቤተሰብ አባላት
አድርጎ ይሖዋ እንደተቀበለን
እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል።
ግን ይህን ብናውቅም
አንዳንዴ ልባችን ይኮንነን ይሆናል።
ግን ለምን?
የሚኮንነንስ እንዴት ነው?
በሕሊናችን ምክንያት ነው።
የአምላክ ቃል ልብ የሚለውን ቃል
ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ይጠቀምበታል።
አብዛኛውን ጊዜ የሚያመለክተውም
ሌሎች የማያዩትን
ውስጣዊ ማንነታችንን ነው።
የነሐሴ 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ እንዲህ ይላል፦
“መጽሐፍ ቅዱስ ሕሊናን፣ ውስጣዊ ስሜቶቻችንንና
መንፈሳችንን አካትቶ ከያዘው ከምሳሌያዊው ልብ ጋር ያያይዘዋል።”
መጠበቂያ ግንቡ በመቀጠል
ሮም 2:15ን ይጠቅሳል።
እዚያ ላይ ጳውሎስ
በሙሴ ሕግ ሥር ያልነበሩ ሰዎች ሕሊና እንኳ
እንዴት ይሠራ እንደነበር ጠቅሷል።
ሮም 2:15 እንዲህ ይላል፦
“የሕጉ መሠረታዊ ሐሳብ በልባቸው እንደተጻፈ የሚያሳዩት እነሱ ራሳቸው ናቸው፤
“ሕሊናቸው ከእነሱ ጋር ሆኖ በሚመሠክርበት ጊዜ
“ሐሳባቸው በውስጣቸው እየተሟገተ አንዴ ይከሳቸዋል፣
ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥፋተኛ አይደላችሁም ይላቸዋል።”
ስለዚህ አምላክ የሰጠን ሕሊና ሊከሰን ወይም
ጥፋተኛ አይደላችሁም ሊለን ይችላል።
የተሳሳተ ጎዳና እንዳንከተልም ሊያስጠነቅቀን ይችላል።
ስህተት ከሠራን በኋላም ቢሆን
ሕሊናችን ሊወቅሰን ይችላል።
ዳዊት ከንጉሥ ሳኦል ሸሽቶ ዋሻ ውስጥ በነበረበት ጊዜ
የሳኦልን ልብስ ጫፍ ቆርጦ ነበር።
አንደኛ ሳሙኤል 24፡5
“በኋላ ላይ ግን ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቁረጡ
ልቡ ወቀሰው” ይላል።
እዚህ ላይ ልቡ የሚለው
ሕሊናው ተብሎም ሊተረጎም ይችላል።
ዳዊት በዚያ ወቅት ያደረገው ነገር
የተቀባውን ንጉሥ እንዳቃለለ ስለተሰማው
ሕሊናው ረበሸው።
ስለዚህ ሕሊናችን ራሳችንን ለመርመርና
በራሳችን ላይ ለመፍረድ ያስችለናል።
የሕሊና ወቀሳ እንድንጸጸትና
የማስተካከያ እርምጃ እንድንወስድ ያደርገናል።
ነገር ግን ከመጠን በላይ የሆነ የሕሊና ወቀሳ አደገኛ ነው።
ከልክ በላይ በሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ተውጠን
‘ንስሐ ብገባም ይሖዋ ፈጽሞ ይቅር አይለኝም’
ብለን እንድንደመድም ያደርገናል።
ወይም ከመጠን ያለፈ የሕሊና ወቀሳ
አምላክን ማስደሰትን
ጭራሽ ስህተት ካለመሥራት ጋር
እንድናያይዘው ሊያደርገን ይችላል።
ጳውሎስ በሮም 2፡15 ላይ እንደገለጸው
ሕሊናችንን ልክ እንደ አንድ ዳኛ
በእኛ ላይ ፍርድ ያስተላልፋል።
በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፦
ፍርድ ቤት እንደቀረባችሁ አስቡ።
ዳኛው ልክ ሕሊናችን ማለት ነው።
እውነታውን ለማግኘትና መረጃ ለመሰብሰብ
ምሥክሮቹን ማለትም
የምናስባቸውን ሐሳቦች ያዳምጣል።
አንድ ጥሩ ዳኛ ፍትሐዊና
ትክክለኛ ፍርድ ለማስተላለፍ
የግራ ቀኝ ምሥክሮችን ቃል ያዳምጣል
ግን እስቲ አስቡት፦
ዳኛው የሚያዳምጠው የከሳሹን ወይም
የአቃቤ ሕጉን ምሥክሮች ቃል ብቻ ቢሆንስ?
እነዚህ ምሥክሮች የሚፈልጉት ደግሞ
ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድባችሁ ነው።
በእናንተ ላይ ሲመሠክሩ
‘የጥፋቱን ክብደት መገንዘብ አለበት!’
‘ማድረግ የሌለበትን ነገር ነው ያደረገው!’
‘ደካማ ነው!’
‘መጥፎ ምኞቶች አሉት።’
‘እስር ቤት ገብቶ እዚያው መማቀቅ አለበት’ ይላሉ።
ስለዚህ የእነዚህን ምሥክሮች ቃል ብቻ
የሰማው ዳኛ የእናንተን ምሥክሮች ሳያዳምጥ
‘ጥፋተኛ ስለሆናችሁ ወህኒ ትወርዳላችሁ’
የሚል ፍርድ ያስተላልፋል።
በተመሳሳይም በተገቢው መንገድ ያልሠለጠነ ሕሊና
ልክ እንደዚያ ፍርደ ገምድል ዳኛ ይሆናል።
በምሳሌያዊ ሁኔታ
በጥፋተኝነት ስሜት ውስጥ ያስረናል።
በአሉታዊ ስሜትና በተስፋ መቁረጥ እንድንዋጥ ያደርገናል።
ወደፊት እንዳንሄድ አንቆ ይይዘናል።
ታዲያ ግን የእናንተ ሕሊና ምን ዓይነት ዳኛ ነው?
ማስታወስ ያለብን በሚገባ የሠለጠነ ሕሊና
ያለልክ ከሚኮንነን ሐሳብም
ጥበቃና ከለላ እንድናገኝ ያደርጋል።
ሕሊናችን ተገቢውን ፍርድ እንዲያስተላልፍ
ስለ ይሖዋ ሕጎች ብቻ ሳይሆን
ሕጎቹን ስለሰጠን ስለ ታላቁ ዳኛ
ስለ ይሖዋ በመማር ልናሠለጥነው ይገባል።
የመስከረም 1, 1976 መጠበቂያ ግንብ
ሕሊናችንን ይበልጥ ጠቃሚ እንዲሆን ማሠልጠን
በሚለው ርዕስ ሥር እንዲህ የሚል ሐሳብ ይዞ ወጥቶ ነበር፦
“ሕሊናችንን ስናሠለጥን፣
“የአምላክ ዋነኛ ባሕርይ ፍቅር መሆኑን ማስታወስ አለብን።
“ይህንንም ፍቅር በመጽሐፍ ቅዱስና
አገልጋዮቹን በሚንከባከብበት መንገድ በግልጽ አሳይቷል።”
ቁልፉ ነገር ይሄ ነው።
ይሖዋ ፍትሕን እንደሚወድ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።
ግን ፍርድ ሲያስተላልፍ
ምንጊዜም ምክንያታዊ ነው።
ይሖዋ ሁልጊዜ ምሕረትና ታማኝ ፍቅር ያሳያል።
እንደውም ይሖዋ ራሱ ፍቅር ነው ተብሏል።
የይሖዋን ባሕርያት ማወቃችን
ሕሊናችን በእኛ ላይ በሚያስተላልፈው ፍርድ
ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳናል።
ልል በመሆን ስህተት ስንሠራ ሰበብ እንዳንደረድር
በሌላ በኩል ደግሞ
በራሳችን ላይ አለልክ ጥብቅ በመሆን እንዳንጨክን ይረዳናል።
ወደ ቅድሙ ምሳሌ ስንመለስ
ይሖዋን በደንብ የሚያውቅ አንድ ጥሩ ዳኛ
የተከሳሹንም ምሥክሮችም ያዳምጣል።
እነዚህ ምሥክሮች ደግሞ
‘ክቡር ዳኛ በዚህ ስህተቱ ላይ ብቻ ተመሥርቶ
‘ፍርድ ሊተላለፍበት አይገባም።
‘ይቅርታ ሊደረግለትና ክሱ ሊሰረዝለት ይገባል።
‘የእስካሁኑ ቅጣትና የጸጸት አለንጋ ይበቃዋል፣
‘ንስሐም ገብቷል።
‘ያለፈውን ነገር መቀየር አይችልም፣
‘ግን የንስሐ ፍሬዎችን አሳይቷል።
ሙሉ በሙሉም ለውጥ አድርጓል’ ይላሉ።
ይሖዋን ማወቃችንና
እሱም እንደሚያውቀን መገንዘባችን
ልባችን በፊቱ እንዲረጋጋ ያደርጋል።
“ይህን የምናደርገው ልባችን እኛን በሚኮንንበት ነገር ሁሉ ነው።
“ምክንያቱም አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው።
ደግሞም ሁሉንም ነገር ያውቃል።”
እንዴት የሚያጽናና ነው!
ይሖዋ ምሳሌያዊ ልባችንን
ውስጣዊ ማንነታችንን ያውቃል።
ስህተቶቻችንን ብቻ ሳይሆን
ዝንባሌያችንን፣ ስሜታችንን፣
ትክክል የሆነውን ለማድረግ ያለንን ፍላጎትና
አቅማችንን ያውቃል።
ሌላው ቀርቶ በዘር የወረስነው ባሕርይና አለፍጽምናችን
በምናደርጋቸው ነገሮች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በሚገባ ይገነዘባል።
ጠለቅ ብሎ ማስተዋል የተባለው መጽሐፍ
ስለይሖዋ ምሕረት ሲናገር እንዲህ ይላል፦
“በእርግጥም የሰው ዘር መሠረታዊና ትልቅ ችግር
“ከአባቱ ከአዳም የወረሰው ኃጢአት ነው።
“ስለዚህ የሰው ዘር በሙሉ ያለው
“በአስከፊና በአሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነው።
“ይሖዋ አምላክ ግን በታላቅ ምሕረቱ
“የሰው ዘር ከዚህ የችግር አዘቅት
ነፃ የሚወጣበትን መንገድ አዘጋጅቷል።”
ስለዚህ ይሖዋ እያንዳንዳችንን የሚያየን
የአካል ጉዳት እንዳለበት ሰው ነው።
ይህ ምሕረት እንዲያሳየን ያነሳሳዋል።
ይሖዋ ከአገልጋዮቹ ልብ ይልቅ
ይበልጥ ታላቅ እንደሆነ ያሳየበትን
አንድ ምሳሌ እንመልከት።
የሐዋርያው ጴጥሮስን ታሪክ።
በዚያ ፈጽሞ በማይረሳው መጥፎ ምሽት
ጴጥሮስ አንዴ ብቻ ሳይሆን ሦስት ጊዜ ኢየሱስን ክዷል።
እንዲያውም ከናካቴው አላውቀውም ብሏል።
በዚያ ምሽት ኢየሱስ ዞር ሲል
ከጴጥሮስ ጋር ዓይን ለዓይን ተገጣጠሙ።
ጴጥሮስ ያንን ቅጽበት
መቼም ቢሆን እንደማይረሳው ግልጽ ነው።
ምናልባትም ደግሞ
ጴጥሮስ ከዚያ በኋላ ዶሮ ሲጮህ በሰማ ቁጥር
ያ ምሽት ትዝ ይለው ይሆን?
የዶሮ ድምፅ በሰማ ቁጥር
በዚያ ምሽት ያደረገው ነገር ትዝ ይለው ይሆን?
‘እኔ አላውቀውም፣ እኔ አላውቀውም
እኔ አላውቀውም’ በማለት ኢየሱስን የካደው?
ሊሆን ይችላል።
በእርግጠኝነት አናውቅም።
ግን ኢየሱስ ጴጥሮስን
ከልክ ባለፈ የጥፋተኝነት ስሜት እንዳይዋጥ እንደረዳው
በእርግጠኝነት እናውቃለን።
ኢየሱስ ትንሣኤ ባገኘበት በዚያው ዕለት
ለጴጥሮስ ለብቻው ተገልጦ ለፈጸመው ስህተት
ንስሐ የሚገባበት አጋጣሚ ሰጥቶታል።
ኢየሱስና ጴጥሮስ ምን እንደተባባሉ ባናውቅም
ያንን ውይይት ጴጥሮስ መቼም እንደማይረሳው ግልጽ ነው።
በኋላም ዮሐንስ ምዕራፍ 21 ላይ እንተጻፈው
ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ ፊት
ለእሱ ያለውን ፍቅር እንዲገልጽ
ለጴጥሮስ አጋጣሚ ሰጥቶታል።
አንዴ ብቻ ሳይሆን ሦስት ጊዜ!
በተጨማሪም ሌሎቹ ሐዋርያት በተገኙበት
ለጴጥሮስ ለየት ያለ ኃላፊነት ሰጥቶታል።
ስለዚህ ከዚህ በኋላ
በጴጥሮስ አእምሮ ውስጥ የሚመላለሰው
‘አላውቀውም፣ እኔ አላወቀውም’ ብሎ መካዱ አይደለም።
አሁን ሊያስታውሰው የሚችል
አዲስ፣ ደስ የሚል ትዝታ አለው።
ይሖዋ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ተጠቅሞ
ከልቡ ይልቅ እጅግ ታላቅ መሆኑን ለጴጥሮስ አሳይቶታል።
እስቲ እስካሁን የተመለከትነውን እንከልስ።
ጥሩ ሕሊና ወደ የትኛውም ጽንፍ አይሄድም።
ከልክ በላይ ጥብቅም፣ ልልም አይሆንም።
ይሖዋ እኛን በሚያይበት መንገድ
ራሳችንን ለማየት ጥረት ማድረግ አለብን።
ይሖዋ እሱን ለማገልገል የምናደርገውን ነገር ሁሉ
ከፍ አድርጎ ይመለከታል።
በእኛ ላይ በጭካኔ አይፈርድም።
አዎ፣ ይሖዋ አምላክ
ከልባችን ይልቅ እጅግ ታላቅ ነው!
ይሖዋ እንደሚወደን ፈጽሞ አንርሳ።
ፈቃዱን በደስታና በመተማመን ስሜት እንድንፈጽም
የሚያደርግልንን አስደናቂ ድጋፍ እንቀበል።
እስቲ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን
ለራሳቸው ያላቸውን አመለካከት ማስተካከል የቻሉት
እንዴት እንደሆነ እንመልከት።
ማንም ሰው ፈጽሞ ሊያየው የማይችልና
ልታስወግደው የማትችለው ችግር ሲኖርብህ
በጣም ከባድ ነው።
ከባለቤቴ ጋር አስደሳች ሕይወት ነበረን።
ሁለት ልጆች ወልደናል።
ባለቤቴ የጉባኤ፣ ሽማግሌ እኔ ደግሞ አቅኚ ነበርኩ።
ግን አንድ ቀን ባልተጠበቀ ሁኔታ በድንገት ሕይወቱ አለፈ።
በደቂቃዎች ውስጥ መበለት ሆንኩ።
ይህን ቃል አልወደውም።
ደካማ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ያደርጋል።
በወቅቱ ማንነቴ ጠፋኝ።
ዋጋ ቢስ እንደሆንኩ ተሰማኝ።
ግራ ገባኝ።
ልጅ ሳለሁ፣ እንደ አባት እኔን የመንከባከብ
ኃላፊነት ተጥሎበት የነበረው ሰው
ኃላፊነቱን በአግባቡ አልተወጣም።
ሁልጊዜ
ምንም ነገር ማድረግ እንደማልችልና
ብቃት እንደሌለኝ እንዲሁም
የማልረባ እንደሆንኩ እዲሰማኝ ያደርግ ነበር።
ካደግኩም በኋላ ይህ ስሜት አልጠፋም።
አሁንም እንኳ አልፎ አልፎ ያስቸግረኛል።
በ22 ዓመቴ ኦ.ሲ.ዲ. የተባለ
የአእምሮ ሕመም እንዳለብኝ አወቅኩ።
በሽታው ሁሉንም ነገር እንድትጠራጠር ያደርግሃል።
ቀኑን ሙሉ ‘የተሳሳተ ነገር ሠርቻለሁ’
እያልክ እንድትብሰለሰል ያደርግሃል።
ሌላው ቀርቶ ወንጀል እንደሠራህ ስለሚሰማህ
በራስህ ላይ ፖሊስ ልትጠራ ትችላለህ።
ጥርጣሬው የማያባራ ስለሆነ በጣም አስጨናቂ ነው።
ከአሉታዊ አስተሳሰብ ጋር የማደርገው ትግል የማያቋርጥ ነው።
ከዚህ ስሜት ጋር በየዕለቱ ትግል አደርጋለሁ።
‘ደህና ነኝ። ጥሩ ነው ያለሁት’ ብዬ ብናገር ደስ ይለኝ ነበር።
ግን አልነበርኩም።
ሽባ ነው የሚያደርግህ።
ከይሖዋም ሆነ ከሕዝቦቹ እርዳታ ባላገኝ ኖሮ
ምንም ማድረግ አልችልም ነበር።
እንደ እኔ ዓይነት ችግር ያለበት ጓደኛ አለኝ።
ሁለታችንም ያለንበት ሁኔታ ተመሳሳይ እንደሆነ እንዲሁም
እንደ እኔ ዓይነት ስሜትና ፍርሃት እንደሚሰማው ማወቄ አጽናንቶኛል።
ይሖዋ ይህን ወንድም ለእኔ እንደላከው ሆኖ ይሰማኛል።
ለጓደኛዬ ስሜቴን ለመግለጽ ብቻ
‘ዛሬ አዝኛለሁ’ ብዬ ስጽፍላት
‘እሺ፣ አለሁልሽ። አዳምጥሻለሁ’ ትለኛለች።
በጉባኤ ውስጥ አንዳንድ ኃላፊነት ሲሰጠኝ
ከእኔ የተሻለ ሰው እንዳለና ለእዛ ኃላፊነት ብቁ እንዳልሆንኩ ይሰማኛል።
ደግሞም ብቁ ሆኜ አይደለም።
ይሖዋ የማደርገውን ጥረት እንደሚያይ ግን አውቃለሁ።
ይሖዋ ልሰጠው የምችለው ነገር ሁሉ ይገባዋል!
ራእይ 4:11 እንደሚለው ‘ግርማ፣ ክብርና ኃይል ሊቀበል ይገባዋል።’
የምሰጠውን ነገር ከፍ አድርጎ እንደሚመለከተውም አውቃለሁ።
ይሖዋ ሁሉም ሰው ምርጡን ሲሰጠው ይደሰታል።
ዋጋ ቢስ እንደሆኑ የሚሰማቸው ሰዎችም ጭምር።
ከጉባኤ ስብሰባዎች አልቀርም።
ስብሰባ እየተካሄደ ወይም መዝሙር ላይ ላለቅስ ብችልም እንኳ
እዚያ ተገኝቼ ከጓደኞቼ ጋር ይሖዋን ማምለክ እንዳለብኝ አውቃለሁ።
እንዲህ መሆኑ ችግር የለውም።
የሚጠበቅ ነገር ነው።
ስሜትን መግለጽ ይጠቅማል።
ከይሖዋም ሆነ ከጉባኤው ጋር ያለህ ወዳጅነት ይጠናከራል።
ራሴን ይሖዋ በሚያየኝ መንገድ ለመመልከት
በየዕለቱ ጥረት ማድረግ አለብኝ።
ጸሎት በጣም ረድቶኛል።
ይሖዋ ስለ ሕመሜ እንደሚያውቅ መረዳቴም አበረታቶኛል።
አንዳንድ ጊዜ በድንገት በፍርሃት እዋጣለሁ።
በዚህ ጊዜ እንዲያረጋጋኝ ወደ ይሖዋ በጸሎት እቀርባለሁ።
ሌላው የረዳኝ ነገር ይሖዋ ጸሎቴን የሚመልስበት መንገድ ነው።
ስለዚህ ስናገር፣ ስሜቴን መቆጣጠር አልችልም!
ለማንም ሳልናገር፣
በጣም ስለምፈልገው ነገር ወደ ይሖዋ ጸልዬ
ሰዎች ያንን ሲያሟሉልኝ ተመልክቻለሁ።
የይሖዋ ሥራ እንደሆነ ግልጽ ነው።
“ይሖዋ ረዳቴ ነው።”
ልክ ኢየሱስ እንዳደረገው ይሖዋን እንደ አባታችሁ ተመልከቱት።
ኢየሱስ ከመገደሉ በፊት ስሜቱን ለአባቱ ገልጿል።
ይህንንም ዮሐንስ 17 ላይ ማየት እንችላለን።
እዚያ ላይ በይሖዋና በኢየሱስ መካከል ያለውን ቅርበት እንመለከታለን።
እኔም ከይሖዋ ጋር እንዲህ ዓይነት ዝምድና እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ መበለቶች
የተጻፉትን ዘገባዎች ማንበቤ በጣም ረድቶኛል።
ከጊዜ በኋላ፣ ይሖዋ ለመበለቶች ያለው አመለካከት
ከዓለም የተለየ እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ።
ይሖዋ መበለቶች እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የሚገልጹ ሕጎችን
ለእስራኤላውያን ሰጥቷቸዋል።
እነዚህ ነገሮች በሙሉ ይሖዋ ከእኔ ጋር እንደሆነ አስገንዝበውኛል።
መበለት የሚለው መጠሪያ አሁን አያስጠላኝም።
ይሖዋ አንደሚያስብልኝና እንደሚንከባከበኝ ተገንዝቤያለሁ።
ይሖዋ ለራሳችን ካለን አመለካከት የበለጠ ከፍ አድርጎ ይመለከተናል።
ስለ ራስህ ጥሩ አመለካከት እንዲኖርህ ይረዳሃል።
ፍቅሩ ያሉህን አሉታዊ አስተሳሰቦች እንድታስወግድ ይረዳሃል።
የይሖዋ አስተሳሰብ ከእኛ እጅግ ከፍ ያለ ነው።
ይሖዋ የሚሰማንን እያንዳንዱን ነገር
ስጋታችንን፣ ሕመማችንን፣ ደስታችንን
ሁሉንም ያውቃል።
ይሖዋ እንደሚወደን ሁሌም እናስታውስ።
ይሖዋ በጸሎትና በሚወዷችሁ ጓደኞቻችሁ አማካኝነት ያጽናናችኋል።
እህት ሆሊ ዉድ
“ይሖዋ እንደሚያስብልኝና እንደሚንከባከበኝ ተገንዝቤያለሁ” ብላለች።
በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የሚወጣውን
ከእሷ ጋር የተደረገውን ሙሉውን ቃለ መጠይቅ በማየት
ተጨማሪ ትምህርት ማግኘት ትችላላችሁ።
አንድ ሰው ደግነት ሲያሳየን በአብዛኛው
እኛም ለሌሎች ደግነት ለማሳየት እንነሳሳለን።
ብረት ብረትን ይስላል በተባለው ቀጣዩ ቪዲዮ ላይ
የይሖዋን ደግነት መኮረጅ የምንችለው እንዴት እንደሆነ እናያለን።
ሰላም! ጆናታን እባላለሁ።
ይህ ብረት ብረትን ይስላል ፕሮግራማችን ነው።
ዛሬ ስለ ደግነት እንነጋገራለን።
ኢየሱስ ደግ ስለነበር
ኃጢአተኞች፣ ሕመምተኞች፣
ልጆችም ጭምር ይቀርቡት ነበር።
ኢየሱስ ልክ ይሖዋ ደግነት አሳይቷል።
ለጥሩም ሆነ ለክፉ ሰዎች።
ኢየሱስ ደግነት ያሳየው
ደግ ለነበሩ ወይም
ለእሱ ጥሩ አመለካከት ላላቸው ሰዎች ብቻ አልነበረም።
ኢየሱስ ሁልጊዜም ደግነት ያሳይ ነበር።
ምክንያቱም በሰዎች ላይ ምን ያህል በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር
እንዲሁም ይሖዋን እንደሚያስከብር ያውቃል።
እኛስ ግን
ደግነት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
የታካሚው መጠየቂያው ሰዓት አልፏል።
ሁላችሁም ውጡ!
ውይ በጣም ይቅርታ
ጊዜ ያለን መሎኝ ነበር።
አምስት ደቂቃ እኮ አለን።
ግድ የለም እንሂድ።
ቶሪ፣ ሌላ ጊዜ መጥተን ደግሞ እንጠይቅሻለን።
እህት ጥሩ እርምጃ ወስዳለች።
ከጓደኞቿ ጋር ሆና ክፍሉን ለቅቃ ወጥታለች።
ምንም እንኳ ተጨማሪ ጊዜ ቢኖራትም።
ግን ሌላስ ምን ማድረግ ትችላለች?
ደግነት ለማሳየት የሚረዳን የመጀመሪያው ነገር
ስሜታቸውን መረዳት ነው።
ራሳችንን ‘የማነጋግረው ሰው
በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ነው?
ምን ያስፈልገዋል?’
ብለን እንጠይቅ።
ከዚያ በትኩረት በማዳመጥ
እንደምናስብላቸው እናሳይ።
እ . . . አንዴ መጣሁ።
እደርስባችኋለሁ።
ታዲያስ?
ሰላም።
ጓደኛዬን በሚገባ እየተንከባከብሻት ስለሆነ
በጣም አመሰግንሻለሁ።
ሥራዬ ነው።
ይቅርታ ቅድም ቅር ካሰኘኋችሁ።
በጣም ሥራ በዝቶብናል።
በቂ ሰው ደግሞ የለንም።
“አመሰግናለሁ” ማለታችን ብቻ እንኳ
ትልቅ ለውጥ ያመጣል።
ለነርሷ ትልቅ ትርጉም ነበረው።
ሰዎች ስሜታቸውን አውጥተው ሲነግሩን
በፍቅርና በአክብሮት ልናነጋግራቸው እንፈልጋለን።
ሁለተኛው ነጥብ ይሄ ነው።
ለሰዎች ከልባችን የምናስብ ከሆነ
በንግግራችን ላይ መታየቱ አይቀርም።
ቃላታችንንም ሆነ የምንናገርበትን መንገድ እንመርጣለን።
ቅር እንዳናሰኛቸው እንጠነቀቃለን።
ይቅርታ፣ በጣም ሥራ በዝቶብናል።
በቂ ሰው ደግሞ የለንም።
ኧረ ምንም አላጠፋሽም።
ሥራችሁ ውስጣዊ እርካታ የሚያስገኝ ቢሆንም
አንዳንዴ ከባድ እንደሚሆን እገምታለሁ።
አዎ፣ ዛሬም ከባድ ቀን ነበር።
ቢያንስ ግን ሻይ መጠጣትሽ ጥሩ ነው።
አይ . . . እሱማ ተደፋብኝ።
ሌላ ለማምጣት ደግሞ ጊዜ አጣሁ።
ውይ . . . በጣም አስቸጋሪ ቀን ነዋ ያሳለፍሽው።
አዎ።
ማንዲ እባላለሁ።
ሜሪ፣ አመሰግናለሁ።
በቃ ቻው፣ ሥራ አላስፈታሽ።
ግሩም ምሳሌ ነው ያየነው።
የነርሷን ስሜት ቀይራዋለች።
ነርሷ ያለችበትን ሁኔታ ካወቀች በኋላ
ሌላስ ምን ማድረግ ትችላለች?
ይህ ወደ ሦስተኛው ነጥብ ይመራናል።
ደግነት አሳቢነት ከማሳየት
ወይም ከንግግር ባለፈ በተግባር መደገፍ አለበት።
ሰዎችን የምንረዳበት አጋጣሚ ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን።
ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን ወይም ጉልበታችንን
መሥዋዕት ማድረግ ቢጠይቅም
ፈጽሞ የሚያስቆጭ ነገር አይደለም።
እ . . . ሜሪ እንቺ።
ውይ . . . ለምን ተቸገርሽ!
ኧረ ችግር የለውም።
አድናቆቴን ለመግለጽ ነው።
በጣም ነው የማመሰግነው።
እ . . . አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?
እሺ።
ልትጠይቂያት የመጣሽው ሴት ማን ናት?
ሊጠይቋት የሚመጡት ብዙ ናቸው።
የቅርብ ጓደኛችን ነች።
ቤተሰብ በያት።
የይሖዋ ምሥክሮች ነን።
እ . . .
የእናንተ ሰዎች ደጎች ናቸው።
እናመሰግናለን።
ብታይ ቶሪ በጣም ጥሩ ጓደኛዬ ነች።
የምናሳየው ደግነት
ከልብ የመነጨ ሊሆን ይገባል።
ደግነት የምናሳየው ሰዎችን ስለምንወድ እንጂ
ለመስበክ ብቻ ብለን አይደለም።
እርግጥ ሰዎች እንደምናስብላቸው ሲያውቁ
ጥሩ ምላሽ ይሰጣሉ።
እስቲ እንከልሰው።
ደግነት ለማሳየት
ሦስት እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን።
አንደኛ፣ ስሜታቸውን መረዳት።
ስለሚያሳስባቸውና ስለሚያስፈልጋቸው ነገር እናስብ።
ስሜታቸውን ሲገልጹ እናዳምጥ።
ሁለተኛ፣ በፍቅርና በአክብሮት ማነጋገር።
እንደምናስብላቸው ከቃላታችንና
ከምንናገርበት መንገድ ማስተዋላቸው አይቀርም።
ሦስተኛ፣ በድርጊታችን እናሳይ።
ሰዎችን ለመርዳት አጋጣሚዎችን እንፈልግ።
እንዲህ ስናደርግ የመስበክ አጋጣሚ እናገኝ ይሆናል።
ግን አስታውሱ፦
ከምንም በላይ የሚያስፈልገን ነገር
ልክ እንደ ኢየሱስ ሰዎችን መውደድ ነው።
ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ
“ፍቅር ደግ ነው” ይላል።
ለሌሎች ልባዊ አሳቢነት ማሳየት የምንችለው
ውስጣችን በአምላክ ቃል ከተቀረጸ ብቻ ነው።
በቀጣዩ ቪዲዮ ላይ የሚክያስን መጽሐፍ ስንመረምር
ጥቅሶችን ከፋፍለን በእያንዳንዱ ክፍልፋይ ላይ
ማሰላሰል የምንችለው እንዴት እንደሆነ እናያለን።
እኔ የምልሽ፣ ስለ ሚክያስ መጽሐፍ ምን ነበር የምታውቂው?
ሚክያስ 6፡8ን እማዬ እንደምትወደው ብቻ።
ከአጠቃላዩ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ጋር
እንዴት እንደሚያያዝ አላውቅም ነበር።
እኔስ ብትይ።
ታዲያ ይበልጥ ለማወቅ ምን አደረግሽ?
መጀመሪያ መጽሐፉ ሲጻፍ የነበረውን ሁኔታ ለመረዳት ምርምር አደረኩ።
አሪፍ ሐሳብ ነው።
መቼቱን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው።
ታዲያ ምን አደረግሽ?
ሚክያስ መጽሐፍ ላይ ያሉትን የኅዳግ ማጣቀሻዎች ስመለከት
ታሪኩ የሚገኝበትን 2 ዜና ምዕራፍ 27 ከቁጥር 27-29ን አገኘሁ።
እነዚህ ምዕራፎች ሚክያስ ስለ ኖረበት ዘመን ይነግሩናል።
ነቢይ ሆኖ ያገለገለው በሦስት ነገሥታት ዘመን ነበር።
በኢዮዓታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን!
የአካዝ የግዛት ዘመን ለይሁዳ ነዋሪዎች በጣም አስከፊ ነበር።
አስከፊ ብቻ!
እሱ እኮ ልጆቹን ሳይቀር መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበ አረመኔ ነው።
ምን እሱ ብቻ ሕዝቡም ቢሆን ለይሖዋ ታማኝ አልነበረም።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን
እንደ ኢዮዓታም ያለ ጥሩ ንጉሥ ሲገዛም
ሕዝቡ ክፉ ድርጊት መፈጸሙን አልተወም።
ልክ ነው።
ሚክያስ የተላከውም ኃጢአታቸውን ለማጋለጥ ነው።
ሚክያስ በሰማርያና በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚመጣው ጥፋት ትንቢት ተናግሯል።
ይሖዋ ግን ምን ጊዜም ለሕዝቡ ተስፋ ይሰጣል።
ምንም ጥያቄ የለውም።
ይሖዋ በጣም ታጋሽ ቢሆንም
መጥፎ ነገሮችን ግን ለዘላለም አይታገስም።
እህ!
ይሖዋ የፍትሕ አምላክ ነው።
ንጹሐን ሰዎች እንዲጎዱ አይፈልግም።
ስለዚህ ለእስራኤላውያን ተግሣጽ መስጠት አስፈልጎታል።
ያም ሆኖ ተስፋ አልቆረጠባቸውም።
ሚክያስ የተናገራቸው ትንቢቶች
ይሖዋ አሁንም ሕዝቡ ከእሱ ጋር
ጥሩ ዝምድና እንዲመሠርት እንደሚፈልግ ያሳያሉ።
አዎ፣ እውነትሽን ነው።
ሚክያስ ከይሖዋ የተቀበለውን መልእክት በታማኝነት አውጇል።
ደግሞም መልእክቱ ከኢሳይያስ ትንቢት ጋር ተመሳሳይነት አለው።
ለምሳሌ ሚክያስ በምዕራፍ 4 ከቁጥር 1-3 ላይ የተናገረው ሐሳብ
በኢሳይያስ ምዕራፍ 2 ከቁጥር 2-4 ላይ
ከሚገኘው ሐሳብ ጋር አንድ ዓይነት ነው።
አይገርምም?
በጣም እንጂ!
ስለ አንድ ክንውን የተጻፉ የተለያዩ ዘገባዎችን መመርመርሽን ወድጄዋለሁ።
እኔ ምርምር ሳደርግ እንዲህ ለማድረግ አስቤያለሁ።
እርግጥ ከሚክያስ ቀድሞ ትንቢት መናገር የጀመረው ኢሳይያስ ነው።
ስለዚህ ይሖዋ ሁለቱም ነቢያት
ተመሳሳይ መልእክት እንዲያውጁ ነግሯቸዋል።
ያም ቢሆን ሁለቱም የተሰጣቸውን ትእዛዝ በታማኝነት ፈጽመዋል።
ሰዎቹ ሚክያስ የሚለውን ሲሰሙ
‘ይህን እኮ ኢሳይያስም ቀደም ብሎ ነግሮናል።
አዲስ አይደለም’ ብለው ይሆናል።
ልክ ነሽ።
ሚክያስም ‘ይሖዋ መልእክቱ በድጋሚ እንዲነገራቸው የፈለገው
ሕዝቡን ስለሚወድና መልእክቱ እንዲገባቸው ስለሚፈልግ ነው’
ብሎ አስቦ ይሆናል።
እኔም እንደ ሚክያስ መሆን እንዳለብኝ ተምሬያለሁ።
የምንሰብከው ምሥራች ተደጋጋሚ ቢመስልም እንኳ
በስብከቱ ሥራዬ መቀጠል እፈልጋለሁ።
አንቺስ ምን ትምህርት አገኘሽ?
የእኔን ትኩረት የሳበው ደግሞ
ይሖዋ ሚክያስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5 ላይ የተናገረው ሐሳብ ነው።
ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦
“በጥርሳቸው ሲነክሱ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣
“አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን
ጦርነት በሚያውጁ ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦”
እ . . . አልገባኝም።
ግልጽ አይደለም አይደል?
አዎ።
መጽሐፍ ቅዱስ ሳነብ በቀላሉ የማይገቡ
እንዲህ ዓይነት ጥቅሶች ሳገኝ ደስ ይለኛል።
ምክንያቱም ቆም ብዬ እንዳስብ ያስገድዱኛል።
በሚገባ ያልተረዳኋቸው ወይም
ጽሑፎቻችን ላይ ያልተብራሩ ጥቅሶች ሳገኝ
በእያንዳንዱ የጥቅሱ ክፍል ላይ አተኩርና
‘ጥቅሱ ምን እያለ ነው?’ ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ።
በጣም ጥሩ ሐሳብ ነው።
ቆይ ማስታወሻዬ ላይ ልጻፈው።
ቆም ብሎ በእያንዳንዱ የጥቅሱ ክፍል ላይ በደንብ ማሰላሰል!
የጥቅሱ የመጀመሪያ ክፍል የሚናገረው በጥርሳቸው ሲነክሱ
‘ሰላም’ እያሉ ስለሚያወጁ የሐሰት ነቢያት ነው።
መጀመሪያ ላይ ስለ ግብዝነታቸው የሚናገር መስሎኝ ነበር።
“ሰላምን እያወጁ መናከስ።”
ግን የግርጌ ማስታወሻው እንደሚለው
በጥርሳቸው ሲነክሱ ሲል
“የሚያላምጡት ነገር ሲያገኙ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ኦ፣ ጥቅሱን የከፋፈልሽበትን መንገድ በጣም ወድጄዋለሁ።
ስለዚህ ሕዝቡ የሚበሉት ነገር ሲሰጣቸው ስለ ሰላም ያወጃሉ ማለት ነው?
ልክ ነው።
ነቢያቱ ከሕዝቡ እንደ ምግብ ያሉ ጥቅማ ጥቅሞችን ሲያገኙ ሰላምን ያወጃሉ።
ግን ሕዝቡ ምንም ካልሰጣቸው
እነዚያው ነቢያት በሕዝቡ ላይ ጦርነት ያውጃሉ።
ስለዚህ የሐሰት ነብያቱ
በዛሬው ጊዜም ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የራስ ወዳድነት ባሕርይ አሳይተዋል።
አዎ።
ጥቅሱ አንድን ነገር ለማድረግ የተነሳሳሁበትን የልብ ዝንባሌና
ሌሎችን የምይዝበትን መንገድ ይሖዋ እንደሚያይ አስታውሶኛል።
ከይሖዋ የተሰወረ ነገር የለም።
ራሴን እንዲህ ብዬ እንድጠይቅ አነሳስቶኛል፦
‘ለሰዎች መልካም ነገር የማደርገው
ስለማስብላቸው ነው ወይስ በምላሹ የሆነ ነገር ጠብቄ?’
‘በአገልግሎትስ የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ አሳያለሁ?’
ለምሳሌ አዲስ ቋንቋ በመማር
ወይም ሰዎች በሚገኙበት ቦታና ሰዓት በማገልገል!
በዛሬው ጊዜ እነዚያ የሐሰት ነቢያት ቢኖሩ
እንዲህ ያሉ ጥሩ ነገሮችን አያደርጉም።
ያገኙትን ይሖዋን የማገልገል መብትና ኃላፊነት አላደነቁም።
ይሖዋም ለድርጊታቸው ተጠያቂ አድርጓቸዋል።
ይህ ለእኛ የሚያጽናና ብቻ ሳይሆን የሚያስጠነቅቅም ዘገባ ነው።
ይሖዋ ለሕዝቡ ያለውን ፍቅርና ፍትሑንም ያሳየናል።
ትክክል ነሽ።
ይህ እማዬ የምትወደውን ጥቅስ ይበልጥ እንድረዳው አድርጎኛል።
ሚክያስ 6፡8 እንዲህ ይላል፦
“ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል።
“ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?
“ፍትሕን እንድታደርግ፣ ታማኝነትን እንድትወድና
ልክህን አውቀህ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው!”
ደስ ሲል፣ እኔም ይህን ጥቅስ ወደዋለሁ።
ይሖዋ ‘እነዚህን ቀላል መመሪያዎች ከተከተልሽ
ሕይወትሽ ትርጉም ያለው ይሆናል’ እያለኝ ነው።
አዎ ደስ ይላል።
እስካሁን ከተነጋገርንበት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው።
ይሖዋ ሚክያስን የላከው የሰዎቹን ራስ ወዳድነትና
የነበረውን የፍትሕ መጓደል ለማጋለጥ ነው።
ሚክያስ ለታማኝነት ትልቅ ቦታ ስለሰጠ
በይሖዋ ላይ ያለውን እምነት ጠብቋል።
ይህን ያደረገው እውቅና ለማግኘት ብሎ አይደለም።
ልኩን አውቆ ከአምላኩ ጋር ሄዷል።
ይገርማል።
በሚክያስ መጽሐፍ ላይ ትንሽ ምርምር በማድረጋችን ብቻ እንኳ
ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶችን አግኝተናል።
ትክክል ነሽ።
እነዚህን ዕንቁዎች ማግኘት የቻልነው መቼቱን በመረዳት፣
የተለያዩ ዘገባዎችን በመመርመር እንዲሁም
በእያንዳንዱ የጥቅሱ ክፍል ላይ ጊዜ ወስደን በማሰላሰል ነው።
አዎ፣ ያደረግነውን ምርምር በጣም ወድጄዋለሁ።
ጊዜ ካለሽ ምርምራችንን ብንቀጥል ደስ ይለኛል።
እሺ፣ ደስ ይለኛል።
ሌሎች ዕንቁዎችንም ለማግኘት እንቆፍር።
በምናነበው ነገር ላይ ካሰላሰልን ተግባራዊ የምናደርጋቸው ነጥቦች እናገኛለን።
እናንተስ ከሚክያስ መጽሐፍ ያገኛችሁት ዕንቁ አለ?
በቀጣዩ የማለዳ አምልኮ ንግግር ላይ ወንድም ማለንፎንት
በይሖዋ ፍቅር ላይ ማሰላሰላችን እንዴት እንደሚጠቅመን ያብራራልናል።
የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ
ይሖዋ አምላክና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ
እኛን የሰው ልጆችን
ምን ያህል እንደሚወዱን ያስታውሰናል።
ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልን ነገር ያለን አድናቆት
አመስጋኝነታችንን ለማሳየት
የሆነ ነገር እንድናደርግ ያነሳሳናል።
ይሖዋ ቤዛዊ መሥዋዕቱን በማዘጋጀት ላሳየን ፍቅር
አድናቆት እንዳለን ማሳየት እንፈልጋለን።
ሁለተኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 14 ላይ ያለው ሐሳብ
ትኩረታችንን ይስባል።
ከስልካችሁ ላይ 2 ቆሮንቶስ 5፡14, 15ን አውጡና
አብረን እናንብበው።
የክርስቶስ ፍቅር ምን ለማድረግ እንደሚያነሳሳን ልብ በሉ።
“አንድ ሰው ለሁሉም መሞቱን ስለተረዳን
“ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናልና፤
“ምክንያቱም ሁሉም ቀድሞውኑ ሞተዋል።
“በሕይወት ያሉትም ከእንግዲህ ለራሳቸው ከመኖር ይልቅ
“ለእነሱ ለሞተውና ለተነሳው እንዲኖሩ
እሱ ለሁሉም ሞቷል።”
የቁጥር 14 የመጀመሪያ ዓረፍተ ነገር
ምን እንደሚል ልብ ብላችኋል?
“ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናል” ይላል።
ለራሳችን ብቻ እንዳንኖር ማለት ነው።
“ግድ ይለናል” የሚለው አገላለጽ
ለራሳችን እንዳንኖር እንገደዳለን።
ወይም የይሖዋን ፈቃድ የምናደርገው
እንዲሁ ግዴታ ስለሆነብን ብቻ ነው ማለት አይደለም።
ይህ አገላለጽ ከዚህ የላቀ ትርጉም አለው።
አንድ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት እንደሚለው
“ግድ ይለናል” ተብሎ የተተረጎመው የእንግሊዝኛ ቃል
በአንድ ሰው ውስጥ ኃይለኛ
ወይም ለተግባር የሚያነሳሳ ስሜት መፍጠር ማለት ነው።
የኢየሱስ መሥዋዕት በውስጣችን የሚፈጥረው ስሜትስ
ተመሳሳይ አይደለም?
ክርስቶስ ላደረገልን ነገር
ከፍተኛ የአመስጋኝነት ስሜት አለን።
ያለን አድናቆት ቀሪውን ሕይወታችንን
የአምላክን ፈቃድ እያደረግን ለመኖር ያነሳሳናል።
አምላካችን ይሖዋ ያደረገልን አስደናቂ ዝግጅት
እንዲህ እንድናደርግ ያነሳሳናል።
ሐዋርያው ጳውሎስም
የተሰማውን ስሜት በግልጽ ተናግሯል።
ጳውሎስ ኢየሱስ የከፈለው ቤዛዊ መሥዋዕት
በእሱ ላይ የፈጠረበትን ስሜትና
ምን እንዲያደርግ እንዳነሳሳው
በግልጽ ተናግሯል።
እባካችሁ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን
ገላትያ ምዕራፍ 2 ላይ አውጡ።
ገላትያ ምዕራፍ 2 ቁጥር 20 እንዲህ ይላል፦
ጳውሎስ ክርስቶስ ኢየሱስ ለእሱ
በግለሰብ ደረጃ ስላደረገለት ነገር እየተናገረ ነው።
እንዲህ ብሏል፦
“እኔ አሁን ከክርስቶስ ጋር በእንጨት ላይ ተቸንክሬአለሁ።
“ከዚህ በኋላ የምኖረው
“እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር አንድ ሆኖ የሚኖረው
“ክርስቶስ ነው።
“አሁን በሥጋ የምኖረውን ሕይወት የምኖረው
“በወደደኝና ለእኔ ሲል ራሱን አሳልፎ በሰጠው
በአምላክ ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።”
ደስ የሚል ነው አይደል?
ቤዛው ለእሱ በግለሰብ ደረጃ
እንደተከፈለለት አድርጎ ተመልክቶታል።
ደግሞም ልክ ነው።
ለእያንዳንዳችን ነው የተከፈለው።
ኢየሱስ የሞተው ለእያንዳንዳችን ነው።
እኛ እንዳንሞት ለእያንዳንዳችን
በግለሰብ ደረጃ ሞቶልናል።
ሌላው ፈጽሞ ልንረሳው የማይገባ ነጥብ ደግሞ
የኢየሱስ መሥዋዕት
የይሖዋ ልግስና ታላቅ መገለጫ መሆኑን ነው።
ይህም ቢሆን በጣም ደስ የሚል ነገር ነው።
የምንኖረው በአምላክ ልጅ ላይ
ባለን እምነት ነው።
ይሖዋ በልግስና በመስጠት ረገድ
በጽንፈ ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ የለውም።
እጅግ ታላቅ ስጦታ ከይሖዋ ተቀብለናል።
ይህ ስጦታ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ
እጅግ አስደናቂ በሆነ መንገድ ተገልጿል።
ሁለተኛ ቆሮንቶስ 9፡15
ይህን አስደናቂ ስጦታ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦
“በቃላት ሊገለጽ ለማይችለው ነፃ ስጦታው
አምላክ የተመሰገነ ይሁን።”
የሚገርም አገላለጽ ነው።
በቃላት ሊገለጽ የማይችል ነፃ ስጦታ።
ቤዛው እጅግ አስደናቂ ስጦታ ከመሆኑ የተነሳ
ቤዛውንም ሆነ በቤዛው አማካኝነት
የምናገኛቸውን በረከቶች ሙሉ በሙሉ
በቃላት ልንገልጻቸው አንችልም።
የ2017 መጠበቂያ ግንብ ለሕዝብ የሚሰራጨው እትም
ቁጥር 2 ገጽ 6 ላይ ስለ ቤዛው ሲናገር እንዲህ ይላል።
በነገራችን ላይ እዚህ ላይ ያለውን ሐሳብ በጣም ነው የወደድኩት።
“የኢየሱስ መሥዋዕት ወደር የማይገኝለት ስጦታ ነው፤
“ምክንያቱም ይህ ስጦታ እጅግ ከፍተኛ ሥልጣን ካለውና
“በጣም ከሚወደን አካል የተሰጠ ነው።
“እንዲሁም የይሖዋ አምላክን ያህል ከፍተኛ መሥዋዕት ከፍሎ
“ስጦታ ሊሰጠን የሚችል ማንም የለም።
“በተጨማሪም የትኛውም ስጦታ
“ከኃጢአትና ከሞት የታደገንን ስጦታ ያህል
“አስፈላጊ ሊሆን አይችልም።
“በእርግጥም በቃላት ሊገለጽ የማይችለውን
የቤዛውን ያህል ዋጋ ሊኖረው የሚችል ስጦታ የለም።”
በእርግጥም መጠበቂያው ላይ ያለው ሐሳብ ጥልቅ ትርጉም ያለው ነው።
ቤዛው ከመዳናችን ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም።
ከዚህ ይልቅ ኢየሱስ ባቀረበው ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት
ሌሎች ብዙ በረከቶችንም እናገኛለን።
ለምሳሌ ከሕመማችን ሙሉ በሙሉ እንፈወሳለን።
ምድራችን ወደ አስደሳች ገነትነት ትለወጣለች።
ይሄም ቢሆን ከምናገኛቸው በረከቶች አንዱ ነው።
ሌላው ሳንጠቅሰው ማለፍ የማንፈልገው ነገር
የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ።
በእርግጥም ኢየሱስ ያደረገልን ነገር
በቃላት ልንገልጸው የማንችል ነፃ ስጦታ ነው።
ሐዋርያው ጴጥሮስ ቤዛውን
ስለምንወደውና ስለተቀበልነው
ለዚህ ነፃ ስጦታ ሊኖረን የሚገባውን አመለካከት
አንደኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ አንድ ላይ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦
አንደኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 8 እና 9ን አብረን እናንብብ።
ጴጥሮስ አስገራሚ በሆነ መንገድ ነው የገለጸው።
እንዲህ ብሏል፦
“እሱን አይታችሁት ባታውቁም ትወዱታላችሁ።”
[ደግሞም ሁላችንም ኢየሱስን አላየነውም]።
“አሁን ባታዩትም እንኳ በእሱ ላይ እምነት እያሳያችሁና
“በቃላት ሊገለጽ በማይችል ታላቅ ደስታ እጅግ ሐሴት እያደረጋችሁ ነው፤
“ምክንያቱም የእምነታችሁ ግብ ላይ እንደምትደርሱ
ይኸውም ራሳችሁን እንደምታድኑ ታውቃላችሁ።”
ይሖዋ እስካሁን ስላደረገልን ነገሮችና
ስለሰጠን ተስፋዎች ቆም ብለን ስናስብና
በዚያ ጊዜ ሰጥተን ስናሰላስል የሚሰማን ደስታ
በእርግጥም በቃላት ሊገለጽ የሚችል አይደለም።
የወደፊቱ ጊዜ ብሩሕ ነው።
ግን ዛሬም እንኳ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ
እሱን የማገልገል፣ እሱን የማክበር፣
ከፀሐይ በታች በምንሠራው ነገር ሁሉ
የመደሰት አጋጣሚ አግኝተናል።
በጣም የሚያስደንቅ ነገር ነው።
ይሖዋ እስካሁን ስላደረገልንና
ወደፊት ስለሚያደርግልን
እጅግ በርካታ መልካም ነገሮች
ቆም ብለን ስናሰላስል
ልባችን በደስታ መሞላቱ አይቀርም።
ከዚህም በተጨማሪ
ይሖዋ ብቻ የሚሰጠው
የአእምሮ ሰላም ይኖረናል።
የይሖዋ መንፈስ በቃላት የማይገለጽ ደስታ እንድናገኝ፣
በአምላካችን እንድንታመንና
አመስጋኝ እንድንሆን ይረዳናል።
ሮም ምዕራፍ 15 ቁጥር 13 የሚለውም ይህንኑ ነው።
ሮም 15፡13
እንዲህ ይላል፦
“በእሱ በመታመናችሁ የተነሳ
“በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተስፋ እንዲትረፈረፍላችሁ
“ተስፋ የሚሰጠው አምላክ
ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ።”
እንዴት ያለ በረከት ነው።
ይሖዋና ኢየሱስ ያደረጉልን አስደናቂ ነገሮች
የይሖዋን ስም ለማክበር፣ ለማወደስና
በሕይወታችን የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ
አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እንድናደርግ ያነሳሱናል።
የመዝሙር መጽሐፍ ስሜታችንን ይገልጽልናል።
እስቲ እባካችሁ መዝሙር 116
ቁጥር 12 እና 14ን አንድ ላይ አውጥተን እናንብብ።
116፡12 እና 14
ቁጥር 12 እንዲህ ይላል፦
“ላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ
ለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ?”
ትንሽ ዝቅ ብለን
ቁጥር 14 ላይ ደግሞ ስንመለከት
ስለ እኛ ድርሻ ምን ይላል?
“በሕዝቡ ሁሉ ፊት
“ስእለቴን [ደግሞም ራሳችንን ስንወስን
ሁላችንም ስእለት ተስለናል]
ለይሖዋ እፈጽማለሁ።”
ታዲያ ለይሖዋ ምን እመልሳለሁ?
ለሚለው ጥያቄ መልሳችን ምንድን ነው?
‘ለእሱ ክብር መስጠት’ የሚል ነው።
በሕይወታችን ውስጥ ክርስቶስን ከማክበር፣
ይሖዋን ከማክበር እንዲሁም
የአምላክን ፈቃድ ከመፈጸም የተሻለ
ልናደርግ የምንችለው ምንም ነገር የለም!
“ለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ?”
ክላውድና ሳንድራ ሳቫዦ
ሁልጊዜ ራሳቸውን ይህን ጥያቄ ይጠይቃሉ።
ለዚህ ጥያቄ የሰጡት መልስ
ብዙ በረከት ያስገኘላቸው እንዴት እንደሆነ እንመልከት።
ወላጆቼ ያሳደሩብኝ ጥሩ ተጽዕኖ
የስብከቱን ሥራ እንድወደው አድርጎኛል።
በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን
አባቴ ከሥራ ሲመለስ
አገልግሎት ይዞኝ ይወጣ ነበር።
እውነትን የሰማሁት በእናቴ በሪታ አማካኝነት ነው።
አንዳንድ መጽሐፎችን ቤት ውስጥ ስታስቀምጥ
እያነሳሁ ማንበብ ጀመርኩ።
ሳነብብ ‘ሕይወት ማለት ይህ ነው።’
‘መኖር የምፈልገው እንዲህ ዓይነት ሕይወት ነው’ እል ነበር።
ገና እንደተጋባን ብዙ ኃላፊነቶች ስላልነበሩበት
አገልግሎታችንን ይበልጥ ለማስፋት ፈለግን።
ይበልጥ ለማገልገል ያለን ፍላጎት
በጊልያድ ትምህርት ቤት ለመማር አነሳሳን።
ከትምህርት ቤቱ ከተመረቅን በኋላ
በመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ እንድናገለግል ተመደብን።
በዚያም አዲስ ቋንቋ ተማርን።
ጥናቶቻችን ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ
በወረፋ ነበር የምናስጠናቸው።
ብዙም ሳይቆይ ግን ታመምኩኝ።
ከበሽታው ማገገም ስላልቻልኩ
ሐኪሙ ሊረዳኝ እንደማይችልና
ወደ አገሬ መመለስ እንዳለብኝ ነገረኝ።
የአገልግሎት ምድባችንን ትቶ መሄድ በጣም ከባድ ነበር።
ምክንያቱም እንዲህ ይሆናል ብለን ስላልጠበቅን
ምን እንደምናደርግ ግራ ተጋባን።
ከተመለስን በኋላ ካደረግናቸው
የወረዳ ስብሰባዎች በአንዱ ላይ
አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካች ንግግር ነበረው።
ይህ የወረዳ የበላይ ተመልካች
ከልጅነቴ ጀምሮ ያውቀኛል።
እ . . . ይህ ወንድም እንዳዘንኩ ስላስተዋለ
መጣና አነጋገረኝ።
እንዲህ አለኝ፦
“ግሩም ሥልጠና ወስደሻል። አሁንም ተጠቀሚበት
“ወደኋላ አትመልከቺ።
“ማድረግ በማትችይው ነገር ላይ አታተኩሪ።
ማድረግ በምትችይው ነገር ላይ ብቻ ትኩረት አድርጊ።”
ይህ ሕይወቴን ለወጠው።
ቀስ በቀስ ጤናዬ ሲሻሻል
ተጨማሪ ነገር ማድረግ ቻልን።
እንደገናም አቅኚ ሆንን።
ከዚያም
በሥራዬ ምክንያት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተዛወርን።
በዚህ ጊዜ ሦስት ምርጫ ነበረን።
በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ ወይም በስፓንኛ ጉባኤ ማገልገል።
የስፓንኛ ጉባኤ የተመሠረተው
ከጥቂት ወራት በፊት ነበር።
በመሆኑም እኔና ሳንድራ ቁጭ ብለን ከተወያየን በኋላ
ያገኘነውን ሥልጠና ተጠቅመን
ይህን ጉባኤ ለመርዳት ወሰንን።
አዲስ ቋንቋ በመማር ረገድ
ሳንድራ ጥሩ ተሰጥኦ አላት።
ለመማር ጥቂት ወራት ነው የፈጀባት።
እኔ ግን ብዙ ጥረት ማድረግ አስፈልጎኛል።
በዚህ ጉባኤ ውስጥ 25 ዓመት ሆኖናል።
ጉባኤውን ወደነዋል።
ምክንያቱም ቋንቋውን መናገር ችለናል።
እኔ ግን ገና እየሞከርኩ ነው።
ደስ የሚሉ ተሞክሮዎችም አግኝተናል።
ዕድሜ ሲገፋ አዳዲስ ችግሮች ያጋጥማሉ።
ይህ ደግሞ ይበልጥ ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል።
ሆኖም ይሖዋ እስከ ዛሬ ሲረዳን ቆይቷል።
ይሖዋ የሚፈልገው የማንችለውን ሳይሆን
የምችንለውን እንድንሰጠው ነው።
ይሖዋ አዲስ አጋጣሚ ሲከፍትልን ለመጠቀም ወሰንን።
በዚህ ወቅት በ50ዎቹ ዕድሜ እንገኝ ነበር።
በአካባቢ ግንባታ ኮሚቴ ውስጥ እያገለገልን እያለ
በዎርዊክ እንድንሠራ ተጋበዝን።
በግንባታ ተካፍለው የመጡ ወንድሞች
በጣም ደስተኞች ነበሩ።
ሥራው ግን አካላዊ ጥንካሬ እንደሚጠይቅ ነገሩን።
በመሆኑም ራሴን ማሠልጠን አለብኝ ብዬ አሰብኩ።
የረሳችው ነገር አለ።
ሳሎን ቤት መሰላል አቁማ ነበር።
የሥልጠና ቦታዋ ሆኖ ነበር።
ወደላይ ወደታች፣
ወደላይ ወደታች፣
ወደላይ ወደታች እያለች ወደ 15ደቂቃ
ትወጣና ትወርድ ነበር።
ይህን ማየት ያስቅ ነበር።
እሷ ግን ራሷን እያዘጋጀች ነበር።
ይህ ደግሞ በደንብ ጠቅሟታል።
ሁለታችን በድምሩ ይሖዋን ከ100 ከሚበልጡ ዓመታት አገልግለናል።
በኤል.ዲ.ሲ. ሥራ እንዲሁም
በእስር ቤቶችና ወደቦች ላይ
በሚሰጥ ምሥክርነት ተካፍለናል።
በእነዚህ ጊዜያት ሁሉ አንድ ነገር አይተናል።
እኛ ለይሖዋ መስጠት የምችለው ነገር
ምንም ሆነ ምን እሱ
ከዚያ በላይ አትረፍርፎ ይሰጠናል።
ፈጽሞ የማንቆጭበት ሕይወት ነው።
አሁንም ቅንዓታችን አልቀዘቀዘም።
ወጣቶች ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ
ማሠልጠን እንፈልጋለን።
ይህ ደስ የሚል ነገር ነው።
ጡረታ አንወጣም
ይሖዋን ማገልገላችንን እንቀጥላልን።
በሕይወታችን ውስጥ ልናደርግ የምንችለው
ከሁሉ የተሻለ ነገር ይሖዋን ማገልገል ነው።
ስለዚህ ያን ማድረጋችንን እንቀጥላለን!
ክላውድና ሳንድራ አሁንም ለይሖዋ የመስጠት ፍላጎታቸው አልቀዘቀዘም።
ስለ አመስጋኝነት ካነሳን አይቀር፣ የዚህ ወር የሙዚቃ ቪዲዮም
ለይሖዋ ልግስና ያለንን አመስጋኝነት ጎላ አድርጎ የሚገልጽ ነው።
ጫካ በግርማው ልብ ሰልቦ፣
ፀሐይ ለብሳ ወርቀ ዘቦ፣
ተሞሽሮ ባይ መስኩ አብቦ፤
ደነቀኝ ሥራህ ’ንከን አልቦ።
ሰጠህ ሁሉን ስስትም የለ፤
ያስቀረኸው ከቶ ምን አለ?
ታየ ቸርነትህ ከመባቻ፤
ለምስጋና ቃል የለ ዝም ብቻ።
እጅህን ብትዘረጋ፣
ፍጥረት ሁሉ ’ንዴት ረካ?
ዛሬስ መቼ ታጠፈ፤
ስጦታህ አልነጠፈ።
መምሰል አንተን ልቤ ጓጓ ተመኝቶ፤
የማይሰለች፣ የማይደክም ሰጥቶ ሰጥቶ።
ልግስናህ ዳር የለው፤
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
ጥሩነትህ እንዲህ ተትረፍርፎ፣
የእውነት ቃልህ፣ ከቃል አልፎ፣
አጥግቦኛል ረክታለች ነፍሴ፤
አንተነትህ ሆኗል ፈውሴ።
የሕይወት ውኃ እንዲያው በነፃ፣
ሰጥተኸኛል ልቤ እንዲነፃ፤
እስኪታጨድ ደርሶ ሰብሉ፣
አወራለሁ ስላንተ ለሁሉ፣ ሁሉ።
እጅህን ብትዘረጋ፣
ፍጥረት ሁሉ ’ንዴት ረካ?
ዛሬስ መቼ ታጠፈ፤
ስጦታህ አልነጠፈ።
መምሰል አንተን ልቤ ጓጓ ተመኝቶ፤
የማይሰለች፣ የማይደክም ሰጥቶ ሰጥቶ።
ልግስናህ ዳር የለው፤
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
እጅህን ብትዘረጋ፣
ፍጥረት ሁሉ ’ንዴት ረካ?
ዛሬስ መቼ ታጠፈ፤
ስጦታህ አልነጠፈ።
መምሰል አንተን ልቤ ጓጓ ተመኝቶ፤
የማይሰለች፣ የማይደክም ሰጥቶ ሰጥቶ።
ልግስናህ ዳር የለው፤
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
ልሁን ’ኔም እንዳንተው።
አምላካችን ይሖዋ በጣም ለጋስ መሆኑ
ወደ እሱ እንድንቀርብ ያነሳሳናል።
ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶችን የያዘውን ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቶናል።
ርኅራኄና ደግነት በማሳየት ሌሎችን የመርዳት መብት ሰጥቶናል።
በተጨማሪም በእሱ ፊት ውድ ዋጋ እንዳለን ያስታውሰናል።
እስቲ አሁን ደግሞ አንድ የሚያስደስት ነገር እንንገራችሁ!
ይህ ነገር ምንድን ነው ?
ዘላለማዊ ደስታ የተባለው የ2026 የክልል ስብሰባ መጋበዣችን!
ደስታ!
ብዙዎች በሕይወታቸው ውስጥ ጥሩ ነገር ሲያገኙ
የሚፈጠር ስሜት እንደሆነ ይሰማቸዋል።
ግን በሕይወታችን ውስጥ
ፈጽሞ ያልጠበቅናቸው አስቸጋሪ ነገሮች ሲፈጠሩስ?
እንዲህ ባለ ጊዜም
ደስታችን ጠብቀ መኖር እንችላለን?
ኢየሱስ ከ2000 ዓመታት በፊት እውነተኛ ደስታ የሚገኘው
ከፈጣሪያችን ጋር ጥሩ ዝምድና በመመሥረት እንደሆነ አስተምሯል።
እነሆ፣
መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው።
ገሮች ደስተኞች ናቸው።
መሐሪዎች ደስተኞች ናቸው።
ልባቸው ንጹሕ የሆነ ደስተኞች ናቸው።
ሰላም ፈጣሪዎች ደስተኞች ናቸው።
ኢየሱስ ያስተማራቸው ትምህርቶች ዛሬም ቢሆን ጠቃሚ ናቸው።
ዘላለማዊ ደስታ በተባለው
በ2026 የይሖዋ ምሥክሮች የክልል ስብሰባ ላይ
አብረውን እንዲገኙ በአክብሮት ጋብዘንዎታል።
በስብሰባው ላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረቱ ንግግሮች፣
በቃለ መጠይቆችና በቪዲዮዎች አማካኝነት
የኢየሱስ ትምህርቶች እውነተኛ ደስታ ለማግኘት የሚረዱን
እንዴት እንደሆነ ይብራራል።
ስብሰባዎቹ የሚደረጉት በዓለም ዙሪያ ነው።
የመግቢያ ክፍያም አይጠየቅም።
ለእርስዎ ቅርብ የሆነውን ቦታ jw.org ላይ ማግኘት ይችላሉ።
በጉጉት እንጠብቅዎታለን!
በዚህ አስደሳች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ
ጎረቤቶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ጋብዙ።
በተጨማሪም የ2026 ክልል ስብሰባ
መዝሙር መውጣቱን ስንገልጽላችሁ በጣም ደስ ይለናል።
ርዕሱ ዓይኖቻችሁ ደስተኞች ናቸው ይላል።
መዝሙሩንና ግጥሙን ከአሁን ጀምሮ
ከJW ላይብረሪና ከjw.org ላይ ማውረድ ትችላላችሁ።
በክልል ስብሰባው ላይ ሞቅ ባለ መንፈስ መዘመር እንድትችሉ
መዝሙሩን እንድትለማመዱት እናበረታታችኋለን።
በተጨማሪም ዓይኖቻችሁ ደስተኞች ናቸው
የተባለው መዝሙር በቋንቋችሁ ከተዘጋጀ
በቅርቡ በሳምንቱ መሃል ስብሰባ ላይ ይዘመራል።
መዝሙሩ የሚዘመረው ሚያዝያ 20, 2026 በሚጀምር ሳምንት ላይ ነው።
በዚህ ወር ሰላምታ ይዘንላችሁ የመጣነው
ከዓመት እስከ ዓመት ብዙ ሰዎች ከሚጎበኙዋት የካሪቢያን ደሴት ነው።
ይህች አገር ዶሚኒካን ሪፑብሊክ ናት።
ካሪቢያን ውስጥ ያለው ትልቁ ተራራም ሆነ
በጣም ተፈላጊ የሆነው ሰማያዊ አንበር የሚገኘው በዚህች አገር ነው።
በተራሮችና በፏፏቴዎች አጠገብ ስትጓዙ ለየት ያሉ እንስሳትን ታያላችሁ።
ከነዚህ እንስሳት መካከል ራይኖሰረስ ኢጓና፣
ኢስፓኒዮላን ሰለነዶን ወይም አጉታ
እንዲሁም ፓልምቻት የተባለ ድምፁ የሚረብሽ ወፍ ይገኝበታል።
የዶሚኒካን ሰዎች ሞቅ ያለ መንፈስ ያላቸውና በቀላሉ የሚቀረቡ ናቸው።
እዚያ እንግድነት አይሰማችሁም።
ሰብሰብ ብለው ሲጨወቱ ብዙዎች የሚወዱትን
ሳንኮቾ የተባለውን ምግብ ያዘጋጃሉ።
ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ማሪንጌ የተባለው ሙዚቃ የተገኘበት ቦታ ነው።
የማሪንጌ ሙዚቃና ዳንስ
ከማኅበረሰቡ የዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው።
የዶሚኒካን ሪፐብሊክ ባንዲራ
ላዩ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ምስል ያለበት ብቸኛው ባንዲራ ነው።
መጽሐፍ ቅዱሱ ዮሐንስ 8፡32 ላይ ተከፍቷል።
‘እውነት ነፃ ያወጣችኋል’ የሚለው ጥቅስ ላይ!
ኢየሱስ የተናገራቸው እነዚህ ቃላት ትክክል ናቸው።
በዶሚኒካን ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እውነትን ተምረው
ከብሔራዊ ስሜትና ከሐሰት ሃይማኖት ትምህርቶች ነፃ ወጥተዋል።
የስብከቱ ሥራ የጀመረው
ሌናርትና ቨርጂኒያ ጆንሰን የተባሉ ሚስዮናውያን
ሚያዝያ 1945 ወደ አገሪቱ ሲመጡ ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጠናት የጀመሩት
እዚያ በደረሱ በመጀመሪያው ዕለት ነበር።
ትንሽ ቆይቶም ሌሎች ሚስዮናውያን መጡ።
ብዙ ሰዎችም በሚስዮናውያኑ ቤት ስብሰባ ላይ መገኘት ጀመሩ።
በሦስት ዓመት ጊዜውጥ 110 የሚያሆኑ አስፋፊዎች
የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ ጀመሩ።
ይህ እድገት ከተቃዋሚዎች እይታ አላመለጠም።
ወንድሞቻችን በአምባገነኑ ራፋኤል ትሩሂዮ እጅ
ከፍተኛ ስደት ደርሶባቸዋል።
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትሮሂዮ ከፍተኛ ኃይል እንዲኖረው አድርጋለች።
በደሴቷ ላይ ያሉ ቤተ ክርስቲያኖች በሙሉ
“አምላክ በሰማይ ትሮሂዮ ደግሞ በምድር ይገዛሉ”
የሚል ምልክት እንዲሰቅሉ ይጠበቅባቸው ነበር።
ወንድሞቻችን ግን ከአቋማቸው ፍንክች አላሉም።
መንግሥት መጀመሪያ በ1950
እንደገና ደግሞ በ1957 በሥራችን ላይ እገዳ ጣለ።
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ወንድሞችና እህቶች አስገራሚ ጽናት አሳይተዋል።
በዘዴ ይሰብኩ እንዲሁም በቀጣዩ ቪዲዮ ላይ እንደምንመለከተው
በድብቅ ጽሑፎችን ያትሙ ነበር።
በዶሚኒካን ያሉት የይሖዋ ሕዝቦች
እገዳ ውስጥ ቢሆኑም አስገራሚ እድገት አሳይተዋል።
የተጣለባቸው ሁለተኛው እገዳ በ1960 ተነሳ።
ዛሬ ከ38,000 የሚበልጡ አስፋፊዎች በየወሩ
ከ45,000 የሚበልጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ይመራሉ።
ከስፓንኛ በተጨማሪ በሄይቲ ክሪኦል፣
በእንግሊዝኛ፣ በአሜሪካ የምልክት ቋንቋ፣
በማንደሪን ቻይንኛና በሩሲያኛ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ።
ከዋና ከተማዋ 150 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ
ኮንስታንዛ የተባለች ተራራ ላይ የምትገኝ ትንሽ ከተማ አለች።
ሰላምታችንን የምንደመድመው
የሎስ ላውሬሌስ ጉባኤን በመጎብኘት ነው።
በጉባኤው ውስጥ 134 አስፋፊዎች ሲኖሩ
36ቱ የዘወትር አቅኚዎች ናቸው።
እነዚህ ወንድሞችና እህቶች በየወሩ
በአማካኝ ከ170 በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ይመራሉ።
በዚህ አካባቢ መስበክ አስደሳች የሆነው አካባቢው ስለሚያምር ብቻ ሳይሆን
በዚያ ቅን ልብ ያላቸውና
ስለ ይሖዋ መማር የሚፈልጉ በርካታ ሰዎች ሳላሉም ነው።
በሎስ ላውሬሌስ ኮንስታንዛ ጉባኤ የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች
ሞቅ ያለ ፍቅራቸውንና ሰላምታቸውን ልከውላችኋል።
ይህ ከይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት የሚተላለፍላችሁ
JW ብሮድካስቲንግ ነው!