JW subtitle extractor

JW ብሮድካስቲንግ—ሰኔ 2026፦ 159ኛው የጊልያድ ምረቃ

Video Other languages Share text Share link Show times

ወንድሞችና እህቶች፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!
መጋቢት 14, 2026
የ159ኛው የጊልያድ ክፍል ተማሪዎች
ለአምስት ወራት የተሰጣቸውን መንፈሳዊ ሥልጠና አጠናቀዋል።
የምረቃው ፕሮግራም ተማሪዎቹን
በሕይወታቸው ለሚያጋጥሟቸው ለውጦችና
ለወደፊቱ ምድባቸው አዘጋጅቷቸዋል።
ለተማሪዎቹ የቀረቡት ንግግሮች
ለእኛም ጠቃሚ ትምህርቶችን ይዘዋል።
ምክንያቱም እኛም ለውጦች ያጋጥሙናል።
ስለዚህ ተግባራዊ ልታደርጓቸው የምትችሏቸውን ነጥቦች
ለማስተዋል ሞክሩ።
ይህን የምረቃ ፕሮግራም በተለያየ መንገድ የምትከታተሉትን ሁሉ
እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ስንቀበላችሁ ደስ ይለናል!
በተለይ ደግሞ ለወራት በትጋት ስታጠኑ የነበራችሁ ተማሪዎች
እንኳን ደስ ያላችሁ!
ውድ ተማሪዎች፣ ትምህርታችሁን በትጋት በማጥናት
ለዚህ ቀን በመብቃታችሁ በጣም ደስ ብሎናል።
ይህን የምረቃ ፕሮግራም
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተከታተሉት ነው።
በመሆኑም ሁላችሁንም
እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን እንቀበላችኋለን!
ይሄ ቀን
የሚደርስ መስሏችሁ ነበር?
አሁን ልትመረቁ ነው።
ለወራት በጉጉት ስትጠባበቁት የነበረው ቀን በእርግጥም ደርሷል።
ደስ ይላል።
ወደተመደባችሁባቸው ቦታዎች የምትሄዱበት ጊዜ ደርሷል።
ላለፉት አምስት ወራት የተማራችሁትን
በሥራ ላይ የምታውሉበትና
ከወንድሞቻችሁ ጋር በአንድነት፣ በሰላምና በፍቅር
መሥራት የምትችሉበት አጋጣሚ ይጠብቃችኋል።
ሰላም የሚለውን ቃል መጥቀሴ ትንሽ አሳሰባችሁ?
የተመደባችሁት አዲስ ቦታ ከሆነ
‘ከወንድሞች ጋር በሰላም ተግባብቼ እሠራ ይሆን?’
የሚለው አሳስቧችኋል?
ወይም ወደነበራችሁበት የምትመለሱ ከሆነ
‘ጊልያድ የተሻለ ሰው እንዳደረገኝ መመልከት ይችሉ ይሆን?’
የሚለው አሳስቧችኋል?
እንዲህ ብታስቡ አይገርምም።
ለዚህ ነው ለንግግሬ የመረጥኩት ርዕስ
“ሰላም ፍጠሩ” የሚል የሆነው።
ሰላም መፍጠር ቀላል እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን።
የዚህን እውነተኝነት ኢየሱስ በማቴዎስ ምዕራፍ 5 ላይ
ግልጽ በሆነ ሁኔታ አስቀምጦታል።
ኢየሱስ ሊያጋጥም የሚችለውን ሁኔታ ሲገልጽ
በማቴዎስ 5:23, 24 ላይ እንዲህ ብሏል።
ይህን የተናገረው ለደቀ መዛሙርቱ ነው።
“እንግዲያው መባህን ወደ መሠዊያው ባመጣህ ጊዜ
“ወንድምህ በአንተ ቅር የተሰኘበት ነገር እንዳለ ትዝ ካለህ
“መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ።
በመጀመሪያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ።”
በሌላ አባባል “ሰላም ፍጠር” ማለት ነው።
“ከዚያም ተመልሰህ መባህን አቅርብ።”
ይህ የኢየሱስ ንግግር ለአድማጮቹ
ከእውነታው የራቀ ሐሳብ ሊመስል ይችላል።
እስቲ አስቡት፣
መሥዋዕት ለማቅረብ ተዘጋጅታችኋል።
ግን መሥዋዕታችሁን መሠዊያው አጠገብ ትታችሁ
በሕዝብ ወደተጨናነቀው ከተማ ሄዳችሁ
ቅር የተሰኘባችሁን ሰው መፈለግ አለባችሁ ማለት ነው።
ከዚያ ደግሞ ይህን ሰው
ከብዙ ሺህ ሰዎች መካከል ለማግኘት ስትኳትኑ ይታያችሁ።
ሰውየውን አግኝታችሁ ሰላም መፍጠርና
ተመልሳችሁ ደግሞ መሥዋዕት ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
ግን ኢየሱስ እዚህ ላይ ማስገንዘብ የፈለገው ነጥብ ምንድን ነው?
ሰላም መፍጠር ቀላል የማይሆንበት ጊዜ አለ።
ሆኖም ራሳችንን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ አለ።
‘ሰላም መፍጠር ቀላል የማይሆነው ለምንድን ነው?
ከባድ ቢሆንም ሰላም ፈጣሪ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?’
ሰላም ፈጣሪዎች እንዳንሆን እንቅፋት የሚሆኑብንን
ሦስት ነገሮች በዚህ ንግግር ላይ እናያለን።
በተጨማሪም አብርሃም ከሎጥ ጋር አለመግባባት ባጋጠመው ወቅት
ሰላሙን ለመጠበቅ የወሰደውን እርምጃ በጥልቀት እንመረምራለን።
አብርሃም ምን ዓይነት ውሳኔ ሊወስን ይችል እንደነበረም እናያለን።
እስቲ የመጀመሪያውን እንመልከት።
በሌሎች ዘንድ ደካማ መስሎ የመታየት ፍርሃት።
አዎ!
ብዙዎቻችን አልፎ አልፎ የዋጋ ቢስነት ስሜት ይሰማናል።
ይህንን የዋጋ ቢስነት ስሜት ለመሸፈን
ከሌሎች ልቀን ለመታየት እንሞክራለን።
ይህ ደግሞ ከሌሎች ጋር ያለንን መልካም ዝምድና ያበላሽብናል።
በዚህም ምክንያት ሰላማችን ይደፈርሳል።
ይህ እውነት ነው።
ታዲያ አብርሃም ከሎጥ ጋር በነበረው ግንኙነት እንዲህ ተሰምቶታል?
እስቲ እባካችሁ ዘፍጥረት ምዕራፍ 13ን አውጡ።
ታሪኩን እንደምናስታውሰው በአብርሃምና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነስቶ ነበር።
ይህ ሁኔታ ከሎጥ ጋር ያለውን ግንኙነት
ሊያበላሽበት እንደሚችል አብርሃም ተገንዝቧል።
ታዲያ አብርሃም ምን አደረገ?
ዘፍጥረት 13:8, 9 እንዲህ ይላል፦
“ስለዚህ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፦
“‘እባክህ በእኔና በአንተ እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል
“ምንም ዓይነት ጠብ አይኑር፤
“እኛ እኮ ወንድማማቾች ነን።
“ምድሪቱ ሁሉ በእጅህ አይደለችም?
“እባክህ ከእኔ ተለይ።
“አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤
አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ ደግሞ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።’”
ይገርማል!
አብርሃም ቅድሚያውን ወስዶ በሎጥ ፊት ራሱን ዝቅ አድርጓል።
ራሱን ከሎጥ እንደሚሻል አድርጎ አልቆጠረም።
ሎጥን ዝቅ ዝቅ በማድረግ እሱ ልቆ ለመታየት አልሞከረም።
እንዲህ ማለት ግን ይችል ነበር።
“እንዴ!
ተከትለኸኝ መጣህ እንጂ ተከትዬህ እኮ አልመጣሁም።
ይሖዋ ‘ወደዚህ ምድር ሂድ’ ያለው እኔን እንጂ አንተን አይደለም።”
አብርሃም እንዲህ ቢል የፈለገውን ያገኝ ነበር።
ግን ይሄን ቢያደርግ በመካከላቸው ሰላም አይወርድም ነበር።
አዎ፣ አብራም እንዲህ አላደረገም።
አብርሃም እንደ ማንኛውም ሰው በሎጥ ፊት
ዝቅ ብሎ መታየትን ላይፈልግ ይችላል።
ግን በሎጥ ፊት ራሱን ዝቅ በማድረግ ምርጫውን ለእሱ ሰጥቶታል።
ግን አብርሃም እንዲህ እንዲያደርግ ያነሳሳው ምንድን ነው?
በአጭር አነጋገር፣ አብርሃም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው
በሰዎች ዘንድ ሳይሆን በይሖዋ ፊት ላለው ቦታ ነው።
ነጥቡ ይሄ ነው።
አብርሃም ይሖዋ ከሰጠው ከተስፋይቱ ምድር አይውጣ እንጂ
በዚያ ውስጥ የትም ይኑር የት ብዙ አላሳሰበውም።
በተስፋይቱ ምድር መገኘቱ በራሱ የይሖዋን ሞገስ እንዳገኘ ያሳያል።
ደግሞም የማቴዎስ 5:23, 24 መልእክትም ቢሆን ይሄ ነው።
የኢየሱስ መልእክት ግልጽ ነው።
ሄዶ እርቅ የፈጠረውን ግለሰብ ተመልሶ መባ እንዲያቀርብ ነግሮታል።
“ተመልሰህ” አዎ “ተመልሰህ መባህን አቅርብ” ብሎታል።
‘ለይሖዋ መባህን አቅርብ’ ብሎታል።
አብርሃምም ከምንም ነገር በላይ የሚፈልገው ይህንኑ ነው።
ከአምላክ ጋር ሰላም መፍጠር።
ስለዚህ ከአብርሃም የምንማረው የመጀመሪያው ትምህርት ምንድን ነው?
‘ሌሎች ደካማ እንደሆንኩ ያስባሉ’
ወይም ‘ያለኝን ተሞክሮ፣ እዚህ ጊልያድ ያገኘሁትን ሥልጠና ከግምት ውስጥ አያስገቡም’
የሚል ፍርሃት በውስጣችን እንዲያድር የምንፈቅድ ከሆነ
ሰላም ፈጣሪዎች እንዳንሆን እንቅፋት ይሆንብናል።
ይህ ደግሞ ከሌሎች ጋር አብሮ መሥራት ከባድ እንዲሆንብን ያደርጋል።
ታዲያ ይህን ስሜት ማስወገድ የምንችለው እንዴት ነው?
ልክ እንደ አብርሃም ባገኘነው ትልቅ መብት ላይ ትኩረት በማድረግ ነው።
በሌላ አባባል፣ በይሖዋ ዘንድ እውቅና በማግኘታችን ረክተን በመኖር።
ተጨማሪ በረከትና መብቶችን ማግኘታችን አስደሳች ቢሆንም
ዋናው ነገር ግን ይሄ አይደለም።
አብርሃም ሎጥን የያዘው በትሕትና ነው።
ምናልባትም አብርሃም ‘እኔ እንዳደረግኩለት ያደርግልኛል’ ብሎ አስቦ ሊሆን ይችላል።
ሎጥ እንዲህ ቢያደርግ ጥሩ ነበር።
ይህ ወደ ሁለተኛው ነጥብ ይመራናል።
ሌሎች መጠቀሚያ ያደርጉኛል ብሎ መፍራት።
እስቲ አስቡት፣
ከአንድ ሰው ጋር አለመግባባት ተፈጠረ ብለን እናስብ።
ከዚያ የሚፈልገውን ነገር እንዲያደርግ ለዚህ ሰው አጋጣሚውን ሰጠነው።
ግን በሌላም ጊዜ የራሱን ጥቅም ብቻ ለማስፈጸም
ይጥራል ብለን ልንፈራ እንችላለን።
አብርሃም ግን ምን አደረገ?
ዘፍጥረት ምዕራፍ 13ን እናውጣና
ካቆምንበት ማንበባችንን እንቀጥል።
ዘፍጥረት 13:10-12 እንዲህ ይላል።
አብርሃም በደግነት ሎጥ ቅድሚያውን ወስዶ ቦታ እንዲመርጥ አጋጣሚውን ሰጥቶታል።
ቁጥር 10 ጀምሮ እንዲህ ይላል፦
“ሎጥም ዓይኑን አቅንቶ መላውን የዮርዳኖስ አውራጃ
“እስከ ዞአር ድረስ ተመለከተ፤
“(ይሖዋ ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት)
“አካባቢው ልክ እንደ ይሖዋ የአትክልት ስፍራ፣
“ልክ እንደ ግብፅ ምድር ውኃ የጠገበ ነበር።
“ከዚያም ሎጥ መላውን የዮርዳኖስ አውራጃ ለራሱ መረጠ፤
“ሎጥም ወደ ምሥራቅ ሄዶ ሰፈረ።
“በዚህ መንገድ አንዳቸው ከሌላው ተለዩ።
“አብራም በከነአን ምድር ኖረ፤
ሎጥ ግን በአውራጃው በሚገኙ ከተሞች አቅራቢያ ኖረ።”
ሎጥ አብርሃም ያሳየውን የትሕትና ባሕርይ
ለራሱ መጠቀሚያ አድርጎታል?
እውነቱን ለመናገር፣ አናውቅም።
በአብርሃምና በሎጥ መካከል ስለነበረው ግንኙነት ዝርዝር መረጃ የለንም።
በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚቀርበው ዋናው ንግግር ስለዚህ ጉዳይ ይበልጥ ያብራራልናል።
በጉጉት ጠብቁ!
ግን ሎጥ የመረጠው ምርጫ
አብርሃም ያልጠበቀው ቢሆን ወይም በሎጥ ምርጫ ቢናደድ ኖሮ
እንዲህ ብሎ ሊያስብ ይችል ነበር፦
“እንዴ!
ይህማ አያዋጣም!
ትሑት መሆኔ ምን ጠቀመኝ?
የፈለግኩትን አላገኘሁም።
ቆፍጠን ብዬ ሎጥን መጫን አለብኝ።”
እንዲህ ብሎ ሊያስብ ይችል ነበር።
ግን አብርሃም እንዲህ ብሎ አስቦ ነበር?
አይ!
የቁጥር 11 መጨረሻና የቁጥር 12 መጀመሪያ
ስለተፈጠረው ሁኔታ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦
“በዚህ መንገድ አንዳቸው ከሌላው ተለዩ።
አብራም በከነአን ምድር ኖረ።”
ተቃውሞ አላሰማም፤
መብቱን ለማስከበር አልታገለም፤
ወይም ‘ተበድያለሁ’ አላለም።
በእርግጥም አብርሃም ትሑት ሰው ነበር።
በኋላ ላይ የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት ለራሱ እያመቻቸ አልነበረም።
አብርሃም የራሱን ፍላጎት ከማስቀደም ይልቅ
የሎጥን ምርጫ በማስቀደም ሰላም መፍጠርን መርጧል።
ስለዚህ ከአብርሃም የምናገኘው ሌላኛው ትምህርት ምንድን ነው?
ደግ በመሆናችን ምክንያት ሌሎች እኛን መጠቀሚያ በማድረግ
የሚገባንን መብትም ሆነ ክብር ይወስዱብናል ብለን ልንሰጋ እንችላለን።
ይህ ደግሞ ደግና ትሑት መሆን
ምንም ጥቅም እንደሌለው ማሰብ እንድንጀምር ሊያደርገን ይችላል።
ይህ ዓይነቱ አመለካከት ደግሞ
ከሌሎች ጋር ሰላም እንዳንፈጥር እንቅፋት ይሆንብናል።
ከዚህ ይልቅ እንደ አብርሃም ሁኑ።
ይሖዋ ሰላም ፈጣሪ እንድንሆን የሰጠን ምክር ምንጊዜም ጠቃሚ እንደሆነ እንመን።
ይህን ማድረግ የማያዋጣ መስሎ በሚሰማን ጊዜም ጭምር።
ይህን ስናደርግ የምንፈልገውን ላናገኝ እንችላለን።
ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር ግን እናገኛለን።
በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረናል፤
ሰላምም እናገኛለን።
ሎጥ ባደርገው መጥፎ ምርጫ ምክንያት ጉዳት ሲደርስበት
አብርሃም ምን ተሰማው?
ሎጥን ይቅር ብሎ ጉዳዩን ትቶት ይሆን?
ወይስ ሎጥ ያደረገበትን ነገር ለመርሳት ከብዶት ይሆን?
በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ የዚህን ጥያቄ መልስ እናገኛለን።
ቀጥሎ የሚቀርብልን “የትውውቅ መድረክ” የተሰኘው ፕሮግራም ነው።
በጊልያድ የምረቃ ፕሮግራም ላይ የሚቀርበውን ይህን ዝግጅት
ሁላችንም በጣም እንወደዋለን።
ደግሞም የዛሬውን “የትውውቅ መድረክ” ፕሮግራምም እንደምትወዱት እርግጠኞች ነን።
ፕሮግራሙ የሚስዮናዊነት መንፈስ ያላቸውን አስፋፊዎች
ሰባኪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉበት ቦታ ለማገልገል የሚያነሳሳ ነው።
የዛሬውን “የትውውቅ መድረክ” ፕሮግራም የሚመራልን
የጊልያድ አስተማሪ የሆነው ወንድም ጄረሚ ክላርክ ነው።
ወደ ትውውቅ መድረክ እንኳን ደህና መጣችሁ!
ኢየሱስ ማቴዎስ 5:6 ላይ
“ጽድቅን የሚራቡ ደስተኞች ናቸው” ብሏል።
ምክንያቱም መንፈሳዊ ፍላጎታቸው ይረካል።
ታዲያ ይሖዋ
የወጣቶችን መንፈሳዊ ፍላጎት የሚያረካው እንዴት ነው?
በዋነኝነት ወላጆቻቸውን በመጠቀም ነው።
ግን ወላጆቻቸው እውነት ውስጥ የሌሉ ወጣቶችንስ
እንዴት ነው የሚረዳቸው?
ይሖዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን በዕድሜ የገፉና
በመንፈሳዊ የበሰሉ ሰዎችን ይጠቀም ነበር።
ለምሳሌ ሊቀ ካህናቱ ዮዳሄ ወጣቱ ንጉሥ ኢዮዓስን
ዘካርያስ ደግሞ ወጣቱ ንጉሥ ዖዝያን ይረዱ ነበር።
በዚህ ፕሮግራም ላይ በልጅነታቸው መንፈሳዊ እርዳታ ያገኙ
የአንዳንድ የጊልያድ ተማሪዎችን ተሞክሮ እንሰማለን።
ያገኙት መንፈሳዊ እርዳታ አገልግሎታቸውን እንዲያሰፉና
ደስተኛ ሕይወት እንዲመሩ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ እናያለን።
ዝግጁ ናችሁ?
መጀመሪያ በዩናይትድ ስቴትስ የሚያገለግሉትን
አንትሮንና ሬቤካን እንተዋወቅ።
ሁለታችሁም እንኳን ደህና መጣችሁ!
አሁን የምታገለግሉት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ነው።
ግን እስቲ ከዚህ በፊት የነበረውን ሕይወታችሁን አጫውቱን።
ምን ይመስል ነበር?
እኔ የተወለድኩትም ያደግኩትም ሳውዝ ካሮላይና ነው።
ሁለቱም ወላጆቼ የይሖዋ ምሥክሮች ስለሆኑ
ያደግኩት እውነት ቤት ውስጥ ነው።
ከአባቴ ሌሎችን እንዴት በደግነት መያዝ እንዳለብኝ ተምሬያለሁ።
እናቴ ደግሞ መንፈሳዊ ግቦችን እንዳወጣና
በዛው እንድጸና ረድታኛለች።
በጉባኤ ውስጥ ትኩረት ይሰጡኝ የነበሩ ሌሎች ወንድሞችም ነበሩ።
ለምሳሌ አንድ ወንድም፣ እኔና የአጎቴን ልጅ
ከእሱ ጋር የምሳሌ መጽሐፍን እንድናጠና ጋብዞን ነበር።
ምሳሌን ለምን መረጠ?
ያኔ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ነበርኩ።
የምሳሌ መጽሐፍ ደግሞ ብዙ ጥበብ ያዘሉ ምክሮች አሉት።
መጽሐፍ ቅዱስ በጥበብ የተሞላ መጽሐፍ መሆኑን
እንድናምን ያደርገናል ብሎ አስቦ ነው።
በእኔ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ሌላ ወንድምም አለ።
አንድ ጉባኤ ውስጥ ነበርን።
የተወሰነ ጊዜ ቤቴል አገልግሎ ተመልሶ መጣ።
ይህ ወንድም
‘ቤቴል ስለመግባት በቁም ነገር ማሰብ አለብህ’ ይለኝ ነበር።
ስለ ቤቴል ማሰብ የጀመርኩት ያኔ ነው።
ሌላ ቋንቋ እንድማርም አበረታታኝ።
እኔም ተማርኩ።
ሁሉንም ምክር ተግባራዊ አድርገሃል።
አዎ።
እነዚህ ወንድሞች ስላበረታቱህ ደስ ብሎናል።
አንቺስ ሬቤካ እውነት ቤት ውስጥ ነው ያደግሽው?
አዎ፣ ያደግኩት ስፔን ነው።
ቤታችን ለቅርንጫፍ ቢሮው በጣም ቅርብ ነበር።
ስለዚህ በልጅነቴ ብዙ ቤቴላውያን
ወደ ቤታችን ተጋብዘው ሲመጡ አስታውሳለሁ።
በጣም ደስ ይላል።
ታዲያ ከሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ጋር
አዘውትሮ መገናኘት ምን ይመስላል?
ብዙ ቁሳዊ ነገር ባይኖራቸውም
ምንም ዓይነት መልካም ነገር እንዳልጎደለባቸው
መመልከት ችያለሁ።
ይሖዋ በሁሉም መንገድ እየተንከባከባቸው እንደሆነ
በግልጽ ማየት ችያለሁ።
ሁልጊዜ ደስተኞች ናቸው።
በጣም የሚገርመው ፈገግታ ተለይቷቸው አያውቅም።
ይህ ደግሞ ልቤን በጥልቅ ነክቶታል።
እኔም እንዲህ ያለውን ደስታ በገዛ ሕይወቴ ማጣጣም ፈለኩ።
በጣም ደስ የሚል ነው።
ታዲያ ወላጆችሽ አንቺን ለመርዳት ያደረጉት ሌላስ ነገር አለ?
አዎ አለ።
አባቴ ከእኔና ከሁለት እህቶቼ ጋር
ሁሌ ማታ ማታ አብሮን ይጸልይ ነበር።
ይህ ብቻ ግን አይደለም።
እኛ ወደ ይሖዋ የምናቀርበውን ጸሎትም መስማት ይፈልግ ነበር።
ይህን የሚያደርገው ይሖዋ እውን አካል ሆኖ እንዲታየን
ለመርዳት ይመስለኛል።
እናቴ በጉባኤያችን ካሉ አቅኚዎች ጋር
የምንችለውን ያህል ብዙ ጊዜ እንድናሳልፍ ታበረታታን ነበር።
እኛም ያደረግነው እንደዛ ነው።
በዚህም ምክንያት ገና ከልጅነታችን አንስቶ
ለአገልግሎት ልዩ ፍቅር ነበረን።
ሁለታችሁም ወላጆቻችሁ እናንተን ካሳደጉበት መንገድ
ጥቅም አግኝታችኋል።
ይሖዋን ይበልጥ ለማገልገል የሚያስችል
ቅንዓትና እምነት ለማዳበር ረድቷችኋል።
ታዲያ ሌሎች አጋጣሚዎችስ አግኝታችኋል?
አዎ አግኝተናል።
እኔና አንትሮን መጠናናት ስንጀምር
ኒው ዮርክ ቤቴል እያገለገለ ነበር።
ብዙም ሳይቆይ ግን
በኡጋንዳ ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ እንዲያገለግል
አዲስ ምድብ ተሰጠው።
ኡጋንዳ!
እኔ ራሴ ይህ ምድብ ሲሰጠኝ በጣም ተገርሜ ነበር።
ግን ደግሞ ለመሄድም ጓጉቼ ነበር።
ከሬቤካ ጋር መጠናናታችንን ቀጠልን።
ከዛ ማድሪድ ውስጥ ተጋባን።
ከተጋባን ከጥቂት ቀናት በኋላ
በኡጋንዳ ቅርንጫፍ ቢሮ አብረን ማገልገል ጀመርን።
ይሄ ፎቶ ኡጋንዳ የተነሳችሁት ነው?
አዎ ቤቴል የተነሳነው ነው።
እዚያ ማገልገል ምን ይመስላል?
በሕይወታችን ፈጽሞ የማንረሳው አጋጣሚ ነው ያገኘነው።
ግን ደግሞ ብዙ ለውጦችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ
ከባድ እንደሆነ አልክድም።
የትዳርና የቤቴል ሕይወትን አንድ ላይ መልመድ ነበረብኝ።
ባሕሉ፣ ቋንቋው፣ ምግቡ ሁሉም አዲስ ነበር።
ሌላው ቀርቶ አዲስ አስተሳሰብ ማዳበር ነበረብኝ።
ስለ ራስህ ብዙ ትማራለህ።
የአንተንና የእነሱን አመለካከት ለማስማማት በምታደርገው ጥረት
እየበሰልክ ትመጣለህ።
ልጅ እያለህ ከምሳሌ መጽሐፍ ላይ የተማርከው ጥበብ
አሁን ጠቀመህ አይደል?
በሚገባ!
ክፍል ውስጥ በምሳሌ 19:11 ላይ ውይይት አድርገን ነበር።
‘በደልን መተዉ ውበት ያጎናጽፋል’ ይላል።
ይሖዋ ውበት የተጎናጸፉ ብዙ ነገሮችን ፈጥሯል።
የሚያስገርመው ግን ይህ ጥቅስ
ሌሎች ሲበድሉን ይቅር ማለትም
ውበት እንደሚያጎናጽፈን ይናገራል።
በኡጋንዳ ያሉት ወንድሞቻችንም ያደረጉት ልክ እንደዚህ ነው።
ሊያበሳጫቸው የሚችል ብዙ ነገር ብናደርግም አያጉረመርሙም።
የምንሠራቸውን ስህተቶች ይቅር በማለት
ውበት እንደተጎናጸፉ ቀጥለዋል።
አዎ ልክ ነው።
ኡጋንዳ ያሉ ወንድሞቻችን ቤተሰብ ሆነውልናል።
ወንድሞችና እህቶችን በወደድካቸው ልክ
እነሱም ይበልጥ እንደሚወዱህ ተምሬያለሁ።
በተለይ አንዳንዴ ቤተሰቦቻችን ሲናፍቁን በጣም ረድተውናል።
አንድ ሚስዮናዊ ባልና ሚስት ያደረጉልንን ፈጽሞ አንረሳውም።
ለስሜታችን በጣም ይጠነቀቁልን ነበር።
ትልቅ ትኩረት ይሰጡን ነበር።
ብዙ ጊዜ አብረውን ይሳልፋሉ።
እነዚህ ባልና ሚስት ያሳዩን ፍቅር
ይሖዋ ምን ያህል እንደሚወደንና እንደሚንከባከበን የሚያሳይ ነበር።
ኡጋንዳ ምን ያህል ቆያችሁ?
10 ዓመት አካባቢ ቆይተናል።
ስትወጡ አልከበዳችሁም?
በጣም፣ በጣም ነው የከበደን።
እንዲያውም ስንለያይ በጣም ነው ያለቀስነው።
ዓይናችን እስኪጠፋ ነው ያለቀሰነው!
አዎ፣ ልክ ነው።
ግን ደስ የሚለው አሁንም ድረስ እንገናኛለን።
በተለይ ደግሞ በጣም ከምቀርባቸው እህቶች ጋር
በደንብ ነው የምንገናኘው።
በቃ፣ እንግድነት እንዳይሰማን የሚያደርጉበት
የራሳቸው መንገድ አላቸው።
እንዲያውም ከዚያ ስንወጣ አንድ ፍየልና
ትንሽ ቁራጭ መሬት ሰጥተውናል።
ምናልባት ከተመለሳችሁ ብለው።
የሚገርም ነው።
ወላጆቻችሁ ከሰጧችሁ ሥልጠና ተጠቅማችኋል።
ሌሎች ብዙ ሰዎች
መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን እንዲያረኩ ረድታችኋል።
ወደፊትም ትረዳላችሁ።
አንትሮንና ሬቤካ ተሞክሯችሁን ስላካፈላችሁን
በጣም እናመሰግናችኋለን።
አንዳንዶቹ የዚህ ክፍል ተማሪዎች
እውትነትን ከአንደኛው ወላጃቸው ብቻ ነው የተማሩት።
ከእነዚህ መካከል አንዷ እህት ጃኋይ ሊን ናት።
ከታይዋን ነው የመጣችው።
እንኳን ደህና መጣሽ!
አመሰግናለሁ።
እስቲ አንቺም ተሞክሮሽን አጫውቺን።
እሺ ደስ ይለኛል።
የተወለድኩትም ሆነ ያደግኩት ታይዋን ውስጥ ነው።
እናቴ እውነትን ተምራ ስትጠመቅ የ10 ዓመት ልጅ ነበርኩ።
በጣም ጥሩ።
አባትሽስ?
አባቴ እንኳ አሁንም ድረስ የይሖዋ ምሥክር አይደለም።
እውነትን ይወድዳል።
እንዲያውም ይደግፈናል።
እኔና ታናሽ ወንድሜ ለይሖዋም ሆነ ለአገልግሎት
ፍቅር እንዲኖረን የረዳችን እናታችን ናት።
ብዙ አስተምራናለች።
እዚህ ላይ አንቺና እናትሽ ናችሁ?
አዎ፣ አዳራሽ ውስጥ የተነሳነው ነው።
ወንድምሽም አለ!
አዎ ልክ ነህ።
እናትሽ ይሖዋን እንደትወጂ የረዳችሽ እንዴት ነው?
እናቴ የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት የጀመረችው
የሙሉ ጊዜ ሥራ እየሠራችና ሁለት ልጆች እያሳደገች ነው።
የአቅኚነት አገልግሎቷን በቁም ነገር ነበር የምትመለከተው።
ደግሞም ትወደዋለች።
ከአገልግሎት ስትመለስ
ፊቷ ላይ ይነበብ የነበረው ደስታ አሁንም ድረስ አይረሳኝም።
እናታችን ስታገለግል ያገኘቻቸውን
አስደሳች ተሞክሮዎች ትነግረን ነበር።
ግን በዚያ ክልል ማገልገል ለእናትሽ ቀላል ነበር? 
አብዛኞቹ ሰዎች ትኩረት የሚያደርጉት
የተደላደለ ሕይወት በመምራት ላይ ስለነበር
የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት ለማድረግ
ያን ያህል ፍላጎት አልነበራቸውም።
ግን እናቴ ሁሌም ፍላጎት ያለው ሰው አታጣም ነበር።
ፍላጎት ያለው ሰው የምታገኘው ደስታዋና
ለሰዎች ያላት ፍቅር በግልጽ ይታይ ስለነበር ይመስለኛል።
ሌላው የማስታውሰው ደግሞ
አዲስ ዓለም ትርጉም ላይ ያሉትን የመግቢያ ሐሳቦች
ከሰዎች ጋር ውይይት ለመጀመር በሚገባ ትጠቀምባቸው ነበር።
በመንፈስ የምትቃጠል ሰው ነበረች ማለት ነው።
ግን የተፈጠረብኝ ጥያቄ አለ።
በታይዋን ያሉ ሰዎች ያተኮሩት
የተደላደለ ሕይወት መምራት ላይ ነው።
እዚያ መስበክ ምን ይመስላል?
የስብከቱ ሥራ በጣም አስደሳች ነው።
እንዲያውም ከዚህ ጋር የተያያዘ ቪዲዮ ብጋብዝህ ደስ ይለኛል።
እኔም ደስ ይለኛል።
ታይዋን ኢሊያ ፎርሞሳ በመባልም ትታወቃለች።
የሚያምር ደሴት ማለት ነው።
ይህች ውብ ደሴት የምትገኘው በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ነው።
የሚያማምሩ የባሕር ዳርቻዎችና ረጃጅም ተራሮች አሏት።
ግን እንደ ሌላው የዓለም ክፍል ሁሉ በታይዋንም በጣም የሚያምሩት
በውስጧ ያሉት ሕዝቦች ናቸው።
በ1948 የስምንተኛው የጊልያድ ክፍል ተመራቂ የሆነው
ወንድም ስታንሊ ጆንስ ታይዋንን ጎብኝቶ ነበር።
በደሴቲቱ ላይ ረጅም ርቀት ተጉዞ
አንድ ትልቅ ስብሰባ ላይ ተገኝቷል።
በዚያ ስብሰባ ላይ 300 ያሚያህሉ ሰዎች ተጠምቀዋል።
ያኔ በታይዋን የተዘራው የእውነት ዘር ፍሬ አፍርቶ
በአሁኑ ጊዜ በዚያች አገር
ከ11,000 የሚበልጡ አስፋፊዎች አሉ።
ታይዋን በዓለማችን ላይ ካሉ
በአንድ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች
ተጨናንቀው ከሚኖሩባቸው ቦታዎች አንዷ ናት።
ለምሳሌ በታይፔ ከተማ ውስጥ
ከ2 ሚልዮን በላይ ሰዎች ይኖራሉ።
እዚህ በቁሳዊ ለመበልጸግ የሚያስችሉ ብዙ አጋጣሚዎች አሉ።
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ግን
ቀደም ሲል በዚያ የነበሩ ሚስዮናውያን የተዉትን ምሳሌ በመከተል
በስብከቱ ሥራ በቅንዓት እየተካፈሉ ነው።
ልጅ እያለሁ ወላጆቼ
ብዙ ጊዜ ስለ ገንዘብ ሲጨቃጨቁ እሰማ ነበር።
ስለዚህ ‘ሳድግ ሀብታም መሆን አለብኝ’ ብዬ ወሰንኩ።
‘ሀብታም ከሆንኩ ቤተሰቤ ደስተኛ ይሆናል’ ብዬ አስቤ ነበር።
17 ዓመት ሲሆነኝ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀመርኩ።
ይሖዋ በገነት ውስጥ
አስደሳች ሕይወት ሊሰጠን እንደሚፈልግ ተገነዘብኩ።
እውነተኛ ደስታ የሚያስገኘው ባለን መርካት እንደሆነም ተማርኩ።
የተጠመኩት በ1999 ነው።
ከተጋባን በኋላ ወደሌላ ቦታ ተዛውረን
በአቅኚነት የማገልገል ግብ ነበረን።
ግን በወቅቱ አባቴ በስትሮክ ተመትቶ
ለስምንት ዓመታት ያህል እየተሠቃየ ነበር።
ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ሥራዬን ይበልጥ እየወደድኩት መጣሁ።
ከሥራዬ የማገኘው እርካታም እየጨመረ መጣ።
አልፎ አልፎ ግን
‘ለቤተሰቤ የሚያስፈልገውን ነገር የማቅረብ ኃላፊነቴን
የተንደላቀቀ ሕይወት ለመምራት
እንደሰበብ እየተጠቀምኩበት ይሆን?’
እያልኩ አስብ ነበር።
ወንድሞችና እህቶች አገልግሎታቸውን በማስፋታቸው
ወይም ኤስ.ኬ.ኢ. በመግባታቸው
ስላገኙት ደስታ ሲናገሩ እንሰማ ነበር።
ይህም በአኗኗራችን ላይ ማስተካከያ እንድናደርግ አነሳስቶናል።
ከጊዜ በኋላ አባቴ አረፈ።
በዚህ ጊዜ ሕይወታችንን ቀላል ለማድረግ
ጊዜው አሁን እንደሆነ ተሰማን።
ወዲያውኑ ሁለታችንም ሥራችንን ለቀቅን።
ከዚያም ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ተዛውረን
በአቅኚነት ማገልገል ጀመርን።
ሥራዬን ልለቅ እንዳሰብኩ ለአለቃዬ ስነግረው
ጨርሶ አልተዋጠለትም።
አለቃዬ የሰማውን ማመን ነው ያቃተው።
“ኢ ሆንግ አብደሃል እንዴ?
“ለመሆኑ በደንብ አስበህበታል?
“ወደፊት ምን ልትሆን ነው?
ቤተሰብህስ ምን ሊሆን ነው?” አለኝ።
እኔ ግን ባደረግኩት ውሳኔ ጸናሁ።
ይሖዋ በእጅጉ ባርኮናል።
አዲሱን አኗኗራችንን ለመልመድም ጊዜ አልፈጀብኝም።
በጉባኤያችን ካሉ ወንድሞችና እህቶች ጋር
ሰፋ ያለ ጊዜ ማሳለፍ ችለናል።
እንዲሁም በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን
ወደ ይሖዋ መቅረብ እንዲችሉ ረድተናል።
የሰይጣን ዓለም
ሰዎች በማይጨበጥ ነገር ላይ እንዲያተኩሩ ያደርጋል።
ሰዎችን ሊማርኩ የሚችሉ ብዙ ነገሮች ያቀርባል።
ግን በሕይወታችን ውስጥ ትልቁን ቦታ ሊይዝ የሚገባው
ከይሖዋ ጋር የመሠረትነው ጥሩ ዝምድና ነው።
ደግሞም በገነት ውስጥ ይሖዋን እያገለገልን
ለዘላለም እንኖራለን።
አሁን ላይ መለስ ብዬ ሳስበው
ከዚህ ቀደም በድፍረት እርምጃ ብወስድ ኖሮ
ይሖዋ ይበልጥ ማገልገል እችል እንደነበረ ይሰማኛል።
ምሳሌ 10፡22 ላይ ያለው እውነታ አሁን ግልጽ ሆኖልኛል፦
አንድን ሰው ባለጸጋ የሚያደርገው የይሖዋ በረከት ነው።
ቀደም ብለው ወደ ታይዋን የመጡት ሚስዮናውያን
ጥሩ መሠረት ጥለዋል።
ዛሬ በሩቅ ምሥራቅ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የይሖዋ አገልጋዮች
ምሥራቹን ለማስፋፋት ራሳቸውን በፈቃደኝነት ያቀረቡት
የእነሱን መልካም ምሳሌ በመከተል ነው።
ወንድሞች ሰዎች ወደ ይሖዋ እንዲቀርቡ ለመርዳት
ጠንክረው ሲሠሩ ማየት ያስደስታል።
አዎ፣ ልክ ነህ።
ግን ጃኋይ ከእናትሽ ሌላ
በመንፈሳዊ ጉዞሽ ያገዙሽ ሌሎች ሰዎች አሉ?
አዎ፣ አሉ።
በዕድሜ ከፍ ካልኩ በኋላ በመንፈሳዊ የደከምኩበት ወቅት ነበር።
ከስብሰባዎች እቀር ነበር።
ግን ጉባኤያችን ያሉ አንድ ሚስዮናዊ ባልና ሚስት
በግለሰብ ደረጃ አሳቢነት አሳዩኝ።
እንዲያውም ከስብሰባ በቀረሁ ቁጥር
ደህንነቴን ለማጣራት ጥረት ያደርጋሉ።
እዚህ ፎቶ ላይ
ከእናትሽና ከወንድምሽ ጋር የሚታዩት እነሱ ናቸው አይደል?
አዎ፣ ልክ ነህ።
ደስ ይላል። ጊልያድ ተምረዋል እንዴ?
አዎ፣ ተምረዋል።
እንዲያውም እስከ ምድር ዳር ድረስ የተባለው ቪዲዮ ላይ አሉ።
ከእነሱ ጋር መሆን በጣም ደስ ይለኝ ነበር።
ግን በኋላ በሌላ ከተማ እንዲያገለግሉ ተመድበው ሄዱ።
በጣም ነበር የከፋኝ።
ግን ብዙም ሳይቆይ ሌላ አዲስ ጓደኛ አገኘሁ።
ታይዋን እንድታገለግል የተመደበች ጃፓናዊት እህት!
ብዙ ጊዜ በተለያዩ የአገልግሎት መስኮች
አብሬያት እንድካፈል ትጋብዘኝ ነበር።
በጣም ትወድሻለች ማለት ነው።
በሌላስ መንገድ ረድታሻለች?
አዎ በደንብ እንጂ።
እንዲያውም የመጀመሪያው የወጣቶች ጥያቄ ቪዲዮ ማለትም
እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው?
የተባለው ቪዲዮ ሲወጣ አብረን እንድናይ ቤቷ ጋብዛኝ ነበር።
ቪዲዮውን ሳይ አንዲት አቅኚ እህት፣
አንዲትን ወጣት እህት በመንፈሳዊ ስትረዳት ተመለከትኩ።
ለካ ይቺ ጃፓናዊት እህትም
ለእኔ እያደረገችው ያለው ልክ እንደዚያው ነው።
እስከዚያ ጊዜ ድረስ እውነት ጠቃሚ እንደሆነ ገብቶኛል።
ደግሞ አሳማኝ ነው።
ግን እህት ያሳየችኝን ፍቅር በገዛ ሕይወቴ ስመለከት
ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብልኝና
እንደሚወደኝ ተገነዘብኩ።
ይሖዋን እንደ ወዳጄ በመቁጠር
ወደ እሱ እንድቀርብ የረዳኝ ይህን ማወቄ ነው።
በጣም ደስ ይላል።
ስለዚህ እናትሽና ሌሎች ሰዎች ረድተውሻል።
ታዲያ ይሄ መንፈሳዊ እድገት እንድታደርጊ የረዳሽ እንዴት ነው?
መጀመሪያ የዘወትር አቅኚ መሆን ችያለሁ።
ከዚያ ወደ እንግሊዘኛ ጉባኤ ተዛወርኩ።
ሰዎች የይሖዋን ፍቅር እንዲያጣጥሙ መርዳት
በጣም አስደናቂ መብት ነው።
ብዙዎች ለመርዳት ወደ ታይዋን መጥተዋል።
ደግሞም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ወንድሞችና እህቶች
ለይሖዋ ሲሉ የራሳቸውን ጥቅም መሥዋዕት አድርገው
ወደዚህ መምጣታቸውን ማየት በጣም የሚያስደስት ነው።
ልክ ነሽ!
ሌሎችን ስለ ይሖዋ እንዲያውቁ ማስተማር
ከፍ አድርገን ልናየው የሚገባ ትልቅ መብት ነው።
እናመሰግናለን!
ይሖዋ አንቺንም ሆነ በታይዋን ያሉ
ወንድሞችን እንዲባርክ እንጸልያለን።
ግሩም ተሞክሮ ነው ያካፈልሽን።
አመሰግናለሁ።
በርካታ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን
እውነትን የተማሩት ከወላጆቻቸው አይደለም።
ታዲያ ማን ያስተማራቸው?
በዩናይትድ ስቴትስ የሚያገለግለውን ዳግ ተራልን እንተዋወቅ።
ዳግ፣ እንኳን ደህና መጣህ!
እስቲ መንፈሳዊ ጉዞህ እንዴት እንደጀመረ አጫውተን።
18 ዓመት አካባቢ እያለሁ
ሕይወቴ በቃ፣ ጥሩ የሚባል ዓይነት አልነበረም።
ስትል? ምን ማለትህ ነው?
ያደግኩት እውነት ቤት ውስጥ አይደለም።
ግን እናቴ እኔን ጨምሮ ወንድሜንና እህቴን
ጥሩ አድርጋ ነው ያሳደገችን።
የሚያሳዝነው ግን መጥፎ ውሳኔዎችን አደረግኩ።
ከማይሆኑ ሰዎች ጋር ገጠምኩ።
በጣም ቁጡ፣ ጭንቀታም፣ ድብርታም ሆንኩ።
እናቴ ያለሁበት ሁኔታ ስላሳሰባት
ቁጭ አድርጋ አነጋገረችኝ።
እርግጥ በዚያ ጊዜም ስለ አምላክ የማወቅ
ከፍተኛ ፍላጎት ነበረኝ።
ወደ ተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት እሄድ ነበር።
ወደ ካቶሊክ፣ ወደ ጴንጤቆስጤ፣ ወደ ሜቶዲስት።
እና ምን አገኘህ?
ምንም አላገኘሁም።
እዚያ ያየሁት ምንም ነገር ልቤን ሊነካው አልቻለም።
ያኔ ማለትም እናቴ ቁጭ አድርጋ ካነጋገረችኝ በኋላ
በጉልበቴ ተንበርክኬ
እያለቀስኩ፣ አምላክ ስለ እሱ ማንነት እንዲገልጽልኝ
እንደጸለይኩ አስታውሳለሁ።
ለጥያቄዎቼ መልስ እንዲሰጠኝ ለመንኩት።
ዳግ ጥያቄዎችህ ምን ነበሩ?
‘በጥሩ ሰዎች ላይ መጥፎ ነገር የሚደርሰው ለምንድን ነው?’
‘በሃይማኖት ውስጥ ይህን ያህል ግብዝነት የበዛው ለምንድን ነው?’
‘አምላክ ስም አለው?’ የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩኝ።
የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ማወቅ የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ።
ታዲያ መልስ አገኘህ?
ይህን ጸሎት ከጸለይኩ ከሁለት ሳምንት በኋላ
የይሖዋ ምሥክሮች በራችንን አንኳኩ።
አብዛኛውን ጊዜ ለይሖዋ ምሥክሮች በር አንከፍትም ነበር።
እና የዚያ ቀን ምን ተገኝቶ በር ከፈታችሁ?
በዚህ ጊዜ ሁኔታው የተለየ ነበር።
ምክንያቱም ከመጡት ሁለት እህቶች መካከል አንደኛዋ
አስተማሪዬ ነበረች።
10ኛ ክፍል ስላስተማረችኝ ደግና አፍቃሪ እንደሆነች አውቃለሁ።
ስለዚህ ሳያት በሩን ከፈትኩት።
ያነሳችልኝ ጥያቄ ደግሞ በጣም የሚያስገርም ነው።
‘አምላክ ስም እንዳለው ታውቃለህ?’ የሚል ነበር።
መዝሙር 83:18ን አሳየችኝ።
ከዚያም 1 ዮሐንስ 5:19ን አነበበችልኝ።
መላው ዓለም በክፉው ቁጥጥር ሥር እንደሆነ ይናገራል።
ከእሷ ጋር ከተወያየሁ በኋላ
ከዚያ በፊት በሕይወቴ ተሰምቶኝ የማያውቅ
ከፍተኛ ደስታ ተሰማኝ።
በጣም ደስ የሚል ነው።
ታዲያ ከአስተማሪህ በተጨማሪ
ስታጠና መንፈሳዊ እድገት እንድታደርግ የረዱህ ሌሎች ሰዎች አሉ?
አዎ፣ አሉ።
ከእሷ ጋር ከተገናኘሁ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀመርኩ።
ለጉብኝት አትላንታ ሄጄ ነበር።
በጣም የምቀርበው ጓደኛዬን ያገኘሁት እዚያ ነው።
እስቲ ስለ እሱ ንገረን።
ያኔ ማጥናት ከጀመርኩ ዓመት አልፎኛል።
ግን የተማርኩትን በሥራ ላይ ለማዋል
አሁንም እርዳታ ያስፈልገኝ ነበር።
እሱም እኔን ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት አደረገ።
የተማኩትን በሥራ ላይ እንዳውል ረድቶኛል።
ደግሞ ጎበዝ አቅኚ ነው።
በዚህ የተነሳ አትላንታ ሄጄ መኖር ጀመርኩ።
ጥናቴንም ከእሱ ጋር ቀጠልኩ።
እንዲያውም ለሰባት ዓመታት አብረን ኖረናል።
በጣም ደስ ይላል።
የቅርብ ወዳጅ መሆን ብቻ ሳይሆን
መንፈሳዊ እድገት እንታደርግም ረድቶሃል።
ከዚያስ ምን ሆነ?
በአንድ ወቅት ጥናቴ ላይ እንዲገኝ
የወረዳ የበላይ ተመልካቹን ጋበዘው።
የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ደግና አፍቃሪ ነበር።
ከወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጋር ካጠናን በኋላ
መንፈሳዊ ግብ ለማውጣት እንዲረዳኝ
ይሖዋን አጥብቄ መለመን እንዳለብኝ ተገነዘብኩ።
እዚህ ላይ ፎቶ መጥቷል።
እዚህ ፎቶ ላይ ያሉት እነማን ናቸው?
ይሄ ስጠመቅ የተነሳሁት ፎቶ ነው።
በስተቀኝ በኩል ያለችው ቤታችንን ያንኳኳችው አስተማሪዬ ናት።
በስተግራ ጫፍ ላይ ያለው ደግሞ
በጣም የምቀርበው ያልኩህ ጓደኛዬ ነው።
በጣም ጥሩ።
ጓደኛህ ከወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጋር አስተዋወቀህ።
ታዲያ ይሄ እድገት እንድታደርግ የረዳህ እንዴት ነው?
በዚያ ወቅት ወደ እውነት ከመምጣቴ በፊት ከነበሩኝ
አንዳንድ መጥፎ ስሜቶች ጋር እየታገልኩ ነበር።
ስለዚህ በዚህ ረገድ እርዳታ ማግኘት ያስፈልገኝ ነበር።
ያኔ ይጎበኘን የነበረው የወረዳ የበላይ ተመልካቻችን
በግል ትኩረት ሰጥቶ ረዳኝ።
የአገልግሎት ችሎታዬን ይበልጥ እንዳሻሽል ረድቶኛል።
በተጨማሪም የማስተማርም ሆነ
እረኝነት የማድረግ ችሎታዬን እንዳሻሽልና
አሉታዊ ስሜቶቼን እንዳሸንፍ ረድቶኛል።
ከዚያ ብዙም ሳይቆይ
የወረዳ የበላይ ተመልካች ሆኜ ማገልገል ጀመርኩ።
በጣም ደስ ይላል።
ታዲያ አሁን ያኔ በመንፈሳዊ እድገት እንድታደርግ
የረዱህን ሰዎች ስታስብ
ምንድን ነው የሚሰማህ?
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰውን አናሲሞስን ነው የማስበው።
ክርስቲያን ከመሆኑ በፊት ከጌታው የኮበለለ ባሪያ ነበር።
በዚያ ወቅት ባሮች እንደ ዕቃ ነበር የሚቆጠሩት።
ከዚያ ክርስቲያን ሆነ።
ሐዋርያው ጳውሎስም ጉባኤውን ለማነጽ ተጠቅሞበታል።
እንደ አናሲሞስ ነበር የሚሰማኝ።
እውነትን ከማወቄ በፊት ለምንም እንደማይጠቅም ዕቃ ነበርኩ።
ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚታየኝ ነገርም አልነበረም።
ግን ይሖዋ እንደ ጳውሎስ ያሉ ሰዎችን
ማለትም አስተማሪዬን፣ የቅርብ ጓደኛዬንና
የወረዳ የበላይ ተመልካቹን በመጠቀም
እኔ ያላስተዋልኩትን እምቅ ችሎታዬን እንድጠቀምበት ረድቶኛል።
ዳግ መንፈሳዊ ግቦችህ ላይ በመድረስህ ደስ ብሎናል።
ወጣቶች ይሖዋን እንዲወዱ ለመርዳት ጊዜ መድቦ
በግለሰብ ደረጃ ትኩረት መስጠት ያለውን ጥቅም ተገንዝበናል።
ጥሩ ተሞክሮ ነው። እናመሰግንሃለን።
አንድ ሰው መንፈሳዊ ፍላጎቱ ሲረካ
ይሖዋን ለማገልገል ይበልጥ እንደሚነሳሳ ግልጽ ነው።
ቀጥሎ በታይላድ የሚያገለግሉ አንድ ባልና ሚስትን እንተዋወቅ።
አንዲና ጁሊ አልተንን።
እሺ አንዲና ጁሊያ፣ ሁለታችሁም እንግሊዛዊ ናችሁ።
የምታገለግሉት ግን በታይላንድ ነው።
እዚያ የሄዳችሁት እንዴት ነው?
ለረጅም ጊዜ፣ በብሪታንያ ቤቴል ውስጥ የማገልገል ግብ ነበረን።
ስለዚህ ፎርም ሞላን።
መልስ ግን የለም።
በተወሰነ መጠን አዝነን ነበር።
ምክንያቱም ይሖዋን የት ማገልገል እንዳለብን አላወቅንም።
አንዳንዴ የምናወጣቸው ግቦች ይኖራሉ።
ሆኖም እነዚህ ግቦች ላይ ባለመድረሳችን
ወይም ባሰብነው ጊዜ ባለማሳካታችን እናዝን ይሆናል።
ታዲያ ምን አደረጋችሁ?
በጉዳዩ ላይ ጸለይን።
ከዚያም ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት
ወደ ታይላንድ ተዘዋውረን የማገልገል አጋጣሚ አገኘን።
ይህ አጋጣሚ እንዴት አገኛችሁ?
እህቴና ባለቤቷ በዚሁ የአገልግሎት ዘርፍ
በታይላንድ ያገለግሉ ነበር።
ስለዚህ እንድንሞክረው አበረታቱን።
በምንኖርበት በማንችስተር አቅራቢያ
በታይ ቋንቋ የሚመራ አንድ ቡድን ነበር።
ይህ ደግሞ ታይላንድ ሄዶ ማገልገል ቀላል እንዲሆንልን አድርጓል።
ታዲያ እንዴት ነበር?
በጣም አስደሳች ነው።
ሆኖም በየስድስት ወሩ ወደ ብሪታንያ እየተመለስን
ሥራ መሥራት ነበረብን።
ስለዚህ ያገኘናቸውን ተመላልሶዎችና ጥናቶች ማስረከብ ነበረብን።
እንደገና ወደ ታይላንድ ስንመለስ
ሁሉን ነገር እንደ አዲስ መጀመር አለብን።
‘አንድ ቀን በብሪታንያ ቤቴል ውስጥ
እናገለግላለን’ የሚለው ግባችን ግን
ከልባችን አልጠፋም።
‘በታይላንድ ማገልገላችንን እንቀጥል?
ወይስ ወደ እንግሊዝ ተመልሰን
በዘወትር አቅኚነት እናገልግል?’ የሚለውን መወሰን ነበረብን።
ያም ቢሆን ግን የብሪታንያ ቤቴል እንድትመጡበት አልፈለገም።
ታዲያ ምን ወሰናችሁ?
በደንብ ከጸለይንበት በኋላ ታይላንድ ለመሄድ ወሰንን።
ይህን ውሳኔ እንድታደርጉ ምን ረዳችሁ?
ያሉንን አማራጮች ካወዳደርንን በኋላ ታይላድን ለመሄድ ወሰንን።
በታይላንድ ብዙ መሥራት እንድምንችል ተገነዘብን።
ስለዚህ በኛ ፍላጎት ላይ ከማተኮር ይልቅ
ወደ ታይላንድ ለመሄድ ወሰንን።
የሚያስፈራንን ነገር ለማድረግ ቆርጠን ነበር።
ግን የሚያስፈራችሁን ነገር ለማድረግ
ምክንያት የሆናችሁ ምንድን ነው?
ያስፈራን ነገር፣ ከለመድነው ቦታ ርቆ መሄድ ነው።
ይህንን ለማድረግ መወሰናችን ደግሞ
ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ እንድንታመን አድርጎናል።
ይህንን ውሳኔ በማድረጋችን ይበልጥ ወደ ይሖዋ መቅረብ ችለናል።
አሁን ይበልጥ ግልጽ ሆነልን።
ቢያስፈራችሁም አድርጋችሁታል።
ታዲያ በታይላንድ ማገልገል እንዴት ነው?
በታይላንድ ማገልገል በጣም ደስ ይላል።
እዚህ ፎቶ ላይ የምታየው እኔና ጁሊያ
ባንኮክ ውስጥ ወደ አገልግሎት ስንሄድ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ።
በታይላንድ የሚገኙ የሚገኙ አብዛኞቹ ሰዎች
የቡድሃ እምነት ተከታይ ናቸው።
ሆኖም የሚማርካቸው ነገር ለማግኘት ይፈልጋሉ።
በተለይ ወጣቶች አዲስ ነገር ለማወቅ እንዲሁም
ትኩረታቸውን የሚስብ ነገር ለማግኘት ይሞክራሉ።
ይህ ደግሞ እውነትን እንዲያውቁ በር ይከፍትላቸዋል።
እንዲያውም ይህን የሚያሳይ ቪዲዮ አምጥተናል።
ታዲያ ለምን አናየውም?
ወደ ታይላንድ እንኳን ደህና መጣችሁ!
ታይላንድ በሕብረ ቀለማት ያሸበረቀች፣
በየመንገዱ ጣፋጭ ምግብ የማይታጣባት፣
ፈገግታ የማይለያቸው ሕዝቦች ያሉባት አገር ናት።
እንግዶችን ተቀብሎ ማስተናገድ የሕይወታቸው ክፍል ነው።
ለቤተሰብና ለወዳጅነት ከፍ ያለ ቦታ ይሰጣሉ።
ሆኖም ከዚህም ያለፈ ትርጉም ያለው ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ።
የታይላንድ ሰዎች የሕይወትን ዓላማ በማወቅ
ዘላቂ ሰላም ማግኘት ይፈልጋሉ።
የናሮማንና የካኒታን ተሞክሮ
እንደ ምሳሌ ማንሳት እንችላለን።
እኔ ባደኩበት አካባቢ ጥሩ ምሳሌ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ
የሃይማኖት መሪዎች ነበሩ።
እነሱ ግን የሚያስተምሩትን ነገር አይሠሩበትም።
ልጅ እያለሁ ጥሩ ሰው ያልሆኑትን እነዚህን የሃይማኖት መሪዎች
‘ሰዎች ይህን ያክል የሚያከብሯቸው ለምንድን ነው?
ለምን ይፈሯቸዋል?’ ብዬ አስብ ነበር።
ሁሌም የሚሰጠኝ መልስ ግን ተመሳሳይ ነው፦
‘እሱ እኮ መሪያችን ነው።
ልናከብረውና ልንታዘዘው ይገባል’ ይሉኛል።
ይህ ግን ለእኔ ፈጽሞ የማይዋጥልኝ ነገር ነበር።
አባቴ አፍቃሪና ደግ ሰው ነበር።
የሚያሳዝነው ግን የአልኮል ሱስ ነበረበት።
በቡድሃ እምነት ትምህርት መሠረት
አንድ ሰው የአልኮል ሱስ ካለበትና
ብዙ የሚጠጣ ከሆነ ወደ ሲኦል ይገባል።
ይህ በጣም ያስፈራኝ ነበር።
ምክንያቱም አባቴ ሲኦል እንዲገባ አልፈልግም።
ስለዚህ ወደ ቤተ መቅደስ ሄጄ ‘አባቴ ሲኦል እንዳይገባ
ማድረግ የሚቻልበት መንገድ ይኖር ይሆን?’ ብዬ ጠየኩኝ።
‘ኃጢያት ስለማይደመሰስ
ምንም ማድረግ አይቻልም’ ብለው መለሱልኝ።
‘ጥሩ ተግባር፣ ለሠራነው መጥፎ ነገር ማካካሻ አይሆንም’ አሉኝ።
ለቤተ መቅደሱ ምጽዋት የምትሰጪ ከሆነ ግን
‘አባትሽ ወደ ሲኦል ሲገባ
ቅጣቱ ቀለል ይልለት ይሆናል’ አሉኝ።
ሆኖም ያገኘሁት ምላሽ ምንም አላረካኝም።
በዚህ ጊዜ ለጥያቄዬ መልስ ለማግኘት ፍለጋ ማድረግ ጀመርኩ።
ሌሎች ሃይማኖቶች ስለዚህ ጉዳይ
ምን እንደሚያስተምሩ ማወቅ ፈለግኩ።
ከልጅነቴ ጀምሮ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ
ምንም ጥያቄ እንዳላነሳ ይነገረኝ ነበር።
እንዲሁ እንዳምን ብቻ ይጠበቅብኝ ነበር።
እኔ ግን በምክንያት ላይ የተመሠረተ
አሳማኝ መልስ ማግኘት ፈልጌ ነበር።
ስለዚህ ሃይማኖትን ስለመቀየር ከሚወያዩ ሰዎች ጋር
በኢንተርኔት መገናኘት ጀመርኩ።
ብዙ ሰዎች ሃይማኖታቸውን መቀየር እንደሚፈልጉ ተገነዘብኩ።
አብሬያቸው ቤተ ክርስቲያን እንድሄድ የጋበዙኝም አሉ።
ለመሄድ ፍላጎቱ ቢኖረኝም ፍርሃት ግን ተሰማኝ።
ብዙም ሳይቆይ መጽሐፍ ቅዱስ አገኘሁ።
ለአንዳንድ ጥያቄዎቼ መልስ ይሰጠኝ ይሆናል ብዬ አሰብኩ።
ስለዚህ መጽሐፉን ተውሼ እቤት ሄጄ ማንበብ ፈለግኩ።
ሆኖም የሃይማኖት አስተማሪው
መጽሐፉን መግዛት እንጂ መዋስ እንደማልችል ነገረኝ።
ስለዚህ “ስንት ነው?” ብዬ ጠየኩት።
“31 ዶላር ነው” አለኝ።
ሆኖም ኢንተርኔት ላይ ብገባ
መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ ማግኘት እንደምችል አሰብኩ።
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ብዬ ኢንተርኔት ላይ ጻፍኩና
መጀመሪያ ላይ ያገኘሁትን ከፈትኩ።
ድረ ገጹ “መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ አጥና።”
“ነፃ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት” ይላል።
በኋላ ላይ ድረ ገጹ jw.org መሆኑን አወቅኩ።
‘ግን በእርግጥ ነፃ ነው?’ ብዬ አሰብኩ።
ይህ ጥርጥሬዬ እንዳለ ቢሆንም ለምን አልሞክረውም ብዬ አሰብኩ።
ከዚያ ድረ ገጹ ላይ ያለውን ፎርም ሞላሁ።
‘የማገኘው ሰው ነፃ እንዳልሆነ ከነገረኝ አቆማለሁ፣
ድጋሚም አላጋኛቸውም’ ብዬ አሰብኩ።
ከሁለት ቀን በኋላ አንዲት ሴት ደወለችልኝ።
“እርግጥ በነፃ ነው ምታስተምሩት?” ብዬ ደጋግሜ ጠየኳት።
እሷም “አዎ፣ መጽሐፍ ቅዱስን
የምናስተምረው በነፃ ነው” አለችኝ።
አንድ ቀን ከአለቃዬ ጋር ምግብ ለመብላት ወጣሁ።
ምግቡ ሲመጣ ጎንበስ ብላ ዓይኗን ጨፈነች።
ለምን እንደዛ እንዳደረገች አልገባኝም።
ምክንያቱን ለማወቅ ጓጓሁ።
ከጨረሰች በኋላ ለምን እንደዛ እንዳደረገች ጠየኳት።
አምላክን ለማመስገን እየጸለየች እንደነበር ነገረችኝ።
ክርስቲያን ስለሆነች አምላኳን ለማመስገን እየጸለየች ነበር።
እኔም “ሃይማኖቴን ለመቀየር እያሰብኩ ነው።
ምን ማድረግ እንዳለብኝ ትነግሪኛለሽ?” አልኳት።
እሷም መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንደምታስተምር ነገረችኝ።
ከዚያም “አንቺም ማጥናት ትፈልጊያለሽ?” አለችኝ።
“አዎ” አልኳት።
በ2019 አባቴ ሞተ።
በጣም ነበር ያዘንኩት።
ሆኖም እንደ በፊቱ ፍርሃት አልተሰማኝም።
ምክንያቱም ወደፊት መልሼ እንደማገኘው አውቃለሁ።
በትንሣኤ ወቅት አባቴ ከሞት ይነሳል።
እንደ በፊቱ ከእሱ ጋር ማውራት የምችልበት አጋጣሚ አገኛለሁ።
ለዘላለም በደስታ ኑር! ከተባለው መጽሐፍ ላይ
ምዕራፍ 27ን ሳጠና ልቤ በጣም ነው የተነካው።
አስጠኚዬ ኢየሱስ ‘እወዳችኋለሁ’ ከማለት ባለፈ
ራሱን ቤዛ አድርጎ በመስጠት እሱና ይሖዋ
ለእኛ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር በተግባር እንዳሳዩን አስገነዘበችኝ።
እኔም እነሱን ነው መከተል ምፈልገው አልኩኝ።
ምክንያቱም የራሳቸውን ጥቅም መሥዋዕት አድርገው ፍቅር ያሳያሉ።
እኛም እንደ ናሩማንና ካኒታ ያሉ ብዙ ሰዎች
እውነትን ሲቀበሉ የማየት አስደሳች አጋጣሚ አግኝተናል።
እውነትን የሚወዱ ሰዎችን የምንፈልገው ለዚህ ነው።
አንድ ሰው እውነትን ሲቀበል በሕይወቱ ላይ ለውጥ ያደርጋል።
እነዚህን እህቶች ታውቋቸዋላችሁ አይደል?
አዎ፣ እናውቃቸዋለን።
መጀመሪያ ወደ ታይላንድ በሄድንበት ወቅት
ናሩማን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነበረች።
አንድ ጉባኤ ነበርን።
ታይላንድን ለምን እንደወደዳችሁ አሁን ገባኝ።
እዚያ ስትሄዱ ቶሎ እንድትለምዱና
ምድባችሁን እንድትወዱት የረዷችሁ አሉ?
አዎ፣ ብዙ ወንድሞችና እህቶች ረድተውናል።
በተለይ ከጊልያድ የተመረቁ አንድ ባልና ሚስት
በጣም ረድተውናል።
ጠንክረን ማገልገል ቢኖርብን ሚዛናዊ እንድንሆን
እንዲሁም
የአገሪቱን ባሕል እንዴት መልመድ እንዳለብን አስተምረውናል።
ለምሳሌ ቤታችን አስደሳችና ምቹ እንዲሆን
እንዲሁም በቂ ዕረፍት በማድረግ
በቀጣዩ ቀን በአዲስ ጉልበት አገልግሎታችንን እንድንጀምር
ጥሩ ምክር ሰጥተውናል።
ደስ ይላል።
ራሳቸው ምሳሌ በበመሆን ተግባራዊ ምክር ሰጥተዋችኋል።
አንዲና ጁሊያ
ይሖዋን ይበልጥ ለማገልገል ፍላጎት እንዲያድርባችሁ
መጀመሪያ ላይ የረዷችሁ ሰዎች አሉ?
በዚህ ረገድ ትልቅ ድጋፍ ያደረጉልኝ ወላጆቼ ናቸው።
ሁለቱም ይሖዋን ይወዳሉ።
ደጎች ናቸው።
ወንድሞችና እህቶችም በልግስና ይረዳሉ።
በተለይ ወጣት እያለሁ ከአባቴ ጋር
በስብሰባ አዳራሽ ግንባታ ላይ አብረን እንካፈል ነበር።
አብረን በመሥራታችን ደስ ይለን ነበር።
አብረውኝ አንድ መሥሪያ ቤት ይሠሩ የነበሩ
ሁለት የጉባኤ ሽማግሌዎችም ረድተውኛል።
ከእነሱ ጋር በስብሰባ አዳራሽ ግንባታ እካፈል ነበር።
እነዚህ ነገሮች ለይሖዋ ያለኝን ፍቅር እንዳሳድግና
መንፈሳዊ ግቦችን እንዳወጣ ረድተውኛል።
አንተ ነህ አይደል?
አዎ፣ ከእናቴና ከአባቴ ጋር ሆኜ ነው።
በጣም ደስ ይላል።
ለእኔም ቢሆን በዋነኝነት ምሳሌ የሆኑኝ ወላጆቼ ናቸው።
እናቴ የተጠመቀችው ልጅ እያለሁ ነው።
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ደግሞ አባቴም ተጠመቀ።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ
ወጥ የሆነ መንፈሳዊ የአገልግሎት ልማድ አዳብረናል።
እርግጥ ይህን ማድረግ
ሰባት ልጆች ላሉበት ቤተሰብ ቀላል አልነበረም።
ሆኖም የፈለገው ቢመጣ ሁሌም አገልግሎት እንወጣለን።
እንሰበሰባለን።
እነዚህ ነገሮች ለድርድር አይቀርቡም።
ከትምህርት ቤት ስመለስ እናቴ የመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብላ
የግል ጥናቷን ስታደርግ አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል።
ጠዋት ላይ ስነሳ ደግሞ አባቴ መጠበቂያ ግንብ ሲያነብ አየው ነበር።
ይሖዋ ለእነሱ ምን ያህል እውን እንደሆነ ስለተረዳሁ
ሁለቱንም መምሰል እፈልግ ነበር።
ሁለቱም ፎቶዎች ላይ አንቺ ነሽ አይደል?
አዎ፣ የመጀመሪያው ከእናቴ ጋር
ሁለተኛው ደግሞ ከአባቴ ጋር የተነሳሁት ነው።
ተሞክሯችሁ በጣም ደስ የሚል ነው።
ተሞክሯችሁ ወላጆች፣ ሚስዮናውያን እንዲሁም ሌሎች ሰዎች
ወጣቶችን በማሠልጠን ረገድ
ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ አሳይቶናል።
ጊዜያቸውን ሰውተው እነሱን መርዳታቸው
ወጣቶች ይሖዋን ለማገልገል
ራሳቸውን እንዲያቀርቡ ያነሳሳቸዋል።
ይሖዋ የአንድን ሰው መንፈሳዊ ፍላጎት ለሟሟላት
በማናችንም ሰው ሊጠቀም እንደሚችል አይተናል።
ራሳችሁን በእነሱ ቦታ ማየት ችላችኋል?
የአንድን ሰው መንፈሳዊ ፍላጎት እንድታሟሉ
ይሖዋ እየተጠቀመባችሁ ያለው እንዴት ነው?
ለምሳሌ እናንተ ወላጆች ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲወዱትና
ምርጣቸውን እንዲሰጡት ሁሌ ስለምትረዷቸው እናመሰግናችኋለን።
የማያምን የትዳር ጓደኛ ያላችሁም በዚህ ረገድ ሊሳካላችሁ ይችላል።
በጉባኤ ያላችሁ የተሾማችሁ ወንዶች፣
ሚስዮናውያን፣ አቅኚዎች፣ አረጋውያን
እነዚህን ውድ ወጣቶች በመቅረጽ ረገድ
ሁላችሁም ድርሻ አላችሁ።
ሁላችንም ብንሆን
ወጣቶች ምርጣቸውን ለይሖዋ እንዲሰጡ
መርዳት እንችላለን።
እነሱም በተራቸው ሌሎችን መርዳት ይችላሉ።
በእነዚህ ተሞክሮዎች እንደተደሰታችሁ ተስፋ እናደርጋለን።
በቀጣዩ ፕሮግራም እስከምንገናኝ ሁላችሁም ደህና ሁኑ!
እሺ፣ ወንድም ክላርክንና በቃለ መጠይቁ ላይ የተካፈሉትን ሁሉ እናመሰግናለን።
እውነትን መስማት የሚፈልጉ በርካታ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ማየታችን
የአገልግሎት ቅንዓታችን እንዲቀጣጠል አድርጓል።
የእናንተን ባላውቅም፣ እኔ ግን ወደ ሚስዮናዊ አገልግሎቴ ሂድ ሂድ ነው ያለኝ።
ለማንኛውም፣ አዎ፣ መምረጥ እንደው አንችልም።
እሺ፣ በዚህ ፕሮግራም የመክፈቻ ንግግር ላይ
በአብርሃምና በሎጥ መካከል ስለተከሰተ ሁኔታ ስናወራ
ስለ ሎጥ ምን ተሰማችሁ?
ሎጥን እንዴት ሳላችሁት?
‘መጥፎ ሰው ነው’ አላችሁ?
ወይም ራስ ወዳድ ሰው እንደሆነ ተሰማችሁ?
አሁን፣ የበላይ አካል አባል የሆነው
ወንድም ዴቪድ ስፕሌን የሎጥን ታሪክ
ከሌላ አቅጣጫ ሊያብራራልን ተዘጋጅቷል።
ለንግግሩ የመረጠው ርዕስ
“የተሟላ መረጃ ሳይኖራችሁ መደምደሚያ ላይ አትድረሱ”
የሚል ነው።
ንግግሩን በትኩረት እናዳምጥ።
በጣም ይገርማል።
ጊዜው ይበራል።
እንደ እናንተ በጊልያድ ትምህርት ቤት ለመማር
ወደ ብሩክሊን ቤቴል ከመጣሁ
ከአንድ ወር በኋላ 60 ዓመት ይሞላኛል።
ያን አስደሳች ጊዜ አልረሳውም።
ከዚያ ከአምስት ወር በኋላ የምንመረቅበት ጊዜ ደረሰ።
ስለዚህ አሁን እየተሰማችሁ ያለውን ስሜት
እኔም ስላለፍኩበት እረዳችኋለሁ።
የዛሬዋ ዕለት ለእናንተ ለተመራቂዎች ልዩ ቀን ናት።
ለዚህ በመብቃታችሁ በጣም ደስ ብሎናል።
ብዙ ደክማችኋል።
ይሖዋም ጥረታችሁን ባርኮላችኋል።
ትምህርታችሁን በትጋት ስታጠኑ የቆያችሁት
ባገኛችሁ እውቀት ሰዎችን ለማስደመም ብላችሁ አይደለም።
ከዚህ ይልቅ ይበልጥ ወደ ይሖዋ ለመቅረብ፣
ይበልጥ ወደ ወንድሞቻችሁ ለመቅረብ ነው።
እኔም በዚህ ንግግሬ ላይ በዋነኝነት የማተኩረው
ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር ስላለን ግንኙነት ነው።
ሁላችንም እንደምናውቀው ይሖዋ አምላክ ስለ እኛ
እያንዳንዷን ነገር ጠንቅቆ ያውቃል።
የተሟላ መረጃ አለው።
ይህ ደግሞ በመጨረሻው ፍርድ ወቅት
የጽድቅ ፍርድ እንደሚያስተላልፍ
እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል።
ምክንያቱም ከይሖዋ እይታ የተሰወረ አንዳች ነገር የለም።
ይሖዋ ችላ ብሎ የሚያልፈው ወይም የሚረሳው ነገር አይኖርም።
ይሖዋ ፍርድ የሚያስተላልፈው
እያንዳንዱን እውነታ ከግምት አስገብቶ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ይሖዋ ለነብዩ ሳሙኤል
“ሰው የሚያየው ውጫዊ ገጽታን ነው” ብሎታል።
ደግሞም ማናችንም ብንሆን ስለ አንድ ሰው
በእሱ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለማስተላልፍ የሚያበቃ
ዝርዝር መረጃ ሊኖረን አይችልም።
ቅድም ጄክ በንግግሩ ላይ ሎጥን እንደ ምሳሌ አድርጎ ተጠቅሟል።
እኔም ሎጥን እንደ ምሳሌ እጠቀማለሁ።
አሁን የሚነሳው ጥያቄ፣
‘አንድ ሰው አንድን ነገር ያደረገበትን ዝንባሌ ከመጠራጠር ይልቅ
ጉዳዩን ጠለቅ ብሎ ስለማየት
የሎጥን ታሪክ በመመርመር ትምህርት እናገኛለን?’ የሚል ነው።
እንግዲህ እኔም ጄክም ስለ ሎጥ ካወራን
የተዘጋጀነው በጋራ ነው ማለት ነው።
መድረኩን በጋራ ነው የምንመራው።
እስቲ ጴጥሮስ ስለ ሎጥ ምን ብሎ እንደጻፈ እናንብብ።
መጽሐፍ ቅዱሳችሁን ሁለተኛ ጴጥሮስ ላይ አውጡ።
ሁለተኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ ሁለት።
አሁን የምናነበው ቁጥር 7 እና 8ን ነው።
ስለ ሎጥ የተሰጠውን መግለጫ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።
እስክታወጡ ልጠብቃችሁ።
ጣቶቻችሁ እንደ እኔ በአርትራይተስ ከተጎዱ
ጥቅሱን ፈልጎ ማውጣት ጥቂት ጊዜ ይወስድባችኋል።
ሁለተኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ 2 ቁጥር 7 እና 8
ይሖዋ ያደረገውን ነገር ሲናገር እንዲህ ይላል፦
“ሆኖም ለሕግ የማይገዙ ሰዎች
“በማንአለብኝነት በሚፈጽሙት ድርጊት
“እጅግ እየተሳቀቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን አድኖታል።
“ይህ ጻድቅ ሰው ዕለት ተዕለት በመካከላቸው ሲኖር
“በሚያየውና በሚሰማው መረን የለቀቀ ድርጊታቸው
ጻድቅ ነፍሱን ያስጨንቅ ነበር” ይለናል።
ቆይ ግን ሎጥን “ጻድቅ” ያለው ማን ነው?
ይሄ የሐዋርያው ጴጥሮስ የግል አመለካከት ነው?
በፍጹም!
ይህ ጴጥሮስ በመንፈስ መሪነት የጻፈው ሁለተኛው ደብዳቤው ነው።
ስለዚህ ጴጥሮስ ደብዳቤውን ሲጽፍ
ይህን መግለጫ እንዲያካትት ያነሳሳው መንፈስ ቅዱስ ነው።
ጴጥሮስ በመንፈስ ተመርቶ
ሎጥን አንዴ ብቻ ሳይሆን ሦስት ጊዜ
‘ጻድቅ ሰው’ ብሎ ጠርቶታል።
ቆይ ግን
መንፈስ ቅዱስን የተጠቀመው ማን ነው?
ይሖዋ አምላክ ነው!
ስለዚህ ሎጥ ሦስት ጊዜ ‘ጻድቅ ሰው ነው’ መባሉን ስናነብ
ይሖዋ ስለ ሎጥ ያለውን አመለካከት
እየነገረን እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብናል።
እውነታው ይሄ ነው።
ታዲያ እናንተስ ለሎጥ ያላችሁ አመለካከት እንደዚህ ነው?
ጻድቅ መሆኑ ይታያችኋል?
ወይስ በአብዛኛው የምታተኩሩት
‘ሠርቷቸዋል’ በሚባሉት ስህተቶች ላይ ነው?
ግን አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ሊያስብ ይችላል፦
‘ሎጥ እኮ አጎቱ አብርሃም
በከነዓን ምድር የሚኖርበትን ቦታ እንዲመርጥ አጋጣሚ ሲሰጠው
‘የተሻለውን ቦታ ለራሱ መርጧል።
‘ቅድሚያውን ለታላቁ ለአብርሃም መስጠት ነበረበት።
ይሄ እኮ ሎጥ ራስ ወዳድ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።’
የዘፍጥረት ዘገባ እያንዳንዱን ዝርዝር መረጃ እንዳልያዘ እናስታውስ።
አንድ ሰው ይህን ዘገባ ብቻ አንብቦ
እንዲህ ያለ መደምደሚያ ላይ ሊደርስ ይችላል።
ደግሞም አይፈረድበትም።
ግን በእርግጥ ሎጥ ራስ ወዳድ ሰው ነበር?
ወይስ ሎጥን በተመለከተ ያላገኘነው ሌላ መረጃ ይኖር ይሆን?
እንዲህ ያለውን መረጃ ማግኘታችን
ስለ ሎጥ ያለንን አመለካከት
በተወሰነ መጠንም ቢሆን ይቀየረው ይሆን?
እስቲ እንዲህ ብለን እናስብ፦
ሎጥ የአብርሃም የወንድሙ ልጅ ቢሆንም
በዕድሜ ከአብርሃም ሊበልጥ ይችላል።
እንዲያውም ሎጥ የብዙ ዓመት ታላቁ ሊሆን ይችላል።
አሁንስ አመለካከታችሁ ትንሽ ተለወጠ?
ቤቴላዊ ከሆናችሁ መለወጡ አይቀርም።
የአገልግሎት ዘመን ብልጫ!
እዚህ ቤቴል ውስጥ አንድ ክፍል ሲለቀቅ
‘ክፍሉን ማን ይውሰደው’ የሚለውን ለመወሰን
የምንከተለው አንድ መመሪያ አለን።
ዕጣ እንጣጣልም፤
ሳንቲም አናነዝርም፤
ወይም ደግሞ ቁጥር አንጠራም።
ወይም ትግል አንገጥምም።
ክፍሉ ይጫረታል።
ለጫረታ ብቁ የሆኑት ቤቴላውያን ክፍሎቹን እየዞሩ ይመለከታሉ።
አንድ ሰው የሚወደውን ክፍል ካገኘ
ያን ክፍል እንደወደደው ለቤቴል ቢሮ ያሳውቃል።
ግን አንዱን ክፍል ሁለት ቤቴላውያን ቢፈልጉትስ?
ክፍሉ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት
ረጅም ጊዜ ላሳለፈው ቤቴላዊ ይሰጣል።
በሌላ አባባል ክፍሉን ማን ይውሰደው የሚለውን የምንለየው
በጫረታ ነው።
ታዲያ ክፍሉን ያላገኘው ሰው
ያ ክፍል የተሰጠውን ቤቴላዊ እንዲህ ይለዋል?
‘አንተ ግን ራስ ወዳድ ነህ።
‘ክፍሉን እንደፈለግኩት ታውቃለህ።
ልትተውልኝ ይገባ ነበር!’
በፍጹም!
ብዙ ዓመት ያገለገለው ክፍሉን ያገኛል።
አሠራሩ እንዲህ ነው።
ቅድም እንዳልነው ሎጥ የአጎቱ የአብርሃም ታላቅ ሊሆን ይችላል።
እንዲያውም ወልዶ ሊያደርሰውም ይችላል።
ግን በእርግጠኝነት መናገር አንችልም።
ምክንያቱም የዘፍጥረት መጽሐፍ
እነዚህን መረጃዎች በግልጽ አይናገርም።
ስለዚህ አንዳንድ መረጃዎችን ጠለቅ ብለን እንመርምር።
አብርሃም ሁለት ወንድሞች አሉት።
ካራን እና ናኮር።
ከሦስቱ ወንድማማቾች ትንሹ
አብርሃም እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም።
እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?
ቆይ እስቲ ታራ አብርሃምን ሲወልድ
ስንት ዓመቱ ነበር?
የ60 ዓመት ሰው ነበር?
በፍጹም!
የ100 ዓመት ሰው ነበር?
አይ!
አብርሃም ሲወለድ አባቱ ታራ ዕድሜው
130 ዓመት አካባቢ ይሆን ነበር።
ይገርማል አይደል?
አብርሃም 100 ዓመት አካባቢ ሲጠጋው
‘ከአሁን በኋላ ልጅ መውለድ አልችልም’ ብሎ አስቦ ነበር።
ግን እኮ አባቱ እሱን የወለደው 130 ዓመት አካባቢ ሆኖት ነው።
ለማንኛው፣ ወንድሞቹ አብርሃምን በዕድሜ ይበልጡት ነበር።
ደግሞም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘውን መረጃ ስናሰላው፣
አብርሃም ሲወለድ የሁሉም ታላቅ ወንድም 60 ዓመቱ ነበር።
ስሌቱ ይህን ነው የሚያሳየው!
ታላቁ ልጅ የሎጥ አባት ይመስላል።
ምክንያቱም ከሁሉ ቀድሞ የሞተው እሱ ነው።
በዚያ ዘመን ወንዶች ልጅ የሚወልዱት
30 ዓመት አካባቢ ሲሆናቸው ነው።
ስለዚህ አብርሃም ሲወለድ የሎጥ አባት 60 ዓመቱ ከሆነ
በዚያ ወቅት ሎጥ ተወልዶ የመሆኑ አጋጣሚ በጣም ሰፊ ነው።
እንዲያውም ሎጥ በወቅቱ ወጣት
ወይም ትልቅ ሰው ሊሆን ይችላል።
ሁኔታው እንዲህ ከሆነ፣ አብርሃም የእሱ ታላቅ የሆነው ሎጥ
በተስፋይቱ ምድር የሚፈልገውን ቦታ እንዲመርጥ
ግብዣ እያቀረበለት ነበር ማለት ነው።
እናንተም ተጫርታችሁ አንድ ክፍል አግኝታችሁ ከሆነ
አብርሃም ይህን ማድረጉ ብዙም አያስደንቃችሁም።
ምናልባት በልባችሁ እንዲህ ብላችሁ እያሰባችሁ ይሆናል፦
‘ሎጥ የአብርሃም ታላቅ እንደሆነ ማስረጃ ልታቀርብ አትችልም።
ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ አይናገርም።’
የእኔም ነጥብ ይሄ ነው።
እናንተም ማስረጃ ማቅረብ አትችሉም።
የዚህ ንግግር ዓላማ
ሎጥ ታላቅ እንደሆነ ማስረጃ ማቅረብ አይደለም።
ሎጥ የተጠቀሰው እንደ ምሳሌ ነው።
የዚህ ንግግር ዓላማ በቂ ማስረጃ ካላገኘን
በሰዎች ላይ ከመፍረድ ይልቅ
ስለ እነሱ ቀና ቀናውን ማሰብ እንዳለብን ማስገንዘብ ነው።
ስለዚህ ጉዳይ የተሟላ መረጃ የለንም።
እሺ ይሄስ ይሁን፣
ግን እኮ ሎጥ ድንኳን ውስጥ መኖር የሚፈልግ ሰው አይደለም።
የተደላደለ ሕይወት መምራት ስለፈለገ ወደ ሰዶም ከተማ ገብቷል።
ታዲያ ይሄ ቁሳዊ ነገሮችን እንደሚወድ የሚያሳይ አይደለም?
ሊመስል ይችላል።
ግን አሁንም የተሟላ መረጃ አለን?
ወደ ሰዶም ከተማ እንዲገባ ያነሳሳውን
እውነተኛ ምክንያት እናውቃለን?
ይበልጥ የተመቻቸ ሕይወት መምራት ስለፈለገ ነው?
ወይስ የቤተሰቡ ደህንነት እንቅልፍ ነስቶት ነው
ወደ ከተማይቱ የገባው?
ሎጥ ታግቶ እንደሚያውቅ አትርሱ።
እስቲ እናንተ ራሳችሁ አስቡት።
ታግታችሁ የምታውቁ ከሆነ
ቤተሰባችሁ እንዲኖር የምትፈልጉት የት ነው።
ሜዳ ላይ?
ወይስ በግንብ የታጠረ ከተማ ውስጥ?
ዛሬም በርካታ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን
አደገኛ በሆኑ አካባቢዎች ይኖራሉ።
ግን እዚያ የሚኖሩት በትልልቅ ከተሞች ውስጥ
የተመቻቸ ሕይወት መምራት ፈልገው አይደለም።
ከዚህ ይልቅ ምርጫ ስለሌላቸው ነው።
ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለ ሎጥ
እኛ የምናውቃቸውን መረጃዎች በሙሉ ያውቃል።
ያም ቢሆን ‘ጻድቅ ሰው ነበር’ ብሎ ጽፏል።
ልብ በሉ፣ ራስ ወዳድ ወይም ቁሳዊ ነገር የሚወድ ሳይሆን
ጻድቅ ሰው ነው ያለው።
ሎጥ ጻድቅ የተባለው ከሰዶም ከወጣ በኋላ አይደለም።
ከዚህ ልቅ ከሰዶም ከተማ እንዲወጣ የተፈቀደለት
ጻድቅ ሰው ስለነበረ ነው።
ሎጥ ቀድሞውኑ በይሖዋ ዘንድ
እንደ ጽድቅ የሚቆጠር ሥራ አከናውኖ ነበር።
ምናልባት ሎጥ የተሻለውን ቦታ መውሰዱ
ራስ ወዳድነት ሊሆን ይችላል።
መኖሪያውን በሰዶም ማድረጉም
ቁሳዊ ነገር እንደሚወድ የሚያሳይ ይሆናል።
ሁኔታው እንደዛ ከሆነ ደግሞ
ሎጥ ይሖዋ ጻድቅ ሰው ብሎ እንዲጠራው የሚያስችል
ሌሎች በርካታ ነገሮችን አድርጓል ማለት ነው።
ሎጥ እኛ ዛሬ የማናውቃቸውን በርካታ መልካም ነገሮች አድርጓል።
ነጥቡ ምንድን ነው?
መደምደሚያ ላይ ከመድረሳችን በፊት
የተሟላ መረጃ ማግኘት አለብን።
አንዳንዴ ግን እነዚህ መረጃዎች ላይኖሩን ይችላሉ።
የተሟላ መረጃ ሳይኖረን አንድ መደምደሚያ ላይ መድረሳችን
የኋላኋላ ለኃፍረት ሊዳርገን ይችላል።
እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ
እንዲህ ያለ ሁኔታ አጋጥሟቸው ነበር።
ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና ግማሹ የምናሴ ነገድ
ለከብቶቻቸው የሚሆን የግጦሽ ቦታ ስላገኙ
ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ሰፈሩ።
ኢያሱ ምዕራፍ 22ን እናውጣና
ታሪኩን እናንብብ።
አሁንም እስክታወጡ እጠብቃችኋለሁ።
እሺ፣ ኢያሱ ምዕራፍ 22
ቁጥር 10 ላይ ያለውን እናነባለን።
ኢያሱ 22:10
“ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ
“በከነአን ምድር ወዳለው የዮርዳኖስ ክልል ሲደርሱ
በዮርዳኖስ አጠገብ ግዙፍ የሆነ አስደናቂ መሠዊያ ሠሩ።”
ሌሎቹ እስራኤላውያን በወንድሞቻቸው ላይ እምነት ከማሳደር ይልቅ
እነዚህ ሦስት ነገዶች ከሃዲ ሆኖዋል ብለው ደመደሙ።
እንዲያውም የጦርነት ነጋሪት ለመጎሰም ተዘጋጁ።
ግን መሠዊያውን ስለሠሩት ነገዶች ምን እናውቃለን?
እነዚህ ሰዎች እኮ ከሌሎች እስራኤላውያን ጋር ሆነው
የተስፋይቱን ምድር ለመቆጣጠር ሲዋጉ ነበር።
ይህን ያደረጉት ደግሞ
ሕይወታቸውንም ጭምር ለአደጋ አጋልጠው ነው።
ይህን እንዴት እናውቃለን?
በጦር ሜዳ ላይ ከፊት ለፊት እንዲሰለፉ ተመድበው ነበር።
በጦርነት ወቅት ሁሌም ቀድመው የሚወጡት እነዚህ ነገዶች ነበሩ።
በመሆኑም ጦርነት ሲጀመር የመጀመሪያ ዒላማ እነሱ ናቸው።
ደፋር ናቸው።
ታዲያ እንዲህ ያሉትን ሰዎች
ከሃዲ ናቸው ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው?
ግን ሌሎቹ እስራኤላውያን
በወንድሞቻቸው ላይ እምነት ከማሳደር ይልቅ
ምን እንዳሏቸው እዚሁ ምዕራፍ ላይ
ከቁጥር 16 እስከ 18 ላይ እናንብብ።
ከ16 እስከ 18
“መላው የይሖዋ ጉባኤ እንዲህ ይላል፦
“‘በእስራኤል አምላክ ላይ
“‘እንዲህ ያለ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት
የፈጸማችሁት ለምንድን ነው?
“‘ለራሳችሁ መሠዊያ በመሥራትና በይሖዋ ላይ በማመፅ
“‘ይኸው ዛሬ ይሖዋን ከመከተል ዞር ብላችኋል።
“‘በፌጎር የሠራነው ስህተት አንሶ ነው?
“‘ምንም እንኳ ያኔ በይሖዋ ጉባኤ ላይ መቅሰፍት ቢወርድም
“‘ይኸው እስከ ዛሬ ድረስ ከዚህ ነገር ራሳችንን አላነጻንም።
“‘እናንተ ደግሞ ዛሬ ይሖዋን ከመከተል ዞር ትላላችሁ!
“‘ዛሬ እናንተ በይሖዋ ላይ ብታምፁ
ነገ ደግሞ እሱ በመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ላይ ይቆጣል።’”
የተናገሩት ይሄን ብቻ አይደለም።
ሌላ ብዙ ነገር ብለዋል!
ከዚያ የአሥሩ ነገድ ተወካዮች ንግግራቸውን ትንሽ ገታ ሲያደርጉ
የሁለት ተኩሉ ነገድ ሽማግሌዎች
መሠዊያውን የሠሩት ለአምልኮ እንዳልሆነ ተናገሩ።
መሠዊያው የተሠራው
ከዮርዳኖስ ማዶ ያሉት ሁለት ተኩል ነገዶችም
ልክ እንደ እነሱ ይሖዋን እንደሚያመልኩ
አሥሩን ነገድ ለማስታወስ ነበር።
ሊቀ ካህናቱና የእስራኤል ሽማግሌዎች
ትክክለኛ መረጃ ሳይኖራቸው
ሊያደርጉት በነበረው ነገር
ምን ያህል አፍረው ሊሆን እንደሚችል አስቡት።
መግቢያችን ላይ ይሖዋ ስለ እኛ
እያንዳንዱ ነገር እንደሚያውቅ ተነጋግረን ነበር።
በተመሳሳይ እኛም
ስለ ወንድሞቻችን ይበልጥ ባወቅን መጠን
ለምሳሌ፣ ስለ አስተዳደጋቸው
ወይም ስላጋጠሟቸው ችግሮች ይበልጥ ስናውቅ
በእነሱ ላይ ከመፍረድ እንቆጠባለን።
ዛሬ ያሉበት ቦታ ላይ ለመድረስ
ምን ያህል አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳሳለፉ ስናውቅ
ለእነሱ ያለን ፍቅር ይጨምራል።
እባካችሁ በቤተሰባችሁ ውስጥ ያሉትን ምርጥ ሰዎች
እውቅ አትንሷቸው።
አንዳንዴ ከአንድ ሰው ጋር አለመግባት ሊያጋጥመን ይችላል።
ግን ስላሳለፈው ሕይወት በሚገባ ካወቅን
ለምሳሌ እውነት ቤት ዘመድ እንደሌለው ወይም
ከዚህ ቀደም ሥነ ምግባር የጎደለው
ሕይወት ይመራ እንደነበር ስናውቅ
ከፍ አድርገን እናየዋለን።
ይሖዋ ይህን ሰው ይወደዋል።
ስለዚህ አንድ ሰው ትንሽ ካበሳጨን
እንዲህ ብለን ማሰባችን ጥሩ ነው፦
‘ይሖዋ ይህን ግለሰብ ጻድቅ ሰው ነው ብሎታል?’
‘ጻድቅ ሰው ነው፣ ጻድቅ ሰው ናት’ ብሏል?
እኛን እኮ አበሳጭተውን ይሆናል።
በይሖዋ ዓይን ግን ጻድቅ ተብለው ሊሆን ይችላል።
‘ታዲያ አሁን ባጋጠመኝ ትንሽ ችግር ላይ ብቻ ማተኮሬ
የተማሟላው ምሥል እንዳይታየኝ አግዶኝ ይሆን?’
አንድ ቤቴል ውስጥ አንድ ወጣት ወንድም
ረጅም ጊዜ በሚወሰድ ፕሮጀክት ላይ
ከአንዲት በዕድሜ የገፋች እህት ጋር
አብሮ እንዲሠራ ተመደበ።
ይህች እህትም ሆነች ባለቤቷ ቅቡዕ ናቸው።
ባለቤቷ፣ የእሱ ዓይነት ጥሩ ሰው በዚህ ምድር ላይ አይገኝም።
እሷስ?
እ . . . ታማኝ እህታችን ናት
አንፍረድባት ብዬ ነው።
ግን አንድን ሥራ እሷ በምትፈልገው መንገድ ካልሠራችሁ
መፈጠራችሁን ነው የምትጠሉት።
እንደሚመስለኝ ራሷን የምትቆጥረው
የሁሉም ሰው አያት እንደሆነች አድርጋ ነው።
ያ ወጣት ወንድም የነበረውን ብስለት ግን በጣም ነው የማደንቀው።
በዚህች እህት ተበሳጭቶ፣
‘እንዴ፣ አንድን ወንድም እንዲህ እንድትናገር
መብት የሰጣት ማን ነው?’ ከማለት ይልቅ
እሷንና ባሏን አንድ ምሽት ቤቱ ጋበዛቸው።
ሲጨዋወቱም በእገዳው ወቅት በታማኝነት እንደጸኑ ተገነዘበ።
በመሆኑም ለእህት ያለው አመለካከት
በተወሰነ መጠንም ቢሆን ተቀየረ።
እሷም ለሱ ያላት አመለካከት
ተቀይሮ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።
ስለዚህ ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ ሲያበሳጯችሁ
ስለ እነሱ ይበልጥ ለማወቅ ጥረት አድርጉ።
አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ።
አብራችሁ አገልግሉ።
ቡና ጋብዟቸው።
ስታውቋቸው ትወዷቸዋላችሁ።
እንግዲህ ሰሞኑን አንድ ሰው ቡና ልጋብዛችሁ ካላችሁ . . .
አንዳንድ ሰው ዓይናፋር
ወይም ደግሞ ፊቱ የማይፈታ ሰው ሊሆን ይችላል።
ከስንት አንዴ ይሆናል ፈገግ የሚለው።
ስለዚህ ጨካኝ፣ ኩራተኛ፣ ሰው ጤፉ ሊመስለን ይችላል።
እንደዚህ ላይሆን ግን ይችላል።
ምን ያድርግ?
በቃ፣ ፈጣሪ የሰጠው ፊት ይሄ ነው።
በጤና ወይም በሌላ ከባድ ችግር የተነሳ
አንድ ሰው የእኛን ያህል መሥራት አይችል ይሆናል።
ግን ስላለበት የጤና እክል አይናገርም።
ስለዚህ እኛ ሰነፍ ነው ብለን እናስባለን።
በይሖዋ ዓይን ግን ምርጡን እየሰጠ ሊሆን ይችላል።
በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው
እኛ ከምናደርገው የበለጠ እያከናወነ ይሆናል።
ታዲያ ‘ልታይ ልታይ ብሎ
እኛን እያሳጣን ነው’ ብለን መደምደም ይኖርብናል?
ያደገበት፣ የሠለጠነበት መንገድ ይሄ ይሆናል።
ምርጡን መስጠት የሚችለው
በዚህ መንገድ እንደሆነ ተሰምቶት ይሆናል።
በወረዳ ሥራ ላይ እያለን
በምጎበኘው ጉባኤ ውስጥ ስላለች አንዲት እህት
ብዙ አሉታዊ ነገር ሲወራ ሰማሁ።
አንዳንዶች እንዲህ ይሉ ነበር፦
‘ታምሜያለሁ ብላ ታስወራለች።
‘ገበያ ሄዳ ዕቃ ስትገዛ ግን አይቻታለሁ።
‘ስብሰባ ለመሄድ አቅሜ አይፈቅድም ብትልም፣
ገበያ ወጥታ ስንት ነገር ስትገዛ አይተናታል።’
ቤቷ ሄጄ ስጎበኛት እንኳን መጣሁ ነው ያልኩት።
የሚገርመው እህት አቅም የሚያሳጣ በሽታ አለባት።
በሽታው ቀን ከሌት ነው የሚያሠቃያት።
ግን አልፎ አልፎ በሽታው ቀለል ይልላታል።
ያኔ አጋጣሚውን ተጠቅማ ወደ ገበያ ሄዳ ዕቃዎች ትገዛለች።
የምትኖረው ብቻዋን ነው።
የሚረዳት ሰው የላትም።
ሥቃዩ ሲጀምራት ግን በቃ፣ ሁሌም አልጋ ላይ ናት።
መነሳት አትችልም።
ይችን እህት ከመንቀፍ ይልቅ
ቀረብ ብሎ መርዳት ምንኛ የተሻለ ነበር!
ቅድም እንዳልኩት የዚህ ንግግር ዓላማ
ስለ ሎጥ ወይም ስለ ሌላ ሰው
አዲስ ግንዛቤ ማስጨበጥ አይደለም።
ዓላማው የተሟላ መረጃ ያለው
ይሖዋ ብቻ እንደሆነ እንድናስታውስ መርዳት ነው።
ይሖዋ ወንድሞቻችንን ይወዳቸዋል።
እኛም እንድንወዳቸው ይፈልጋል።
ስለ ወንድሞቻችን ቀና ቀናውን ስናስብ ይደሰታል።
ከወንድሞቻችሁ ጋር እጅ ለጅ ተያይዛችሁ ስታገለግሉ
ይህን እንደምታደርጉ እንተማመናለን።
ሁላችሁንም በጣም እንደምንወዳችሁ አትርሱ።
ይሖዋ በታማኝነት ስታገለግሉት
አትረፍርፎ እንዲባርካችሁ እንመኛለን።
እሺ፣ ተማሪዎቹ የት እንደተመደቡ ማወቅ ትፈልጋላችሁ?
ምን ጥያቄ አለው?
ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቀው ነው።
እዚህ ጋር ደግሞ ዲፕሎማ በመስጠት ሊያግዘን ወንድም ከርዛን ቆሟል።
ጥሩ!
ለጊልያድ ተመራቂዎቹ ዲፕሎማቸውን በመስጠት ረገድ የሚያግዘን እሱ ነው።
መጀመሪያ የምጠራው ወንድም ኧርቪን ነው።
ወንድም ኧርቪ አጀቫን ወደ ምዕራብ አፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ዶሪን እና እህት ጆርጂያና ወደ ሩማኒያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም አንዲ እና እህት ጁልያ በዛምቢያ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።
ወንድም ላሻ አርሲ አሽዌላ ወደ ጆርጂያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ከርት እና እህት አማንዳ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ባፕቲስታ እና እህት ሲልቫና ወደ ሞዛምቢክ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ብራንደን እና እህት ሮዝመሪ በፖርቱጋል ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።
ወንድም ጄሰን እና እህት ክርስቲ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም አንትሮን እና እህት ሬቤካ በዛምቢያ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።
ወንድም ጆናታን ካሊሞር በምዕራብ አፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግል ተመድቧል።
ወንድም ቶማስ ፊጋሊ ወደ ቼክ ስሎቫክ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ታኮያ ፉጂታ ወደ ጃፓን ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ኤቫን እና እህት ስሌን በሩዋንዳ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።
ወንድም ዮናስ እና እህት ሄለን ወደ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ጆናታን እና እህት ሊዲያ ወደ ስፔን ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ጄሮ እና እህት ጁሊን ወደ ምዕራብ አፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ጄሲ እና እህት ክርስቲን በናይጄርያ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።
ወንድም አንድሬ እና እህት ሳሊና ወደ ስካንዲኔቪያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ኪኒ እና እህት ኢምሪ ወደ ፊጂ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ብሩኖ እና እህት ዴኒስ በስፔን ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።
እህት ጃሁዋይ ሊን ወደ ታይዋን ቅርንጫፍ ቢሮ ትመለሳለች።
ወንድም አንድሬ ሎፔዝ በደቡብ አፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግል ተመድቧል።
ወንድም ባሪ ማክዶናልድ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ኤዳን እና እህት ሻንቴል ወደ አውስትራሌዥያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ክሪስ ሙታሂ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ሴባስቲያን ኔልሰን ወደ ስካንዲኔቪያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ሚካኤልና እህት ኦሉዋቶዬ ወደ ናይጄርያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳሉ።
ወንድም ሁዋን ፕሮቶ ወደ ኮሎምቢያ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
እህት ኢቫና ሻኬዝ ወደ ክሮኤሽያ ቅርንጫፍ ቢሮ ትመለሳለች።
ወንድም ክርስቲያን እና እህት ቫለንቲና በሩዋንዳ ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።
ወንድም ዳክ ቴራል ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ሉካስ ቬትዬከስ ወደ ፊንላንድ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ጆን ዩን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
ወንድም ሪሌ ዛብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ይመለሳል።
እሺ
ተማሪዎቹን አንድ ላይ ማየት ትፈልጋላችሁ?
መጋረጃው ይገለጥ!
በጣም ደስ ብሎናል!
በጣም ነው የኮራንባችሁ!
ትምህርት ላይ እያላችሁ በትጋት ስታጠኑ ነበር።
ለዛሬዋ ቀን የበቃችሁት ይህን በማድረጋችሁ ነው።
ይሖዋ እንደባረካችሁ በማየታችን ተደስተናል።
አሁን ደግሞ የተማሪዎች ደብዳቤ ይነበብልናል።
ደብዳቤውን የሚያነብልን ከአውስትራሌዥያ ቅርንጫፍ ቢሮ የመጣው ወንድም ኤዳን ማሪ ነው።
ውድ የበላይ አካል ወንድሞች፣
ላገኘነው በጊልያድ ትምህርት ቤት የመማር ልዩ መብት
ያለንን ጥልቅ አድናቆትና አመስጋኝነት መግለጽ እንፈልጋለን።
እናንተም ሆናችሁ የቤቴል ቤተሰብ ከመጣንበት ቀን ጀምሮ
ፍቅራዊ እንክብካቤ አድርጋችሁልናል።
ይህም ገና ከመጀመሪያው ወደፊት ለምንማራቸው ነገሮች ጉጉት አሳድሮብናል።
ውድ ጊዜያችሁን ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን።
የሰጣችሁን ትምህርት፣ የረዳቶቻችሁና የውድ አስተማሪዎቻችን ጥረትና
የቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች ክፍል የሰጠን ድጋፍ ልባችንን በጥልቅ ነክቶታል።
ታላቁንም አስተማሪያችንን እንድናይ አድርጎናል።
የትምህርት ቤት ቆይታችን የይሖዋን እንክብካቤና ያሳየንን ታላቅ ፍቅር
ይበልጥ እንድናስተውልና አድናቆታችን ከፍ እንዲል አድርጓል።
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ኃጢአት ከሠሩበት ጊዜ ጀምሮ
ይሖዋ የሰው ዘር ከእሱ ጋር እንዲታረቅ ከማድረግ ወደኋላ አላለም።
ይሖዋ በኤደን ስለሰጠው ተስፋ፣ ከአብርሃምና ከዳዊት ጋር ስለገባቸው ቃል ኪዳኖች
እንዲሁም የሙሴ ሕግ ስላሉት አስደናቂ ገጽታዎች
በተለይ ስለ ስርየት ቀን ማሰላሰላችን ለቤዛው ያለንን አድናቆት ከፍ አድርጎታል።
ስለ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ማጥናታችንና
ፍጹም የአባቱ ነጸብራቅ መሆኑን መማራችን
ይሖዋ እንደሚወደን ይበልጥ እንድንተማመን አድርጎናል።
በተለይ ሐዋርያቱን በትዕግሥት የያዘበት መንገድ፣
ለሴቶች ያሳየው አክብሮትና ደግነት
እንዲሁም ተሠቃይቶ በመከራ እንጨት ላይ እስከመሞት ድረስ ያሳየን ፍቅር
ልባችንን በጥልቅ ነክቶታል።
እውነትም እንደ ኢየሱስ ያለ ንጉሥና ሩኅሩኅ ሊቀ ካህናት ስላለን እጅግ አመስጋኞች ነን።
የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ፍጻሜ መመርመራችን ተስፋችንን አጠናክሮልናል።
የወደፊቱንም ጊዜ በድፍረት እንድንጠብቅ አድርጎናል።
ለምሳሌ፣ ዘካርያስ በራእይ ወደ አራቱም የምድር አቅጣጫዎች ስለሚወጡት አራት ሠረገሎችና
የይሖዋ መንፈስ በሰሜን ምድር ላይ እንዳረፈ አይቷል።
ራእዩ የይሖዋ ኃያላን መላእክት
ጥንትም ሆነ ዛሬ ሕዝቡን የሚጠብቁ ሠራዊት እንደሆኑ
ያለንን እምነት አጠናክሮልናል።
የዓለም ሁኔታ እየተባባሰ ቢሄድም
አብሮን የመላእክት ሠራዊት እንዳለ ማወቃችን
ዛሬም ሆነ በታላቁ መከራ ወቅት
ከይሖዋ ሉዓላዊነት ጎን በልበ ሙሉነት እንድንቆም ያደርገናል።
ክፍል ውስጥ ሰዎችን ውደዱ ከተባለው ብሮሹር ያገኘናቸው ተግባራዊ ትምህርቶች
ቅንዓታችንን አቀጣጥለውልናል።
የቀረቡልን ሠርቶ ማሳያዎች
በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ለመስበክ የሚያስፈልጉንን ግሩም ባሕርያት እንድናስተውል ረድተውናል።
አዝመራው ስለነጣ የመንግሥቱን ምሥራች ስንሰብክ
ከበፊቱ የበለጥ ፍቅር፣ ግለትና የጥድፊያ ስሜት እንዲኖረን አነሳስቶናል።
ላለፉት አምስት ወራት ከታላቁ አስተማሪያችን ያገኘናቸውን ትምህርቶች
በሙሉ ልብ ተግባራዊ ለማድረግ ቆርጠናል።
ቁርጥ ውሳኔያችን ከእናንተም ጋር ሆነ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ውድ ወንድሞቻችን ጋር
እጅ ለእጅ ተያይዘን ስናገለግል
የጉባኤውን ራስ ኢየሱስን በመምሰል ለሰማዩ አባታችን ለይሖዋ
ክብርና ውዳሴ ማምጣት ነው።
የ159ኛው ክፍል የጊልያድ ተማሪዎች።
እስቲ አሁን ጥቂት የማጠቃለያ ሐሳብ እናካፍላችሁ።
ቅድም እንዲህ የሚል ጥያቄ አንስተን ነበር፦
ሎጥ ባደረገው ምርጫ የተነሳ ጉዳት ሲደርስበት
አብርሃም ምን ተሰማው?
በራሱ ምርጫ የደረሰበትን ሲያይ ምን ተሰማው?
ይህ ወደ ሦስተኛው ፍርሃት ይወስደናል።
ሰላም እንዳንፈጥር እንቅፋት የሚሆንብን ሌላኛው ምክንያት
የደረሰብንን በደል መርሳት አለመፈለጋችን ነው።
መርሳት አለመፈለግ
እንደምናስታውሰው፣ ሎጥ በሰዶምና በገሞራ አካባቢ ያለውን ቦታ መርጦ ከሄደ በኋላ
ብዙም ሳይቆይ እሱና ቤተሰቡ ተማርከው ነበር።
እርስ በርሳቸው በሚዋጉ ነገሥታት።
ቆይ ግን፣ አብርሃም እስከዚያ ጊዜ ድረስ ቂም ይዞ ቢቆይ ኖሮ
በሎጥ ላይ የደረሰውን ሲሰማ ምን የሚል ይመስላችኋል?
‘አዎ!
‘አሁን የእጁን አገኘ!
እዚያ ምን ሊያጋጥመው እንደሚችል አስቀድሞ ማሰብ ነበረበት።’
ግን አብርሃም ምን አደረገ?
እስቲ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን
ዘፍጥረት ምዕራፍ 14 ላይ አውጡ።
ዘፍጥረት ምዕራፍ 14
አብርሃም ሎጥ ያደረሰበትን በደል መርሳት
የተፈጸመበትን በደል አቅልሎ እንደማየት አልፎ ተርፎም
ይህን በደል በድጋሚ ለመፈጸም የልብ ልብ ይሰጠዋል ብሎ ሊሰጋ ይችል ነበር።
ግን ምን እንዳደረገ ዘፍጥረት 14:14 ላይ እንመልከት።
ቁጥር 14 የሚናገረው አብርሃም በሎጥ ላይ የደረሰውን ሲሰማ ያደረገውን ነገር ነው።
እንዲህ ይላል፦
“በዚህ መንገድ አብራም ዘመዱ በምርኮ መወሰዱን ሰማ።
ስለሆነም በቤቱ የተወለዱትን 318 የሠለጠኑ አገልጋዮች ሰብስቦ ተነሳ፤
ወራሪዎቹንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።”
አብርሃም ያደረገው ይህንን ነው።
ከማምሬ እስከ ዳን ያለው ርቀት 200 ኪሎ ሜትር ገደማ እንደሆነ እናውቃለን።
ስለዚህ ጉዞው ብዙ ቀን ሊፈጅ ይችላል።
ይህ ብቻ ግን አይደለም።
ወጪ እንደሚያስወጣው፣ ለአደጋ እንደሚያጋልጠው ግልጽ ነው።
ቀላል ባይሆንም ይህን ሁሉ አድርጓል።
ትንሽ ቆየት ብሎም ከቁጥር 21 እስከ 23 ላይ እንደምናነበው ደግሞ
አብርሃም ሎጥን ለመታደግ ባደረገው ጥረት የደረሰበትን ኪሳራ መሸፈን የሚችልበት አጋጣሚ አግኝቶ ነበር።
ግን አብርሃም ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም።
ሎጥን ለማዳን የተነሳሳው ጥቅም ፈልጎ አይደለም።
ሎጥን ለመርዳት የተነሳሳው ትሑት ስለሆነ ነው።
ሎጥ ያደረገው ውሳኔ ሊያጣላቸው ይችል ነበር።
ግን አብርሃም በዚህ ምክንያት ችግር ሲደርስበት እንኳ ረድቶታል።
አብርሃም ትኩረት ያደረገው ሰላም መፍጠር ላይ ነው።
ይሄን ለማድረግ ቆርጦ ነበር።
ታዲያ አብርሃም ከተወው ምሳሌ የምናገኘው ትምህርት ምንድን ነው?
እናንተ ባታምኑበትም በሌሎች ሐሳብ ተስማምታችሁ ታውቃላችሁ?
ለብዙሃኑ ስትሉ ከተስማማችሁ በኋላ እነሱ ያሰቡት ነገር ሳይሳካ ሲቀር ምን ትላላችሁ?
በዚህ ጊዜ “ድሮም እኮ ነግሬያችሁ ነበር” ለማለት ትፈተኑ ይሆን?
ወይም ደግሞ በዚህ ውሳኔ ውስጥ የእናንተ እጅ እንደሌለበት በሆነ መንገድ ለማሳየት ትሞክሩ ይሆን?
ፈገግ አላችሁ አይደል?
ግን ያጋጥማል!
ቂም ይዛችሁ ላለመቆየት ጥረት አድርጉ።
እንደ አብርሃም ሁኑ።
ባትስማሙበትም እንኳ የተደረገውን ውሳኔ ለመደገፍ ጥረት አድርጉ።
የተፈለገውን ውጤት ካላስገኘ ደግሞ የአብርሃምን ምሳሌ ተከተሉ።
ልክ እንደ አብርሃም በትሕትና የመፍትሔው አካል ለመሆን ጥረት አድርጉ።
ለተፈጠረው አስቸጋሪ ሁኔታ ሌሎች ላይ ጣት ከመቀሰር ተቆጠቡ።
ለምን?
ምክንያቱም እንዲህ ማድረግ ሰላም ያሰፍናል።
ከሰዎች ጋር ሰላም ሲኖረን ከአምላክ ጋር ሰላም ይኖረናል።
ከዚህ ይበልጥ የምንፈልገው ምንም ነገር የለም።
ታዲያ እስካሁን ካደረግነው ውይይት ምን ትምህርት አገኘን?
ከአብርሃም ብዙ ትምህርት አግኝተናል።
አብርሃም ሰላም ፈጣሪ ሰው ነው።
ደካማ መስዬ እታያለሁ ብሎ አልፈራም፤
ሌሎች መጠቀሚያ ያደርጉኛል ብሎ አልፈራም፤
ወይም ደግሞ ‘የደረሰብኝን በደልማ አልረሳም’ አላለም።
ታዲያ አብርሃም እንዲህ ያለ ሰው መሆኑ ጎድቶታል?
አብርሃም ሰላም ፈጣሪ ለመሆን ያደረገውን ጥረት ሎጥ ከጊዜ በኋላ ተገንዝቦ ይሆን?
ይህን በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም።
ወንድም ስፕሌን ቅድም እንዳብራራው መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ አይናገርም።
ግን ይሄ ምንም ለውጥ አያመጣም።
አብርሃም ይህን ሁሉ ያደረገው ከሎጥ ምስጋና ለማግኘት ብሎ አይደለም።
ታዲያ ለምንድን ነው?
በጣም የሚያስገርመው በእነዚህ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ላይ ከተከሰተው ነገር በኋላ
ማለትም አብርሃም ከሎጥ ጋር ሰላም ለመፍጠር ጥረት ባደረገባቸው በሁለቱም ጊዜያት
ይሖዋ አምላክ ለአብርሃም ለየት ያለ ነገር አድርጎለታል።
ምንድን ነው ያደረገለት?
ዘፍጥረት 13:14 ላይ፣ በኋላ ደግሞ ዘፍጥረት 15:1 ላይ እንደምናነበው
ይሖዋ ለአብርሃም ሞገሱን እንዳሳየው በግልጽ ነግሮታል፤
እንደሚወደውም አረጋግጦለታል።
ደግሞም አብርሃምም የፈለገው ይህንን ነው።
ወደ ይሖዋ መሠዊያ ለመሄድ ከአምላክ ጋር ሰላም ሊኖረው ይገባል።
አብርሃም ያደረገው ይህንን ነው።
ስለዚህ ሰላማችሁን የሚያደፈርስ ነገር ሲፈጠር በፍርሃት አትሸነፉ።
ሰላም የሚያደፈርሱ ነገሮች በቤቴል፣
ወይም ደግሞ በቤታችሁ፣
በተመደባችሁበት ጉባኤ
ማጋጠማቸው አይቀርም።
ትሑት በመሆን በእናንተ ቅር የተሰኘባችሁን ሰው ለመፈለግ ሂዱ።
ከዚያም ከዚያ ሰው ጋር ሰላም ፍጠሩ።
ይሄን ማድረግ ቀላል ነው?
አይደለም።
ሰላም ለመፍጠር ጥረት ስታደርጉ ሌላኛው ወገን ሁልጊዜ ፈቃደኛ ይሆናል?
ላይሆን ይችላል።
ይሖዋ ግን ጥረታችሁን ያያል።
ከዚያስ?
ከዚያማ ወደ መሠዊያው ተመልሳችሁ
መሥዋዕታችሁን ታቀርባላችሁ።
ይሖዋ እዚያ ሆኖ መሥዋዕታችሁን ለመቀበል ይጠብቃችኋል።
ለምን?
ምክንያቱም እናንተ ሰላም ለመፍጠር የምትችሉትን ሁሉ አድርጋችኋል።
የ159ኛው የጊልያድ ክፍል ተመራቂዎች፣
ሁላችሁንም በጣም እንወዳችኋለን!
በምትሄዱበት ሁሉ የይሖዋ በረከት እንዳይለያችሁ
መጸለያችንን እንቀጥላለን።
በምረቃው ወቅት የቀረቡት ሌሎች የሚያበረታቱ ንግግሮች
በቅርቡ jw.org ድረ ገጽ ላይና
JW ላይብረሪ ላይ ይወጣሉ።
ከመለያየታችን በፊት ወደ ደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ተጉዘን
በአውስትራሊያ የሚገኙ ወንድሞቻችንን እንጎበኛለን።
አውስትራሊያ በምድር ላይ ካሉ አህጉራት ሜዳማ ክፍል የሚበዛበት ነው።
ከአንታርክቲካ በመቀጠል ደረቅ የአየር ንብረት ያለበት አህጉር ነው።
“አውስትራሊያ” የሚለው ስያሜ ከላቲን የመጣ ሲሆን
ትርጉሙም “የማይታወቀው የደቡብ ምድር” የሚል ነው።
በተጨማሪም እንደ ነጭ ኦፓል ያሉ ውድ ማዕድናት በብዛት የሚገኙበት አህጉር ነው።
አውስትራሊያ የተለያዩ ባሕሎች ያሏቸው ሰዎች መኖሪያ ናት።
በአገሪቱ ውስጥ ከ270 የሚበልጡ ባሕሎች ይገኛሉ።
ከአውስትራሊያ ነዋሪዎች መካከል ከ25 በመቶ የሚበልጡት የተወለዱት በሌላ አገር ነው።
አብዛኞቹ አውስትራሊያውያን ወጣ ብለው መዝናናት ይወዳሉ።
ከሚያስደስቷቸው ነገሮች መካከል የውኃ ላይ ሸርተቴ፣
የአውስትራሊያ ኳስ ጨዋታ
እንዲሁም ከቤት ውጪ ሥጋ ጠብሶ መብላት ይገኙበታል።
ውጪ ብረት ምጣድ ላይ ሥጋ ጠብሶ መብላት
አውስትራሊያውያን የሚታወቁበት ነው።
እንግዶች ተጋብዘው ሲመጡ ባዶ እጃቸውን አይመጡም።
ስለዚህ አንድ ላይ ተሰብስበው ሲመገቡ
የተለያዩ አገራት የባሕል ምግቦችን የመመገብ አጋጣሚ ያገኛሉ።
ሌላው ታዋቂ የአውስትራሊያ ምግብ ቬጂማት ይባላል።
መሠራት የጀመረው ሜልበርን ከተማ ውስጥ ከ1923 አንስቶ ነው።
ይህ ጠቆር ያለ ቡኒ ቀለም ያለው ማባያ የሚሠራው ከቢራ እርሾ ነው።
ደስ የሚልና ለየት ያለ ቃና አለው።
ብዙዎች የሥጋ ዓይነት ጣዕም እንዳለው ይናገራሉ።
ደረቅ ባለ ወይም በተጠበሰ ዳቦ ላይ ቬጂማት ቀብቶ መብላት
ብዙዎቹን አውስትራሊያውያን ያስደስታቸዋል።
የአውስትራሊያ ሕዝብ ለቡና ባለው ፍቅርም ይታወቃል።
ሦስት አራተኛ የሚሆነው የአገሪቱ ነዋሪ
በየቀኑ ቡና የመጠጣት ልማድ አለው።
95 በመቶ የሚሆኑት ካፌዎች የተያዙት በግለሰቦች ነው።
ከሌላ አገር የሚያስመጡትን ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና ይጠቀማሉ።
ጣፋጭና ማራኪ ላቴ በማዘጋጀት የተካኑ ናቸው።
በ18ኛው መቶ ዘመን መገባደጃ ላይ
በመቶዎች የሚቆጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች በመርከብ ወደ አውስትራሊያ ገቡ።
በ19ኛው መቶ ዘመን ይሖዋ እና ጅሆቫ የሚሉትን አጠራሮች ጨምሮ
መለኮታዊው ስም በአንዳንድ የአገሬው ቀደምት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ ይገኝ ነበር።
በርካታ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ልባቸው ተነክቷል።
ከእነዚህ መካከል ታዳጊዋ ካርታኒያ ትገኝበታለች።
በ11 ዓመቷ የአገሬው ቋንቋ በሆነው በካሩና እንዲህ ብላ ጽፋ ነበር፦
“ምንጊዜም ይሖዋን አምልኩ።
ይሖዋ ፈጣሪያችን ነው።
ይሖዋ ከኃጢአታችን ያድነናል።”
ከምዕራብ አውስትራሊያ የመጣው አርተር ዊሊስ ሰዎችን ስለ አምላክ የማስተማር ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው።
በ1931 በ19 ዓመቱ አቅኚ ከሆነ በኋላ ራቅ ያሉ ቦታዎች ሄዶ መስበክ ጀመረ።
በ1932 የአገሪቱን ቀደምት ነዋሪዎች ለማግኘትና ለእነሱ ለመስበክ ጥረት ማድረግ ጀመረ።
አርተር በ1943 ወደ ፒንግሊ ከተማ በመሄድ የአቦሪጂን ዝርያ ላለው አንድ ቤተሰብ ሰበከ።
ጄምስና ባለቤቱ ሜብል 17 ልጆች ነበሯቸው።
መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጠኑት ቤታቸው ነበር።
ይህ ቤተሰብ ከጊዜ በኋላ በአውስትራሊያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለተቋቋመውና
ቀደምት የአገሪቱ ነዋሪዎች ላሉበት ጉባኤ መሠረት ሆኗል።
የጄምስና የሜብል የልጅ ልጆች በአሁኑ ወቅት በአውስትራሊያ የአምላክን መንግሥት ከሚሰብኩት
ከ71,000 የሚበልጡ አስፋፊዎች መካከል ይገኙበታል።
አስፋፊዎች ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ለማግኘት
ወደ ባሕር ዳርቻዎች፣
ወደ እርሻ ቦታዎች
እንዲሁም ወደ መሐል ከተማ ይሄዳሉ።
በተጨማሪም እንደ ማንደሪን፣ ቻይንኛ ያሉ ቋንቋዎችን ለመማርና
ባሕሉን ለመልመድ ጥረት ያደርጋሉ።
በሜልበርን የሚገኘው የካርልተን ጉባኤ ቀናተኛ አስፋፊዎች አሉት።
የሚሰበሰቡት የተለያየ ባሕል ያላቸው ሰዎች በሚገኙበት
በሜልበርን ማዕከላዊ ክፍል ነው።
የጉባኤው አስፋፊዎች ከ21 የተለያዩ አገራት የተውጣጡ ናቸው።
በዚያ የሚገኙት ወንድሞችና እህቶች ሞቅ ያለ ክርስቲያናዊ ሰላምታቸውን ልከውላችኋል።
እኛም ፍቅራዊ ሰላምታችንን ልከንላችኋል።
ይህ ከይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት የሚተላለፍላችሁ
JW ብሮድካስቲንግ ነው።