JW subtitle extractor

JW ብሮድካስቲንግ—ሐምሌ 2026

Video Other languages Share text Share link Show times

ሁላችሁም ለJW ብሮድካስቲንግ ፕሮግራማችን እንኳን ደህና መጣችሁ!
ሁላችንም ጥሩ ውሳኔ በማድረግ
የወደፊቱን ጊዜ በልበ ሙሉነት መጠበቅ እንፈልጋለን።
ይህን ለማድረግ ግን መመሪያ ማግኘት ያስፈልገናል።
ይህን መመሪያ ከየት ማግኘት እንደምንችልና
መመሪያውን እንዴት መከተል እንዳለብን እናያለን።
የቾምባ ቤተሰብ የተሰጣቸውን መመሪያ በታማኝነት ታዝዘዋል።
በዚህ የተነሳ የተባረኩት እንዴት እንደሆነ እናያለን።
ከዕንባቆም መጽሐፍ አንድን ኃላፊነት ወይም አስቸጋሪ ሁኔታ
መወጣት እንደማንችል ሆኖ ሲሰማን
መረጋጋት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።
ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት
ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ሄዶ የሚያገለግል አንድ ወንድም
ውሎው ምን እንደሚመስል እናያለን።
በዚህ ፕሮግራም ላይ ሌሎች በርካታ ነገሮችንም እንማራለን።
ይህ JW ብሮድካስቲንግ ነው!
በየት መሄድ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ?
የዚህ ንግግር ጭብጥ የተመሠረተው
በኢያሱ 3:4 ላይ ነው።
መቼቱ እንደሚጠቁመን የእስራኤል ብሔር
ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ደፍ ላይ ደርሷል።
ለ40 ዓመታት በምድረ በዳ ከተጓዘ በኋላ!
ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ጉዞ ግን ቀላል አይደለም።
በተስፋይቱ ምድር ቃል የተገባላቸውን በረከት ለማግኘት
እምነትና ድፍረት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
ታዲያ አመራር የሚሰጣቸው ማን ነው?
እስቲ ኢያሱ 3:2-4ን እናንብብ።
ይሖዋ በዚህ ወሳኝ ወቅት ሕዝቡን የመራው
እንዴት እንደሆነ ይነግረናል።
“ከሦስት ቀን በኋላም አለቆቹ በሰፈሩ ውስጥ በመዘዋወር
“ሕዝቡን እንዲህ በማለት አዘዙ፦
“‘ሌዋውያን የሆኑት ካህናት የአምላካችሁን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ስታዩ
“‘ከሰፈራችሁበት ቦታ ተነስታችሁ ታቦቱን ተከተሉት።
“‘ሆኖም ወደ እሱ አትቅረቡ፤
“‘በእናንተና በታቦቱ መካከል 2,000 ክንድ ያህል ርቀት ይኑር፤
“‘ከዚህ በፊት በዚህ አቅጣጫ ሄዳችሁ ስለማታውቁ
በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ በዚህ ትረዳላችሁ።’”
እስራኤላውያን በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባቸው ለማወቅ
የቃል ኪዳኑን ታቦት መከተል ነበረባቸው።
እንደምናውቀው ግን እስራኤላውያን
የሚሰጣቸውን መመሪያ የመከተል ችግር ነበረባቸው።
ብዙውን ጊዜ አመራር በሚሰጧቸው ሰዎች ድክመት ላይ ያተኩሩ ነበር።
ከዚህም በተጨማሪ
ኩራትና በራስ የመመራት ዝንባሌ ተጠናውቷቸው ነበር።
ይህ ትኩረታችንን የሚስበው ለምንድን ነው?
እኛም የምንኖረው በሰው ልጅ ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ነው።
ማስረጃዎቹ ሁሉ የሚጠቁሙት
ወደ መጨረሻዎቹ ቀናት ጠልቀን እንደገባን ነው።
ወደ አርማጌዶን ጦርነት የሚያመራው ታላቁ መከራ በቅርቡ ይጀምራል።
መመሪያ መከተል የሞትና የሕይወት ጉዳይ ነው።
ግን ወዴት መሄድ እንዳለብን የምናውቀው እንዴት ነው?
ልክ እንደ ኢያሱ ዘመን ሁሉ
ዛሬም ይሖዋ ሕዝቡን የሚመራበትን መንገድ ማወቅና
ያንን መንገድ መከተል ይኖርብናል።
እስቲ ለሦስት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት እንሞክር።
(1) መንገዱን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
(2) ከመንገዱ እንዳንወጣ ምን እናድርግ?
(3) እኩል ለመሄድ ምን እናድርግ?
እስቲ ከመጀመሪያው ጥያቄ እንነሳ፦
መንገዳችንን በትክክል ማወቅ የምችለው እንዴት ነው?
እስራኤላውያን ሙሴና አሮን በምድረ በዳ ሲመሯቸው
ይሖዋ መንገዱን እንደሚያሳያቸው የሚጠቁም ግልጽ ማስረጃ ነበራቸው።
በቀን የደመና ዓምድ በምሽት ደግሞ
የእሳት ዓምድ ይመራቸው እንደነበር እናውቃለን።
አሁን ግን ይሖዋ ለሕዝቡ አመራር የሚሰጥበትን መንገድ ቀየረ።
ሕዝቡ ይሖዋ ኢያሱን ተጠቅሞ እየመራቸው እንዳለ ማመን ነበረባቸው።
ይሖዋ እንዲተማመኑበት ይፈልግ ነበር።
የቃል ኪዳኑ ታቦት ከፊት ከፊት እንዲሄድ በማድረግ
ኢያሱ አሁንም አመራር እየሰጣቸው ያለው
ይሖዋ መሆኑን ሕዝቡ እንዲገነዘብ አድርጓል።
ዛሬስ ይሖዋ ማንን ነው የሚጠቀመው?
ኢየሱስ መልሱን ሰጥቶናል።
እባካችሁ ማቴዎስ 24:45ን አብረን እናውጣ።
ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦
“በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው
“ጌታው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው
ታማኝና ልባም ባሪያ በእርግጥ ማን ነው?”
“ታማኝና ልባም ባሪያ”!
ይህ ባሪያ ማን ነው?
በዛሬው ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮችን የበላይ አካል ያመለክታል።
በዓለም ዙሪያ ላሉ የይሖዋ ምሥክሮች መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባሉ።
እንዲሁም መመሪያና ተግባራዊ እርዳታ ይሰጣሉ።
‘ይህን ትምህርት አውቀዋለሁ።
ይህን ጥቅስም ቢሆን ብዙ ጊዜ አንብቤዋለሁ’ እንል ይሆናል።
ግን ‘እንዲህ ብዬ ያመንኩት ለምንድን ነው?’
ብለን ራሳችንን እንጠይቃለን?
ለዘላለም በደስታ ኑር የተባለው መጽሐፍ 54ኛው ምዕራፍ
ታማኝና ልባም ባሪያየሚጫወተው ሚና የሚል ርዕስ አለው።
እዚህ ምዕራፍ ላይ እንዲህ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል፦
“የበላይ አካሉን የሚመራው
ኢየሱስ ነው ብለህ እንድታምን የሚያደርግህ ምንድን ነው?”
“በክርስቶስ የተሾመው ‘ታማኝና ልባም ባሪያ’ የበላይ አካሉ እንደሆነ ታምናለህ?”
እነዚህ ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው።
መልሳችሁ ምንድን ነው?
ምናልባትም በቀጣዩ የቤተሰብ አምልኮ ወይም የግል ጥናታችሁ ላይ
‘ምርምር አድርግ’ የሚለውን ክፍል ጨምሮ
ይህን ምዕራፍ ማጥናታችሁ ይጠቅማችሁ ይሆናል።
ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገ?
እስቲ አስቡት፦
እስራኤላውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙትን ካህናት ተከትለው
እስከ አፍንጫው ወደ ሞላው ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ለመግባት
ካህናቱን እየመራቸው ያለው ይሖዋ አምላክ መሆኑን
ሙሉ በሙሉ መተማመን ነበረባቸው።
በተመሳሳይም፣ እኛም ከፊታችን በሚጠብቁን አስቸጋሪ ጊዜያት
የበላይ አካሉን መመሪያ ለመከተል
በልጁ በኢየሱስ ተጠቅሞ እየመራን ያለው
አምላካችን ይሖዋ መሆኑን ሙሉ በሙሉ ልንተማመን ይገባል።
‘መንገዱን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?’
ለሚለው የመጀመሪያው ጥያቄያችን መልሱን አገኘን?
ታማኝ እስራኤላውያን እንዳደረጉት
ይሖዋ እኛን ለመምራት የሾማቸውን ሰዎች መታዘዝ አለብን!
ሁለተኛው ጥያቄያችን፦ ‘ከመንገዱ እንዳንወጣ ምን እናድርግ?’
የምንስማማበትን መመሪያ መታዘዝ
ያን ያህል እንደማይከብደን ግልጽ ነው።
ምክንያታዊ እንዳልሆነ የሚሰማንን መመሪያ መታዘዝ ግን
ለማናችንም ቀላል አይደለም።
በዚህ ጊዜ ምን እናድርግ?
በዚህ ረገድ ሐዋርያው ጳውሎስ ግሩም ምሳሌ ትቶልናል።
የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 21 ላይ
ሐዋርያው ጳውሎስ በሚስዮናዊነት ስላከናወነው ሥራ
ለያዕቆብና ለሽማግሌዎቹ ሪፖርት አቅርቧል።
እነሱም በሰሙት ነገር እጅግ ተደሰቱ።
ግን አንድ ችግር ነበር።
በአይሁዳውያን ክርስቲያኖች መካከል ስለ እሱ የተወራውን ወሬ ነገሩት።
የሐዋርያት ሥራ 21:21 እንዲህ ይላል፦
“እነሱም አንተ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁዳውያን ሁሉ
“ልጆቻቸውን እንዳይገርዙም ሆነ የቆየውን ልማድ እንዳይከተሉ በመንገር
“የሙሴን ሕግ እንዲተዉ ስታስተምር እንደቆየህ
ስለ አንተ የሚወራውን ወሬ ሰምተዋል።”
ግን ጳውሎስ እንዲህ እንዳደረገ የሚጠቁም ነገር የለም።
ያም ቢሆን ግን ወሬው ተዛምቷል።
ታዲያ ምን መመሪያ ሰጡት?
የሐዋርያት ሥራ 21:24 ምን እንደሚል እንመልከት፦
“እነዚህን ሰዎች ይዘህ በመሄድ ከእነሱ ጋር የመንጻት ሥርዓት ፈጽም፤
“ራሳቸውንም እንዲላጩ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ክፈልላቸው።
“ይህን ካደረግክ በአንተ ላይ የተወራው ሁሉ ከንቱ መሆኑንና
አንተም ሕጉን እያከበርክ በሥርዓት እንደምትኖር ሁሉም ሰው ያውቃል።”
ታዲያ ጳውሎስ ምን አደረገ?
አልተከራከረም ወይም አልተቃወመም።
ቁጥር 26 እንደሚነግረን
“ጳውሎስ በማግስቱ ሰዎቹን ይዞ በመሄድ
አብሯቸው የመንጻት ሥርዓቱን ፈጸመ።”
ስለዚህ ጳውሎስ ስለ እሱ የተነገረው የሐሰት ወሬ
ውሸት መሆኑን ለማሳየት በራሱ ገንዘብ
እንዲያደርግ የማይጠበቅበትን ነገር ለማድረግ ፈቃደኛ ሆኗል።
ለምን?
ምክንያቱም ጳውሎስ ይሖዋ አመራር እንዲሰጡ ለሾማቸው ሰዎች ታማኝ ነበር!
ምን እንማራለን?
የማንስማማበት ወይም ደግሞ
አስፈላጊ እንዳልሆነ የሚሰማን መመሪያ ሲሰጠን
በይሖዋ በመታመን መመሪያውን እንታዘዛለን?
የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች እስካልተጣሱ ድረስ
የሚሰጠንን ግልጽ መመሪያ እንታዘዝ።
ምናልባት ይሖዋ ነገሮችን ለሆነ ዓላማ እያመቻቸ ይሆናል።
ባይሆን እንኳ ለታማኝነታችን ይባርከናል።
አንዳንዴ ታዛዥነት የሞትና የሕይወት ጉዳይ ይሆናል።
መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ! የሚለው ድራማ
አፍሪካ ውስጥ ሕይወታቸውን ለማትረፍ የሸሹ ወንድሞቻችን
ያጋጠማቸውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው።
ዛሬም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ወንድሞቻችን
ተመሳሳይ ነገር እያጋጠማቸው ነው።
እየደረሰባቸው ባለው ነገር በጣም እናዝናለን።
ድራማው ከባድ ወይም አስፈላጊ እንዳልሆነ የሚሰማን መመሪያ ሲሰጠን
እያንዳንዳችን ‘ምን ዓይነት ምላሽ እሰጣለሁ?’ የሚለውን
ቆም ብለን እንድናስብ አድርጎናል።
ድራማውን በቤተሰብ አምልኳችን እንደገና አይተን
እያንዳንዳችን ምን ምላሽ እንደምንሰጥ መወያየታችን ይጠቅመናል።
እንዲህ የምናደርገው ለምንድን ነው?
እስቲ ይሄን ለማሰብ ሞክሩ፦
‘በታላቁ መከራ ወቅት ግልጽ መመሪያ እናገኛለን?’
‘ምን ማድረግ እንዳለብን ወይም እንደሌለብን የሚገልጽ መመሪያ ይሰጠን ይሆን?’
‘መመሪያውን የምናገኘው እንዴት ነው?’
‘ምክንያታዊ እንደሆነ ይሰማን ይሆን?’
በይሖዋና በልጁ ላይ ሙሉ እምነት ካለን
አመራር እንዲሰጡን የተሾሙ ወንድሞችን ለመታዘዝ
ምንጊዜም ዝግጁ እንሆናለን።
‘መንገዱን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?’
እንዲሁም ‘ከመንገዱ እንዳንወጣ ምን እናድርግ?’ የሚሉትን አይተናል።
ሦስተኛው ጥያቄ፣ ወደኋላ ላለመቅረት ምን እናድርግ?
ተስፋ መቁረጥ፣ ስደት ወይም ሌሎች የተለያዩ ችግሮች
አመራር እንዲሰጡ የተሾሙትን ወንድሞች
መታዘዛችንን እንድናቆምም ሆነ
እንድናመነታ እንዳያደርጉን መጠንቀቅ አለብን።
እርግጥ ነው ከበላይ አካሉ በቀጥታ ለምናገኘው መመሪያ
ፈጣን ምላሽ እንሰጥ ይሆናል።
ግን መመሪያውን ያገኘነው ከጉባኤ ሽማግሌዎች ወይም
ከወረዳ የበላይ ተመልካቻችን ሲሆንስ?
በግለሰብ ደረጃ ስለምናውቃቸው ጉድለቶቻቸውን እናያለን።
ታዲያ ይሄ እንድናመነታ ወይም እንዳንታዘዝ ሊያደርገን ይገባል?
በዚህ ጊዜም የመመሪያው ምንጭ ይሖዋ እንደሆነ እናስተውላለን?
ዛሬም የይሖዋን ድርጅት በቅርበት መከተል ያስፈልገናል።
ለምን?
ለምሳሌ ከአንድ ወዳጃችሁ ጋር በመኪና ተከታትላችሁ እየሄዳችሁ ነው እንበል።
ግን መንገዱ ስለተጨናነቀባችሁ ቀድሟችሁ ርቆ ሄደ።
እንዲያውም ሳታስተውሉት አቅጣጫ ቀይሮ ታጥፎ ሄደ።
ይህ የሆነው ለምንድን ነው?
በቅርበት ስላልተከተላችሁት!
በተመሳሳይም የይሖዋን ድርጅት በቅርበት መከተል አለብን።
እንዴት?
በተደጋጋሚ የሚሰጡንን ማሳሰቢያዎች ማስታወሳችን እንዲህ ለማድረግ ይረዳናል።
የትኞቹን?
ሁሌም በስብሰባዎች ላይ መገኘት፣
በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ፣
ቋሚ የግል ጥናት፣ ጸሎት እንዲሁም አገልግሎት!
እነዚህ ከይሖዋ ድርጅት ጋር በቅርበት ለመጓዝ ይረዱናል።
ግን አንዳንዴ በድርጅቱ አሠራር ወይም በሚደረጉ ውሳኔዎች
ቅር የሚሰኙ አንዳንድ ሰዎች አሉ።
ይህም ለመታዘዝ እንዲያመነቱ፣ እንዲቀዘቅዙ
ወይም ከጉባኤ እንዲርቁ አድርጓቸዋል።
ግን እነዚህ ሰዎች ያላስተዋሉት ነገር
ልክ በእስራኤላውያን ዘመን እንደነበረው ዛሬም ፍጹም የሆነ አሠራር የለም።
ምክንያቱም ይሖዋ እየተጠቀመ ያለው ፍጽምና የጎደላቸውን ሰዎች ነው!
በሌላ በኩል ደግሞ ፍጹም የሆነ ሌላ ድርጅትም የለም።
ፍጹም ሰው የነበረው ኢየሱስ ብቻ ነው።
ስለዚህ በድርጅቱ ውስጥ የምናገኘው ፍጹም ያልሆኑ ሰዎችን ነው።
ግን አቅማቸው በፈቀደ መጠን ፍጹም የሆነውን ኢየሱስን ይታዘዛሉ።
በወረዳ የበላይ ተመልካችነት ለረጅም ጊዜ ያገለገለ
አንድ አስተዋይ ወንድም እንዲህ ብሏል፦
“ፍጹም ባይሆንም ከዚህ የተሻለ ድርጅት በምድር ላይ የለም።”
ደግሞም ልክ ነው!
ይህ ዮሐንስ ምዕራፍ 6 ላይ የሚገኘውን ዘገባ ያስታውሰናል።
ዘገባው እዚህ ላይ እንደሚነግረን አንዳንዶች
ኢየሱስ ስለ ሥጋውና ስለ ደሙ በተናገረው ነገር ተሰናክለዋል።
ከዚህም የተነሳ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ
ትተውት ወደነበረው ነገር ተመለሱ።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እሱን መከተላቸውን አቆሙ።
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ 12ቱን
“እናንተም መሄድ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው።
ምላሻቸው ምን ነበር?
ዮሐንስ 6:68 ላይ ተመዝግቦ የምናገኘው
ጴጥሮስ የሰጠው ምላሽ እምነቱን ያሳያል።
እንዲህ ብሏል፦
“ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን?
አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ።”
“ወደ ማን እንሄዳለን?”
ጴጥሮስም ሆነ ሌሎቹ ሐዋርያት
ኢየሱስን ትተው እንደሄዱት ደቀ መዛሙርት
ኢየሱስ የተናገረው ነገር አልገባቸውም።
ግን ከእሱ ውጪ ወደማንም ሊሄዱ እንደማይችሉ ገብቷቸዋል።
ዛሬም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።
ያለንን ነገር ፈጽሞ አንርሳ።
ዛሬስ ቢሆን ከይሖዋ ድርጅት ውጭ መመሪያ፣ መንፈሳዊ ምግብና
ማጽናኛ ለማግኘት የት መሄድ እንችላለን?
ይህን የትም አናገኝም።
ገና ለገና አንዳንድ ነገሮች ስላልገቡን ብቻ
በድርጅቱ ውስጥ ያገኘናቸውን መልካም ነገሮች አቅልለን አንመልከት።
ታዲያ እስካሁን ምን ትምህርት አገኘን?
ያለነው በመጨረሻዎቹ ቀናት መጨረሻ ላይ ነው።
በጉጉት የምንጠብቀው አዲሱ ሥርዓት ለመግባት ደፍ ላይ ነን።
በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ላይ እንደነበሩ እስራኤላውያን
ዛሬም ታዛዥነትና መመሪያ መከተል ሕይወታችንን ያተርፍልናል።
ይሖዋ መመሪያ ለመስጠት የበላይ አካሉን እየተጠቀመ መሆኑን
ከአሁኑ እርግጠኞች መሆን አለብን።
ተስፋ መቁረጥ ወይም የሌሎች አለፍጽምና
ጉዟችንን እንዲያደናቅፍብን አንፍቀድ።
ፍጹም ባይሆንም ዓለም አቀፍ አንድነት ያለው ድርጅት ውስጥ መታቀፋችን
ምን ያህል ታላቅ መብት እንደሆነ ፈጽሞ መርሳት አይኖርብንም።
በተጨማሪም ወደፊት ምንም ዓይነት አስቸጋሪ ነገር ቢያጋጥመን
ከይሖዋ ድርጅት ጋር በታማኝነት እስከተጣበቅንና
መመሪያዎችን እስከታዘዝን ድረስ
ሁሌም በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን እናውቃለን።
ሎይክ እና ዮሐሪ ቾምባ በኮንጎ የሚገኙ ወንድምና እህት ናቸው።
የሚሰጣቸውን መመሪያ በታማኝነት መከተል
የሞትና የሕይወት ጉዳይ መሆኑን ካጋጠማቸው ተሞክሮ ተምረዋል።
መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ የሚለው ድራማ
ለእኔ ልዩ ትርጉም አለው።
ምክንያቱም የእኛም ቤተሰብ ተመሳሳይ ሁኔታ አጋጥሞት ነበር።
ከ1995 በፊት ሕይወት ጥሩ ነበር።
አብዛኞቻችን ገና ልጆች ነበርን።
ድንገት ግን ጦርነት ተነሳ።
ስለዚህ ቤተሰባችን ኮንጎን ጥሎ ተሰደደ።
ቅርንጫፍ ቢሮው ለሁላችንም የሰጠን መመሪያ
ቀላልና የማያሻማ ነበር።
አንዳንዶች ግን ሳይታዘዙ ቀሩ።
በዚህም ምክንያት
የራሳቸውንም ሆነ የቤተሰባቸውን ሕይወት አጥተዋል።
አባቴ ቤተሰባችንን ሰላማዊ ወደሆነ ቦታ
በአንድ ጊዜ ለመውሰድ በቂ ገንዘብ አልነበረውም።
ስለዚህ ተለያይተን መጓዝ ነበረብን።
እናታችን እኔንና ሌሎች አራት ልጆቿን ይዛ
ወደ ታንዛኒያ ተጓዝን።
አባታችን ስለምንገናኝበት ቦታ መመሪያ ሰጥቶን ነበር።
ስለዚህ ተለያይተን ብንጓዝም
አባታችን ያለንን በመስማታችን በኋላ ላይ
መልሰን መገናኘትና አንድ ላይ መሆን ችለናል።
መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ በሚለው ድራማ ላይ
ወላጆቹ ከልጆቻቸው ጋር መልሰው ሲገናኙ ይታያል።
ይህ እኛም መልሰን ስንገናኝ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሰኛል።
በጣም ደስ ይል ነበር።
በስደተኞች ካምፕ ውስጥ የነበረው ሕይወት
ውጥረት የበዛበት ነበር።
ወታደሮች በካምፑ ላይ
ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ነበር።
ግን መንፈሳዊ አደጋም ነበረው።
በአገልግሎታችን ላይ ማተኮር ከባድ ነበር።
ስለዚህ እንደገና ከታንዛኒያ ወደ ሞዛምቢክ ተሰደድን።
በአንድ ወቅት አንድ የጭነት መኪና ተሳፍረን ስንጓዝ
ያጋጠመንን አሁንም አስታውሳለሁ።
መንገዱ ጥሩ አልነበረም።
አባጣ ጎርባጣ የበዛውና ለጉዞ የማይመች ነበር።
የተወሰነ ከተጓዝን በኋላ
ሌሊት 9 ሰዓት አካባቢ መኪናው ሲቆም
የምናርፍ መስሎኝ ነበር።
ግን መኪናው እንደቆመ አባታችን ሁላችንንም
“ኑ ከመኪናው እንውረድና የዕለት ጥቅስ እናድርግ” አለን።
እኛ የፈለግነው ያንን ማድረግ አልነበረም።
ልጆች ስለሆንን የፈለግነው መተኛት ነው።
ይህ አጋጣሚ መቼም ቢሆን ከአእምሮዬ የማይጠፋ ትውስታ ነው።
ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን
አባታችን ምንጊዜም ለመንፈሳዊ ነገሮች ቅድሚያ ይሰጣል።
አባታችን በሚያደርገው ነገር ሁሉ ምንጊዜም በይሖዋ ይታመናል።
የጸሎት ሰው ነው።
ምንም ዓይነት ነገር ሲያጋጥመው ይጸልያል።
ለጸሎቱም ይሖዋ የሚሰጠውን ምላሽ በትዕግሥት ይጠብቃል።
ሞዛምቢክ እያለን እናታችን ታመመች።
ስለዚህ አስፈላጊውን ሕክምና እንድታገኝ
ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ ወደ ኬፕታውን መሄድ ነበረባት።
ግን የተሰጣት ሕክምና አላዳናትም።
በ2003 ሕይወቷ አለፈ።
አባታችን ብቻውን እኛን ማሳደግ ጀመረ።
በእናታችን ሞት የተሰማው ሐዘን ከባድ ቢሆንም በይሖዋ ታምኗል።
አባታችን ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ ያደረገው
በይሖዋ ላይና እኛ ልጆቹን በእውነት ውስጥ በማሳደግ ላይ ነው።
“እናታችሁን መልሳችሁ እንድታገኙ እፈልጋለሁ” ይለናል።
ለሁላችንም የሚለን አንድ አባባል ነበረው።
እንዲህ ይለናል፦ “ይህ ሥርዓት እንደሆነ አልቆለታል።
መሥራት ያለብን ለአዲሱ ሥርዓት ነው።”
ይህን የሚለው ‘ለይሖዋ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን።
በዚህ ሥርዓት ውስጥ ምንም ዋጋ ያለው ነገር የለም’ ለማለት ነው።
ሁልጊዜም ቢሆን አባታችን
የሚያበረታታንና ግባችን እንዲሆን የሚፈልገው
ይሖዋን በሙሉ ጊዜ ማገልገል ነው።
እኔም ትምህርቴን ስጨርስ በአቅኚነት ማገልገል ጀመርኩ።
በኋላም በአካባቢ ንድፍና ግንባታ ውስጥ የማገልገል
ልዩ መብት አገኘሁ።
አሁን ይሖዋን በቤቴል የማገልገል ልዩ መብት አግኝቻለሁ።
ስለዚህ በየዕለቱ ያለኝን ጊዜ የምጠቀመው
ይሖዋን ለማገልገል የምችለውን ሁሉ በማድረግ ነው።
ወደ ቤቴል ለመምጣትና በግንባታ ሥራ ለመካፈል ራሴን አቀረብኩ።
ሁሉም ልጆቼ በእውነት ውስጥ እየተመላለሱ መሆኑ እጅግ ያስደስተኛል።
በሕይወቴ በጣም ከባድ በሆኑት ጊዜያትም ጭምር
የይሖዋን እጅ አይቻለሁ።
ልጆቻችንን ስናሳድግ ቀጥሎ ምን እንደሚያጋጥመን
ወይም ወዴት እንደምንሄድ ያላወቅንባቸው ጊዜያት ነበሩ።
ይሖዋ ግን ሁልጊዜም ከጎናችን ነበር።
በይሖዋ አምላክ ከመመካት ውጪ
ሌላ አማራጭ ታይቶን አያውቅም።
መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ የሚለው ድራማ
ይሖዋ ሁኔታችንን ማየት ብቻ ሳይሆን
ስሜታችንንም እንደሚረዳልን አስገንዝቦኛል።
በእርግጥም መታዘዝ ሕይወት ያተርፋል።
መመሪያው የተሰጠን ለምን እንደሆነ ባይገባንም እንኳ መታዘዝ አለብን!
ምክንያቱም ለእኛ የተሻለውን ነገር የሚያውቀው ይሖዋ ነው!
ወንድም ሊያን ቾምባ፣ በሕይወት ለመትረፍና ለይሖዋ ያላቸውን ታማኝነት ለመጠበቅ
እሱንና ልጆቹን ምን እንደረዳቸው ጥሩ አድርጎ ገልጾልናል።
ምን እንዳለ ታስታውሳላችሁ?
“በይሖዋ አምላክ ከመመካት ውጭ ሌላ አማራጭ ታይቶን አያውቅም።”
የቾምባ ቤተሰብ መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ የሚለው ድራማ
የቤተሰባቸውን ሁኔታ እንደሚያስታውሳቸው ተናግረዋል።
ሁላችሁም ይህን አበረታች ድራማ በድጋሚ በማየት
ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ መታዘዝ
ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ትምህርት ማግኘት ትችላላችሁ።
ስንጨነቅ ወይም መረጋጋት ሲያቅተን
መመሪያን መከተል ከባድ ሊሆንብን ይችላል።
ሆኖም የዕንባቆም ታሪክ በዚህ ወቅት መረጋጋት፣ ትኩረታችንን መሰብሰብና
መታዘዝ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል።
በቤተሰብ አምልኳችን
የዕንባቆምን መጽሐፍ ልናጠና በመሆኑ ደስ ብሎኛል።
አዎ፣ የምርምር መሣሪያዎችን ሳንጠቀምም
ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ውድ ሀብቶችን እናገኛለን።
ለምን የመጽሐፉን ይዘት በማየት አንጀምርም?
ጥሩ፣ የሚጀምረው “ነብዩ እርዳታ ለማግኘት ያሰማው ጩኸት፣
ይሖዋ ሆይ፣ እስከ መቼ ነው?” በማለት ነው።
በደንብ የምናውቀው አባባል ነው።
ግን እንደዚህ የተሰማው ለምንድን ነው?
እስቲ የጊዜ ሰንጠረዡን እንመልከትና
በዕንባቆም ዘመን የተከናወኑትን ነገሮች እንይ።
እሺ፣ ደስ ይለኛል።
ሰንጠረዡ እንደሚያሳየን፣ ዕንባቆም የኖረው
ከኢዮስያስ የግዛት ዘመን መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ
እስከ ኢዮዓቄም ዘመን ድረስ ነው።
በኢዮስያስ የግዛት ዘመን ሕዝቡ
የይሖዋን ቃል ይሰማና ያከብር እንደነበር አስታውሳለሁ።
ያ ጊዜ ለዕንባቆም አስደሳችና የተረጋጋ ወቅት ነበር።
አንዲት ቀስት ግን ሁሉን ነገር ለወጠችው።
ኢዮስያስ ተገደለ፣ ከዚያ ክፉ ነገሥታት ሥልጣን ያዙ።
ሕዝቡም እንደገና የሐሰት አማልክትን ማምለክና
መጥፎ ነገር መሥራት ጀመሩ።
ልክ ነሽ፣ ልባቸው አልተለወጠም ነበር ማለት ነው።
በተለይ ኢዮዓቄም የይሖዋን ነብያት ያሳድድ ነበር።
እንዲያውም ዑሪያህ አስገድሎታል።
ዕንባቆም እንዲህ ዓይነት ስደት ቢደርስበት
ምን ሊሰማው እንደሚችል መገመት እንችላለን።
የተረጋጋና አስደሳች ሕይወት እየኖርሽ፣
ድንገት ሕይወትሽን ለማጥፋት ከሚፈልጉ ሰዎች ስትሸሺ ይታይሽ።
ዕንባቆም እርዳታ ለማግኘት መጮሁ አያስገርምም።
እርዳታ በጣም ያስፈልገው ነበር።
እውነትሽ ነው፣
ታዲያ ይሖዋ ለዕንባቆም ምላሽ የሰጠው እንዴት ነው?
ጥሩ ጥያቄ ነው።
መጽሐፉን ስታነቢ፣ ይሖዋ ዕንባቆምን
‘እንዴት እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ትጠይቀኛለህ?’
ያለበትን ቦታ አግኝተሻል?
ኧረ በፍጹም!
እኔም አላገኘሁም።
ይሖዋ ዕንባቆምን ከያዘበት መንገድ ብዙ እንማራለን።
አዎ፣ ይሖዋ ዕንባቆምን አዳምጦታል።
ስለተሰማው ስሜት አልወቀሰውም።
ዕንባቆም የነበረበትን ሁኔታ በሚገባ ተረድቷል።
እንዲያውም ለሌሎች ትምህርት እንዲሆን
ስሜቱን በግልጽ እንዲያሰፍር አድርጎታል።
ይህ በዕንባቆም ላይ ምን ስሜት አሳድሮበት ይሆን?
ከልባችን የምንጠይቀውን ነገር ከፍ አድርጎ ይመለከታል።
ይሖዋ እንዲህ ዓይነት አምላክ ነው።
አዎ፣ ወደ እሱ መቅረብ ቀላል ነው።
ይሖዋ እንዲህ ያለን ያህል ነው፦
‘የዕንባቆምን ስሜት እንደተረዳሁ፣ የእናንተንም ስሜት እረዳለሁ።
እንዲህ የተሰማችሁ ለምን እንደሆነ ይገባኛል’ ያለን ያህል ነው።
ዕንባቆም 2:4 ላይ ይሖዋ የተናገረው ነገር ትኩረቴን ስቦታል።
“ጻድቅ ግን በታማኝነቱ በሕይወት ይኖራል።”
የሚገርም ሐሳብ ነው።
በማስታወሻዬ ላይ እንዲህ ብዬ ጽፌያለሁ፦
“ይህ እንዲሁ ተራ አባባል ሳይሆን
ወሳኝ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ነው።”
ይሖዋ በእሱ የሚታመኑትን ሰዎች እንደማይረሳ ማረጋገጫ እየሰጠው ነው።
“በሕይወት ይኖራሉ” እያለው ነው።
ደግሞም እንዳለው ነው የሆነው።
ኤርምያስ፣ ባሮክ፣ ኤቤድሜሌክና ሬካባውያን ከጥፋቱ ተርፈዋል።
ይሖዋ እምነት የሚጣልበት አምላክ ነው።
ሌላም የምንማረው ነገር አለ።
የኅዳግ ማጣቀሻውን በመመልከት ተጨማሪ ነገሮችን ማግኘት እንችላለን።
አየሽው እዚህ ላይ?
ጳውሎስ ይህን ሐሳብ ሦስት ጊዜ በመጥቀስ
በመከራ ውስጥ የነበሩትን ክርስቲያኖች አበረታቷል።
እኔና አንቺ እንድንማርበት ሲል
ይሖዋ እነዚህን ቃላት በተደጋጋሚ አጽፎልናል።
ይሖዋ ‘ለዕንባቆም የነገርኩትን ነገር አስታውሱ’ ያለን ያህል ነው።
የይሖዋ ምላሽ በዕንባቆም ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ልብ አልከው?
ምዕራፍ 3:18 ላይ በይሖዋ ሐሴትና ደስታ እንደሚያገኝ ተናግሯል።
በአንድ የማለዳ አምልኮ ንግግር ላይ
‘በደስታ መዝለል ወይም እየጨፈሩ መሽከርከር’
የሚል ቀጥተኛ ትርጉም እንዳለው ተገልጾ ነበር።
ዕንባቆም የነበረበት ሁኔታ አልተለወጠም።
ሆኖም የልቡን አውጥቶ ለይሖዋ ስሜቱን ሲናገር
ለገጠመው ነገር ያለው አመለካከት ተለወጠ።
አዎ፣ ይሖዋ እምነት የሚጣልበትና የሚቀረብ አምላክ መሆኑ
ዕንባቆም ከደረሰበት መከራ እንዲጽናና አስችሎታል።
በጣም ደስ የሚል ነው።
እኛስ ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን?
አንቺን ይበልጥ የነካሽ የትኛው ነው?
ይሖዋ የሚቀረብ አምላክ መሆኑ!
ስጸልይ የልቤን አውጥቼ መናገር እንደምችል ተገንዝቤያለሁ።
ምንም ነገር መደበቅ አያስፈልገኝም።
ይሖዋ ስሜቴን ስለሚረዳ
ስሜቴን ስለምገልጽባቸው ቃላት ከልክ በላይ መጨነቅ አያስፈልገኝም።
የማስበውን፣ የሚሰማኝን፣ ለሌላ ሰው የማልነገረውን እንኳ
ለይሖዋ የመናገር ነፃነቱ አለኝ።
ለስሜቴ ትልቅ ቦታ ይሰጣል።
በጣም ጥሩ ነጥብ ነው።
እኔም ልክ እንደ ይሖዋ የምቀረብ መሆን እፈልጋለሁ።
የምናገረው ነገር ብቻ ሳይሆን
የማደርገው ነገርና ፊቴ ላይ የሚነበበው ስሜት
ሌሎች እንዲቀርቡኝ የሚያደርግ እንዲሆን እፈልጋለሁ።
አንቺም ሆንሽ ሌሎች ሰዎች በቀላሉ እንድትቀርቡኝ እፈልጋለሁ።
አንድ ሰው እንደ ዕንባቆም ስሜታዊ ሆኖ ቢያናግረኝ እንኳ
በተናገራቸው ቃላት ላይ ከማተኮር ይልቅ
እንደዚህ ያደረገው ለምን እንደሆነ ለመረዳት እጥራለሁ።
ይህም ጥሩ ነጥብ ነው።
ይሖዋ እምነት የሚጣልበት አምላክ መሆኑን ማወቄ በጣም አስደስቶኛል።
ስለ ወደፊቱ ጊዜ የተናገረው ነገር እንደሚፈጸም እተማመናለሁ።
“ጻድቃን በሕይወት ይተርፋሉ።”
ይህ ወሳኝ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ነው።
የሚያጋጥመኝ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣
ልክ እንደ ዕንባቆም ደስተኛ መሆን እችላለሁ።
ዕንባቆም በምዕራፍ ሦስት ላይ እንዳደረገው
እኔም ይሖዋ ስላደረጋቸው ነገሮች አስላስላለሁ።
ሁኔታዎች እየከፉ ሲሄዱ ይሖዋን በትዕግሥት እጠብቃለሁ።
መመሪያዎቹንም እታዘዛለሁ።
መጨረሻው የሚመጣው መቼም ይሁን መች፣
ዋናው ነገር በየዕለቱ ለይሖዋ ታማኝ ሆኖ መገኘት ነው።
ደስ ይላል።
ይሖዋ የሚቀረብና እምነት የሚጣልበት አምላክ ነው።
በዚህ ጊዜ የሚያስፈልገን እንዲህ ያለ እምነት ነው።
ማጣቀሻዎቹን ብቻ በመጠቀምና
ቀደም ሲል ከምናውቃቸው ነገሮች ጋር በማዛመድ
ብዙ ውድ ሀብቶች አግኝተናል።
ዕንባቆም ይሖዋን ተጠያቂ ሲያደርገው፣ ይሖዋ ስላሳየው ትዕግሥት
ወይም ዕንባቆም ወቀሳ ይሰጠኛል ብሎ ያሰበው
ለምን እንደሆነ አልተነጋገርንም።
ገና ብዙ የምንማረው ነገር አለ።
አዎ፣ መቆፈራችንን እንቀጥል።
ዕንባቆም ይህን ሐሳብ የጻፈው . . .
“ጻድቅ ግን በታማኝነቱ በሕይወት ይኖራል።”
ዕንባቆም የኖረው በዚህ መንገድ ነው።
እኛም ይህን ማድረግ እንችላለን።
በይሖዋ መታመን ከታዛዥነት ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው?
ወንድም ዊሊያም ተርነር በማለዳ አምልኮ ንግግር ላይ
ይህን ሲያብራራ አብረን እንከታተል።
በይሖዋ አምላክ መታመን ያለብን እንዴት ነው?
በይሖዋ የምንታመነው ምንጊዜም
ሙሉ በሙሉ መሆን ይኖርበታል።
በጣም የሚገርመው ግን፣
መታመን የሚለውን ቃል ጽሑፎቻችን ላይ ብንፈልግ
ልንታመንባቸው የሚገቡ ሌሎች አቅጣጫዎችንም ይጠቁመናል።
ለምሳሌ በይሖዋ ስም፣
በቃሉ፣
በድርጅቱና
ልጁ በሚሰጠን አመራር።
ግን አንድ ጥያቄ እናንሳ።
ሙሉ በሙሉ መታመን ያለብን በይሖዋ አምላክ ላይ ከሆነ፣
አሁን በጠቀስናቸው ነገሮች ላይም እምነት መጣል ለምን አስፈለገ?
በመጀመሪያ በይሖዋ ሙሉ በሙሉ መታመን
ምን ማለት እንደሆነ እንወያይ።
እስቲ እባካችሁ ምሳሌ ምዕራፍ ሦስትን እናውጣ።
ጥቅሱን በደንብ እናውቀዋለን።
ምሳሌ 3:5, 6ን እናነባለን።
“በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን፣
“ደግሞም በገዛ ራስህ ማስተዋል አትመካ።
“በመንገድህ ሁሉ እሱን ግምት ውስጥ አስገባ፤
እሱም ጎዳናህን ቀና ያደርገዋል።”
JW ላይብረሪ አፕልኬሽናችሁ ላይ፣
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
የሚል ደስ የሚል ገጽታ አለ።
ምሳሌ 3:5, 6 በዚህ ጽሑፍ ላይ እንዴት እንደተብራራ እንመልከት።
ይህን ጽሑፍ ለማግኘት መነሻ ገጹ ላይ ሆናችሁ
ላይብረሪ የሚለውን ክፈቱ።
የሕትመት ውጤቶች በሚለው ሥር
ተከታታይ ርዕሶች የሚለውን ታገኛላችሁ።
ወደታች ስትወርዱ የምሳሌ መጽሐፍን ታገኛላችሁ።
ከዚያ ምሳሌ 3:5, 6 የሚለውን ክፈቱ።
በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን
በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ምን እንደሚል ተመልከቱ።
ወደ መሃል ገባ ብላችሁ 5ተኛው ዓረፍተ ነገር ላይ እንዲህ ይላል፦
“ስለዚህ በሙሉ ልባችን በአምላክ መታመን እንዲሁ የስሜት ጉዳይ ብቻ አይደለም።
“በሙሉ ልባችን በአምላክ የምንታመነው
“ፈጣሪያችን ለእኛ የተሻለውን ነገር እንደሚያውቅ
እርግጠኞች ስለሆንን ነው።”
በይሖዋ ሙሉ በሙሉ ለመታመን የምንወስነው
በስሜት ላይ ተመሥርተን አይደለም።
ይህ ምርጫ ነው።
በይሖዋ ለመታመን የምንወስነው
የማሰብ ችሎታችንንና ሕሊናችንን ተጠቅመን ነው።
ይህን የምናደርገው ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ባይገባንም
ወይም ዝርዝር ጉዳዮች ባይነገሩንም ጭምር ነው።
እስቲ ይሄን በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደግፈው።
እባካችሁ 2 ነገሥት ምዕራፍ 9ን አብረን እናውጣ።
2 ነገሥት ምዕራፍ 9
ኢዩ ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ የሚገልጽ ዘገባ ይዟል።
ከቁጥር 1 እስከ ቁጥር 3 ያለውን ዘገባ ስናነብ፣ ነብዩ ኤልሳዕ
ከነብያት ልጆች አንዱን ሄዶ ኢዩን እንዲቀባው እንዳዘዘው ይናገራል።
ኤልሳዕ የሰጠው መመሪያ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ ነው።
ኢዩ እንዴት እንደሚቀባ የሚገልጽ።
ከዚያም ኤልሳዕ የላከው ነብይ
የተሰጠውን ተልዕኮ ካጠናቀቀ በኃላ
በኢዩና በሠራዊቱ አለቆች መካከል
የተደረገውን ውይይት እናነባለን።
2 ነገሥት ምዕራፍ 9ን አውጥተን
ቁጥር 11ን እናንብብ።
እንዲህ ይላል፦
“ኢዩ ወጥቶ ወደ ጌታው አገልጋዮች ሲሄድ
“‘ሁሉም ነገር ደህና ነው?
“‘ይህ እብድ ወደ አንተ የመጣው ለምንድን ነው?’
ብለው ጠየቁት።
“እሱም ‘መቼም ሰውየውንም ሆነ የሚናገረውን ነገር
ታውቁታላችሁ’ አላቸው።
“እነሱ ግን ‘ይሄ እንኳ ትክክል አይደለም!
“‘ይልቅስ እውነቱን ንገረን’ አሉት።
“ከዚያም ኢዩ ‘እንግዲህ የነገረኝ ይህ ነው፤
“‘ደግሞም እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“‘“በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ።”’”
እስቲ እዚህ ጋር ቆም ብለን እናስብ።
እስካሁን ሁለት ነገሮችን አውቀናል።
አንደኛ ከኢዩ ጋር የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች
ነብዩ ያደረገውን ነገር ሙሉ በሙሉ አልተረዱትም ነበር።
ያደረገው ግራ የሚያጋባና እንግዳ የሆነ ነገር ነው።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ፣
ነብዩ ይዞ የመጣው መልእክት የራሱ ሳይሆን
ከሚያውቁት አካል የመጣ እንደሆነ ተገንዝበዋል።
የኢዩ አኳኋን አንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው
ነገር እንደተከናወነ የሚጠቁም ነው።
ኢዩ ነብዩ ያለውን ማለትም
ይሖዋ በወኪሉ አማካኝነት ምን እንዳለ ሲነግራቸው ምን አደረጉ?
ቁጥር 13ን እናንብብ።
“በዚህ ጊዜ እያንዳንዳቸው ቶሎ ብለው ልብሳቸውን በማውለቅ
“ደረጃዎቹ ላይ አነጠፉለት፤
ቀንደ መለከትም ነፍተው ‘ኢዩ ነግሦአል!’ አሉ።”
ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ ባይረዱትም፣
ዝርዝር ጉዳዮችን ባያውቁም፣
በሚያውቁት ነገር ላይ አሰላስለውበታል።
መመሪያው የመጣው ከየት እንደሆነ ገብቷቸዋል።
ስለዚህ በፍጥነት ድጋፋቸውን ሰጡት።
የሠራዊቱ አለቆች ኢዩን ቢጠራጠሩት
ወይም ደግሞ ስሜታዊ ቢሆኑ ኖሮ
በወቅቱ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስባችሁታል?
ይህ በኢዩ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድርበት ነበር?
ቁጥር 11 ላይ እንደምናየው
ኢዩ ነብዩ ያመጣውን መልዕክት
አድበስብሶ ለማለፍ የፈለገ ይመስላል።
ኢዩ፣ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን
በግልጽ መናገር ያልፈለገው
ለምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም።
ግን የሠራዊቱ አለቆች ለኢዩ ድጋፍ ለመስጠት
ፈጣን እርምጃ መውሰዳቸው
እንዲሁም መልእክቱ የመጣው ከይሖዋ እንደሆነ መተማመናቸው
በኢዩ ላይ ያሳደረውን አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማስተዋል ሞክሩ።
ቁጥር 14 እንደሚለው ‘እርምጃ እንዲወስድ አድርጎታል’።
ኢዩ የተሰጠውን ሥራ ወዲያውኑ ለመፈጸም ብርታት አግኝቷል።
ከዚህ ዘገባ የምናገኘው ትምህርት ምንድን ነው?
የዓለም ሁኔታ በጣም እየተለዋወጠ ስለሆነ እዚህ ቤቴልም ይሁን በመስኩ ላይ ላለን
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የተለያዩ መመሪያዎች ተሰጥተውናል።
ለውጡ ሊያሳስበን አልፎ ተርፎም
ሊያስጨንቀን እንደሚችል ይሖዋ ይገነዘባል።
በተለይ አንድ ጉዳይ ካልገባን
ወይም ዝርዝር ሁኔታዎችን ካላወቅን
ልንጨነቅ እንደምንችል ያውቃል።
ስለዚህ እኛም ልክ እንደ እነዚያ የሠራዊት አለቆች
ይሖዋ በሚጠቀምባቸው ወኪሎች ስንታመን
የተሰጠን መመሪያ ምንጭ እሱ እንደሆነ እምነት ሲኖረን
ይሖዋ ምን እንደሚሰማው አስቡ።
በመሆኑም በተሰጠን መመሪያ ስንታመንና
መመሪያውን ተግባራዊ ስናደርገው
ይሖዋ ባደረግነው ምርጫ እጅግ ይደሰታል።
እንዲሁም ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል።
ይህ ፍቅራችንንና በእሱ እንደምንታመን ከማሳየቱም በላይ
ታዛዥነታችን ሌሎችንም ያበረታታል!
ያጠናክራል!
ይሖዋም እንደሚባርከን ጥርጥር የለውም።
ታዲያ ይሄ ቅድም በጠቀስናቸው ነገሮች ላይ
ከመታመን ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው?
በአምላክ ስም፣ በቃሉ፣ በድርጅቱ ከመታመን ጋር እንዴት ይያያዛል?
ደግሞም ከየትኛውም ዝምድና ጋር በተያያዘ
የተናገርነው ነገር የሚረጋገጠው በድርጊታችን ነው።
ስለዚህ ይሖዋም ቢሆን ምን ያህል እንደምንወደውና
እንደምንተማመንበት በጸሎት አማካኝነት ስንገልጽለት ደስ ይለዋል።
ግን የተናገርነው ከልባችን እንደሆነ የሚታየው
ከእሱ ጋር ያለን ግንኙነት የሚጠናከረው
የተናገርነውን ነገር በተግባር ስንደግፈው ነው።
ይህ ደግሞ ይሖዋ ነገሮችን በሚያከናውንበት መንገድ
መታመንንና ከዚያ ጋር መተባበርን ይጨምራል።
በልጁ መታመንን፣ ጉባኤውን እንደሚመራ ማመንን፣
የድርጅቱ ምድራዊ ክፍል ማለትም ታማኝና ልባም ባሪያ በሚሰጠው መመሪያ መታመንን፣
አልፎ ተርፎም በጉባኤ ውስጥ ባሉ ሽማግሌዎች መታመንን ይጨምራል።
ሽማግሌዎች ፍጹማን ባይሆኑም እንኳ
ይሖዋ እንደሚተማመንባቸው ማስታውስ ይኖርብናል።
በእነዚህ ነገሮች ለመታመን ስንመርጥ
ለሌሎች የአምላክ አገልጋዮችም ጥሩ ምሳሌ እንሆናለን።
ከፊት ለፊታችን
ብዙ አስደሳች ነገሮች እንደሚጠብቁን እናውቃለን።
ግን ማስረጃዎቹ እንደሚጠቁሙት
የምንኖረው ለመቋቋም በሚያስቸግር
በዓይነቱ ልዩ በሆነ ዘመን ውስጥ ነው።
ስለዚህ በኢሳይያስ 30:15 ላይ የሚገኘውን
በመንፈስ መሪነት የተሰጠንን ምክር
ተግባራዊ ማድረጋችን ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ነው።
ሳንረበሽ በአምላካችን በይሖዋ ተማምነን በመኖር
ብርቱ መሆናችንን ማሳየታችንን እንቀጥላለን።
በይሖዋ የምንታመነው እንዲሁ ያለ ምክንያት አይደለም።
ከዚህ ይልቅ ይሖዋ ምንጊዜም የተሻለውን ነገር
እንደሚያደርግልን ስለምንተማመን ነው።
በይሖዋና በእሱ ደርጅት ስንታመን ውጤቱ አንድነት ነው።
የዚህ ወር የሙዚቃ ቪዲዮ
ምንም እንኳ የዚህ ዓለም መልክ እየተለዋወጠ ቢሆንም
አንድነታችን ለጥንካሬያችን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ያጎላል።
ስማኝ ጓዴ፣
ተጨንቋል ውስጤ፤
ወጀቡ ጸንቷል፤ ሊያሰምጠኝ ተቃርቧል።
አምላክ ወዶኝ ልጁን ሰጥቶኛል።
ልቤ ግን ሊያምን አልቻለም፤ አልረባም ይላል።
ና፣ አዳምጠኝ ላፍታ፤
አጽናናኝ፣ ልበርታ።
ሆነህ አይዞህ ባዬ፣ ስትቆም ከጎኔ፤
ተጠገነ ቅስሜ፣ ታበሰ ’ንባዬ።
እኛ ተደጋግፈን፣ ይሖዋን ይዘን
እንቆማለን ጸንተን፤ ለዘላለም አብረን።
ዘላለም አብረን።
አይዞህ ጓዴ፣
ሐዘንህ ሐዘኔ።
ብቻዬን ነኝ ብለህ እንዳትሰጋ።
አለሁ ጎንህ፣ መቼም አልተውህ፤
ይሖዋም ካጠገብህ መቼም አይርቅህ።
ልምጣ፣ ላዳምጥህ ላፍታ፤
ላጽናናህ፣ ላበርታህ።
ልሁን አይዞህ ባይህ፣ ልቁም ከጎንህ፤
እንዲጠገን ቅስምህ፣ ታብሶ እንባህ።
እኛ ተደጋግፈን፣ ይሖዋን ይዘን
እንቆማለን ጸንተን።
ልሁን አይዞህ ባይህ፣ ልቁም ከጎንህ፤
እንዲጠገን ቅስምህ፣ ታብሶ እንባህ።
እኛ ተደጋግፈን፣ ይሖዋን ይዘን
እንቆማለን ጸንተን፤
ለዘላለም አብረን።
አብረን ነን።
ዘላለም አብረን፣
አብረን ነን።
አደጋዎች ሲከሰቱ ከመንፈሳዊ ቤተሰባችን የምናገኘው ማጽናኛ
በዋጋ ሊተመን አይችልም።
በይሖዋ ድርጅት ላይ ያለን እምነት ሌሎች እምነታቸውን እንዲያጠናክሩ ያስችላቸዋል።
ወጣቶች፣ ጓደኞቻችሁ በየትኛውም መንገድ አምላክን ቢያመልኩ
ተቀባይነት እንዳለው ይሰማቸዋል?
እንዲህ ያለውን አስተሳሰብ ማስተካከል የሚቻለው እንዴት ነው?
ሁለት ወጣቶች አስተሳሰባቸውን ማስተካከል የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንይ።
‘እውነተኛው ሃይማኖት አንድ ብቻ ነው’
ብሎ ማመን ሊከብድ የሚችለው ለምንድን ነው?
በትምህርት ቤት ሁሉም ሃይማኖትና የአኗኗር ዘይቤ
ትክክል እንደሆነ እንድናምን ተጽዕኖ ይደረግብናል።
በአንድ ወቅት አገልግሎት ላይ አንድ ሰው በጣም ተቆጥቶ
“የእኛ ሃይማኖት ሆስፒታል ይሠራል፣ እርዳታ ይሰጣል።
ብዙ ነገር እናደርጋለን። እናንተ ግን ምንም አታደርጉም” አለን።
የተናገረው ነገር ትክክል ነው።
ግን እኛ እንደዛ የማናደርገው ለምንድን ነው?
‘ሌሎች ሃይማኖቶችም ጥሩ ነገር የሚያደርጉ ከሆነ
እውነተኛው የእኛ ሃይማኖት ብቻ እንዴት ይሆናል’ ብዬ አሰብኩ።
ነርሲንግ ስማር በተሰጠን የሙያ ሥነ ምግባር ትምህርት ላይ
ሃይማኖታችን ሕሙማንን በምንንከባከብበት መንገድ ላይ ስላለው ተጽዕኖ ተምረን ነበር።
ስለ ግብረ ሰዶማውያን፣ ፆታቸውን ስለቀየሩ ሰዎችና
የተለየ የአኗኗር ዘይቤ ስላላቸው ሰዎች ስንማር፣
አስተማሪዋ እያንዳንዳችን ያለንን አመለካከት ለማወቅ እየዞረች ጠየቀችን።
እኔ እንዳልጠየቅ በጣም ስለፈራሁ መሬት አፏን ከፍታ በዋጠችኝ ብዬ ነበር።
በጣም ነበር የተጨነኩት።
የምታምኑበት ነገር ትክክል መሆኑን ያረጋገጣችሁት እንዴት ነው?
ማቴዎስ 7:13, 14 ስለ ሁለት መንገዶች ይናገራል።
ትክክለኛው መንገድ አንድ ብቻ ነው።
ሌላው የተሳሳተ ነው።
ስለዚህ እምነቴን ማጠናከርና
ትክክለኛውን ቀጭኑን መንገድ እንደመረጥኩ ማረጋገጥ ነበረብኝ።
የግል ጥናት ሳደርግ ከሰውየው ጋር ያደረግነውን ውይይት መለስ ብዬ በማሰብ
ያነሳቸውን ጥያቄ በሙሉ ጻፍኩ።
ከዚያ በእያንዳንዱ ጥያቄ ላይ ምርምር አደረግኩ።
አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አገኘሁ።
ማቴዎስ 7:22, 23
እዚያ ላይ ኢየሱስ በስሙ ብዙ ተዓምራት ስላደረጉ ብቻ
በእሱ ዘንድ ተቀባይነት እንደማያገኙ አስጠንቅቋል።
እኛ የምናደርጋቸውን ነገሮች አሰብኩ።
ከፖለቲካ ገለልተኞች ነን።
ሁሉንም ዓይነት ሰዎች እንወዳለን።
በዓለም ዙሪያ ምሥራቹን እንሰብካለን።
ኢየሱስም ያዘዘው እነዚህን እንድናደርግ ነው።
ወዲያው መጸለይ ጀመርኩ።
ይሖዋም ረድቶኛል።
በድፍረት “ሕይወቴን የምመራው በራሴ ሳይሆን
በይሖዋ መሥፈርቶች ነው” ብዬ እንድመልስ ረድቶኛል።
ዮሐንስ 18:38 ላይ ጲላጦስ ኢየሱስን
“እውነት ምንድን ነው?” ብሎ በምጸት የጠየቀው
እውነት የሚባል ነገር እንደሌለና
ኢየሱስም ሊያገኘው እንደማይችል ስለተሰማው ነው።
ግን እሱ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች እውነት የሚባል ነገር እንደሌለና
ሰዎች እንደፈለጉት መኖር እንደሚችሉ ይሰማቸዋል።
ምሳሌ 22:3 “ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል” ስለሚል
ወደ ክፍል ከመግባታችን በፊት ምን እንደምንማር አይቼ ለመግባት እሞክራለሁ።
ተዘጋጅቼ ካልገባሁ ለእምነቴ በሚገባ ጥብቅና መቆም አልችልም።
ስለዚህ jw.orgን ተጠቀምኩ።
በድረ ገጹ ላይ የማምንበትን ነገር በዘዴ ለማስረዳት የሚረዱኝን የተለዩ ጽሑፎች አገኘሁ።
ያጋጠመኝ ነገር አገልግሎት ከመውጣት ወደኋላ እንድል ሊያደርገኝ እንደማይገባ ተገነዘብኩ።
ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ስለ እምነቴ የምናገርበት ሌላ አጋጣሚ አገኘሁ።
ለሰዎች የምናምንበትን ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ስላሳየናቸው ብቻ
እንዲያምኑበት ማድረግ አንችልም።
ለራሳችን ግን እውነትን እንዳገኘን ያረጋገጥልናል።
እውነተኛው ሃይማኖት አንድ ብቻ እንደሆነ ማመናችሁ የጠቀማችሁ እንዴት ነው?
በጣም ዓይናፋር ስትሆን ሌሎች በቀላሉ ተጽዕኖ ያሳድሩብሃል።
ለምታምንበት ነገር ጥብቅና መቆም በጣም ያስፈራል።
ግን በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው፣
እሱን የምናገለግልበት እውነተኛ መንገድ አንድ ብቻ ነው።
1 ቆሮንቶስ 1:10 ‘በአስተሳሰብ ፍጹም አንድነት ይኑራችሁ’ ይላል።
እርስ በርስ የሚቃረኑ ብዙ እውነቶች ሊኖሩ አይችሉም።
ይሖዋ ስለ እሱም ሆነ ስለ እውነተኛው ሃይማኖት የማወቅ ውድ መብት ሰጥቶኛል።
ይህን መብት ስለሰጠኝ የሚሰማኝን ጥልቅ ደስታና
የአመስጋኝነት ስሜት በቃላት ልገልጸው አልችልም።
ይህ ደግሞ ለሌሎች ስለ ይሖዋ በመናገር
እነሱም ይህን ውድ ስጦታ እንዲያገኙ ለመርዳት የምችለውን ሁሉ እንዳደርግ ያነሳሳኛል።
እውነተኛው ሃይማኖት አንድ ብቻ እንደሆነ ማመኔ ግራ እንዳልጋባና
አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜም ጭምር ጥሩ ውሳኔዎችን እንዳደርግ ረድቶኛል።
የአምላክ ቃል ለጥያቄዎቼ መልስ ስለሚሰጠኝና ስለሚመራኝ
በሕይወቴ ውስጥ ምንም ነገር ቢያጋጥመኝ ግራ አልጋባም።
ምክንያቱም እውነታውን አውቃለሁ።
አዎ፣ ድርጅታችን ሆስፒታሎችን አይገነባም።
ግን ሥራችን ሕይወት አድን ነው።
ሰዎች ከይሖዋ አምላክ ጋር እውነተኛ ወዳጅነት እንዲመሠርቱ እየረዳን ነው።
አስተማሪዎቻችሁ ወይም እኩዮቻችሁ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠይቀዋችሁ ያውቃሉ?
እንደ ናኦሚና እንደ ቪንስ እምነታችሁን ለማጠናከር ለምን ግብ አታወጡም?
ጥረት ማድረጋችሁን ከቀጠላችሁ ይሖዋ ለሚፈጠርባችሁ ማንኛውም ጥያቄ መልስ ይሰጣችኋል።
ወደ እሱ እንድትቀርቡም ይረዳችኋል።
ይሖዋ አገልግሎታቸውን ለማስፋት ብለው
የተመቻቸ ሕይወታቸውን ለመተው ፈቃደኛ የሆኑትን ይባርካል።
ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልግበት ቦታ የሄዱ ይህን ይነግሯችኋል።
ሰላም፣ ሮበርት ሚጊ እባላለሁ።
ሰባኪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉበት ቦታ እያገለገልኩ ነው።
አገሪቱ ውስጥ የሚያማምሩ ብዙ ቦታዎች ቢኖሩም
ይህን ቦታ ልዩ የሚያደርጉት ሰዎቹ ናቸው።
በልጅነቴ ወደ ሌላ አገር በመሄድ ሚስዮናዊ ሆኖ የማገልገል ምኞት ነበረኝ።
አሁን በየዕለቱ ያንን ማድረግ ችያለሁ።
ናፍቆትና አንዳንድ ሌሎች ነገሮች
ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄዶ ማገልገልን ከባድ ያደርጉታል።
ግን እዚህ ያገኘኋቸው ወንድሞች ልክ እንደ ቤተሰብ ሆነውልኛል።
ሁልጊዜም እንግዶችን ለመርዳት ፈቃደኞች ናቸው።
እኔንም በተደጋጋሚ ረድተውኛል።
መጀመሪያ ስመጣ የመኖሪያ ቤት እንዳገኝ ረድተውኛል።
ደህንነቴ ስለሚያሳስባቸው በየጊዜው እየመጡ ይጠይቁኛል።
ምግብም ያመጡልኛል።
አልፎ አልፎ ናፍቆት ቢያስቸግረኝም
እዚህ ያገኘሁት ቤተሰብ እንድቋቋመው ረድቶኛል።
በአገልግሎት የማሳልፈው ጊዜ በውሳኔዬ እንዳልቆጭ አድርጎኛል።
በዶሚኒካን ሪፑፕሊክ ውሎዬ ምን እንደሚመስል ላሳያችሁ።
ጠዋት 1:15 አካባቢ ከእንቅልፌ እነሳለሁ።
ከዚያም 2:30 ላይ ከቤት እወጣለሁ።
እዚህ ብዙ ሰው መኪና የለውም።
አብዛኛው ሰው የሚንቀሳቀሰው በሞተር ሳይክል ነው።
ደግሞም ይበልጥ ወጪ ቆጣቢ ነው።
በፊት ሞተር ሳይክል መንዳት አልችልም።
ለአገልግሎትም እጠቀምበታለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም።
ግን እንደ እኔ ከሌላ አገር የመጡና እዚህ ያሉ ወንድሞች መንዳት አስተማሩኝ።
አሁን የምንቀሳቀሰው በሞተር ሳይክል ነው።
ወደ አዳራሹ ለመድረስ 15 ደቂቃ አካባቢ ይፈጅብኛል።
የማገለግለው በአሜሪካ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ ውስጥ ነው።
ከስምሪት ስብሰባ በኋላ ወደ አገልግሎት ክልላችን እንሄዳለን።
እዚህ አገልግሎት በጣም ቀላል ነው።
ሰዎቹ ወዳጃዊና የሚቀረቡ ናቸው።
አገልግሎት ላይ የምናገኛቸው መስማት የሚችሉ ሰዎች
መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሚኖሩበትን ቦታ ያሳዩናል።
እነሱን ለማግኘት አንዳንዴ ረዘም ያለ መንገድ መጓዝ ይኖርብናል።
የመጣሁ ሰሞን እንዲህ ማድረግ ያስፈራኝ ነበር።
ግን የአገልግሎት ጓደኞቼ የተረጋጉ መሆናቸው
ፍርሃቴን እንዳሸንፍ ረድቶኛል።
የአካባቢው ሰዎች መስማት የተሳናቸውን ሰዎች እንድናገኝ ይረዱናል።
ለእነሱ መልካም ማድረጋችን ያስደስታቸዋል።
አብዛኞቹ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ስላላቸው
ውይይት መጀመር ቀላል ነው።
በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ካገለገልን በኋላ
ሁላችንም ኃይለኛውን የሙቀት ሰዓት
በየቤታችን አረፍ ብለን እናሳልፋለን።
ይህችን መልመድ አልከበደኝም።
በዚህ የእረፍት ሰዓት ምሳዬን እበላለሁ።
በጣም ከምወዳቸው ምግቦች አንዱ ላቫንዴራ ነው።
ሩዝ፣ ባቄላና የሆነ ዓይነት ሥጋ ይኖረዋል።
በምሳ ሰዓት ቡና እጠጣለሁ፤ ወይም አረፍ እላለሁ።
አሊያም የግል ጥናቴን አደርጋለሁ።
ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተመልሰን እንገናኝና
እስከ ምሽት ድረስ ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ እናስጠናለን።
እዚህ የፈለጋችሁትን ያህል ጥናት ማግኘት ትችላላችሁ።
እኔም ከምንም በላይ የወደድኩት ይህንን ነው።
ወደ ሌላ አገር ለመሄድ ስታስቡ ቶሎ ወደ አእምሯችሁ የሚመጣው
የምትከፍሉት መሥዋዕት ሊሆን ይችላል።
ግን በረከቱንም አስቡ።
በጣም የምወደውን ነገር ማድረግ
ማለትም ሌሎችን ስለ ይሖዋ ማስተማር ችያለሁ።
እንዲያውም አንዳንዶቹ እድገት አድርገው ተጠምቀዋል።
ከዚህ በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም።
እዚህ ባልመጣ ኖሮ የማላገኛቸውን ብዙ ተሞክሮዎች አግኝቻለሁ።
ከጉባኤውም ጋር አስደሳች ጊዜ እያሳለፍኩ ነው።
ይሖዋ ወንድሞችን፣ እህቶችን፣ እናቶችንና አባቶችን ስለሰጠኝ ብቸኝነት አይሰማኝም።
በዓለም ዙሪያ ወንድሞችና እህቶች እንዳሉን ማወቃችን ያስደስተናል።
ግን በዓይናችሁ ስታዩት ደግሞ ልዩ ስሜት ይፈጥርባችኋል።
መዝሙር 34:8 “ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም” ይላል።
እንዲህ ስታደርጉ ጣፋጭ ከሆኑ መንፈሳዊ በረከቶች ብፌ ማንሳት ትችላላችሁ።
ሰዎችን ስለ ይሖዋ ማስተማር የሚያስገኘው ደስታ
ከምንም ነገር ጋር ሊወዳደር አይችልም።
ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ መሄድ ካልቻላችሁ፣
አገልግሎታችሁን በሌላም መንገድ ማስፋት ትችላላችሁ።
በዚህ ፕሮግራም ላይ ከይሖዋ ድርጅት የሚሰጠንን መመሪያ መከተላችን
የሞትና የሕይወት ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ተምረናል።
ልክ እንደ ዕምባቆም ደግሞ ልባችንን በፊቱ በማፍሰስ
ውስጣችንን ማረጋጋትና በይሖዋ ይበልጥ መታመን እንችላለን።
የቾምባ ቤተሰብም በአስቸጋሪ ወቅት ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ታምኗል።
እንዲሁም መመሪያውን ተከትሏል።
በተጨማሪም በታማኝና ልባም ባሪያ በኩል
ከይሖዋ የሚሰጠንን መመሪያ መከተል ከፈለግን
እውነትን በራሳችን መርምረን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
በዚህ ወር ሰላምታ ይዘንላችሁ የመጣነው ከሰርቢያ ነው።
ሰርቢያ የባሕር በር የሌላት አገር ናት።
በስተሰሜን ለም የሆኑ ሜዳዎች፣
በስተምሥራቅ የኖራ ድንጋይ ሸለቆዎች፣
በስተምዕራብ የኮረብታ ሸንተረሮች፣
በስተደቡብ ደግሞ ተራሮች ያሏት አገር ናት።
ለም የሆነው መሬቷ ብዙ ምግብ ያመርታል።
ሰርቢያ እንጆሪ በብዛት በማምረት ወደ ውጪ በመላክ ትታወቃለች።
ሬብ ሲድ የሚባል የቅባት እህል በስፋት ይመረታል።
ከብቶቻቸውም የሚሰማሩት እዛው ነው።
ከከብቶቹ ስጋ ቼቫፒ የሚባል ታዋቂ የሆነ የባልካን ምግብ ያዘጋጃሉ።
የሚዘጋጀው እንዴት ነው?
የተፈጨ ሥጋ በደንብ ከተቀመመ በኋላ በረጅሙ ይጠቀለልና ይጠበሳል።
ከወተት ተዋጽኦ ከሚዘጋጅ ካይማክ ከሚባል ክሬም ጋር ተደርጎ
ጠፍጣፋ ቂጣ ውስጥ ይገባል።
እሁድ እንግዲህ ምሳ ተጋብዛችኋል።
አደራ አንዳትቀሩ!
ከሰዓት ቤተሰብ አንድ ላይ ተሰብስቦ እየተጨዋወቱ መመገብ የሰርቢያ ባሕል ነው።
ይህ ደግሞ ቤተሰቦች እንዲቀራረቡ ያደርጋል።
የአሁኗ ሰርቢያ በምትገኝበት በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ
የመንግሥቱን ምሥራች ለማዳረስ ብዙዎች በትጋት ሠርተዋል።
ከእነዚህ መካከል አንዱ ወታደር የነበረው ኒካ ትሬሊያ ነው።
በ1918 በኦስትሪያ-ሃንጋሪ ጦር ሰራዊት ውስጥ ወታደር እያለ
በሩሲያ ጦር ተማርኮ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቃ ወደምትገኘው
ወደ ሳይቤሪያ ተላከ።
እውነትን የሰማው እዛው ነው።
ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ አገሩ ተመልሶ ስብሰባዎችን ማደራጀት ጀመረ።
እዚያ የነበረው ሌላኛው ሰው ደግሞ ፍራንዝ ብራንድ የተባለ ወጣት ፀጉር አስተካካይ ነበር።
የመጋቢት 2026 ብሮድካስቲንግ ላይ ተጠቅሶ ነበር።
“በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ፀጉር አስተካካዮች”
በመባል ከሚታወቁት ውስጥ አንዱ ነበር።
ፍራንዝና የቀድሞ ደንበኛው ማለትም
በኋላ ላይ የአገልግሎት ጓደኛው የሆነው ሩዶልፍ ካሊ
የቅርንጫፍ ቢሮው የበላይ ተመልካቾች ሆነው አገልግለዋል።
በ1930 ማርቲን ፖይትጺንገርን ጨምሮ
ተሞክሮ ያላቸው 20 አቅኚዎች የስብከቱን ሥራ ለማስፋፋት ተላኩ።
የአገሪቱን ቋንቋ መናገር ስለማይችሉ
የመንግሥቱን ምሥራች ለመስበክ የምሥክርነት መስጫ ካርዶችን ይጠቀሙ ነበር።
ማርቲን ፖይትጺንገር በጽሑፍ የተሞላ ቦርሳውን ተሸክሞ
ምሥራቹን መስማት ለሚፈልጉ ሁሉ
በገጠራማ የአገሪቱ ክፍሎች ይሰብክ እንደነበር ተናግሯል።
ዛሬም ቢሆን በሰርቢያ እውነትን ለማዳረስ ብዙዎች ጠንክረው ይሠራሉ።
በቮይቪዲና ገበሬዎች በመከር ወቅት ብዙ ሥራ ይበዛባቸዋል።
ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች በብስክሌት ረጅም ርቀት በመጓዝ
እነዚህን ሰዎች ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ።
ሰርቢያ ውስጥ ከብዙ አገሮች የመጡ ሰዎች ይኖራሉ።
የሩሲያ፣ የቻይና፣ የኡሩዱ፣ የፋርሲና የሩማኒ ቋንቋ ተናጋሪዎች ይገኛሉ።
አስፋፊዎች የሩማኒ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለማግኘት
የሩማኒ ሰዎች ወደሚበዙባቸው አካባቢዎች ይሄዳሉ።
የሩማኒ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚኖሩት
ተጠጋግተው በተሠሩ ትናንሽ ቤቶች ውስጥ ነው።
አስደናቂ ውጤቶችም ተገኝተዋል።
የቤልግሬድ ሩማኒ ጉባኤ አስፋፊዎች
46 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ይመራሉ።
የአስፋፊዎችን እጥፍ የሚያህል ሰው በስብሰባዎች ላይ ይገኛል።
በቤልግሬድ ሩማኒ ጉባኤ ውስጥ የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች
ሞቅ ያለ ፍቅራዊ ሰላምታቸውን ልከውላችኋል።
የእኛም ፍቅራዊ ሰላምታ ይድረሳችሁ።
ይህ ከይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት የሚተላለፍላችሁ
JW ብሮድካስቲንግ ነው!