JW ብሮድካስቲንግ—ጥቅምት 2026
Video
Other languages
Share text
Share link
Show times
Hide times
00:00:00
ወንድሞችና እህቶች፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!00:00:04
00:00:04
ጥሩ እይታ እንዳለን ለማወቅ በየጊዜው የዓይን ምርመራ እናደርጋለን።00:00:09
00:00:09
ግን መንፈሳዊ እይታችንንስ እንመረምራለን?00:00:12
00:00:12
መንፈሳዊ እይታችን እየደበዘዘ እንደሆነ ከተሰማን 00:00:16
00:00:16
ጥርት ያለ እይታ እንዲኖረን ምን ማድረግ እንችላለን?00:00:19
00:00:19
አንዳንዶች ጥርት ያለ መንፈሳዊ እይታ እንዲኖራቸው የረዳቸው አንዱ ነገር ቤቴል በተመላላሽነት ማገልገላቸው ነው።00:00:26
00:00:26
ይህ ምን እንደሚመስል እናያለን።00:00:29
00:00:29
ስለ አስደናቂው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ታሪካችንም እንመለከታለን።00:00:33
00:00:35
ይህ JW ብሮድካስቲንግ ነው!00:00:37
00:00:57
እይታችሁ እንዴት ነው?00:00:58
00:00:59
እንደ እኔ መነጽር የምታደርጉ ከሆነ 00:01:01
00:01:01
ዓይናችሁ በመጠኑም ቢሆን ችግር አለበት ማለት ነው።00:01:04
00:01:04
የኔ ችግር ማዮፒያ ይባላል።00:01:06
00:01:06
ከርቀት የማየት ችግር ነው።00:01:07
00:01:08
አንድን ነገር ሳይ የማየው ነገር ምሥል ሬቲናዬ ላይ ከማረፍ ይልቅ 00:01:12
00:01:12
ከሬቲናዬ ፊት ለፊት ይቀመጣል። 00:01:14
00:01:15
ይህ ደግሞ ሩቅ ያሉ ነገሮች በደንብ አንዳይታዩኝ ያደርጋል።00:01:18
00:01:18
የዚህ ተቃራኒ ችግር ደግሞ ሃይፕሮፒያ ይባላል። 00:01:21
00:01:21
ቅርብ የሆነ ነገር የማየት ችግር ነው።00:01:23
00:01:23
የምናየው ምሥል ከሬቲናችን ጀርባ ስለሚሄድ 00:01:25
00:01:25
ቅርብ ያሉ ነገሮችን ጥርት አድርጎ ማየት ያስቸግራል።00:01:28
00:01:29
ሁለቱም ችግሮች ሊኖሩብንም ይችላል። 00:01:31
00:01:31
አንዱ ከቅርብ፣ አንዱ ከሩቅ ማየት ሊቸግረው ይችላል።00:01:33
00:01:34
ያም ሆነ ይህ ችግሩን ለማስተካከል ተገቢውን መነጽር ስናደርግ 00:01:38
00:01:38
ዓይናችን በትክክል ማየት ይችላል።00:01:41
00:01:42
አንደ ዓይነስውርነት ያለ የከፋ ችግርም አለ።00:01:44
00:01:44
ይህ የሚስተካከለው ግን በአዲሱ ሥርዓት ነው።00:01:47
00:01:48
ሆኖም አሁን ከጠቀስኩት ይበልጥ እጅግ አደገኛ የሆነ የእይታ ችግር አለ።00:01:53
00:01:54
ይህን ችግር ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ ጠቅሶታል።00:01:57
00:01:57
ማቴዎስ ምዕራፍ 6ን እናውጣና 00:01:59
00:01:59
ቁጥር 22 እና 23 ላይ ምን እንዳለ እንመልከት።00:02:03
00:02:04
“የሰውነት መብራት ዓይን ነው።”00:02:06
00:02:07
እስቲ እዚህ ላይ ቆም እንበል።00:02:08
00:02:08
ኢየሱስ “የሰውነት መብራት ዓይን ነው” ሲል ምን ማለቱ ነው?00:02:12
00:02:13
ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው።00:02:14
00:02:15
ዓይናችን በጨለማ መንገድ ላይ እንደተተከለ መብራት ነው።00:02:18
00:02:18
ሳንደናቀፍ እንድንሄድ ይረዳናል።00:02:21
00:02:22
በተጨማሪም ኢየሱስ ስለ ምሳሌያዊው ዓይናችንም መናገር ፈልጓል።00:02:26
00:02:26
ይሖዋ ያዘዘንን ነገር ለማደርግ ያለንን አመለካከት ማለት ነው!00:02:30
00:02:31
በመቀጠል ደግሞ ኢየሱስ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን አነጻጽሮ ተናገረ።00:02:36
00:02:36
ንባባችንን እንቀጥል።00:02:37
00:02:37
“ዓይንህ በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ ከሆነ መላ ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል።00:02:41
00:02:41
ይሁን እንጂ ዓይንህ ምቀኛ ከሆነ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል።”00:02:46
00:02:46
ያነጻጸረው በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ ዓይንንና ምቀኛ የሆነን ዓይን ነው።00:02:51
00:02:51
የመጀመሪያው ሕይወታችንን ብሩህ ያደርጋል።00:02:53
00:02:53
ሁለተኛው ደግሞ ሕይወታችንን ያጨልማል።00:02:56
00:02:56
የምንመርጠው ነገር በሕይወታችን ላይ ለውጥ ያመጣል።00:02:59
00:02:59
በጥሩ ወይም በመጥፎ!00:03:01
00:03:02
እኛም በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ምንጊዜም ትኩረት ማድረግ አለብን።00:03:06
00:03:06
የዚህ ንግግር ጭብጥም ትኩረታችን የአምላክን ፈቃድ በመፈጸም ላይ ይሁን የሚል ነው።00:03:11
00:03:12
ግን አምላክ ለእኛ ያለው ፈቃድ ምንድን ነው?00:03:15
00:03:15
በአጭሩ እሱ ከእኛ የሚፈልገው እንድናውቀው፣ 00:03:18
00:03:18
ወደ እሱ እንድንቀርብ፣ እንድንታዘዘው፣ እንድንወደውና እንድናገለግለው ነው።00:03:22
00:03:22
በሙሉ ልባችን!00:03:24
00:03:24
በዚህ ረገድ ኢየሱስ ጥሩ ምሳሌ ትቶልናል።00:03:27
00:03:27
ዮሐንስ 6:38 ላይ የሕይወቱ ዋነኛ ዓላማ 00:03:31
00:03:31
‘የእሱን ፈቃድ ሳይሆን የላከውን ፈቃድ መፈጸም’ እንደሆነ ተናግሯል።00:03:34
00:03:35
የኢየሱስ ዓይን ያተኮረው በአንድ ነገር ላይ ብቻ ነበር።00:03:38
00:03:38
በአገልግሎቱ ላይ!00:03:39
00:03:40
ጊዜውንና ጉልበቱን መንግሥቱን ለማስፋፋት ተጠቅሞበታል።00:03:43
00:03:43
ዓለማዊ ግቦችን ለማሳደድ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ለማግኘት 00:03:47
00:03:47
ወይም ቁሳዊ ነገሮችን ለማካበት አልሞከረም።00:03:50
00:03:51
ተከታዮቹንም ምንጊዜም ይሖዋን በማገልገል ላይ እንዲያተኩሩ አበረታቷቸዋል።00:03:55
00:03:56
ወደ አምላክ መንግሥት የሚገቡት የአባቱን ፈቃድ የሚያደርጉ ብቻ እንደሆኑ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል።00:04:01
00:04:03
ሁላችንም ትኩረት ማድረግ ያለብን በዚህ ላይ ነው።00:04:05
00:04:05
መንግሥቱን በማስቀደምና በቅንዓት በመስበክ 00:04:08
00:04:08
ሕይወታችን በአምላክ ፈቃድ ዙሪያ እንዲያጠነጥን ማድረግ ይኖርብናል።00:04:13
00:04:14
በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ ዓይን ያለው ሰው ቀላል ሕይወት ይመራል።00:04:17
00:04:17
ኑሮውንም አያወሳስብም።00:04:19
00:04:19
የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ለማግኘት ወይም00:04:22
00:04:22
ዓለም የሚያቀርበውን ሁሉ ለማግበስበስ አንሯሯጥም።00:04:25
00:04:26
በአምላክ ፈቃድ ላይ ብቻ በማተኮር መንፈሳዊው ዓይናችን ብሩህ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ እንችላለን።00:04:31
00:04:32
ይህ ደግሞ ምቀኛ ዓይን ካላቸውና አስፈላጊ በሆነው ነገር ላይ ማተኮር ከማይችሉ ሰዎች ዓይን በጣም የተለየ ነው። 00:04:39
00:04:39
የእነዚህ ሰዎች መንፈሳዊ ዓይን ቅብዝብዝ፣ ሸውራራና ስግብግብ ነው።00:04:44
00:04:45
ምሳሌ 17:24 እንደሚለው ዓይናቸው ‘እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታል’።00:04:50
00:04:50
አስተሳሰባቸውና ምኞታቸው እዚህም እዚያም የተበታተነ ነው።00:04:54
00:04:54
ዋናውን ነገር ግን ይተዉታል።00:04:56
00:04:57
አምላክን ከማገልገል ይልቅ በቁሳዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ሕይወታችን ጨለማ እንዲሆን ያደርጋል።00:05:02
00:05:04
ኢየሱስ ያለውን ለመረዳት ዓይናችን የሚሠራበትን መንገድ እንመልከት።00:05:08
00:05:09
ይህ ሥዕል በ1915 የታተመ ነው።00:05:13
00:05:13
ያዘጋጀው ዊሊያም ሂል የተባለ ታዋቂ ሠዓሊ ነው።00:05:16
00:05:16
እዚህ ሥዕል ላይ የሁለት ሰዎች ጭንቅላትና ትከሻ ይታያል።00:05:23
00:05:23
የአንዲት ወጣትና የአንዲት አሮጊት ሴት!00:05:25
00:05:26
ሁለቱንም አያችኋቸው?00:05:28
00:05:28
የወጣቷ ፊት በከፊል ነው የሚታየው።00:05:30
00:05:31
ይሄ የግራ ጉንጯ ነው።00:05:33
00:05:34
የግራ ጆሮዋ፣ 00:05:35
00:05:36
አፍንጫዋ፣ 00:05:37
00:05:37
ሽፋሽፍቷ፣ 00:05:39
00:05:39
ይሄ ደግሞ መንጋጭላዋ።00:05:40
00:05:40
አንገቷ ላይ ደግሞ የሆነ ነገር አስራለች።00:05:42
00:05:43
ይሄ ጸጉሯ ነው፤ 00:05:44
00:05:44
ይሄ ደግሞ ኮፍያዋ።00:05:46
00:05:46
ይሄ ትከሻዋ ነው።00:05:47
00:05:49
አሮጊቷ ሴትስ?00:05:50
00:05:50
የሚታየው የግራ ፊቷ ነው።00:05:52
00:05:53
ይህ አፍንጫዋ ነው።00:05:54
00:05:56
ግራ ዓይኗ፣ 00:05:57
00:05:58
አፏ፣00:05:59
00:05:59
አገጯ፣ 00:06:00
00:06:00
ይሄ ደግሞ ጸጉሯ፣ 00:06:02
00:06:02
ኮፍያዋ፣ 00:06:03
00:06:03
ይሄ ደግሞ ትከሻዋ።00:06:04
00:06:05
በአንድ ጊዜ ሁለቱንም ሴቶች ማየት አትችሉም።00:06:07
00:06:07
አንዱ ላይ ማተኮር ይኖርባችኋል።00:06:09
00:06:09
የምታዩት ትኩረት ያደረጋችሁባትን ሴት ነው።00:06:12
00:06:13
እስቲ ከምንጋገርበት ነጥብ ጋር እናያይዘው።00:06:15
00:06:16
በዙሪያችሁ ያለውን አሮጌ ዓለም ከአምላክ አዲስ ዓለም አንጻር እንዴት ታዩታላችሁ?00:06:21
00:06:22
ሰይጣን የእሱን ዓለም ማራኪ፣ አጓጊና አስደሳች ነገሮች የሞሉበት አድርጎ ለማቅረብ ይሞክራል።00:06:28
00:06:29
እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የእሱ አሮጌ ዓለም እዚህ ላይ እንደምትታየው አሮጊት ነው።00:06:34
00:06:34
በቅርቡ የአምላክ መንግሥት መጥቶ ሙሉ በሙሉ ጠራርጎ ያጠፋዋል።00:06:38
00:06:39
ከዚህ በተቃራኒው አዲሱን ዓለም በወጣቷ ሴት ልንመስለው እንችላላን።00:06:43
00:06:43
የአምላክ አዲስ ዓለም ውበቱን እንደያዘ ለዘላለም ይቀጥላል።00:06:47
00:06:47
በዚያ የሕያዋን ፍጥረታት ፍላጎት ሁሉ ይሟላል።00:06:51
00:06:52
ስለዚህ ይሖዋ የሰጠንን የማስተዋልና የማመዛዘን ችሎታ ተጠቅመን 00:06:56
00:06:56
በሰይጣን ዓለምና በአዲሱ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ አለብን።00:07:00
00:07:00
የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በዚህ ረገድ ይረዳናል።00:07:04
00:07:04
በአንድ ጊዜ ሁለቱም ነገሮች ላይ ማተኮር አንችልም።00:07:07
00:07:07
ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ቁሳዊ ነገሮችን እያሳደደ 00:07:11
00:07:11
ይሖዋ አምላክን በሙሉ ልቡ ማገልገል አይችልም።00:07:15
00:07:18
ሐዋርያው ዮሐንስ ለዚህ ዓለም የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ነበረው።00:07:22
00:07:22
ይህን ዓለም አስመልክቶ የተናገረውን 1 ዮሐንስ 2:15-17 ላይ እንመልከት። 00:07:28
00:07:28
ልንወዳቸው የማይገቡ ሁለት ነገሮችን ጠቅሷል።00:07:31
00:07:32
ከእነዚህ ሁለት ነገሮች አለመውደድ የሚቀልለን የትኛውን ነው?00:07:38
00:07:38
“ዓለምንም ሆነ በዓለም ውስጥ ያሉትን ነገሮች አትውደዱ።00:07:42
00:07:42
“ማንም ዓለምን የሚወድ ከሆነ የአብ ፍቅር በውስጡ የለም፤ 00:07:47
00:07:47
“ምክንያቱም በዓለም ያለው ነገር ሁሉ ይኸውም የሥጋ ምኞት፣ የዓይን አምሮትና 00:07:54
00:07:54
“ኑሮዬ ይታይልኝ ማለት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመነጭ አይደለም።00:07:58
00:07:58
“ከዚህም በተጨማሪ ዓለምም ሆነ ምኞቱ ያልፋሉ፤00:08:02
00:08:02
የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።”00:08:07
00:08:08
አትውደዱ ከተባልናቸው ሁለት ነገሮች ማለትም ከዚህ ዓለምና በውስጡ ካሉት ነገሮች አለመውደድ የሚቀለን የቱ ነው?00:08:16
00:08:16
ዓለምን አለመውደድ ይቀላል ቢባል አትስማሙም?00:08:19
00:08:19
ምክንያቱም የሰይጣን ዓለም ማለትም የሐሰት ሃይማኖት፣ የፖለቲካው ሥርዓት፣ የንግዱ ሥርዓት 00:08:25
00:08:25
ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፉ ለማየት እንመኛለን።00:08:29
00:08:30
ሆኖም የሰይጣን ዓለም ትኩረታችንን የሚከፋፍሉ በርካታ ነገሮችን ያቀርባል።00:08:35
00:08:35
በዚህ ዓለም ውስጥ ያሉ አንዳንድ ነገሮች በጣም የሚያጓጉ፣ የሚያማልሉና የሚማርኩ ሊሆኑ ይችላሉ።00:08:41
00:08:41
ሰይጣን እነዚህን ነገሮች ተጠቅሞ የሰው ልጆችን ያሳስታል።00:08:45
00:08:45
የሰው ልጆችን በማታለል ረገድ በጣም ውጤታማ ከሆኑለት መሣሪያዎች አንዱ የዓይን አምሮት ነው።00:08:52
00:08:53
አንዲት ፍሬ ብቻ በመጠቀም ሔዋንን ጉድ እንደሠራት አስታውሱ!00:08:57
00:08:58
‘በዓለም ውስጥ ያሉ ነገሮች እየማረኩኝ ነው?’ የሚለውን ለማጣራት በየጊዜው ልባችንን እንፈትሽ። 00:09:04
00:09:04
አንድ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ባሉ ነገሮች ላይ ካተኮረ 00:09:07
00:09:07
አልፎ ተርፎም እነዚህን ነገሮች መመኘት ከጀመረ00:09:10
00:09:10
ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን የአምላክን ፈቃድ ማድረግ ከባድ ይሆንበታል።00:09:14
00:09:15
ስለዚህ ትኩረታችን ይሖዋን በሙሉ ልባችን በመውደድና 00:09:19
00:09:19
ለእሱ ምርጣችንን በመስጠት ላይ ማረፍ ይኖርበታል።00:09:22
00:09:23
በየጊዜው የዓይን ምርመራ ማድረጋችን ጠቃሚ እንደሆነ ሁሉ 00:09:27
00:09:27
መንፈሳዊ እይታችንን ማስተካከል ያስፈልግ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ00:09:31
00:09:31
በየጊዜው ራሳችንን መመርመራችንም ጥበብ ነው።00:09:34
00:09:35
መንፈሳዊ እይታችንን እንዴት እንመርምር?00:09:37
00:09:38
ለዓይን ምርመራ የምንጠቀምበትን ሰንጠረዥ ታውቁታላችሁ? 00:09:41
00:09:41
ዓይናችንን ለመመርመር የምንጠቀምበት ሰንጠረዥ ነው።00:09:44
00:09:44
በተመሳሳይም 2 ጴጥሮስ 1:5-7 ላይ ለምርመራ የሚረዱ ባሕርያት ተዘርዝረዋል።00:09:50
00:09:51
እስቲ እናንብባቸው።00:09:53
00:09:54
“በመሆኑም ልባዊ ጥረት በማድረግ በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ጨምሩ፤ 00:09:59
00:09:59
“በበጎነት ላይ እውቀትን፣ በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፣ 00:10:04
00:10:04
“ራስን በመግዛት ላይ ጽናትን፣ በጽናት ላይ ለአምላክ ማደርን፣ 00:10:10
00:10:10
“ለአምላክ በማደር ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣ 00:10:13
00:10:13
በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።”00:10:16
00:10:17
እነዚህን ባሕርያት በሕይወታችን በማንጸባረቅ ረገድ እንዴት ነን?00:10:21
00:10:21
እስቲ አንድ በአንድ እንያቸው።00:10:23
00:10:24
እምነት፣ 00:10:25
00:10:25
ሌሎቹን ባሕርያት በሙሉ ለማዳበር ይህ ባሕርይ የግድ ያስፈልገናል።00:10:29
00:10:29
እምነታችንን በየጊዜው ማጠናከር ይኖርብናል።00:10:33
00:10:33
ጠንካራ እምነት ካለን ይሖዋ የሰጣቸው ተሰፋዎች በሙሉ እንደሚፈጸሙ እርግጠኞች እንሆናለን።00:10:38
00:10:38
በእምነት ዓይናችን ወደፊት የሚፈጸሙትን ተስፋዎች ማየት እንችላለን።00:10:42
00:10:42
በጎነት፣ 00:10:44
00:10:44
በጎነት በአምላክ ዓይን ትክክል የሆነውን ማድረግ ማለት ነው።00:10:48
00:10:48
ሌሎችን የሚጎዳ ወይም መጥፎ ነገር ከማድረግ እንድንቆጠብ ያደርገናል።00:10:52
00:10:52
በተጨማሪም ለሌሎች መልካም ለማድረግ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን እንድንፈልግ ያደርገናል።00:10:57
00:10:57
እውቀት፣ 00:10:59
00:10:59
በተለይ አዳዲስ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን 00:11:01
00:11:01
ትክክል የሆነውን ካልሆነው ለመለየት እውቀት የግድ ያፈልገናል።00:11:05
00:11:05
መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት በማጥናት ይሖዋ ከእኛ ምን እንደሚፈልግ መረዳት እንችላለን።00:11:10
00:11:10
በሕይወታችን ውስጥ ጥበብ ያዘሉ ውሳኔዎችንም ማድረግ እንችላለን።00:11:14
00:11:14
ራስን መግዛት፣ 00:11:16
00:11:16
ግሪክኛው ቃል በቃል “ራስን አጥብቆ መያዝ” የሚል ፍቺ አለው።00:11:20
00:11:20
ኃጢአት እንዳንሠራ በአስተሳሰባችን፣ በንግግራችንና በድርጊታችን ላይ ገደብ በማበጀት 00:11:26
00:11:26
ሕይወታችንን ከአምላክ መሥፈርቶች ጋር በሚስማማ መንገድ እንድንመራ ይረዳናል።00:11:31
00:11:32
ጽናት፣ 00:11:33
00:11:33
ይሖዋ በሚሰጠው ጥንካሬ በመታመን በድፍረት ተስፋ ሳይቆርጡ መቀጠል ማለት ነው።00:11:39
00:11:39
አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ተስፋው እንዳይጠፋብን ይረዳናል።00:11:43
00:11:43
ጽናት ስደት ሲያጋጥመንና በፈተና እንዳንወድቅ ጥረት ስናደርግ የይሖዋን እጅ ለማየት ያስችለናል።00:11:49
00:11:50
ለአምላክ ማደር፣ 00:11:52
00:11:52
በውስጣችን ስለ ይሖዋ የሚሰማን ስሜት ነው።00:11:55
00:11:55
አምላከን እንድናከብረው፣ እንድንፈራው፣ ለሉዓላዊነቱ እንድንገዛ ያደርገናል።00:11:59
00:12:00
ይሖዋ ሕዝቦቹን እንዴት እንደያዛቸው እንድናይ ያስችለናል።00:12:03
00:12:03
ለአምላክ ባለን ፍቅር ተነሳስተን እሱን በሚያስደስት መንገድ እንድንኖር ያነሳሳናል።00:12:08
00:12:09
ወንድማዊ መዋደድ፣00:12:11
00:12:11
ወንድማዊ መዋደድ ይሖዋን ለመምሰል ያስችለናል።00:12:14
00:12:14
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ድክመት ላይ እንዳናተኩር ያደርገናል።00:12:18
00:12:19
እንደ ቤተሰባችን እንድንወዳቸውና በተቻለን መጠን እንድንረዳቸው ያነሳሳናል።00:12:24
00:12:24
ፍቅር፣ 00:12:26
00:12:26
ለወንድሞቻችን ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር የይሖዋ ዓይነት አመለካከት እንዲኖረን ያስችለናል።00:12:32
00:12:32
በመንፈሳዊ እንድንረዳቸው ማለትም ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመን እውነትን እንድንነግራቸው ያነሳሳናል።00:12:39
00:12:40
ምሳሌያዊውን ሰንጠረዥ ተጠቅመን እይታችንን መርምረናል።00:12:43
00:12:43
ቀጣዩቹ ቁጥሮች ደግሞ የምርመራውን ውጤት ይነግሩናል።00:12:46
00:12:46
“እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና ቢትረፈረፉ፣ 00:12:49
00:12:49
“ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ትክክለኛ እውቀት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ00:12:53
00:12:53
“ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ይጠብቋችኋል።00:12:57
00:12:57
እነዚህ ነገሮች የሚጎድሉት ማንኛውም ሰው ብርሃን ላለማየት ዓይኑን የጨፈነ ዕውር ሰው ነው።”00:13:02
00:13:03
ጥሩ መንፈሳዊ እይታ ያለን መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው።00:13:06
00:13:06
ይህን ምክር በመከተል ልባዊ ጥረት ካደረግን እነዚህ ስምንት ባሕርያት በውስጣችን ይትረፈረፋሉ።00:13:12
00:13:13
ከአምልኳችን ጋር በተያያዘ ሥራ ፈት ወይም ፍሬ ቢስ አንሆንም።00:13:16
00:13:17
ከዚህ ይልቅ የአምላክ ፈቃድ በማደረግ ረገድ ፍሬያማ እንሆናለን።00:13:21
00:13:21
እነዚህን ባሕርያት ማንጸባረቅ ከተሳንን ግን በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት እናጣለን።00:13:26
00:13:26
በመንፈሳዊም እንታወራለን።00:13:28
00:13:29
በአንዳንዶቹ ባሕርያት ረገድ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገን አስተውለን ይሆናል።00:13:33
00:13:34
እይታችንን በማጥራት ትክክለኛው ነገር ላይ ማተኮር ይኖርብን ይሆናል።00:13:38
00:13:38
ይህን እንዴት እናድርግ?00:13:40
00:13:40
እስቲ አራት ነገሮችን እንመልከት።00:13:42
00:13:43
አንደኛ፣ የአምላክን ቃል ማጥናትና ማሰላሰል00:13:46
00:13:47
የዓይን ሐኪም ጋር ብትሄዱ ዓይናችሁ እርጥበት እንዲኖረውና ቶሎ እንዲድን ጠብታ ያዝላችሁ ይሆናል።00:13:53
00:13:53
ዓይናችሁ እንዲያርፍና መድኃኒቱ እንዲሠራም የዓይን መሸፈኛ ሊሰጣችሁ ይችላል።00:13:57
00:13:58
በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መንፈሳዊ ዓይናችን00:14:01
00:14:01
በእውነት ውኃ እንዲረጥብና በአምላክ ቃል እንዲታከም ያደርጋል።00:14:05
00:14:06
ማሰላሰል ደግሞ መመሪያዎቹ ከእኛ ጋር እንዲዋሃዱና ወደ ልባችን ጠልቀው እንዲገቡ ያስችላል።00:14:12
00:14:12
ይህ ደግሞ የይሖዋን ፈቃድ፣ አስደናቂ ሥራዎቹን እንዲሁም የሰጠንን ተስፋ እንዳንረሳ ይረዳናል።00:14:19
00:14:20
የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የሆኑት ዊሊያም ባርክሌ እንዲህ ብለዋል፦ 00:14:23
00:14:23
“ለአንድ ቅን ክርስቲያን የአምላክን ቃል ማጥናት የሚያስደስት ነገር እንጂ አድካሚ ሥራ አይደለም።00:14:29
00:14:29
ምክንያቱም ልቡ የሚናፍቀውን ምግብ የሚያገኘው ከዚህ የአምላክ ቃል እንደሆነ ያውቃል።”00:14:34
00:14:35
ሁለተኛ፣ የተማርነውን ተግባራዊ ማድረግ00:14:38
00:14:38
እይታችንን እየለዋወጥን የዓይናችንን ጡንቻዎች ማሠራት እንችላለን።00:14:42
00:14:42
በተመሳሳይም የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች በሕይወታችን ተግባራዊ ስናደርግ ምክሮቹ ጠቃሚ እንደሆኑ እንገነዘባለን።00:14:49
00:14:49
በተጨማሪም በአገልግሎት በቅንዓት በመካፈልና በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ በመስጠት እምነታችንን በሥራ መደገፍ እንችላለን።00:14:57
00:14:58
ሦስተኛ፣ የመንፈስ ቅዱስን አመራር መከተል00:15:01
00:15:03
አንዳንድ ውስብስብ የሆኑ የዓይን ችግሮችን ለማከም የጨረር ሕክምና ማግኘት ያስፈልግ ይሆናል።00:15:09
00:15:10
የአምላክ መንፈስ በምሳሌያዊ ሁኔታ መንፈሳዊነታችንን እንደሚያክም ጨረር ነው ማለት ይቻላል።00:15:16
00:15:16
የአምላክ መንፈስ አስተሳሰባችንና ድርጊታችንን እንዲመራው በፈቀድን መጠን መንፈሳዊ እድገታችንም እየጨመረ ይመጣል።00:15:23
00:15:23
አራተኛ፣ የሌሎችን እርዳታ መቀበል00:15:26
00:15:26
አንዳንዴ ሐኪማችን የዓይን ቀዶ ሕክምና ማድረግ እንዳለብን ሊወስን ይችላል።00:15:31
00:15:32
በተመሳሳይም አንዳንድ ጊዜ ሽማግሌዎች ከምንም ነገር በላይ ስለት ያለውን የአምላክን ቃል በመጠቀም00:15:37
00:15:37
ቀጥተኛ ምክር ወይም ከባድ ተግሣጽ ሊሰጡን ይችላሉ።00:15:41
00:15:41
የሚሰጠንን ምክር ከተቀበልን ተጠቃሚዎች እንሆናለን።00:15:45
00:15:47
እስካሁን ምን ተማርን?00:15:48
00:15:49
እይታችን በትክክለኛው ነገር ላይ ካተኮረ አእምሯችን ስለ አምላክ ፈቃድ፣00:15:54
00:15:54
ስለ መንግሥቱና ስለሰጠን ተስፋዎች ጥርት ያለ እይታ ይኖረዋል።00:15:58
00:15:58
ምቀኛ ዓይን ካለን ስለ አዲሱ ዓለም ያለን እይታ ደብዛዛ ይሆንብናል።00:16:03
00:16:03
እውን ሆኖም አይታየንም።00:16:04
00:16:05
ቅድም እንዳሳየኋችሁ ዓይናችን በተመሳሳይ ጊዜ በሁለት ነገሮች ላይ ማተኮር አይችልም።00:16:10
00:16:11
በዚህ አሮጌ ዓለም ባሉ ነገሮች የምንቀና ከሆነ የአምላክ ፈቃድ እየደበዘዘብን ይመጣል።00:16:16
00:16:16
ቀስ በቀስ ደግሞ ከእይታችን ይሰወራል።00:16:19
00:16:19
ማናችንም ብንሆን ይህ እንዲደርስብን አንፈልግም።00:16:23
00:16:24
መንፈሳዊ ዓይናችን ምንጊዜም በአምላክ ፈቃድ ላይ እንዲያተኩር ማድረጋችን በጣም አስፈላጊ ነው።00:16:29
00:16:29
እንግዲያው ለሰማያዊው አባታችን ለዘላለም የሙሉ ነፍስ አገልግሎት ማቅረባችንን እንቀጥል።00:16:36
00:16:38
አንድ ባልና ሚስት ጥርት ያለ መንፈሳዊ እይታ እንዲኖራቸውና00:16:42
00:16:42
ደስተኞች እንዲሆኑ የረዳቸው ምን እንደሆነ እስቲ እንመልከት።00:16:45
00:16:49
ገና በሃያዎቹ ዕድሜ መጀመሪያ ላይ እያለን 00:16:52
00:16:52
ቪየና ከተማ ውስጥ ዓይን የሆነ ቦታ ላይ አፓርታማ ገዛን።00:16:55
00:16:55
በየወሩ ግን የባንክ ዕዳ መክፈል ነበረብን።00:16:58
00:16:58
በጣም የሚያምር አፓርታማ ነበር።00:17:00
00:17:00
አዎ ልክ ነሽ።00:17:01
00:17:02
ደግሞም እኮ የራስ ነገር ሲኖር በጣም ነው ደስ የሚለው።00:17:05
00:17:07
ሐሳቤ ሁሉ ገንዘብ ማግኘት ላይ ነበር።00:17:10
00:17:10
ምክንያቱም ይህ ዶሪስን እንደሚያስደስታት አስብ ነበር።00:17:13
00:17:17
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ከክርስቲያናዊ ስብሰባዎች መቅረት ጀመርን።00:17:20
00:17:21
ምንም ዓይነት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ አናደርግም ነበር።00:17:24
00:17:24
ይህ ደግሞ እርስ በርስ እያራራቀን መጣ።00:17:27
00:17:27
ይህን ያስተዋለ አንድ ሽማግሌ እረኝነት አደረገልን።00:17:31
00:17:31
ይህ ወንድም ቀጥተኛ ምክር ነው የሰጠኝ።00:17:33
00:17:33
የቤተሰቡ ራስ እኔ እንደሆንኩ አስታውሶኝ በግልጽ ምክር ሰጠኝ።00:17:37
00:17:38
ራስ ከሆንኩ ደግሞ የዶሪስን መንፈሳዊነት የመንከባከብ ኃላፊነት ያለብኝ እኔ ነኝ።00:17:43
00:17:44
ስለዚህ . . .00:17:45
00:17:45
በቁሳዊ ነገር ብቻ አይደለም።00:17:46
00:17:46
ልክ ነሽ።00:17:46
00:17:46
በቁሳዊ ብቻ አይደለም።00:17:48
00:17:48
የተናገረው ነገር ቆም ብዬ እንዳስብ አደረገኝ።00:17:50
00:17:50
ኃላፊነቴን መወጣት አለብኝ።00:17:52
00:17:52
ከምንም በላይ ዶሪስን ማስደሰት እፈልጋለሁ።00:17:54
00:17:54
ይህ እንዲሆን ደግሞ ሕይወታችን በይሖዋ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት።00:17:58
00:17:58
ስለ ጉዳዩ በደንብ አወራንበት።00:18:01
00:18:01
አብረን የመጸለይ ልማድም አዳብርን።00:18:03
00:18:03
በየቀኑ!00:18:04
00:18:04
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ውድና ቅንጡ የሆነውን አፓርትመንታችንን 00:18:08
00:18:08
አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብን ተሰማን።00:18:10
00:18:10
ስለ ጉዳዩ ደግመን ደጋግመን ጸለይን።00:18:12
00:18:12
ይሖዋን ‘ከዚህ ቤት ጣጣ እንድትገላግለን እንፈልጋለን። እባክህ እርዳን።00:18:16
00:18:16
ተጨማሪ ሸክም እንዲሆንብን አንፈልግም’ ብለን ለመንነው።00:18:19
00:18:19
ደግሞም ተሳክቶልናል።00:18:21
00:18:22
አፓርታማውን መሸጥ ቻልን።00:18:24
00:18:24
ስለዚህ ከዕዳ ነፃ ሆንን ማለት ነው።00:18:26
00:18:27
በ2014 ያደረግነው የክልል ስብሰባ ደግሞ ተጨማሪ ብርታት ሰጠን።00:18:32
00:18:32
መንግሥቱን እንድናስቀድምና የቀረውን ለይሖዋ እንድተወው ተማርን።00:18:37
00:18:38
ትምህርቱን በሕይወታችን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ አደረግን።00:18:41
00:18:41
የይሖዋን እጅም አይተናል።00:18:42
00:18:42
ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእኛም ብዙ ነገር አድርጎልናል።00:18:46
00:18:46
ከስብሰባው በኋላ ወዲያውኑ ወደ ይሖዋ ጸለይን።00:18:48
00:18:48
በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የአምላክን መንግሥት ለማስቀደም ቆርጬ ተነሳሁ።00:18:52
00:18:52
ተሳካልን።00:18:53
00:18:53
ልክ ነሽ።00:18:54
00:18:55
ስብሰባው ከተካሄደ ከጥቂት ወራት በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆንን።00:19:01
00:19:01
እኔ በተሰማራሁበት የግንባታ ዘርፍ ለተወሰነ ሰዓት ብቻ መሥራት የተለመደ አይደለም።00:19:06
00:19:06
ስለዚህ ማስተካከያ በማድረግ ከመደበኛው የሥራ ሰዓት ቀንሼ ለመሥራት ስወሰን00:19:10
00:19:11
ጉዳዩን በይሖዋ እጅ መተው ነበረብኝ።00:19:13
00:19:13
ወጪያችንንና ገቢያችንን ቆም ብዬ ሳሰላ ‘እንዴት ልንቀጥል ነው?’ ብዬ አሰብኩ።00:19:19
00:19:21
ስለ ጉዳዩ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ።00:19:22
00:19:22
ደጋግሜ ለመንኩት።00:19:24
00:19:24
አለቃዬ በየቀኑ ከመደበኛው የሥራ ሰዓቴ ላይ00:19:28
00:19:28
አንድ አንድ ሰዓት እንዲቀንስልኝ ለመጠየቅ ድፍረት አስፈልጎኛል።00:19:32
00:19:32
ይሖዋ እንዲህ ለማድረግ እንዲረዳኝና 00:19:35
00:19:35
በእሱ ላይ ሙሉ በሙሉ እንድታመን ጸለይኩ።00:19:37
00:19:38
ረዳት አቅኚ ሆነን ስናገለግል በጣም ወደድነው።00:19:41
00:19:41
ስለዚህ ‘በቀጣዩ ዓመት ለምን አቅኚ አንሆንም?’ ተባባልን።00:19:44
00:19:44
እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ ደግሞ የተለያዩ ዕቅዶች ማውጣት ጀመርን።00:19:48
00:19:48
“አሁን አቅኚ መሆን የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም” ተባባልን።00:19:52
00:19:52
የተሰማን ደስታ አትጠይቀን።00:19:54
00:19:54
ደስ የሚለው ሁሉም ነገር ተሳካ።00:19:56
00:19:56
ሁሉ ነገር መስመር ያዘ።00:19:58
00:19:58
ከጊዜ በኋላ ደግሞ አኗኗራችንን ይበልጥ ቀላል ለማድረግ ወሰን።00:20:02
00:20:02
ቤታችንን አነስ ወዳለ አፓርታማ ቀየርን።00:20:05
00:20:05
ግን የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ አለው።00:20:07
00:20:07
ሁለታችንም ወደነዋል።00:20:09
00:20:09
ቆይ አንድ መጠበቂያ ግንብ ላሳይህ።00:20:11
00:20:11
በሕይወታችን ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል።00:20:13
00:20:13
መጠበቂያ ግንቡ “በየዕለቱ ከይሖዋ ጋር ሥሩ” የሚል ርዕስ ይዟል።00:20:16
00:20:16
በርዕሱ መጨረሻ ላይ የሚገኝ አንቀጽ ላይ አንድ ዓረፍተ ነገር አለ።00:20:20
00:20:21
እርግጥ ጥያቄ ነው።00:20:22
00:20:22
እንዲህ ይላል፦ 00:20:22
00:20:23
“ቅዱስ አገልግሎት ለማከናወን የበለጠ ብቁ እንድትሆን የሚረዳ ተጨማሪ ሥልጠና ማግኘት ትፈልጋለህ?00:20:27
00:20:27
ከሆነ በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት መሠልጠን ትችል ይሆናል።”00:20:31
00:20:31
ለእኛ ተብሎ እንደተጻፈ ነው የተሰማን።00:20:34
00:20:34
አሁን ምንም ሰበብ የለንም።00:20:36
00:20:36
ስለዚህ . . . 00:20:37
00:20:37
መጋበዣው ደረሰን። 00:20:39
00:20:39
. . . SKE ተጋበዝን።00:20:41
00:20:41
በጣም ነበር ደስ ያለን። 00:20:43
00:20:43
SKE ለመማር ሁለት ወር ፈቃድ ማግኘት ቀላል አልነበረም።00:20:47
00:20:47
ደግሞም ፈቃድ አላገኘሁም።00:20:49
00:20:49
ሥራዬን ነበር የለቀቅኩት።00:20:50
00:20:50
እውነቱን ለመናገር ይሄን በማድረጌ አይቆጨኝም።00:20:53
00:20:53
አሁንም አጋጣሚውን ባገኝ ተመሳሳይ ነገር ነው የማደርገው። 00:20:56
00:20:56
SKE ገብቶ መማር . . . 00:20:58
00:20:58
ይሖዋ እንደሚወደን የሚያረጋግጥ ነው።00:20:59
00:20:59
. . . ወደፊት ሊጠቀምብን እንደሚፈልግ የሚያሳይ ነበር።00:21:02
00:21:04
ይሄ 00:21:05
00:21:07
በጣም ደስ የሚል ነው።00:21:08
00:21:11
እንድናገለግል የተመደብንበት ጉባኤ በጣም አፍቃሪ ነው።00:21:14
00:21:14
ከዶሪስ ጋር በአቅኝነት ያሳለፍኩትን ጊዜ በጣም ነው የምወደው።00:21:17
00:21:17
የይሖዋ ፍቅርና እንክብካቤ ተለይቶን አያውቅም።00:21:20
00:21:20
የሚያስፈልገን ሁሉ አሟልቶልናል።00:21:22
00:21:23
ከበፊቱ አንጻር ሲታይ አሁን ያለን ነገር ትንሽ ነው።00:21:26
00:21:26
ግን ሸክማችንም ቀሏል።00:21:28
00:21:28
ምክንያቱም ይሖዋ እየተንከባከበን ነው።00:21:30
00:21:30
የሚቆጨን አንዳች ነገር የለም።00:21:32
00:21:32
እኔ ግን አለኝ።00:21:34
00:21:34
እንዴ ምን?00:21:35
00:21:35
ይሄን ነገር ቀደም ብለን ብንጀምረው ጥሩ ነበር።00:21:38
00:21:38
እሱስ እውነት ነው።00:21:39
00:21:42
ይህ ቤተሰብ ይሖዋ ሕይወታችንን ቀላል እንድናደርግ የሰጠንን ምክር ተግባራዊ አድርጓል።00:21:47
00:21:48
በውጤቱም ከጠበቁት በላይ አስደሳችና ትርጉም ያለው ሕይወት መምራት ችለዋል።00:21:52
00:21:53
ግን ኑሯችሁን ቀላል ማድረግ ከባድ እንደሆነ ከተሰማችሁ ተስፋ አትቁረጡ።00:21:59
00:21:59
ከዘካርያስ መጽሐፍ ጥሩ ትምህርት ታገኛላችሁ።00:22:02
00:22:07
የዘካርያስ መጽሐፍ እንደ አዲስ አስገርሞኛል።00:22:10
00:22:10
አይደል፣ እኔ ራሱ የምናጠናበት ቀን አልደርስ ብሎኝ ነበር። 00:22:13
00:22:13
እንጀምር?00:22:14
00:22:14
እሺ፣ በባለፈው ጥናታችን ሕይወት ለአይሁዳውያን ከባድ እንደሆነ አይተናል።00:22:18
00:22:19
በወቅቱ ጠላቶቻቸውና ተቃዋሚዎቻቸው ባደረሱባቸው ጫና ተስፋ ቆርጠዋል።00:22:24
00:22:24
ቤተ መቅደሱን ከመገንባት በተጨማሪ ኢየሩሳሌምንም መልሰው መገንባት ነበረባቸው።00:22:29
00:22:29
ቤተሰባቸውንም መንከባከብ ይጠበቅባቸዋል።00:22:31
00:22:31
ይህ ሁሉ አድክሟቸዋል።00:22:33
00:22:33
እኛም ዛሬ እንደዛ ይሰማናል።00:22:35
00:22:35
እውነትሽን ነው።00:22:36
00:22:37
በሰብዓዊ ዓይን ሲታይ የሚሳካላቸው አይመስልም።00:22:39
00:22:39
የጦር ሰራዊትም ሆነ ሥልጣን አልነበራቸውም።00:22:42
00:22:42
ቁጥራቸው ትንሽ፣ ችግራቸው ግን ብዙ ነበር።00:22:45
00:22:45
ለዛም ነው ይሖዋ ሐጌንና ዘካርያስን በመላክ ያበረታታቸው።00:22:49
00:22:49
አዎ፣ ሐጌ የተሰጣቸውን ሥራ ለመጀመር የሚያስችል ግልጽ መመሪያ ሰጣቸው።00:22:54
00:22:54
ዘካርያስ ደግሞ በሥራው እንዲጸኑ ጥልቀት ያለው መንፈሳዊ ማበረታቻ ሰጣቸው።00:22:59
00:22:59
የዘካርያስ መጽሐፍ ብዙ ትምህርት ስለያዘ 00:23:01
00:23:01
በትንሽ በትንሹ ከፋፍለን ብናጠናው ጥሩ ነው።00:23:04
00:23:05
እውነትሽን ነው።00:23:05
00:23:05
የማስተዋወቂያ ቪዲዮው ቁልፍ የሆኑ የመጽሐፉን ክፍሎች ይጠቁማል።00:23:09
00:23:09
በተለይ ከመሲሑ ጋር የተያያዙት ትንቢቶችን!00:23:11
00:23:11
ልክ ነህ።00:23:12
00:23:12
አዲስ ዓለም ትርጉም ላይ የመጽሐፉ ይዘት የሚለውን ክፍልም ወድጄዋለሁ።00:23:16
00:23:16
የጀመርኩት “መቅረዝና ሁለት የወይራ ዛፎች” ከሚለው ከአምስተኛ ራእይ ነው።00:23:21
00:23:21
ጥሩ ነው። ታዲያ ምን አገኘሽ?00:23:23
00:23:23
ምርምር ሳደርግ “ዘካርያስ ያየው ይታያችኋል?” የሚል የጥናት ርዕስ 00:23:27
00:23:27
በመጋቢት 2022 መጠበቂያ ግንብ ላይ አገኘሁ። 00:23:30
00:23:30
ጽሑፉ ላይ የተጠቀሱት ነጥቦችና ሥዕሉ በጣም ጠቅመውኛል።00:23:34
00:23:34
ደስ ይላል።00:23:35
00:23:35
ጽሑፉን ያገኘሽው ግን እንዴት ነው? 00:23:36
00:23:36
የምርምር መርጃ ላይ ያለውን የጥቅስ ማውጫ ተጠቅሜ ነው።00:23:39
00:23:40
በጣም ጥሩ ዘዴ ነው።00:23:41
00:23:42
ጽሑፉ ከዛፎቹ የሚመነጨው ዘይት ኃያል የሆነውንና 00:23:46
00:23:46
ፈጽሞ የማይነጥፈውን የይሖዋን ቅዱስ መንፈስ እንደሚያመለክት ይናገራል።00:23:50
00:23:51
አይሁዳውያኑ በዚህ በጣም ተበረታተው መሆን አለበት።00:23:54
00:23:54
ዝለውና ተስፋ ቆርጠው ነበር።00:23:56
00:23:56
ግን ይሖዋ ከጎናቸው እንደሚሆንና እርዳታው እንደማይለያቸው አረጋገጠላቸው።00:24:02
00:24:03
በተጨማሪም 4:6, 7 ላይ እንዲህ ብሏቸው፦ 00:24:07
00:24:07
“‘በመንፈሴ እንጂ፣ በወታደራዊ ኃይል ወይም በጉልበት አይደለም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።00:24:13
00:24:13
ታላቅ ተራራ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ መሬት ትሆናለህ።”00:24:19
00:24:20
የሚገርም አገላለጽ ነው።00:24:21
00:24:21
አይሁዳውያኑ እንደ ተራራ ያለ ተቃውሞ ቢያጋጥማቸውም ዘካርያስ ደልዳላ መሬት እንደሚሆን ተናግሯል።00:24:27
00:24:28
ስለዚህ የፋርስ መንግሥትም ሆነ ሌላ የትኛውም ተቃዋሚ00:24:31
00:24:31
ወይም እገዳ ሥራውን ፈጽሞ ሊያስቆመው አይችልም።00:24:34
00:24:34
የጦር ሰራዊት ባይኖራቸውም ይሖዋ አለላቸው።00:24:37
00:24:37
ይህን ሲሰሙ አንድ ትልቅ ተራራ ተደርምሶ ደልዳላ መሬት ሲሆን በዓይነ ሕሊናቸው አይተው ይሆናል።00:24:43
00:24:43
ይህ ብቻ ግን አይደለም።00:24:45
00:24:45
ስኬታቸው የተመካው በይሖዋ መንፈስ ላይ እንጂ 00:24:47
00:24:47
በግለሰቦች ችሎታ ወይም በሁኔታዎች ላይ እንዳልሆነ ግልጽ የሚያደርግ ነው።00:24:52
00:24:52
አዎ፣ እውነታው ያ ነው።00:24:54
00:24:54
በመልእክቱ ተበረታተዋል።00:24:56
00:24:56
ብዙ ከባባድ ችግሮች ቢያጋጥሟቸው በይሖዋ በመታመን በሥራው ገፍተዋል።00:25:01
00:25:01
ከአራት ዓመት ገደማ በኋላ የቤተ መቅደሱ ግንባታ አለቀ።00:25:05
00:25:05
የይሖዋን እጅ አይተዋል።00:25:06
00:25:06
ድንገት በግንባታ ሥራው ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ።00:25:10
00:25:10
በዙሪያቸው ለነበሩት ብሔራትም ለግንባታ ሥራው ድጋፍ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ተሰጠ።00:25:15
00:25:15
ይህ ሁሉ የሆነው በይሖዋ መንፈስ እንጂ በሰው ጥረት አይደለም።00:25:18
00:25:18
ይሖዋ ተራራውን ሜዳ አደረገው።00:25:20
00:25:20
ታዲያ ይህ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?00:25:23
00:25:23
የዘካርያስ ራእዮች የይሖዋ መንፈስ የማይቻል የሚመስለንን ነገር ማከናወን እንደሚችል አስተምረውኛል።00:25:30
00:25:30
ትክክል፣ እኛም አንዳንዴ እንደ አይሁዳውያኑ እንደሚሰማን ይሖዋ ያውቃል።00:25:34
00:25:34
ልንዝል፣ ተስፋ ልንቆርጥና ልንፈራ እንችላለን።00:25:36
00:25:36
ስለዚህ ኃይሉ እውን እንዲሆንልን ይፈልጋል።00:25:39
00:25:39
የዘካርያስ ትንቢት ይህን ለማድረግ ይረዳናል።00:25:42
00:25:42
አዎ ጠቃሚ ነጥብ ነው።00:25:43
00:25:43
መጽሐፉን ሳጠና ክንውኑን በዓይነ ሕሊናዬ ለማየት ጥረት ማድረግ።00:25:48
00:25:48
በትክክል፣ “ዘካርያስ ያየው ይታያችኋል?” የሚለው ርዕስ በራሱ እንዲህ እንድናደርግ ያበረታታናል።00:25:54
00:25:54
ግን ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?00:25:56
00:25:56
እውነቱን ለመናገር አንዳንዴ ድክም ይለኛል።00:25:59
00:25:59
ከምናደርጋቸው ብዙ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ00:26:02
00:26:02
የቤተሰብ ኃላፊነት፣ ሰብዓዊ ሥራ፣ ጤንነታችንን መንከባከብና00:26:07
00:26:07
የሰይጣን ዓለም የሚያደርስብንን ጫና መቋቋም አለብን።00:26:10
00:26:10
በዚህ ጊዜ ይህን ሁሉ ማድረግ እንደማንችል ይሰማናል።00:26:13
00:26:13
እኔም አንዳንዴ ስብሰባዎችን በቪዲዮ ለመከታተል እፈተናለሁ።00:26:16
00:26:17
እኔም አንዳንዴ እንደዛ ይሰማኛል።00:26:19
00:26:19
ግን ራእዩን በዓይነ ሕሊናዬ መመልከቴ የሚያስፈልገኝን አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጥንካሬ 00:26:25
00:26:25
ይሖዋ እንደሚሰጠኝ ስለሚያስታውሰኝ ያበረታኛል።00:26:28
00:26:28
እኔም መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደከበደኝ ሲሰማኝ 00:26:32
00:26:32
ይሖዋ መንፈሱን እንዲሰጠኝ እጸልያለሁ።00:26:34
00:26:34
ከዛም እርምጃው እወስዳለሁ።00:26:36
00:26:36
ማለትም ራሴን አስገድጄም ቢሆን ስብሰባ እሄዳለሁ።00:26:38
00:26:38
አገልግሎት እወጣለሁ።00:26:40
00:26:40
የሚያስፈልገኝን ኃይል ይሖዋ እንደሚሰጠኝ እተማመናለሁ።00:26:43
00:26:43
እኔም የይሖዋን ምሳሌ በመከተል ሌሎችን ለማበረታታት የምችለውን ሁሉ እንዳደርግ አነሳስቶኛል።00:26:49
00:26:49
በተለይ ተስፋ ሲቆርጡ ወይም ሲፈሩ!00:26:52
00:26:52
ይሖዋ እንደሚያስብላቸውና እንደሚያበረታቸው ላስታውሳቸው እፈልጋለሁ።00:26:56
00:26:56
አዎ እንዲህ ማድረግ አለብን።00:26:58
00:26:58
ዛሬ ያገኘነው ትምህርት ወደፊት ስደት ወይም አስፈሪ ሁኔታ ሲያጋጥመንም ይጠቅመናል።00:27:04
00:27:04
ቅድም ያልከው እውነት ነው።00:27:05
00:27:05
ስኬታችን የተመካው በችሎታችን ወይም በሁኔታዎች ላይ ሳይሆን በይሖዋ መንፈስ ላይ ነው።00:27:10
00:27:10
የዘካርያስን መጽሐፍ ያጠናንበትን መንገድ ወድጄዋለሁ።00:27:14
00:27:14
ከፋፍሎ በትንሽ በትንሹ ማጥናት፣ 00:27:16
00:27:16
የጥቅስ ማውጫውን መጠቀምና በዓይነ ሕሊናችን መሳል።00:27:19
00:27:19
በዚህ መንገድ ማጥናታችን የአምላክን ቃል ሕያው ያደርግልናል።00:27:22
00:27:23
ልክ ነህ፣ ቀጥሎ ደግሞ ስለ ሁለቱ በትሮች ትርጉም እንወያይ?00:27:26
00:27:26
ጥሩ ነው፣ እኔም ስለ መሲሑ የሚናገሩትን ትንቢቶች መመርመርና 00:27:30
00:27:30
ከአጠቃላዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጥ ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ማየት እፈልጋለሁ። 00:27:34
00:27:34
ለምሳሌ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን የሚያረጋገጡ የዘካርያስ ድርጊቶችን።00:27:38
00:27:38
መጽሐፉ ሌሎች ብዙ ራእዮችም ይዟል።00:27:40
00:27:40
ትክክል፣ የዘካርያስን መጽሐፍ በዚህ መልኩ ከመረመርን 00:27:43
00:27:43
ለቤተሰብ አምልኳችን የሚሆኑ ጥሩ ግብዓቶችን እናገኛለን።00:27:47
00:27:49
ተግባራዊ የሚሆን ትምህርት ነው ያገኘነው።00:27:51
00:27:51
ስኬታችን የተመካው ባለንበት ሁኔታ ወይም በችሎታችን ላይ አይደለም።00:27:56
00:27:56
ይሖዋ ታዛዦች እስከሆንን ድረስ መንፈሱን በመስጠት አብዝቶ ይባርከናል።00:28:01
00:28:03
አንዳንዶች ጥሩ እይታ እንዲኖራቸው የረዳቸው00:28:05
00:28:05
ቤቴል በተመላላሽነት ለማገልገል ራሳቸውን ማቅረባቸው ነው።00:28:09
00:28:10
ቀጣዩ ቪዲዮ ምን እንደሚያከናውኑ ያሳየናል።00:28:12
00:28:12
ውሏቸው ምን ይመስላል? 00:28:14
00:28:14
ተመላላሽ ቤቴላውያን! 00:28:15
00:28:17
ሰላም፣ ሄ-ኢን እባላለሁ።00:28:19
00:28:19
በኮሪያ ቅርንጫፍ ቢሮ በተመላላሽነት እያገለገልኩ ነው።00:28:22
00:28:37
አልፎ አልፎ ተመላላሽ ስለሆንኩ 00:28:39
00:28:39
ወደ ቤቴል የምሄደው በቋሚነት ሳይሆን ለሥራ ስፈለግ ብቻ ነው።00:28:43
00:28:44
ቤቴል ለመድረስ የሚፈጅብኝ ጊዜ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ የተመካ ነው።00:28:48
00:28:49
በአብዛኛው ከ45 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ይፈጃል።00:28:52
00:28:53
ደስ የሚለው መንዳት እወዳለሁ።00:28:56
00:28:56
ስለዚህ መመላለሱ አያሰለቸኝም።00:28:58
00:29:01
ቤቴል ሁልጊዜ ቀኑን የምንጀምረው የማለዳ አምልኮ በማድረግ ነው።00:29:05
00:29:06
በቅርቡ የሰማሁትን አንድ ንግግር አልረሳውም።00:29:08
00:29:08
በያዕቆብ 1:2-4 ላይ የተመሠረተ ነው።00:29:11
00:29:12
የሚያጋጥሙንን ፈተናዎችና መከራዎች እድገት ለማድረግ እንደሚረዱ አስተማሪዎች እንድናያቸው የሚያበረታታ ነበር።00:29:19
00:29:20
እርግጥ መከራ ውስጥ ስትሆን ‘ከዚህ ሁኔታ ምን ትምህርት አገኛለሁ?’ ብሎ ራስን መጠየቅ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም።00:29:27
00:29:27
ሆኖም መልእክቱ ግልጽ ነው።00:29:29
00:29:29
ፈተናዎች ሲያጋጥሙን የግል ጥናት ማድረጋችንን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበባችንን፣ 00:29:34
00:29:34
መጸለያችንንና ማሰላሰላችንን የምንቀጥል ከሆነ ፈተናዎቹ እያሉም በደስታ መጽናት እንችላለን።00:29:40
00:29:40
የማለዳ አምልኮ ሁሌም ያበረታታኛል።00:29:43
00:29:43
የሆነ የምማረው ነገር አይጠፋም።00:29:45
00:29:47
የምሠራው በትራንስፖርት ዲፓርትመንት ውስጥ ነው።00:29:50
00:29:50
ሥራችን በዋነኝነት ከውጭ አገር ቤቴልን ለመጎብኘት ለሚመጡ00:29:54
00:29:54
የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ነው።00:29:58
00:30:13
ቤቴል ውስጥ የሚከናወኑት ሥራዎች ዓላማ 00:30:16
00:30:16
በመስኩ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መደገፍ እንደሆነ ሁልጊዜ ለማስታወስ እሞክራለሁ።00:30:21
00:30:23
ሥራዬ ቤቴልን ለመጎብኘት ከተለያየ የዓለም ክፍል ከሚመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ጋር ያገናኘኛል።00:30:29
00:30:29
በጣም አመስጋኞች ናቸው።00:30:31
00:30:31
ይህ ደግሞ በቤቴል የምናከናውነው ሥራ ምን ያህል እየጠቀማቸው እንዳለ እንዳስብ ያደርገኛል።00:30:37
00:30:37
ይህም ጥልቅ እርካታ አስገኝቶልኛል።00:30:39
00:30:41
ጉዞው በአብዛኛው ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ሁለት ሰዓት ድረስ ይወስዳል።00:30:45
00:30:45
በዚህ ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ነገሮችን እናወራለን።00:30:48
00:30:48
ገና የተገናኘን ቢሆንም ላየን ሰው የቆዩ ጓደኛሞች ነው የምንመስለው።00:30:53
00:30:53
የልባችንን አውጥተን እናወራለን።00:30:55
00:30:55
ለምሳሌ ይሖዋ እንዴት እንደደገፈን፣ 00:30:57
00:30:57
አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንድንቋቋም የረዳን እንዴት እንደሆነ እናወራለን።00:31:01
00:31:01
በጉዞ ላይ የምናሳልፋቸውን እንዲህ ያሉ ጊዜያት በጣም ነው የምወዳቸው። 00:31:06
00:31:09
መጀመሪያ ላይ ቤቴል የማገልገል ያን ያህል ፍላጎት አልነበረኝም።00:31:13
00:31:13
ስለዚህ ማመልከቻውን ለመሙላት ሳመነታ ነበር።00:31:16
00:31:16
በኋላ ግን አንድ የምቀርበው ወንድም00:31:19
00:31:19
‘ይሖዋን ለማገልገል ራሳችንን እስካቀረብን ድረስ የምንሠራውን ሥራ መምረጥ አንችልም’ አለኝ።00:31:24
00:31:24
በጉዳዩ ላይ ሳስብበት ይህ ወንድም ያለኝ ትክክል እንደሆነ ገባኝ።00:31:29
00:31:29
ስለዚህ ጉዳዩን ለይሖዋ ትቼ ዝም ብዬ ማመልከቻውን ሞላሁ።00:31:33
00:31:33
እንግዲህ ቤቴል ማገልገል የጀመርኩት በዚህ መልኩ ነው።00:31:36
00:31:36
አሁንም እዛው እያገለገልኩ ነው።00:31:38
00:31:44
እርግጥ በሥራ ፕሮግራሜ ላይ ማስተካከያ ማድረግ 00:31:47
00:31:47
ትንሽ ተፈታታኝ ሆኖብኝ ነበር።00:31:49
00:31:49
በጣም ያሳሰበኝ ‘በቂ ገቢ አገኝ ይሆን?’ የሚለው ነበር።00:31:53
00:31:53
ቤቴል መመላለስ ስጀምር ግን ሁሉም ነገር መልክ መልክ ያዘ።00:31:57
00:31:58
የሥራ ፕሮግራሜ ቤቴል መመላለስ በሚያስችለኝ መልኩ ተስተካከለልኝ።00:32:02
00:32:05
ከሥራዬና ቤቴል ከመመላለስ በተጨማሪ 00:32:08
00:32:08
የቤተሰቤን አባላት የመንከባከብ ኃላፊነትም አለብኝ።00:32:11
00:32:12
መንፈሳዊ ልማዶቼን ይዤ ለመቀጠል የግል ጥናት የማደርግበት አንድ ቀን መድቤያለሁ።00:32:18
00:32:18
መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን በቋሚነት ማድረግ አስፈላጊ ነው።00:32:22
00:32:22
ምክንያቱም ስዝል ኃይል እንዳገኝ ይረዱኛል።00:32:26
00:32:26
ይህ ደግሞ በቤቴል ማገልገሌን እንድቀጥልና የመስክ አገልግሎቴን በቅንዓት እንዳከናውን ይረዳኛል።00:32:33
00:32:34
እንዲህ ያሉት ልማዶች በመንፈሳዊ ሕያው ሆኜ እንድቀጥል ይረዱኛል።00:32:38
00:32:38
ምንም ያህል ጊዜዬ የተጣበበ ቢሆን ምንጊዜም ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ጊዜ እመድባለሁ።00:32:44
00:32:46
‘በሌላ ቦታ አንድ ሺህ ቀን ከመኖር በይሖዋ ቤት ውስጥ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል።’00:32:51
00:32:51
ወደ ቤቴል በምመጣበት ቀን የማስበው ይህን ጥቅስ ነው።00:32:55
00:32:56
ወደፊት የሚሰጠኝ የሥራ ምድብ ምንም ይሁን ምን 00:32:59
00:33:00
ይሖዋን በደስታና በአመስጋኝነት ስሜት ማገልገል እፈልጋለሁ።00:33:04
00:33:15
ተመላላሽ ሆኖ ማገልገል ጊዜያችንንና ጉልበታችንን መሥዋዕት ማድረግ ይጠይቃል።00:33:20
00:33:20
ሄ-ኢን ሚዛናዊ እንድትሆንና ኃይሏ እንዳይሟዋጠጥ የረዳት ምንድን ነው?00:33:25
00:33:25
በቋሚነት ጥልቀት ያለው የግል ጥናት የምታደርግበት ጊዜ መመደቧ ነው።00:33:29
00:33:30
ስለ ይሖዋ ቃል ማጥናት መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን በማከም፣00:33:34
00:33:34
ስለ ወደፊቱ ጊዜ ጥርት ያለ እይታ እንዲኖረን ያስችለናል።00:33:38
00:33:38
ቀጣዩ የማለዳ አምልኮ ንግግር በዚህ ረገድ ከዳንኤል ምን እንደምንማር ይነግረናል።00:33:43
00:33:44
የዛሬው ንግግራችን ጭብጥ 00:33:45
00:33:45
በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩ የሚል ነው።00:33:49
00:33:50
ግን ማጠናከር ያለብን ለምንድን ነው?00:33:52
00:33:53
ምክንያቱም ያሳለፍነው ሕይወት፣ አስተዳደጋችን፣ ያጋጠሙን ነገሮች 00:33:58
00:33:58
ወይም ደግሞ ከዚህ በፊት የፈጸምናቸው አንዳንድ ስህተቶች 00:34:02
00:34:02
ይሖዋ የሚወደን መሆኑን እንድንጠራጠር ሊያደርጉን ይችላሉ። 00:34:07
00:34:07
ወይም ደግሞ አሁን እያጋጠሙን ያሉ ችግሮች ይኖራሉ።00:34:11
00:34:11
ለምሳሌ ያለብን የቤተሰብ ኃላፊነት፣ የሥራ ጫና፣ የጤንነት ችግር 00:34:17
00:34:17
ወይም ሌሎች ነገሮች እያስጨነቁን ይሆናል።00:34:20
00:34:20
እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን የይሖዋ ፍቅራዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገን እንገነዘባለን።00:34:26
00:34:27
ወደፊትም ቢሆን እምነታችንን የሚፈትኑ ነገሮች እንደሚያጋጥሙን እናውቃለን።00:34:32
00:34:32
‘ያኔ በታማኝነት እጸና ይሆን?’ የሚለው ጉዳይ በጣም ያስጨንቀን ይሆናል።00:34:37
00:34:38
ከዚህ በፊት ያጋጠመን፣ አሁን እያጋጠመን ያለው 00:34:41
00:34:41
ወይም ወደፊት የሚያጋጥመን ነገር ምንም ይሁን ምን ይሖዋ ታማኝ ፍቅር ያሳየናል።00:34:46
00:34:47
ዳንኤል 9:4ን መመርመራችን ይሖዋ ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳየን እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል።00:34:54
00:34:54
ጥቅሱ በዛሬው የዕለት ጥቅሳችን ላይ በከፊል ተጠቅሷል።00:34:57
00:34:57
ዳንኤል 9:4 እንዲህ ይላል፦ 00:35:00
00:35:02
“ወደ አምላኬ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ፤ ደግሞም ተናዘዝኩ፤ እንዲህም አልኩ፦00:35:06
00:35:07
“‘እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ለሚወዱህ፣ ትእዛዛትህንም ለሚያከብሩ 00:35:12
00:35:13
ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅና ታማኝ ፍቅር የምታሳይ ታላቅና የምትፈራ አምላክ ነህ።’”00:35:19
00:35:19
ይህ እንግዲህ ከዳንኤል ጸሎት ላይ የተወሰደ ሐሳብ ነው።00:35:22
00:35:22
በጸሎቱ ላይ ስለ ይሖዋ ታማኝ ፍቅርና ይሖዋ ቃል ኪዳኑ እንደሚጠብቅ ጠቅሷል።00:35:28
00:35:28
ይሖዋ ይህን የሚያደርገው ለሚወዱት እንዲሁም ቃል ኪዳኑን ለሚጠብቁ ነው።00:35:35
00:35:35
ስለዚህ ይህንን ጸሎትና በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ መመርመራችን 00:35:40
00:35:40
ይሖዋ ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳየን እንድንተማመን ያደርገናል።00:35:44
00:35:44
በመጀመሪያ ግን ዳንኤል እንዲህ ብሎ እንዲጸልይ ያነሳሳው ምንድን ነው?00:35:49
00:35:49
እስቲ ዳንኤል 9:2ን እናንብብ፦00:35:51
00:35:52
“አዎ፣ በዘመነ መንግሥቱ የመጀመሪያ ዓመት እኔ ዳንኤል00:35:56
00:35:57
“ለነቢዩ ኤርምያስ በተነገረው የይሖዋ ቃል ላይ በተጠቀሰው መሠረት00:36:00
00:36:00
ኢየሩሳሌም ፈራርሳ የምትቆየው ለ70 ዓመት እንደሆነ ከመጻሕፍቱ አስተዋልኩ።”00:36:05
00:36:06
ስለዚህ ይህ የሆነው መቼ ነበር?00:36:09
00:36:09
በ539 ዓመተ ዓለም!00:36:12
00:36:12
በዚያን ወቅት ኢየሩሳሌም ለ68 ዓመታት ፈራርሳ ቆይታለች።00:36:17
00:36:17
ዳንኤልም መጻሕፍቱን፣ የግርጌ ማስታወሻው እንደሚለው ቅዱሳን መጻሕፍትን እየመረመረ ነበር።00:36:24
00:36:24
ዳንኤል በወቅቱ ኤርምያስ ከጻፋቸው በተጨማሪ ሙሴ፣ ኢሳይያስ፣ ሕዝቅኤል፣ 00:36:29
00:36:29
አሞጽና ሆሴዕ የጻፏቸውን መጻሕፍት ማግኘት ይችል ነበር።00:36:33
00:36:34
ዳንኤል፣ ኤርምያስ 29:10ን አንብቦ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።00:36:38
00:36:38
ኤርምያስ 29:10 እንዲህ ይላል፦ 00:36:41
00:36:41
“ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በባቢሎን የምትኖሩበት 70 ዓመት ሲፈጸም ትኩረቴን ወደ እናንተ አዞራለሁ፤ 00:36:48
00:36:49
ወደዚህም ስፍራ መልሼ በማምጣት፣ የገባሁትን ቃል እፈጽማለሁ።’”00:36:53
00:36:54
በወቅቱ እየተፈጸሙ የነበሩት ነገሮች ከትንቢቶች ጋር የሚያያዙት እንዴት እንደሆነ ማስተዋል ይችል ነበር።00:37:00
00:37:01
በትንቢት በተነገረው መሠረት እስራኤላውያንን ነፃ የሚያወጣው በወቅቱ እየገዛ ያለው ቂሮስ እንደሆነ ያውቃል።00:37:07
00:37:08
እያንዳንዱ ትንቢት እንዴት እንደሚፈጸም በዝርዝር ባያውቅም ጊዜው መድረሱን ግን ተረድቶ ነበር።00:37:13
00:37:14
በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ላይ ትኩረት ያደረገውን ይህን ጸሎት እንዲያቀርብ ያነሳሳው ይኸው ነው።00:37:19
00:37:19
ቁጥር አራት ላይ የጀመረው የዳንኤል ጸሎት የሚደመደመው ቁጥር 19 ላይ ነው።00:37:24
00:37:24
የጸሎቱ ይዘትና የተጠቀመባቸው ቃላት 00:37:27
00:37:27
ኤርምያስ በጻፋቸው መጻሕፍቶች ውስጥ ያነበባቸው ነገሮች ከአእምሮውና ከልቡ እንዳልጠፉ ያሳያል።00:37:33
00:37:33
እንዲያውም አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንዳለው ዳንኤል ያቀረበው ጸሎት የተመሠረተው 00:37:38
00:37:38
ኤርምያስ መጽሐፍ ላይ ባሉ አንድ ወይም ሁለት ጥቅሶች ላይ ሳይሆን በመላው መጽሐፍ ላይ ነው።00:37:43
00:37:43
ይህ ጸሎት እስራኤላውያን የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ምን ያህል እንደሚያስፈልጋቸው ያሳያል።00:37:48
00:37:49
የይሖዋን ታማኝነትና ርኅራኄ ከእስራኤላውያን ዓመፀኝነትና ታማኝ አለመሆን ጋር ያነጻጽራል።00:37:56
00:37:57
ዳንኤል እስራኤላውያን ያጋጠማቸው ነገር ሁሉ ይሖዋ በትንቢት አስቀድሞ የተናገረው እንደሆነ ጎላ አድርጎ ገልጿል።00:38:04
00:38:04
ቁጥር 13ን እናንብብ።00:38:06
00:38:06
ዳንኤል ያጋጠማቸውን ሁኔታ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦00:38:10
00:38:10
“በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው ይህ ሁሉ ጥፋት ደረሰብን።”00:38:13
00:38:14
ዳንኤል በእስራኤላውያን ላይ ቅጣት እንደሚመጣባቸው የሚናገሩት እነዚሁ ትንቢቶች 00:38:19
00:38:19
ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ የሚገልጽ ተስፋም እንዳያዙ ያውቃል።00:38:24
00:38:24
የዘሌዋውያን፣ የዘዳግም፣ የኢሳይያስና የኤርምያስ መጻሕፍትም 00:38:29
00:38:29
እስራኤላውያን ንስሐ ከገቡ ይሖዋ ወደ አገራቸው እንደሚመልሳቸው የሚገልጽ ተስፋ ይዘዋል።00:38:34
00:38:36
ጸሎቱን ቁጥር 19 ላይ ምን ብሎ እንደደመደመ እንመልከት።00:38:40
00:38:41
ዳንኤል እንዲህ ብሎ ጸልዩአል፦ 00:38:43
00:38:43
“ይሖዋ ሆይ፣ ስማ። ይሖዋ ሆይ፣ ይቅር በል።00:38:46
00:38:46
“ይሖዋ ሆይ፣ ትኩረት ስጥ፤ እርምጃም ውሰድ!00:38:49
00:38:49
“አምላኬ ሆይ፣ ለራስህ ስትል አትዘግይ፤ 00:38:52
00:38:52
ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቷልና።”00:38:55
00:38:56
ዳንኤል ለስምህ ስትል ብሎ የለመነው ለምንድን ነው?00:38:59
00:38:59
በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ የይሖዋ ስም 19 ጊዜ ተጠቅሷል።00:39:03
00:39:03
ከዚህ ውስጥ 18 ጊዜ የተጠቀሰው እዚሁ ምዕራፍ ውስጥ ነው።00:39:07
00:39:07
በጣም የሚያስገርመው ደግሞ 14ቱ የሚገኙት ዳንኤል ባቀረበው በዚህ ልመና ላይ ነው።00:39:13
00:39:13
ግን ዳንኤል በጸሎቱ ላይ ልመናውን ከይሖዋ ስም ጋር ያያያዘው ለምንድን ነው?00:39:18
00:39:19
ዳንኤል ይሖዋ እርምጃ ካልወሰደ በይሖዋ ስም ላይ ነቀፋ እንደሚመጣ ያውቃል።00:39:25
00:39:25
ምክንያቱም ይሖዋ እስራኤላውያንን ነፃ እንደሚያወጣ ቃል ገብቷል።00:39:29
00:39:29
ይህን ካላደረገ በስሙ ላይ ነቀፋ ይመጣል።00:39:32
00:39:32
ዳንኤል የይሖዋን ማንነት፣ የስሙን ትርጉም ለመረዳት 00:39:35
00:39:35
ይሖዋ ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ አምላክ እንደሆነ አምኖ መቀበል እንደሚያስፈልግ ያውቃል።00:39:41
00:39:41
ሕዝቡን ለማዳን ሲል የሚወስደው እርምጃ ትልቅ ነገር ያከናውናል።00:39:45
00:39:45
ስሙ እንዲቀደስ ያደርጋል።00:39:48
00:39:49
ታዲያ ከዚህ ጸሎት ይሖዋ ለእኛም ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳየን እንድንተማመን የሚያደርግ ምን ትምህርት እናገኛለን?00:39:58
00:39:59
አንደኛ፣ ይሖዋ ሕዝቡን ፈጽሞ እንደማይተው ያስተምረናል።00:40:03
00:40:03
እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ እንዳለው ለክፉ ድርጊታቸው የዘሩትን አጭደዋል።00:40:09
00:40:09
ስለዚህ ንስሐ ገብተው ወደ ይሖዋ ከተመለሱ 00:40:12
00:40:13
ቃል የገባላቸውን መልካም ነገሮችም ማጨዳቸው አይቀርም።00:40:16
00:40:16
ደግሞም የሆነው ልክ እንደዚህ ነው።00:40:19
00:40:19
ይህን ማወቅ በጣም ያጽናናል።00:40:21
00:40:21
ሁላችንም ስህተት መሥራታችን አይቀርም።00:40:24
00:40:24
ግን ስህተታችንን ለማስተካከል እርምጃ ከወሰድን፣00:40:27
00:40:27
ይሖዋ ከዳንኤልና ከእስራኤላውያን ጋር እንደነበረው ሁሉ ከእኛም ጋር ይሆናል።00:40:32
00:40:32
አምላካችን ይሖዋ ፈጽሞ አይተወንም።00:40:35
00:40:36
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ፣ 00:40:38
00:40:39
የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች ማጥናታችን በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል።00:40:46
00:40:46
ዳንኤል ትንቢቶችን ማጥናቱ ይሖዋ እርምጃ እንደሚወስድ እርግጠኛ እንዲሆን አድርጎታል።00:40:52
00:40:52
ለእኛም ቢሆን ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።00:40:54
00:40:54
የነሐሴ 2023 መጠበቂያ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ተማሩ በሚለው የጥናት ሥር እንዲህ ይላል፦00:41:00
00:41:01
“በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ያገኙት እንዴት እንደሆነ ስንመለከት 00:41:06
00:41:06
“በይሖዋና በሚሰጠን አመራር ላይ የማይናወጥ እምነት እናዳብራለን።00:41:10
00:41:11
“በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን00:41:14
00:41:14
የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ እንዲኖረን ይረዱናል።”00:41:19
00:41:20
ሦስተኛው ትምህርት ደግሞ ታማኝ ፍቅር ከይሖዋ ስምና ከማንነቱ ጋር የተያያዘ ነው።00:41:26
00:41:26
አይነጣጠሉም።00:41:28
00:41:28
እንደ ዳንኤል ሁሉ እኛም ይህን እናውቃለን።00:41:31
00:41:31
ደግሞም ለእኛ ፍቅር ማሳየት የይሖዋ የማንነቱ ክፍል ነው።00:41:36
00:41:37
ይሖዋ ለስሙ ሲል እርምጃ ይወሰዳል።00:41:39
00:41:39
ይህ ደግሞ እኛን እንደሚንከባከበን የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ከሁሉ የላቀ ማረጋገጫ ይሆነናል።00:41:46
00:41:47
አራተኛ፣ ይሖዋ መረጃዎችን የሚሰጠን በትክክለኛው ጊዜ ነው።00:41:52
00:41:53
ዳንኤል እየተፈጸሙ የነበሩትን ነገሮች ከትንቢቶች ጋር ማያያዝ ችሏል።00:41:57
00:41:57
ይሖዋ ለዳንኤል የሚያስፈልገውን መረጃ የሰጠው በሚያስፈልገው ወቅት ነው።00:42:02
00:42:03
ይሖዋ ዛሬ ላሉት ሕዝቦችም ተመሳሳይ ነገር እያደረገ ነው።00:42:06
00:42:07
በታላቁ መከራ ወቅት የሚፈጸሙትን ጨምሮ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ያለን ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።00:42:15
00:42:15
ይህም ይሖዋ እየመራን እንደሆነ የሚያረጋገጥ ነው።00:42:18
00:42:19
በዳንኤል ጸሎት ላይ ማሰላሰላችን በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል።00:42:26
00:42:26
በተጨማሪም ከዚህ በፊት ያጋጠመን፣ አሁን እያጋጠመን ያለው ወይም ወደፊት የሚያጋጥመን ምንም ይሁን ምን፣ 00:42:32
00:42:32
ይሖዋ ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳየን እርግጠኞች ነን።00:42:36
00:42:37
ከእነዚህ ጥቂት ጥቅሶች ብዙ ትምህርት አግኝተናል።00:42:40
00:42:40
ይሖዋ ቃል ስለገባቸው ተስፋዎች ማጥናት አዎንታዊ ሆነን የወደፊቱን ጊዜ እንድንጠብቅ ይረዳናል።00:42:45
00:42:47
ወደፊት በትንሣኤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እንቀበላለን።00:42:51
00:42:52
እናንተስ መልሳችሁ ለማግኘት፣ እቅፍ ለማድረግ የምትጓጉት ሰው አለ?00:42:56
00:42:57
ይህን ሰው በአእምሯችሁ ይዛችሁ የተኙት ሲነቁ የሚል ርዕስ ያለውን ቀጣዩን የሙዚቃ ቪዲዮ አጣጥሙ።00:43:03
00:43:20
አይሽር እንዲህ በዋዛ፤00:43:25
00:43:26
ሰው ያጣ ሰው፣ ቁስሉን አይረሳ።00:43:31
00:43:32
መጽናናት እምቢ ሲል ልቤ፣00:43:38
00:43:38
እሥለዋለሁ ነገን በምናቤ።00:43:45
00:43:45
ድምፁን ይሰማሉ ሰዓቱ ደርሶ፤00:43:51
00:43:52
ከ’ንቅልፍ ይቀሰቅሳቸዋል አስታውሶ።00:43:58
00:43:58
እንደኔ ናፍቀው፣ ቀን የሚጠብቁ፣00:44:09
00:44:09
ይታየኛል ሲፈነድቁ፣ የተኙት ሲነቁ።00:44:25
00:44:35
ሐዘኑ ሲያገረሽ አድሮ፣00:44:41
00:44:41
ድቅን ሲል ትዝታው ኖሮ ኖሮ፣00:44:47
00:44:48
ሕመሜን ስነግረው ለሱ00:44:54
00:44:54
ያረጋጋኛል በመንፈሱ።00:45:00
00:45:00
ድምፁን ይሰማሉ ሰዓቱ ደርሶ፤00:45:07
00:45:07
ከ’ንቅልፍ ይቀሰቅሳቸዋል አስታውሶ።00:45:13
00:45:13
እንደኔ ናፍቀው፣ ቀን የሚጠብቁ፣00:45:25
00:45:25
ይታየኛል ሲፈነድቁ፣ የተኙት ሲነቁ።00:45:41
00:45:52
አንድ ቀን፣ በቅርቡ በማለዳ00:45:58
00:45:58
የናፈቀኝ ያ ፈገግታ፣00:46:01
00:46:01
በሬን አንኳኩቶ ሲመጣ፤00:46:04
00:46:05
ሕልሜ ነው ብዬ፣ ዓይኔን ሳሸው፣ ሳመነታ፤00:46:10
00:46:10
ስዘል፣ ስቦርቅ በደስታ፤00:46:13
00:46:13
የምሆነውን እስካጣ።00:46:20
00:46:41
ድምፁን ይሰማሉ ሰዓቱ ደርሶ፤00:46:48
00:46:48
ከ’ንቅልፍ ይቀሰቅሳቸዋል አስታውሶ።00:46:54
00:46:55
እንደኔ ናፍቀው፣ ቀን የሚጠብቁ፣00:47:06
00:47:07
ይታየኛል ሲፈነድቁ፣ 00:47:17
00:47:18
የተኙት ሲነቁ።00:47:28
00:47:31
የተኙት ሲነቁ።00:47:41
00:47:45
ሞት የነጠቀንን መልሰን ለማግኘት ምን ያህል እንደምንጓጓ ይሖዋ ያውቃል።00:47:49
00:47:49
እሱም እነሱን ለማስነሳት ይጓጓል።00:47:51
00:47:51
ቃሉ እንደሚያረጋግጥልን በእሱ ፊት ሁሉም ሕያዋን ናቸው።00:47:55
00:47:56
ይሖዋ በሰጠን ተስፋዎች ላይ ጠንካራ እምነት እንዲኖረን 00:47:59
00:47:59
የአምላክን ቃል በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ማግኘታችን ይጠቅመናል።00:48:02
00:48:03
ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክልና በተቻለ መጠን በብዙ ቋንቋዎች ለመተርጎም ምን አድርገናል?00:48:08
00:48:13
የክርስቲያን ግሪከኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በ1950 ሲወጣ00:48:18
00:48:18
የተዘጋጀበትን ዓላማ በተመለከተ 00:48:20
00:48:20
ወንድም ናታ ኖር እንዲህ ብሎ ነበር፦ 00:48:22
00:48:26
“ዓላማው እነዚህ መጻሕፍት በተጻፉበት ዘመን የነበሩት የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በቀላሉ ይረዱት እንደነበረው 00:48:32
00:48:32
ዛሬም ያሉ አንባቢዎች በቀላሉ የሚረዱት ትርጉም ማዘጋጀት ነው።”00:48:36
00:48:46
በቀጣዮቹ ዓመታት ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተተረጎሙ።00:48:49
00:48:50
ከዚያም በ1961 ሙሉ አዲስ ዓለም ትርጉም በእንግሊዝኛ ወጣ።00:48:54
00:48:54
ይህም ትክክለኛ፣ በቀላሉ የሚገባና የይሖዋ ስም ያለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲኖረን አስችሏል።00:49:00
00:49:01
በተመሳሳይ ወቅት ይህን መጽሐፍ ቅዱስ በሌሎች ስድስት ቋንቋዎች ለማዘጋጀት ሥራ ተጀመረ።00:49:06
00:49:06
ከዚያም በ1963 ሥራው ተጠናቅቆ በስድስት ቋንቋዎች ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ወጣ።00:49:11
00:49:12
ያም ቢሆን የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ሥራ አዝጋሚ ነበር።00:49:15
00:49:15
እንዲያውም አንዳንድ ቋንቋዎች ይህን ትርጉም ለማጠናቀቅ ከ20 ዓመት በላይ ፈጅቶባቸዋል።00:49:20
00:49:20
በዚህ የተነሳ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ በእንግሊዝኛ ከወጣ ከ30 ዓመታት በኋላ እንኳ 00:49:25
00:49:25
አዲስ ዓለም ትርጉም የሚገኘው በ12 ቋንቋዎች ብቻ ነበር።00:49:28
00:49:29
ስለዚህ የበላይ አካሉ የትርጉም ሥራውን ለማቀላጠፍ 00:49:32
00:49:32
በ1989 በዋናው መሥሪያ ቤት ሥር የትርጉም አገልግሎት ክፍል የሚባል አንድ ዲፓርትመንት አቋቋመ።00:49:38
00:49:39
የዚህ ዲፓርትመንት ዓላማ ያኔም ሆነ ዛሬ ተመሳሳይ ነው።00:49:42
00:49:42
መጽሐፍ ቅዱስንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን የመተርጎሙን ሥራ ማገዝ፣00:49:46
00:49:46
ተርጓሚዎችን ማሠልጠን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ተርጓሚዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች መመለስ።00:49:52
00:49:52
ደግሞም ተርጓሚዎች ሐሳቡን በትክክል ለማስተላለፍ በርካታ ጥያቄዎች እንደሚያነሱ የሚጠበቅ ነው።00:49:58
00:49:58
ታዲያ የትርጉም አገልግሎት ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ቡድኖችን የሚያደራጀው እንዴት ነው?00:50:03
00:50:03
ሥራው የሚጀመረው መሠረታዊ የትርጉም መመሪያዎችን በተመለከተ ለቡድኑ ሥልጠና በመስጠት ነው።00:50:08
00:50:09
ምሳሌያዊ አባባሎች፣ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫዎች፣ 00:50:12
00:50:12
እንዲሁም ምሥል ከሳች ቃላት እንዴት መተርጎም እንዳለባቸው ይሰለጥናሉ።00:50:16
00:50:16
ተርጓሚዎቹ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን በትክክል መተርጎም እንዲችሉ00:50:20
00:50:20
ሐሳቡን በቅድሚያ በሥዕል ማስረዳት የግድ አስፈላጊ ነበር።00:50:24
00:50:25
ከዚያም የትርጉም ቡድኑ በዋናው ጽሑፍ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በትክክል የሚያስተላልፍ ቃል ይመርጣል።00:50:30
00:50:31
የትርጉም ቡድኑ ጥያቄ ከተፈጠረበት ማብራሪያ ለማግኘት የትርጉም አገልግሎት ክፍሉን መጠየቅ ይችላል።00:50:36
00:50:37
ለጥያቄው የተሰጠው መልስ በአንድ ለየት ያለ የኮምፒውተር ሶፍትዌር አማካኝነት በሰነድ መልክ ይቀመጣል።00:50:42
00:50:42
እስከ ዛሬ ድረስ 140 ሺህ ጥያቄዎች በዚህ መልኩ ተቀምጠዋል።00:50:46
00:50:47
እነዚህ ጥያቄዎች የትርጉም ሥራን ፍጥነትና ጥራትን የሚያሻሽል ተጨማሪ ሥልጠና ለመስጠት ያገለግላሉ። 00:50:53
00:50:54
የበላይ አካል አባል የነበረው ወንድም አልበርት ሽሮደር00:50:56
00:50:56
“አዲስ ዓለም ትርጉምን በስንት ቋንቋዎች ማዘጋጀት ታስባላችሁ?” ተብሎ ሲጠየቅ 00:51:01
00:51:01
“የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት በሚተረጎምበት በእያንዳንዱ ቋንቋ” ሲል መልሷል። 00:51:05
00:51:05
ሰዎች እውነትን እንዲማሩ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሚያስፈልግ ተገንዝቦ ነበር።00:51:10
00:51:11
በ1990ዎቹ አጋማሽ በተለያዩ ቋንቋዎች ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የማግኘት ፍላጎት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እየጨመረ መጣ።00:51:19
00:51:19
አዲስ ዓለም ትርጉም በቋንቋቸው ያልነበራቸው ወንድሞች የሚጠቀሙት ሌሎች ትርጉሞችን ነበር።00:51:24
00:51:25
ከፍተኛ ዕድገት በነበራቸው አንዳንድ ጉባኤዎች ውስጥ የሚኖረው አንድ ወይም ሁለት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።00:51:30
00:51:30
በወቅቱ የነበሩት ሌሎች ትርጉሞች ደግሞ ትክክል ያልሆኑ ወይም የሐሰት ትምህርትን የሚደግፉ ነበሩ።00:51:35
00:51:36
እንዲያውም አንዳንድ ትርጉሞች የይሖዋን ስም በባዕድ አምላክ ስም ተክተዋል።00:51:39
00:51:39
የትርጉም መሣሪያዎች፣ ቴክኖሎጂዎችና ሥልጠናዎች እየተሻሻሉ መጡ።00:51:44
00:51:44
በመሆኑም የበላይ አካሉ በ2004 መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት እንዲተረጎም መመሪያ አስተላለፈ።00:51:49
00:51:49
አንድ የትርጉም ቡድን መጠበቂያ ግንብ መተርጎም ከጀመረ በኋላ ቀጣይ ግቡ መጽሐፍ ቅዱስ መተርጎም ሆነ።00:51:55
00:51:55
ይህም የወንድም ሽሮደር ምኞት እንዲሳካ ጥሩ መንደርደሪያ ሆነ።00:51:59
00:51:59
የትርጉም ቡድኖቹ ከፊታቸው አስደናቂ ሥራ ይጠብቃቸው ነበር።00:52:03
00:52:03
ሥራው ግን አንዴ ተርጉሞ በመጨረስ ብቻ የሚያበቃ አይደለም።00:52:06
00:52:06
ቋንቋ በየጊዜው እየተለወጠ ስለሚሄድ ትርጉሙም መገምገም ያስፈልገዋል።00:52:10
00:52:11
ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት በትክክል እንዲተላለፍ ያደርጋል።00:52:14
00:52:15
በአሁን ወቅት ወደ 700 የሚጠጉ ወንድሞችና እህቶች የአምላክን ቃል በመተርጎሙ ሥራ ሙሉ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ።00:52:21
00:52:21
መጽሐፍ ቅዱስን ከኢንተርኔት ለማውረድ ጥቂት ሰከንዶች ብቻ ሊበቁ ይችላሉ።00:52:25
00:52:25
ሆኖም መላውን መጽሐፍ ቅዱስ ለመተርጎም ከአምስት እስከ ሰባት ዓመታት ይፈጃል።00:52:30
00:52:30
በአሁኑ ወቅት የይሖዋ በረከት ተጨምሮበት 00:52:33
00:52:33
የእሱን ስም የሚያስከብር የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ከ325 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛል።00:52:38
00:52:39
ደግሞም ይህ ትርጉም ትክክለኛና በቀላሉ የሚገባ ነው።00:52:42
00:52:42
ጥቂት አስፋፊዎች ያሏቸው ቡድኖችም እንኳ በራሳቸው ቋንቋ አዲስ ዓለም ትርጉምን ማግኘት ይችላሉ።00:52:47
00:52:47
ለመሆኑ ትሑት ሰዎች የአምላክን ቃል ልባቸውን በሚነካ ቋንቋ ሲያገኙ ምን ይሰማቸዋል?00:52:52
00:52:52
ይደሰታሉ!00:52:54
00:52:54
በደስታ ይፈነድቃሉ! 00:52:55
00:52:56
የአምላክን ቃል በምድር ላይ ለሚኖር ብሔር፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ መተርጎም 00:53:01
00:53:01
ምሥራቹ የሰዎችን ልብ እንዲነካ የሚያስችል አንድ እርምጃ ብቻ ነው።00:53:05
00:53:06
ወሳኙን እርምጃ የምትወስደው አንተ ነህ።00:53:08
00:53:08
መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ ልብህን እንዲነካው ፍቀድ።00:53:11
00:53:11
በውስጡ የሚገኘውን ሕይወት አድን መልእክትም00:53:13
00:53:13
ለብዙዎች ለማዳረስ የምትችለውን ሁሉ አድርግ።00:53:16
00:53:19
እናንተም እንደነዛ ወንድሞች በደስታ ጨፍራችሁ ነበር?00:53:22
00:53:22
አዲስ ዓለም ትርጉምን በራሳችን ቋንቋ ማግኘት እጅግ ያስደስታል።00:53:27
00:53:29
ከዚህ ወር ፕሮግራም ምን ትምህርት አገኘን?00:53:31
00:53:32
ከአምላክ ቃል የምናገኘው ጠቃሚ ምክር 00:53:34
00:53:34
ቀላል ዓይንና ብሩሕ ሰውነት እንዲኖረን ያስችለናል።00:53:37
00:53:37
አንዳንድ መሥዋዕቶች ቢያስከፍለንም 00:53:39
00:53:39
አገልግሎታችንን ለማስፋት ስንል ኑሯችንን ቀላል ማድረጋችን እውነተኛ ደስታ ያስገኝልናል። 00:53:45
00:53:46
በአቅራቢያችሁ ቅርንጫፍ ቢሮ የሚገኝ ከሆነ 00:53:48
00:53:48
በተመላላሽነት ማገልገል ትችሉ እንደሆነ ለምን አታስቡበትም?00:53:53
00:53:54
የዘካርያስ መጽሐፍ ይሖዋ ምን ያህል ኃይል እንዳለውና00:53:57
00:53:57
ልክ እንደ ይሖዋ ሌሎችን ማበረታታት የምንችለው እንዴት እንደሆነ አስተምሮናል።00:54:01
00:54:02
ደስ የሚል የሙዚቃ ቪዲዮም አይተናል።00:54:04
00:54:05
እኔ በጣም ወድጄዋለሁ፣ እናንተስ?00:54:07
00:54:08
ሞት የነጠቀንን የምንወዳቸውን ሰዎች መልሰን ስናገኝ ምን ያህል እንደምንደሰት አስቡት!00:54:14
00:54:17
በዚህ ወር ሰላም ታይዘንላችሁ የመጣነው 00:54:19
00:54:19
በሉክሰምበርግ ከሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ነው።00:54:22
00:54:23
ሉክሰምበርግ በማዕከላዊ አውሮፓ የምትገኝ ትንሽ አገር ናት።00:54:26
00:54:26
ስያሜዋ የተገኘው “ትንሽ ምሽግ” የሚል ትርጉም ካላቸው ቃላት ነው።00:54:30
00:54:31
ይህ መሆኑ አያስገርምም።00:54:32
00:54:32
በአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ከ70 የሚበልጡ ጥንታዊ የድንጋይ ግንቦች ይገኛሉ።00:54:38
00:54:38
እዚህ ላይ የምታዩት የቦርሻይድ ግንብ ከሲውር ወንዝ ከፍ ብሎ ይገኛል።00:54:42
00:54:42
ዙሪያውን 11 የድንጋይ ማማዎች አሉት።00:54:45
00:54:45
በአቅራቢያው ከ700 ዓመት በላይ ያስቆጠረው የቪያንደን ግንብ ይገኛል።00:54:49
00:54:49
የተገነባው ሮማውያን ከ1700 ዓመታት በፊት በገነቡት ሕንፃ መሠረት ላይ ነው።00:54:55
00:54:56
ለብዙ መቶ ዓመታት ጸንተው እንደቆሙት እንደነዚህ ግንቦች 00:54:59
00:54:59
በዚያ የሚገኙ ታማኝ ምሥክሮችም በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ጸንቶ ቆመዋል።00:55:05
00:55:06
ለምሳሌ ከአካባቢው ቀሳውስት ከባድ ተጽዕኖና ተቃውሞ ቢያጋጥመውም00:55:10
00:55:10
ዩጂን ሮይተር ቤቱን ለመንግሥቱ ሥራ ክፍት አድርጓል።00:55:14
00:55:15
በ1933 በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች ማስቀመጫና ማሰራጫ ሆኖ ያገለገለው የእሱ ቤት ነበር።00:55:24
00:55:25
በሩ ላይ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበርን ምልክት ማንጠልጠሉ00:55:28
00:55:29
የነበረውን እምነትና ድፍረት ያሳያል።00:55:31
00:55:32
በ1940 የጀርመን ሰራዊት አገሪቱን ሲቆጣጠር 00:55:36
00:55:36
ሮዛሊ ፎንክ በቤቷ ጽሑፎች ስለተገኙ ታሰረች።00:55:39
00:55:40
ባለሥልጣናቱ የእምነት አጋሮቿንና የመሪዋን ማንነት እንድትናገር ሊያስገድዷት ሞከሩ።00:55:46
00:55:46
እሷ ግን “መሪዬ ይሖዋ አምላክ ነው” በማለት መለሰችላቸው።00:55:50
00:55:51
በዚያው ጊዜ ቪክተር ብሮ ለጦርነቱ ድጋፍ ስላልሰጠ ታሰረ።00:55:56
00:55:56
ወደ ቡኸንቫልድ የማጎሪያ ካምፕም ተላከ።00:55:59
00:55:59
ባለሥልጣናቱ ወንድሞችን ለሰዓታት እንዲቆሙ፣ ለሊቱን ሙሉ እንዲሠሩና00:56:04
00:56:04
የማይመች የእንጨት ጫማ አድርገው እንዲጓዙ ያስገድዷቸው ነበር። 00:56:08
00:56:08
ወንድሞች ግን እርስ በርስ ይበረታቱ ነበር።00:56:10
00:56:10
በኋላም ቪክተር ወደ ኦሽዋቲዝ የማጎሪያ ካምፕ ቢወሰድም እምነቱ አልተዳከመም።00:56:16
00:56:16
በዚያም ምሥራቹን መስበኩን ቀጥሏል።00:56:18
00:56:19
ዛሬም ቢሆን በአገሪቱ የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ተመሳሳይ ፍቅርና እምነት እያሳዩ ነው።00:56:24
00:56:24
በአሥር የተለያዩ ቋንቋዎች ምሥራቹን የሚሰብኩ ከ2,000 በላይ አስፋፊዎች ይገኛሉ።00:56:30
00:56:30
ወንድሞችና እህቶች እርስ በርስ ይበረታታሉ።00:56:33
00:56:33
የባቄላ ሾርባ፣ በጭስ የተጠበሰ የአሳማ ሥጋና ቦሎቄ የመሳሰሉ ጣፋጭ ምግቦች ይመገባሉ።00:56:40
00:56:40
በስብሰባዎችም ላይ አንድ ላይ በደስታ ይዘምራሉ።00:56:42
00:56:43
በአለማንድ ጉባኤ ውስጥ የሚገኙ 84 አስፋፊዎች ይሖዋን በመዝሙር ሲያወድሱ እናዳምጥ።00:56:49
00:56:56
በሉክሰምበርግ የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ሞቅ ያለ ፍቅራቸውንና ሰላምታቸውን ልከዋል።00:57:02
00:57:02
የእኛም ሰላምታ ይድረሳችሁ።00:57:04
00:57:04
ይህ ከይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት የሚተላለፍላችሁ 00:57:08
00:57:08
JW ብሮድካስቲንግ ነው!00:57:10
JW ብሮድካስቲንግ—ጥቅምት 2026
-
JW ብሮድካስቲንግ—ጥቅምት 2026
ወንድሞችና እህቶች፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!
ጥሩ እይታ እንዳለን ለማወቅ በየጊዜው የዓይን ምርመራ እናደርጋለን።
ግን መንፈሳዊ እይታችንንስ እንመረምራለን?
መንፈሳዊ እይታችን እየደበዘዘ እንደሆነ ከተሰማን
ጥርት ያለ እይታ እንዲኖረን ምን ማድረግ እንችላለን?
አንዳንዶች ጥርት ያለ መንፈሳዊ እይታ እንዲኖራቸው የረዳቸው አንዱ ነገር ቤቴል በተመላላሽነት ማገልገላቸው ነው።
ይህ ምን እንደሚመስል እናያለን።
ስለ አስደናቂው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ታሪካችንም እንመለከታለን።
ይህ JW ብሮድካስቲንግ ነው!
እይታችሁ እንዴት ነው?
እንደ እኔ መነጽር የምታደርጉ ከሆነ
ዓይናችሁ በመጠኑም ቢሆን ችግር አለበት ማለት ነው።
የኔ ችግር ማዮፒያ ይባላል።
ከርቀት የማየት ችግር ነው።
አንድን ነገር ሳይ የማየው ነገር ምሥል ሬቲናዬ ላይ ከማረፍ ይልቅ
ከሬቲናዬ ፊት ለፊት ይቀመጣል።
ይህ ደግሞ ሩቅ ያሉ ነገሮች በደንብ አንዳይታዩኝ ያደርጋል።
የዚህ ተቃራኒ ችግር ደግሞ ሃይፕሮፒያ ይባላል።
ቅርብ የሆነ ነገር የማየት ችግር ነው።
የምናየው ምሥል ከሬቲናችን ጀርባ ስለሚሄድ
ቅርብ ያሉ ነገሮችን ጥርት አድርጎ ማየት ያስቸግራል።
ሁለቱም ችግሮች ሊኖሩብንም ይችላል።
አንዱ ከቅርብ፣ አንዱ ከሩቅ ማየት ሊቸግረው ይችላል።
ያም ሆነ ይህ ችግሩን ለማስተካከል ተገቢውን መነጽር ስናደርግ
ዓይናችን በትክክል ማየት ይችላል።
አንደ ዓይነስውርነት ያለ የከፋ ችግርም አለ።
ይህ የሚስተካከለው ግን በአዲሱ ሥርዓት ነው።
ሆኖም አሁን ከጠቀስኩት ይበልጥ እጅግ አደገኛ የሆነ የእይታ ችግር አለ።
ይህን ችግር ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ ጠቅሶታል።
ማቴዎስ ምዕራፍ 6ን እናውጣና
ቁጥር 22 እና 23 ላይ ምን እንዳለ እንመልከት።
“የሰውነት መብራት ዓይን ነው።”
እስቲ እዚህ ላይ ቆም እንበል።
ኢየሱስ “የሰውነት መብራት ዓይን ነው” ሲል ምን ማለቱ ነው?
ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው።
ዓይናችን በጨለማ መንገድ ላይ እንደተተከለ መብራት ነው።
ሳንደናቀፍ እንድንሄድ ይረዳናል።
በተጨማሪም ኢየሱስ ስለ ምሳሌያዊው ዓይናችንም መናገር ፈልጓል።
ይሖዋ ያዘዘንን ነገር ለማደርግ ያለንን አመለካከት ማለት ነው!
በመቀጠል ደግሞ ኢየሱስ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን አነጻጽሮ ተናገረ።
ንባባችንን እንቀጥል።
“ዓይንህ በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ ከሆነ መላ ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል።
ይሁን እንጂ ዓይንህ ምቀኛ ከሆነ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል።”
ያነጻጸረው በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ ዓይንንና ምቀኛ የሆነን ዓይን ነው።
የመጀመሪያው ሕይወታችንን ብሩህ ያደርጋል።
ሁለተኛው ደግሞ ሕይወታችንን ያጨልማል።
የምንመርጠው ነገር በሕይወታችን ላይ ለውጥ ያመጣል።
በጥሩ ወይም በመጥፎ!
እኛም በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ምንጊዜም ትኩረት ማድረግ አለብን።
የዚህ ንግግር ጭብጥም <i>ትኩረታችን</i><i> </i><i>የአምላክን</i><i> </i><i>ፈቃድ</i><i> </i><i>በመፈጸም</i><i> </i><i>ላይ</i><i> </i><i>ይሁን</i><i> </i>የሚል ነው።
ግን አምላክ ለእኛ ያለው ፈቃድ ምንድን ነው?
በአጭሩ እሱ ከእኛ የሚፈልገው እንድናውቀው፣
ወደ እሱ እንድንቀርብ፣ እንድንታዘዘው፣ እንድንወደውና እንድናገለግለው ነው።
በሙሉ ልባችን!
በዚህ ረገድ ኢየሱስ ጥሩ ምሳሌ ትቶልናል።
ዮሐንስ 6:38 ላይ የሕይወቱ ዋነኛ ዓላማ
‘የእሱን ፈቃድ ሳይሆን የላከውን ፈቃድ መፈጸም’ እንደሆነ ተናግሯል።
የኢየሱስ ዓይን ያተኮረው በአንድ ነገር ላይ ብቻ ነበር።
በአገልግሎቱ ላይ!
ጊዜውንና ጉልበቱን መንግሥቱን ለማስፋፋት ተጠቅሞበታል።
ዓለማዊ ግቦችን ለማሳደድ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ለማግኘት
ወይም ቁሳዊ ነገሮችን ለማካበት አልሞከረም።
ተከታዮቹንም ምንጊዜም ይሖዋን በማገልገል ላይ እንዲያተኩሩ አበረታቷቸዋል።
ወደ አምላክ መንግሥት የሚገቡት የአባቱን ፈቃድ የሚያደርጉ ብቻ እንደሆኑ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል።
ሁላችንም ትኩረት ማድረግ ያለብን በዚህ ላይ ነው።
መንግሥቱን በማስቀደምና በቅንዓት በመስበክ
ሕይወታችን በአምላክ ፈቃድ ዙሪያ እንዲያጠነጥን ማድረግ ይኖርብናል።
በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ ዓይን ያለው ሰው ቀላል ሕይወት ይመራል።
ኑሮውንም አያወሳስብም።
የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ለማግኘት ወይም
ዓለም የሚያቀርበውን ሁሉ ለማግበስበስ አንሯሯጥም።
በአምላክ ፈቃድ ላይ ብቻ በማተኮር መንፈሳዊው ዓይናችን ብሩህ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ እንችላለን።
ይህ ደግሞ ምቀኛ ዓይን ካላቸውና አስፈላጊ በሆነው ነገር ላይ ማተኮር ከማይችሉ ሰዎች ዓይን በጣም የተለየ ነው።
የእነዚህ ሰዎች መንፈሳዊ ዓይን ቅብዝብዝ፣ ሸውራራና ስግብግብ ነው።
ምሳሌ 17:24 እንደሚለው ዓይናቸው ‘እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታል’።
አስተሳሰባቸውና ምኞታቸው እዚህም እዚያም የተበታተነ ነው።
ዋናውን ነገር ግን ይተዉታል።
አምላክን ከማገልገል ይልቅ በቁሳዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ሕይወታችን ጨለማ እንዲሆን ያደርጋል።
ኢየሱስ ያለውን ለመረዳት ዓይናችን የሚሠራበትን መንገድ እንመልከት።
ይህ ሥዕል በ1915 የታተመ ነው።
ያዘጋጀው ዊሊያም ሂል የተባለ ታዋቂ ሠዓሊ ነው።
እዚህ ሥዕል ላይ የሁለት ሰዎች ጭንቅላትና ትከሻ ይታያል።
የአንዲት ወጣትና የአንዲት አሮጊት ሴት!
ሁለቱንም አያችኋቸው?
የወጣቷ ፊት በከፊል ነው የሚታየው።
ይሄ የግራ ጉንጯ ነው።
የግራ ጆሮዋ፣
አፍንጫዋ፣
ሽፋሽፍቷ፣
ይሄ ደግሞ መንጋጭላዋ።
አንገቷ ላይ ደግሞ የሆነ ነገር አስራለች።
ይሄ ጸጉሯ ነው፤
ይሄ ደግሞ ኮፍያዋ።
ይሄ ትከሻዋ ነው።
አሮጊቷ ሴትስ?
የሚታየው የግራ ፊቷ ነው።
ይህ አፍንጫዋ ነው።
ግራ ዓይኗ፣
አፏ፣
አገጯ፣
ይሄ ደግሞ ጸጉሯ፣
ኮፍያዋ፣
ይሄ ደግሞ ትከሻዋ።
በአንድ ጊዜ ሁለቱንም ሴቶች ማየት አትችሉም።
አንዱ ላይ ማተኮር ይኖርባችኋል።
የምታዩት ትኩረት ያደረጋችሁባትን ሴት ነው።
እስቲ ከምንጋገርበት ነጥብ ጋር እናያይዘው።
በዙሪያችሁ ያለውን አሮጌ ዓለም ከአምላክ አዲስ ዓለም አንጻር እንዴት ታዩታላችሁ?
ሰይጣን የእሱን ዓለም ማራኪ፣ አጓጊና አስደሳች ነገሮች የሞሉበት አድርጎ ለማቅረብ ይሞክራል።
እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የእሱ አሮጌ ዓለም እዚህ ላይ እንደምትታየው አሮጊት ነው።
በቅርቡ የአምላክ መንግሥት መጥቶ ሙሉ በሙሉ ጠራርጎ ያጠፋዋል።
ከዚህ በተቃራኒው አዲሱን ዓለም በወጣቷ ሴት ልንመስለው እንችላላን።
የአምላክ አዲስ ዓለም ውበቱን እንደያዘ ለዘላለም ይቀጥላል።
በዚያ የሕያዋን ፍጥረታት ፍላጎት ሁሉ ይሟላል።
ስለዚህ ይሖዋ የሰጠንን የማስተዋልና የማመዛዘን ችሎታ ተጠቅመን
በሰይጣን ዓለምና በአዲሱ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ አለብን።
የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በዚህ ረገድ ይረዳናል።
በአንድ ጊዜ ሁለቱም ነገሮች ላይ ማተኮር አንችልም።
ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ቁሳዊ ነገሮችን እያሳደደ
ይሖዋ አምላክን በሙሉ ልቡ ማገልገል አይችልም።
ሐዋርያው ዮሐንስ ለዚህ ዓለም የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ነበረው።
ይህን ዓለም አስመልክቶ የተናገረውን 1 ዮሐንስ 2:15-17 ላይ እንመልከት።
ልንወዳቸው የማይገቡ ሁለት ነገሮችን ጠቅሷል።
ከእነዚህ ሁለት ነገሮች አለመውደድ የሚቀልለን የትኛውን ነው?
“ዓለምንም ሆነ በዓለም ውስጥ ያሉትን ነገሮች አትውደዱ።
“ማንም ዓለምን የሚወድ ከሆነ የአብ ፍቅር በውስጡ የለም፤
“ምክንያቱም በዓለም ያለው ነገር ሁሉ ይኸውም የሥጋ ምኞት፣ የዓይን አምሮትና
“ኑሮዬ ይታይልኝ ማለት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመነጭ አይደለም።
“ከዚህም በተጨማሪ ዓለምም ሆነ ምኞቱ ያልፋሉ፤
የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።”
አትውደዱ ከተባልናቸው ሁለት ነገሮች ማለትም ከዚህ ዓለምና በውስጡ ካሉት ነገሮች አለመውደድ የሚቀለን የቱ ነው?
ዓለምን አለመውደድ ይቀላል ቢባል አትስማሙም?
ምክንያቱም የሰይጣን ዓለም ማለትም የሐሰት ሃይማኖት፣ የፖለቲካው ሥርዓት፣ የንግዱ ሥርዓት
ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፉ ለማየት እንመኛለን።
ሆኖም የሰይጣን ዓለም ትኩረታችንን የሚከፋፍሉ በርካታ ነገሮችን ያቀርባል።
በዚህ ዓለም ውስጥ ያሉ አንዳንድ ነገሮች በጣም የሚያጓጉ፣ የሚያማልሉና የሚማርኩ ሊሆኑ ይችላሉ።
ሰይጣን እነዚህን ነገሮች ተጠቅሞ የሰው ልጆችን ያሳስታል።
የሰው ልጆችን በማታለል ረገድ በጣም ውጤታማ ከሆኑለት መሣሪያዎች አንዱ የዓይን አምሮት ነው።
አንዲት ፍሬ ብቻ በመጠቀም ሔዋንን ጉድ እንደሠራት አስታውሱ!
‘በዓለም ውስጥ ያሉ ነገሮች እየማረኩኝ ነው?’ የሚለውን ለማጣራት በየጊዜው ልባችንን እንፈትሽ።
አንድ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ባሉ ነገሮች ላይ ካተኮረ
አልፎ ተርፎም እነዚህን ነገሮች መመኘት ከጀመረ
ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን የአምላክን ፈቃድ ማድረግ ከባድ ይሆንበታል።
ስለዚህ ትኩረታችን ይሖዋን በሙሉ ልባችን በመውደድና
ለእሱ ምርጣችንን በመስጠት ላይ ማረፍ ይኖርበታል።
በየጊዜው የዓይን ምርመራ ማድረጋችን ጠቃሚ እንደሆነ ሁሉ
መንፈሳዊ እይታችንን ማስተካከል ያስፈልግ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ
በየጊዜው ራሳችንን መመርመራችንም ጥበብ ነው።
መንፈሳዊ እይታችንን እንዴት እንመርምር?
ለዓይን ምርመራ የምንጠቀምበትን ሰንጠረዥ ታውቁታላችሁ?
ዓይናችንን ለመመርመር የምንጠቀምበት ሰንጠረዥ ነው።
በተመሳሳይም 2 ጴጥሮስ 1:5-7 ላይ ለምርመራ የሚረዱ ባሕርያት ተዘርዝረዋል።
እስቲ እናንብባቸው።
“በመሆኑም ልባዊ ጥረት በማድረግ በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ጨምሩ፤
“በበጎነት ላይ እውቀትን፣ በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፣
“ራስን በመግዛት ላይ ጽናትን፣ በጽናት ላይ ለአምላክ ማደርን፣
“ለአምላክ በማደር ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣
በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።”
እነዚህን ባሕርያት በሕይወታችን በማንጸባረቅ ረገድ እንዴት ነን?
እስቲ አንድ በአንድ እንያቸው።
እምነት፣
ሌሎቹን ባሕርያት በሙሉ ለማዳበር ይህ ባሕርይ የግድ ያስፈልገናል።
እምነታችንን በየጊዜው ማጠናከር ይኖርብናል።
ጠንካራ እምነት ካለን ይሖዋ የሰጣቸው ተሰፋዎች በሙሉ እንደሚፈጸሙ እርግጠኞች እንሆናለን።
በእምነት ዓይናችን ወደፊት የሚፈጸሙትን ተስፋዎች ማየት እንችላለን።
በጎነት፣
በጎነት በአምላክ ዓይን ትክክል የሆነውን ማድረግ ማለት ነው።
ሌሎችን የሚጎዳ ወይም መጥፎ ነገር ከማድረግ እንድንቆጠብ ያደርገናል።
በተጨማሪም ለሌሎች መልካም ለማድረግ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን እንድንፈልግ ያደርገናል።
እውቀት፣
በተለይ አዳዲስ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን
ትክክል የሆነውን ካልሆነው ለመለየት እውቀት የግድ ያፈልገናል።
መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት በማጥናት ይሖዋ ከእኛ ምን እንደሚፈልግ መረዳት እንችላለን።
በሕይወታችን ውስጥ ጥበብ ያዘሉ ውሳኔዎችንም ማድረግ እንችላለን።
ራስን መግዛት፣
ግሪክኛው ቃል በቃል “ራስን አጥብቆ መያዝ” የሚል ፍቺ አለው።
ኃጢአት እንዳንሠራ በአስተሳሰባችን፣ በንግግራችንና በድርጊታችን ላይ ገደብ በማበጀት
ሕይወታችንን ከአምላክ መሥፈርቶች ጋር በሚስማማ መንገድ እንድንመራ ይረዳናል።
ጽናት፣
ይሖዋ በሚሰጠው ጥንካሬ በመታመን በድፍረት ተስፋ ሳይቆርጡ መቀጠል ማለት ነው።
አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ተስፋው እንዳይጠፋብን ይረዳናል።
ጽናት ስደት ሲያጋጥመንና በፈተና እንዳንወድቅ ጥረት ስናደርግ የይሖዋን እጅ ለማየት ያስችለናል።
ለአምላክ ማደር፣
በውስጣችን ስለ ይሖዋ የሚሰማን ስሜት ነው።
አምላከን እንድናከብረው፣ እንድንፈራው፣ ለሉዓላዊነቱ እንድንገዛ ያደርገናል።
ይሖዋ ሕዝቦቹን እንዴት እንደያዛቸው እንድናይ ያስችለናል።
ለአምላክ ባለን ፍቅር ተነሳስተን እሱን በሚያስደስት መንገድ እንድንኖር ያነሳሳናል።
ወንድማዊ መዋደድ፣
ወንድማዊ መዋደድ ይሖዋን ለመምሰል ያስችለናል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ድክመት ላይ እንዳናተኩር ያደርገናል።
እንደ ቤተሰባችን እንድንወዳቸውና በተቻለን መጠን እንድንረዳቸው ያነሳሳናል።
ፍቅር፣
ለወንድሞቻችን ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር የይሖዋ ዓይነት አመለካከት እንዲኖረን ያስችለናል።
በመንፈሳዊ እንድንረዳቸው ማለትም ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመን እውነትን እንድንነግራቸው ያነሳሳናል።
ምሳሌያዊውን ሰንጠረዥ ተጠቅመን እይታችንን መርምረናል።
ቀጣዩቹ ቁጥሮች ደግሞ የምርመራውን ውጤት ይነግሩናል።
“እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና ቢትረፈረፉ፣
“ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ትክክለኛ እውቀት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ
“ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ይጠብቋችኋል።
እነዚህ ነገሮች የሚጎድሉት ማንኛውም ሰው ብርሃን ላለማየት ዓይኑን የጨፈነ ዕውር ሰው ነው።”
ጥሩ መንፈሳዊ እይታ ያለን መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው።
ይህን ምክር በመከተል ልባዊ ጥረት ካደረግን እነዚህ ስምንት ባሕርያት በውስጣችን ይትረፈረፋሉ።
ከአምልኳችን ጋር በተያያዘ ሥራ ፈት ወይም ፍሬ ቢስ አንሆንም።
ከዚህ ይልቅ የአምላክ ፈቃድ በማደረግ ረገድ ፍሬያማ እንሆናለን።
እነዚህን ባሕርያት ማንጸባረቅ ከተሳንን ግን በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት እናጣለን።
በመንፈሳዊም እንታወራለን።
በአንዳንዶቹ ባሕርያት ረገድ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገን አስተውለን ይሆናል።
እይታችንን በማጥራት ትክክለኛው ነገር ላይ ማተኮር ይኖርብን ይሆናል።
ይህን እንዴት እናድርግ?
እስቲ አራት ነገሮችን እንመልከት።
አንደኛ፣ የአምላክን ቃል ማጥናትና ማሰላሰል
የዓይን ሐኪም ጋር ብትሄዱ ዓይናችሁ እርጥበት እንዲኖረውና ቶሎ እንዲድን ጠብታ ያዝላችሁ ይሆናል።
ዓይናችሁ እንዲያርፍና መድኃኒቱ እንዲሠራም የዓይን መሸፈኛ ሊሰጣችሁ ይችላል።
በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መንፈሳዊ ዓይናችን
በእውነት ውኃ እንዲረጥብና በአምላክ ቃል እንዲታከም ያደርጋል።
ማሰላሰል ደግሞ መመሪያዎቹ ከእኛ ጋር እንዲዋሃዱና ወደ ልባችን ጠልቀው እንዲገቡ ያስችላል።
ይህ ደግሞ የይሖዋን ፈቃድ፣ አስደናቂ ሥራዎቹን እንዲሁም የሰጠንን ተስፋ እንዳንረሳ ይረዳናል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የሆኑት ዊሊያም ባርክሌ እንዲህ ብለዋል፦
“ለአንድ ቅን ክርስቲያን የአምላክን ቃል ማጥናት የሚያስደስት ነገር እንጂ አድካሚ ሥራ አይደለም።
ምክንያቱም ልቡ የሚናፍቀውን ምግብ የሚያገኘው ከዚህ የአምላክ ቃል እንደሆነ ያውቃል።”
ሁለተኛ፣ የተማርነውን ተግባራዊ ማድረግ
እይታችንን እየለዋወጥን የዓይናችንን ጡንቻዎች ማሠራት እንችላለን።
በተመሳሳይም የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች በሕይወታችን ተግባራዊ ስናደርግ ምክሮቹ ጠቃሚ እንደሆኑ እንገነዘባለን።
በተጨማሪም በአገልግሎት በቅንዓት በመካፈልና በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ በመስጠት እምነታችንን በሥራ መደገፍ እንችላለን።
ሦስተኛ፣ የመንፈስ ቅዱስን አመራር መከተል
አንዳንድ ውስብስብ የሆኑ የዓይን ችግሮችን ለማከም የጨረር ሕክምና ማግኘት ያስፈልግ ይሆናል።
የአምላክ መንፈስ በምሳሌያዊ ሁኔታ መንፈሳዊነታችንን እንደሚያክም ጨረር ነው ማለት ይቻላል።
የአምላክ መንፈስ አስተሳሰባችንና ድርጊታችንን እንዲመራው በፈቀድን መጠን መንፈሳዊ እድገታችንም እየጨመረ ይመጣል።
አራተኛ፣ የሌሎችን እርዳታ መቀበል
አንዳንዴ ሐኪማችን የዓይን ቀዶ ሕክምና ማድረግ እንዳለብን ሊወስን ይችላል።
በተመሳሳይም አንዳንድ ጊዜ ሽማግሌዎች ከምንም ነገር በላይ ስለት ያለውን የአምላክን ቃል በመጠቀም
ቀጥተኛ ምክር ወይም ከባድ ተግሣጽ ሊሰጡን ይችላሉ።
የሚሰጠንን ምክር ከተቀበልን ተጠቃሚዎች እንሆናለን።
እስካሁን ምን ተማርን?
እይታችን በትክክለኛው ነገር ላይ ካተኮረ አእምሯችን ስለ አምላክ ፈቃድ፣
ስለ መንግሥቱና ስለሰጠን ተስፋዎች ጥርት ያለ እይታ ይኖረዋል።
ምቀኛ ዓይን ካለን ስለ አዲሱ ዓለም ያለን እይታ ደብዛዛ ይሆንብናል።
እውን ሆኖም አይታየንም።
ቅድም እንዳሳየኋችሁ ዓይናችን በተመሳሳይ ጊዜ በሁለት ነገሮች ላይ ማተኮር አይችልም።
በዚህ አሮጌ ዓለም ባሉ ነገሮች የምንቀና ከሆነ የአምላክ ፈቃድ እየደበዘዘብን ይመጣል።
ቀስ በቀስ ደግሞ ከእይታችን ይሰወራል።
ማናችንም ብንሆን ይህ እንዲደርስብን አንፈልግም።
መንፈሳዊ ዓይናችን ምንጊዜም በአምላክ ፈቃድ ላይ እንዲያተኩር ማድረጋችን በጣም አስፈላጊ ነው።
እንግዲያው ለሰማያዊው አባታችን ለዘላለም የሙሉ ነፍስ አገልግሎት ማቅረባችንን እንቀጥል።
አንድ ባልና ሚስት ጥርት ያለ መንፈሳዊ እይታ እንዲኖራቸውና
ደስተኞች እንዲሆኑ የረዳቸው ምን እንደሆነ እስቲ እንመልከት።
ገና በሃያዎቹ ዕድሜ መጀመሪያ ላይ እያለን
ቪየና ከተማ ውስጥ ዓይን የሆነ ቦታ ላይ አፓርታማ ገዛን።
በየወሩ ግን የባንክ ዕዳ መክፈል ነበረብን።
በጣም የሚያምር አፓርታማ ነበር።
አዎ ልክ ነሽ።
ደግሞም እኮ የራስ ነገር ሲኖር በጣም ነው ደስ የሚለው።
ሐሳቤ ሁሉ ገንዘብ ማግኘት ላይ ነበር።
ምክንያቱም ይህ ዶሪስን እንደሚያስደስታት አስብ ነበር።
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ከክርስቲያናዊ ስብሰባዎች መቅረት ጀመርን።
ምንም ዓይነት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ አናደርግም ነበር።
ይህ ደግሞ እርስ በርስ እያራራቀን መጣ።
ይህን ያስተዋለ አንድ ሽማግሌ እረኝነት አደረገልን።
ይህ ወንድም ቀጥተኛ ምክር ነው የሰጠኝ።
የቤተሰቡ ራስ እኔ እንደሆንኩ አስታውሶኝ በግልጽ ምክር ሰጠኝ።
ራስ ከሆንኩ ደግሞ የዶሪስን መንፈሳዊነት የመንከባከብ ኃላፊነት ያለብኝ እኔ ነኝ።
ስለዚህ . . .
በቁሳዊ ነገር ብቻ አይደለም።
ልክ ነሽ።
በቁሳዊ ብቻ አይደለም።
የተናገረው ነገር ቆም ብዬ እንዳስብ አደረገኝ።
ኃላፊነቴን መወጣት አለብኝ።
ከምንም በላይ ዶሪስን ማስደሰት እፈልጋለሁ።
ይህ እንዲሆን ደግሞ ሕይወታችን በይሖዋ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት።
ስለ ጉዳዩ በደንብ አወራንበት።
አብረን የመጸለይ ልማድም አዳብርን።
በየቀኑ!
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ውድና ቅንጡ የሆነውን አፓርትመንታችንን
አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብን ተሰማን።
ስለ ጉዳዩ ደግመን ደጋግመን ጸለይን።
ይሖዋን ‘ከዚህ ቤት ጣጣ እንድትገላግለን እንፈልጋለን። እባክህ እርዳን።
ተጨማሪ ሸክም እንዲሆንብን አንፈልግም’ ብለን ለመንነው።
ደግሞም ተሳክቶልናል።
አፓርታማውን መሸጥ ቻልን።
ስለዚህ ከዕዳ ነፃ ሆንን ማለት ነው።
በ2014 ያደረግነው የክልል ስብሰባ ደግሞ ተጨማሪ ብርታት ሰጠን።
መንግሥቱን እንድናስቀድምና የቀረውን ለይሖዋ እንድተወው ተማርን።
ትምህርቱን በሕይወታችን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ አደረግን።
የይሖዋን እጅም አይተናል።
ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእኛም ብዙ ነገር አድርጎልናል።
ከስብሰባው በኋላ ወዲያውኑ ወደ ይሖዋ ጸለይን።
በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የአምላክን መንግሥት ለማስቀደም ቆርጬ ተነሳሁ።
ተሳካልን።
ልክ ነሽ።
ስብሰባው ከተካሄደ ከጥቂት ወራት በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆንን።
እኔ በተሰማራሁበት የግንባታ ዘርፍ ለተወሰነ ሰዓት ብቻ መሥራት የተለመደ አይደለም።
ስለዚህ ማስተካከያ በማድረግ ከመደበኛው የሥራ ሰዓት ቀንሼ ለመሥራት ስወሰን
ጉዳዩን በይሖዋ እጅ መተው ነበረብኝ።
ወጪያችንንና ገቢያችንን ቆም ብዬ ሳሰላ ‘እንዴት ልንቀጥል ነው?’ ብዬ አሰብኩ።
ስለ ጉዳዩ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ።
ደጋግሜ ለመንኩት።
አለቃዬ በየቀኑ ከመደበኛው የሥራ ሰዓቴ ላይ
አንድ አንድ ሰዓት እንዲቀንስልኝ ለመጠየቅ ድፍረት አስፈልጎኛል።
ይሖዋ እንዲህ ለማድረግ እንዲረዳኝና
በእሱ ላይ ሙሉ በሙሉ እንድታመን ጸለይኩ።
ረዳት አቅኚ ሆነን ስናገለግል በጣም ወደድነው።
ስለዚህ ‘በቀጣዩ ዓመት ለምን አቅኚ አንሆንም?’ ተባባልን።
እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ ደግሞ የተለያዩ ዕቅዶች ማውጣት ጀመርን።
“አሁን አቅኚ መሆን የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም” ተባባልን።
የተሰማን ደስታ አትጠይቀን።
ደስ የሚለው ሁሉም ነገር ተሳካ።
ሁሉ ነገር መስመር ያዘ።
ከጊዜ በኋላ ደግሞ አኗኗራችንን ይበልጥ ቀላል ለማድረግ ወሰን።
ቤታችንን አነስ ወዳለ አፓርታማ ቀየርን።
ግን የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ አለው።
ሁለታችንም ወደነዋል።
ቆይ አንድ መጠበቂያ ግንብ ላሳይህ።
በሕይወታችን ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል።
መጠበቂያ ግንቡ “በየዕለቱ ከይሖዋ ጋር ሥሩ” የሚል ርዕስ ይዟል።
በርዕሱ መጨረሻ ላይ የሚገኝ አንቀጽ ላይ አንድ ዓረፍተ ነገር አለ።
እርግጥ ጥያቄ ነው።
እንዲህ ይላል፦
“ቅዱስ አገልግሎት ለማከናወን የበለጠ ብቁ እንድትሆን የሚረዳ ተጨማሪ ሥልጠና ማግኘት ትፈልጋለህ?
ከሆነ በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት መሠልጠን ትችል ይሆናል።”
ለእኛ ተብሎ እንደተጻፈ ነው የተሰማን።
አሁን ምንም ሰበብ የለንም።
ስለዚህ . . .
መጋበዣው ደረሰን።
<i>. . . SKE</i> ተጋበዝን።
በጣም ነበር ደስ ያለን።
<i>SKE</i> ለመማር ሁለት ወር ፈቃድ ማግኘት ቀላል አልነበረም።
ደግሞም ፈቃድ አላገኘሁም።
ሥራዬን ነበር የለቀቅኩት።
እውነቱን ለመናገር ይሄን በማድረጌ አይቆጨኝም።
አሁንም አጋጣሚውን ባገኝ ተመሳሳይ ነገር ነው የማደርገው።
<i>SKE</i> ገብቶ መማር . . .
ይሖዋ እንደሚወደን የሚያረጋግጥ ነው።
. . . ወደፊት ሊጠቀምብን እንደሚፈልግ የሚያሳይ ነበር።
ይሄ
በጣም ደስ የሚል ነው።
እንድናገለግል የተመደብንበት ጉባኤ በጣም አፍቃሪ ነው።
ከዶሪስ ጋር በአቅኝነት ያሳለፍኩትን ጊዜ በጣም ነው የምወደው።
የይሖዋ ፍቅርና እንክብካቤ ተለይቶን አያውቅም።
የሚያስፈልገን ሁሉ አሟልቶልናል።
ከበፊቱ አንጻር ሲታይ አሁን ያለን ነገር ትንሽ ነው።
ግን ሸክማችንም ቀሏል።
ምክንያቱም ይሖዋ እየተንከባከበን ነው።
የሚቆጨን አንዳች ነገር የለም።
እኔ ግን አለኝ።
እንዴ ምን?
ይሄን ነገር ቀደም ብለን ብንጀምረው ጥሩ ነበር።
እሱስ እውነት ነው።
ይህ ቤተሰብ ይሖዋ ሕይወታችንን ቀላል እንድናደርግ የሰጠንን ምክር ተግባራዊ አድርጓል።
በውጤቱም ከጠበቁት በላይ አስደሳችና ትርጉም ያለው ሕይወት መምራት ችለዋል።
ግን ኑሯችሁን ቀላል ማድረግ ከባድ እንደሆነ ከተሰማችሁ ተስፋ አትቁረጡ።
ከዘካርያስ መጽሐፍ ጥሩ ትምህርት ታገኛላችሁ።
የዘካርያስ መጽሐፍ እንደ አዲስ አስገርሞኛል።
አይደል፣ እኔ ራሱ የምናጠናበት ቀን አልደርስ ብሎኝ ነበር።
እንጀምር?
እሺ፣ በባለፈው ጥናታችን ሕይወት ለአይሁዳውያን ከባድ እንደሆነ አይተናል።
በወቅቱ ጠላቶቻቸውና ተቃዋሚዎቻቸው ባደረሱባቸው ጫና ተስፋ ቆርጠዋል።
ቤተ መቅደሱን ከመገንባት በተጨማሪ ኢየሩሳሌምንም መልሰው መገንባት ነበረባቸው።
ቤተሰባቸውንም መንከባከብ ይጠበቅባቸዋል።
ይህ ሁሉ አድክሟቸዋል።
እኛም ዛሬ እንደዛ ይሰማናል።
እውነትሽን ነው።
በሰብዓዊ ዓይን ሲታይ የሚሳካላቸው አይመስልም።
የጦር ሰራዊትም ሆነ ሥልጣን አልነበራቸውም።
ቁጥራቸው ትንሽ፣ ችግራቸው ግን ብዙ ነበር።
ለዛም ነው ይሖዋ ሐጌንና ዘካርያስን በመላክ ያበረታታቸው።
አዎ፣ ሐጌ የተሰጣቸውን ሥራ ለመጀመር የሚያስችል ግልጽ መመሪያ ሰጣቸው።
ዘካርያስ ደግሞ በሥራው እንዲጸኑ ጥልቀት ያለው መንፈሳዊ ማበረታቻ ሰጣቸው።
የዘካርያስ መጽሐፍ ብዙ ትምህርት ስለያዘ
በትንሽ በትንሹ ከፋፍለን ብናጠናው ጥሩ ነው።
እውነትሽን ነው።
የማስተዋወቂያ ቪዲዮው ቁልፍ የሆኑ የመጽሐፉን ክፍሎች ይጠቁማል።
በተለይ ከመሲሑ ጋር የተያያዙት ትንቢቶችን!
ልክ ነህ።
አዲስ ዓለም ትርጉም ላይ የመጽሐፉ ይዘት የሚለውን ክፍልም ወድጄዋለሁ።
የጀመርኩት “መቅረዝና ሁለት የወይራ ዛፎች” ከሚለው ከአምስተኛ ራእይ ነው።
ጥሩ ነው። ታዲያ ምን አገኘሽ?
ምርምር ሳደርግ “ዘካርያስ ያየው ይታያችኋል?” የሚል የጥናት ርዕስ
በመጋቢት 2022 <i>መጠበቂያ</i><i> </i><i>ግንብ</i> ላይ አገኘሁ።
ጽሑፉ ላይ የተጠቀሱት ነጥቦችና ሥዕሉ በጣም ጠቅመውኛል።
ደስ ይላል።
ጽሑፉን ያገኘሽው ግን እንዴት ነው?
<i>የምርምር መርጃ</i> ላይ ያለውን የጥቅስ ማውጫ ተጠቅሜ ነው።
በጣም ጥሩ ዘዴ ነው።
ጽሑፉ ከዛፎቹ የሚመነጨው ዘይት ኃያል የሆነውንና
ፈጽሞ የማይነጥፈውን የይሖዋን ቅዱስ መንፈስ እንደሚያመለክት ይናገራል።
አይሁዳውያኑ በዚህ በጣም ተበረታተው መሆን አለበት።
ዝለውና ተስፋ ቆርጠው ነበር።
ግን ይሖዋ ከጎናቸው እንደሚሆንና እርዳታው እንደማይለያቸው አረጋገጠላቸው።
በተጨማሪም 4:6, 7 ላይ እንዲህ ብሏቸው፦
“‘በመንፈሴ እንጂ፣ በወታደራዊ ኃይል ወይም በጉልበት አይደለም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
ታላቅ ተራራ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ መሬት ትሆናለህ።”
የሚገርም አገላለጽ ነው።
አይሁዳውያኑ እንደ ተራራ ያለ ተቃውሞ ቢያጋጥማቸውም ዘካርያስ ደልዳላ መሬት እንደሚሆን ተናግሯል።
ስለዚህ የፋርስ መንግሥትም ሆነ ሌላ የትኛውም ተቃዋሚ
ወይም እገዳ ሥራውን ፈጽሞ ሊያስቆመው አይችልም።
የጦር ሰራዊት ባይኖራቸውም ይሖዋ አለላቸው።
ይህን ሲሰሙ አንድ ትልቅ ተራራ ተደርምሶ ደልዳላ መሬት ሲሆን በዓይነ ሕሊናቸው አይተው ይሆናል።
ይህ ብቻ ግን አይደለም።
ስኬታቸው የተመካው በይሖዋ መንፈስ ላይ እንጂ
በግለሰቦች ችሎታ ወይም በሁኔታዎች ላይ እንዳልሆነ ግልጽ የሚያደርግ ነው።
አዎ፣ እውነታው ያ ነው።
በመልእክቱ ተበረታተዋል።
ብዙ ከባባድ ችግሮች ቢያጋጥሟቸው በይሖዋ በመታመን በሥራው ገፍተዋል።
ከአራት ዓመት ገደማ በኋላ የቤተ መቅደሱ ግንባታ አለቀ።
የይሖዋን እጅ አይተዋል።
ድንገት በግንባታ ሥራው ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ።
በዙሪያቸው ለነበሩት ብሔራትም ለግንባታ ሥራው ድጋፍ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ተሰጠ።
ይህ ሁሉ የሆነው በይሖዋ መንፈስ እንጂ በሰው ጥረት አይደለም።
ይሖዋ ተራራውን ሜዳ አደረገው።
ታዲያ ይህ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?
የዘካርያስ ራእዮች የይሖዋ መንፈስ የማይቻል የሚመስለንን ነገር ማከናወን እንደሚችል አስተምረውኛል።
ትክክል፣ እኛም አንዳንዴ እንደ አይሁዳውያኑ እንደሚሰማን ይሖዋ ያውቃል።
ልንዝል፣ ተስፋ ልንቆርጥና ልንፈራ እንችላለን።
ስለዚህ ኃይሉ እውን እንዲሆንልን ይፈልጋል።
የዘካርያስ ትንቢት ይህን ለማድረግ ይረዳናል።
አዎ ጠቃሚ ነጥብ ነው።
መጽሐፉን ሳጠና ክንውኑን በዓይነ ሕሊናዬ ለማየት ጥረት ማድረግ።
በትክክል፣ “ዘካርያስ ያየው ይታያችኋል?” የሚለው ርዕስ በራሱ እንዲህ እንድናደርግ ያበረታታናል።
ግን ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
እውነቱን ለመናገር አንዳንዴ ድክም ይለኛል።
ከምናደርጋቸው ብዙ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ
የቤተሰብ ኃላፊነት፣ ሰብዓዊ ሥራ፣ ጤንነታችንን መንከባከብና
የሰይጣን ዓለም የሚያደርስብንን ጫና መቋቋም አለብን።
በዚህ ጊዜ ይህን ሁሉ ማድረግ እንደማንችል ይሰማናል።
እኔም አንዳንዴ ስብሰባዎችን በቪዲዮ ለመከታተል እፈተናለሁ።
እኔም አንዳንዴ እንደዛ ይሰማኛል።
ግን ራእዩን በዓይነ ሕሊናዬ መመልከቴ የሚያስፈልገኝን አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጥንካሬ
ይሖዋ እንደሚሰጠኝ ስለሚያስታውሰኝ ያበረታኛል።
እኔም መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደከበደኝ ሲሰማኝ
ይሖዋ መንፈሱን እንዲሰጠኝ እጸልያለሁ።
ከዛም እርምጃው እወስዳለሁ።
ማለትም ራሴን አስገድጄም ቢሆን ስብሰባ እሄዳለሁ።
አገልግሎት እወጣለሁ።
የሚያስፈልገኝን ኃይል ይሖዋ እንደሚሰጠኝ እተማመናለሁ።
እኔም የይሖዋን ምሳሌ በመከተል ሌሎችን ለማበረታታት የምችለውን ሁሉ እንዳደርግ አነሳስቶኛል።
በተለይ ተስፋ ሲቆርጡ ወይም ሲፈሩ!
ይሖዋ እንደሚያስብላቸውና እንደሚያበረታቸው ላስታውሳቸው እፈልጋለሁ።
አዎ እንዲህ ማድረግ አለብን።
ዛሬ ያገኘነው ትምህርት ወደፊት ስደት ወይም አስፈሪ ሁኔታ ሲያጋጥመንም ይጠቅመናል።
ቅድም ያልከው እውነት ነው።
ስኬታችን የተመካው በችሎታችን ወይም በሁኔታዎች ላይ ሳይሆን በይሖዋ መንፈስ ላይ ነው።
የዘካርያስን መጽሐፍ ያጠናንበትን መንገድ ወድጄዋለሁ።
ከፋፍሎ በትንሽ በትንሹ ማጥናት፣
የጥቅስ ማውጫውን መጠቀምና በዓይነ ሕሊናችን መሳል።
በዚህ መንገድ ማጥናታችን የአምላክን ቃል ሕያው ያደርግልናል።
ልክ ነህ፣ ቀጥሎ ደግሞ ስለ ሁለቱ በትሮች ትርጉም እንወያይ?
ጥሩ ነው፣ እኔም ስለ መሲሑ የሚናገሩትን ትንቢቶች መመርመርና
ከአጠቃላዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጥ ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ማየት እፈልጋለሁ።
ለምሳሌ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን የሚያረጋገጡ የዘካርያስ ድርጊቶችን።
መጽሐፉ ሌሎች ብዙ ራእዮችም ይዟል።
ትክክል፣ የዘካርያስን መጽሐፍ በዚህ መልኩ ከመረመርን
ለቤተሰብ አምልኳችን የሚሆኑ ጥሩ ግብዓቶችን እናገኛለን።
ተግባራዊ የሚሆን ትምህርት ነው ያገኘነው።
ስኬታችን የተመካው ባለንበት ሁኔታ ወይም በችሎታችን ላይ አይደለም።
ይሖዋ ታዛዦች እስከሆንን ድረስ መንፈሱን በመስጠት አብዝቶ ይባርከናል።
አንዳንዶች ጥሩ እይታ እንዲኖራቸው የረዳቸው
ቤቴል በተመላላሽነት ለማገልገል ራሳቸውን ማቅረባቸው ነው።
ቀጣዩ ቪዲዮ ምን እንደሚያከናውኑ ያሳየናል።
<i>ውሏቸው</i><i> </i><i>ምን</i><i> </i><i>ይመስላል</i><i>? </i>
<i>ተመላላሽ</i><i> </i><i>ቤቴላውያን</i><i>! </i>
ሰላም፣ ሄ-ኢን እባላለሁ።
በኮሪያ ቅርንጫፍ ቢሮ በተመላላሽነት እያገለገልኩ ነው።
አልፎ አልፎ ተመላላሽ ስለሆንኩ
ወደ ቤቴል የምሄደው በቋሚነት ሳይሆን ለሥራ ስፈለግ ብቻ ነው።
ቤቴል ለመድረስ የሚፈጅብኝ ጊዜ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ የተመካ ነው።
በአብዛኛው ከ45 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ይፈጃል።
ደስ የሚለው መንዳት እወዳለሁ።
ስለዚህ መመላለሱ አያሰለቸኝም።
ቤቴል ሁልጊዜ ቀኑን የምንጀምረው የማለዳ አምልኮ በማድረግ ነው።
በቅርቡ የሰማሁትን አንድ ንግግር አልረሳውም።
በያዕቆብ 1:2-4 ላይ የተመሠረተ ነው።
የሚያጋጥሙንን ፈተናዎችና መከራዎች እድገት ለማድረግ እንደሚረዱ አስተማሪዎች እንድናያቸው የሚያበረታታ ነበር።
እርግጥ መከራ ውስጥ ስትሆን ‘ከዚህ ሁኔታ ምን ትምህርት አገኛለሁ?’ ብሎ ራስን መጠየቅ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም።
ሆኖም መልእክቱ ግልጽ ነው።
ፈተናዎች ሲያጋጥሙን የግል ጥናት ማድረጋችንን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበባችንን፣
መጸለያችንንና ማሰላሰላችንን የምንቀጥል ከሆነ ፈተናዎቹ እያሉም በደስታ መጽናት እንችላለን።
የማለዳ አምልኮ ሁሌም ያበረታታኛል።
የሆነ የምማረው ነገር አይጠፋም።
የምሠራው በትራንስፖርት ዲፓርትመንት ውስጥ ነው።
ሥራችን በዋነኝነት ከውጭ አገር ቤቴልን ለመጎብኘት ለሚመጡ
የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ነው።
ቤቴል ውስጥ የሚከናወኑት ሥራዎች ዓላማ
በመስኩ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መደገፍ እንደሆነ ሁልጊዜ ለማስታወስ እሞክራለሁ።
ሥራዬ ቤቴልን ለመጎብኘት ከተለያየ የዓለም ክፍል ከሚመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ጋር ያገናኘኛል።
በጣም አመስጋኞች ናቸው።
ይህ ደግሞ በቤቴል የምናከናውነው ሥራ ምን ያህል እየጠቀማቸው እንዳለ እንዳስብ ያደርገኛል።
ይህም ጥልቅ እርካታ አስገኝቶልኛል።
ጉዞው በአብዛኛው ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ሁለት ሰዓት ድረስ ይወስዳል።
በዚህ ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ነገሮችን እናወራለን።
ገና የተገናኘን ቢሆንም ላየን ሰው የቆዩ ጓደኛሞች ነው የምንመስለው።
የልባችንን አውጥተን እናወራለን።
ለምሳሌ ይሖዋ እንዴት እንደደገፈን፣
አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንድንቋቋም የረዳን እንዴት እንደሆነ እናወራለን።
በጉዞ ላይ የምናሳልፋቸውን እንዲህ ያሉ ጊዜያት በጣም ነው የምወዳቸው።
መጀመሪያ ላይ ቤቴል የማገልገል ያን ያህል ፍላጎት አልነበረኝም።
ስለዚህ ማመልከቻውን ለመሙላት ሳመነታ ነበር።
በኋላ ግን አንድ የምቀርበው ወንድም
‘ይሖዋን ለማገልገል ራሳችንን እስካቀረብን ድረስ የምንሠራውን ሥራ መምረጥ አንችልም’ አለኝ።
በጉዳዩ ላይ ሳስብበት ይህ ወንድም ያለኝ ትክክል እንደሆነ ገባኝ።
ስለዚህ ጉዳዩን ለይሖዋ ትቼ ዝም ብዬ ማመልከቻውን ሞላሁ።
እንግዲህ ቤቴል ማገልገል የጀመርኩት በዚህ መልኩ ነው።
አሁንም እዛው እያገለገልኩ ነው።
እርግጥ በሥራ ፕሮግራሜ ላይ ማስተካከያ ማድረግ
ትንሽ ተፈታታኝ ሆኖብኝ ነበር።
በጣም ያሳሰበኝ ‘በቂ ገቢ አገኝ ይሆን?’ የሚለው ነበር።
ቤቴል መመላለስ ስጀምር ግን ሁሉም ነገር መልክ መልክ ያዘ።
የሥራ ፕሮግራሜ ቤቴል መመላለስ በሚያስችለኝ መልኩ ተስተካከለልኝ።
ከሥራዬና ቤቴል ከመመላለስ በተጨማሪ
የቤተሰቤን አባላት የመንከባከብ ኃላፊነትም አለብኝ።
መንፈሳዊ ልማዶቼን ይዤ ለመቀጠል የግል ጥናት የማደርግበት አንድ ቀን መድቤያለሁ።
መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን በቋሚነት ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ምክንያቱም ስዝል ኃይል እንዳገኝ ይረዱኛል።
ይህ ደግሞ በቤቴል ማገልገሌን እንድቀጥልና የመስክ አገልግሎቴን በቅንዓት እንዳከናውን ይረዳኛል።
እንዲህ ያሉት ልማዶች በመንፈሳዊ ሕያው ሆኜ እንድቀጥል ይረዱኛል።
ምንም ያህል ጊዜዬ የተጣበበ ቢሆን ምንጊዜም ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ጊዜ እመድባለሁ።
‘በሌላ ቦታ አንድ ሺህ ቀን ከመኖር በይሖዋ ቤት ውስጥ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል።’
ወደ ቤቴል በምመጣበት ቀን የማስበው ይህን ጥቅስ ነው።
ወደፊት የሚሰጠኝ የሥራ ምድብ ምንም ይሁን ምን
ይሖዋን በደስታና በአመስጋኝነት ስሜት ማገልገል እፈልጋለሁ።
ተመላላሽ ሆኖ ማገልገል ጊዜያችንንና ጉልበታችንን መሥዋዕት ማድረግ ይጠይቃል።
ሄ-ኢን ሚዛናዊ እንድትሆንና ኃይሏ እንዳይሟዋጠጥ የረዳት ምንድን ነው?
በቋሚነት ጥልቀት ያለው የግል ጥናት የምታደርግበት ጊዜ መመደቧ ነው።
ስለ ይሖዋ ቃል ማጥናት መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን በማከም፣
ስለ ወደፊቱ ጊዜ ጥርት ያለ እይታ እንዲኖረን ያስችለናል።
ቀጣዩ የማለዳ አምልኮ ንግግር በዚህ ረገድ ከዳንኤል ምን እንደምንማር ይነግረናል።
የዛሬው ንግግራችን ጭብጥ
<i>በይሖዋ</i><i> </i><i>ታማኝ</i><i> </i><i>ፍቅር</i><i> </i><i>ላይ</i><i> </i><i>ያላችሁን</i><i> </i><i>እምነት</i><i> </i><i>አጠናክሩ</i><i> </i>የሚል ነው።
ግን ማጠናከር ያለብን ለምንድን ነው?
ምክንያቱም ያሳለፍነው ሕይወት፣ አስተዳደጋችን፣ ያጋጠሙን ነገሮች
ወይም ደግሞ ከዚህ በፊት የፈጸምናቸው አንዳንድ ስህተቶች
ይሖዋ የሚወደን መሆኑን እንድንጠራጠር ሊያደርጉን ይችላሉ።
ወይም ደግሞ አሁን እያጋጠሙን ያሉ ችግሮች ይኖራሉ።
ለምሳሌ ያለብን የቤተሰብ ኃላፊነት፣ የሥራ ጫና፣ የጤንነት ችግር
ወይም ሌሎች ነገሮች እያስጨነቁን ይሆናል።
እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን የይሖዋ ፍቅራዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገን እንገነዘባለን።
ወደፊትም ቢሆን እምነታችንን የሚፈትኑ ነገሮች እንደሚያጋጥሙን እናውቃለን።
‘ያኔ በታማኝነት እጸና ይሆን?’ የሚለው ጉዳይ በጣም ያስጨንቀን ይሆናል።
ከዚህ በፊት ያጋጠመን፣ አሁን እያጋጠመን ያለው
ወይም ወደፊት የሚያጋጥመን ነገር ምንም ይሁን ምን ይሖዋ ታማኝ ፍቅር ያሳየናል።
ዳንኤል 9:4ን መመርመራችን ይሖዋ ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳየን እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል።
ጥቅሱ በዛሬው የዕለት ጥቅሳችን ላይ በከፊል ተጠቅሷል።
ዳንኤል 9:4 እንዲህ ይላል፦
“ወደ አምላኬ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ፤ ደግሞም ተናዘዝኩ፤ እንዲህም አልኩ፦
“‘እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ለሚወዱህ፣ ትእዛዛትህንም ለሚያከብሩ
ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅና ታማኝ ፍቅር የምታሳይ ታላቅና የምትፈራ አምላክ ነህ።’”
ይህ እንግዲህ ከዳንኤል ጸሎት ላይ የተወሰደ ሐሳብ ነው።
በጸሎቱ ላይ ስለ ይሖዋ ታማኝ ፍቅርና ይሖዋ ቃል ኪዳኑ እንደሚጠብቅ ጠቅሷል።
ይሖዋ ይህን የሚያደርገው ለሚወዱት እንዲሁም ቃል ኪዳኑን ለሚጠብቁ ነው።
ስለዚህ ይህንን ጸሎትና በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ መመርመራችን
ይሖዋ ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳየን እንድንተማመን ያደርገናል።
በመጀመሪያ ግን ዳንኤል እንዲህ ብሎ እንዲጸልይ ያነሳሳው ምንድን ነው?
እስቲ ዳንኤል 9:2ን እናንብብ፦
“አዎ፣ በዘመነ መንግሥቱ የመጀመሪያ ዓመት እኔ ዳንኤል
“ለነቢዩ ኤርምያስ በተነገረው የይሖዋ ቃል ላይ በተጠቀሰው መሠረት
ኢየሩሳሌም ፈራርሳ የምትቆየው ለ70 ዓመት እንደሆነ ከመጻሕፍቱ አስተዋልኩ።”
ስለዚህ ይህ የሆነው መቼ ነበር?
በ539 ዓመተ ዓለም!
በዚያን ወቅት ኢየሩሳሌም ለ68 ዓመታት ፈራርሳ ቆይታለች።
ዳንኤልም መጻሕፍቱን፣ የግርጌ ማስታወሻው እንደሚለው ቅዱሳን መጻሕፍትን እየመረመረ ነበር።
ዳንኤል በወቅቱ ኤርምያስ ከጻፋቸው በተጨማሪ ሙሴ፣ ኢሳይያስ፣ ሕዝቅኤል፣
አሞጽና ሆሴዕ የጻፏቸውን መጻሕፍት ማግኘት ይችል ነበር።
ዳንኤል፣ ኤርምያስ 29:10ን አንብቦ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።
ኤርምያስ 29:10 እንዲህ ይላል፦
“ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በባቢሎን የምትኖሩበት 70 ዓመት ሲፈጸም ትኩረቴን ወደ እናንተ አዞራለሁ፤
ወደዚህም ስፍራ መልሼ በማምጣት፣ የገባሁትን ቃል እፈጽማለሁ።’”
በወቅቱ እየተፈጸሙ የነበሩት ነገሮች ከትንቢቶች ጋር የሚያያዙት እንዴት እንደሆነ ማስተዋል ይችል ነበር።
በትንቢት በተነገረው መሠረት እስራኤላውያንን ነፃ የሚያወጣው በወቅቱ እየገዛ ያለው ቂሮስ እንደሆነ ያውቃል።
እያንዳንዱ ትንቢት እንዴት እንደሚፈጸም በዝርዝር ባያውቅም ጊዜው መድረሱን ግን ተረድቶ ነበር።
በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ላይ ትኩረት ያደረገውን ይህን ጸሎት እንዲያቀርብ ያነሳሳው ይኸው ነው።
ቁጥር አራት ላይ የጀመረው የዳንኤል ጸሎት የሚደመደመው ቁጥር 19 ላይ ነው።
የጸሎቱ ይዘትና የተጠቀመባቸው ቃላት
ኤርምያስ በጻፋቸው መጻሕፍቶች ውስጥ ያነበባቸው ነገሮች ከአእምሮውና ከልቡ እንዳልጠፉ ያሳያል።
እንዲያውም አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንዳለው ዳንኤል ያቀረበው ጸሎት የተመሠረተው
ኤርምያስ መጽሐፍ ላይ ባሉ አንድ ወይም ሁለት ጥቅሶች ላይ ሳይሆን በመላው መጽሐፍ ላይ ነው።
ይህ ጸሎት እስራኤላውያን የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ምን ያህል እንደሚያስፈልጋቸው ያሳያል።
የይሖዋን ታማኝነትና ርኅራኄ ከእስራኤላውያን ዓመፀኝነትና ታማኝ አለመሆን ጋር ያነጻጽራል።
ዳንኤል እስራኤላውያን ያጋጠማቸው ነገር ሁሉ ይሖዋ በትንቢት አስቀድሞ የተናገረው እንደሆነ ጎላ አድርጎ ገልጿል።
ቁጥር 13ን እናንብብ።
ዳንኤል ያጋጠማቸውን ሁኔታ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦
“በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው ይህ ሁሉ ጥፋት ደረሰብን።”
ዳንኤል በእስራኤላውያን ላይ ቅጣት እንደሚመጣባቸው የሚናገሩት እነዚሁ ትንቢቶች
ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ የሚገልጽ ተስፋም እንዳያዙ ያውቃል።
የዘሌዋውያን፣ የዘዳግም፣ የኢሳይያስና የኤርምያስ መጻሕፍትም
እስራኤላውያን ንስሐ ከገቡ ይሖዋ ወደ አገራቸው እንደሚመልሳቸው የሚገልጽ ተስፋ ይዘዋል።
ጸሎቱን ቁጥር 19 ላይ ምን ብሎ እንደደመደመ እንመልከት።
ዳንኤል እንዲህ ብሎ ጸልዩአል፦
“ይሖዋ ሆይ፣ ስማ። ይሖዋ ሆይ፣ ይቅር በል።
“ይሖዋ ሆይ፣ ትኩረት ስጥ፤ እርምጃም ውሰድ!
“አምላኬ ሆይ፣ ለራስህ ስትል አትዘግይ፤
ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቷልና።”
ዳንኤል ለስምህ ስትል ብሎ የለመነው ለምንድን ነው?
በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ የይሖዋ ስም 19 ጊዜ ተጠቅሷል።
ከዚህ ውስጥ 18 ጊዜ የተጠቀሰው እዚሁ ምዕራፍ ውስጥ ነው።
በጣም የሚያስገርመው ደግሞ 14ቱ የሚገኙት ዳንኤል ባቀረበው በዚህ ልመና ላይ ነው።
ግን ዳንኤል በጸሎቱ ላይ ልመናውን ከይሖዋ ስም ጋር ያያያዘው ለምንድን ነው?
ዳንኤል ይሖዋ እርምጃ ካልወሰደ በይሖዋ ስም ላይ ነቀፋ እንደሚመጣ ያውቃል።
ምክንያቱም ይሖዋ እስራኤላውያንን ነፃ እንደሚያወጣ ቃል ገብቷል።
ይህን ካላደረገ በስሙ ላይ ነቀፋ ይመጣል።
ዳንኤል የይሖዋን ማንነት፣ የስሙን ትርጉም ለመረዳት
ይሖዋ ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ አምላክ እንደሆነ አምኖ መቀበል እንደሚያስፈልግ ያውቃል።
ሕዝቡን ለማዳን ሲል የሚወስደው እርምጃ ትልቅ ነገር ያከናውናል።
ስሙ እንዲቀደስ ያደርጋል።
ታዲያ ከዚህ ጸሎት ይሖዋ ለእኛም ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳየን እንድንተማመን የሚያደርግ ምን ትምህርት እናገኛለን?
አንደኛ፣ ይሖዋ ሕዝቡን ፈጽሞ እንደማይተው ያስተምረናል።
እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ እንዳለው ለክፉ ድርጊታቸው የዘሩትን አጭደዋል።
ስለዚህ ንስሐ ገብተው ወደ ይሖዋ ከተመለሱ
ቃል የገባላቸውን መልካም ነገሮችም ማጨዳቸው አይቀርም።
ደግሞም የሆነው ልክ እንደዚህ ነው።
ይህን ማወቅ በጣም ያጽናናል።
ሁላችንም ስህተት መሥራታችን አይቀርም።
ግን ስህተታችንን ለማስተካከል እርምጃ ከወሰድን፣
ይሖዋ ከዳንኤልና ከእስራኤላውያን ጋር እንደነበረው ሁሉ ከእኛም ጋር ይሆናል።
አምላካችን ይሖዋ ፈጽሞ አይተወንም።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ፣
የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች ማጥናታችን በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል።
ዳንኤል ትንቢቶችን ማጥናቱ ይሖዋ እርምጃ እንደሚወስድ እርግጠኛ እንዲሆን አድርጎታል።
ለእኛም ቢሆን ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።
የነሐሴ 2023 <i>መጠበቂያ</i>፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ተማሩ በሚለው የጥናት ሥር እንዲህ ይላል፦
“በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ያገኙት እንዴት እንደሆነ ስንመለከት
“በይሖዋና በሚሰጠን አመራር ላይ የማይናወጥ እምነት እናዳብራለን።
“በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን
የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ እንዲኖረን ይረዱናል።”
ሦስተኛው ትምህርት ደግሞ ታማኝ ፍቅር ከይሖዋ ስምና ከማንነቱ ጋር የተያያዘ ነው።
አይነጣጠሉም።
እንደ ዳንኤል ሁሉ እኛም ይህን እናውቃለን።
ደግሞም ለእኛ ፍቅር ማሳየት የይሖዋ የማንነቱ ክፍል ነው።
ይሖዋ ለስሙ ሲል እርምጃ ይወሰዳል።
ይህ ደግሞ እኛን እንደሚንከባከበን የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ከሁሉ የላቀ ማረጋገጫ ይሆነናል።
አራተኛ፣ ይሖዋ መረጃዎችን የሚሰጠን በትክክለኛው ጊዜ ነው።
ዳንኤል እየተፈጸሙ የነበሩትን ነገሮች ከትንቢቶች ጋር ማያያዝ ችሏል።
ይሖዋ ለዳንኤል የሚያስፈልገውን መረጃ የሰጠው በሚያስፈልገው ወቅት ነው።
ይሖዋ ዛሬ ላሉት ሕዝቦችም ተመሳሳይ ነገር እያደረገ ነው።
በታላቁ መከራ ወቅት የሚፈጸሙትን ጨምሮ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ያለን ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።
ይህም ይሖዋ እየመራን እንደሆነ የሚያረጋገጥ ነው።
በዳንኤል ጸሎት ላይ ማሰላሰላችን በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል።
በተጨማሪም ከዚህ በፊት ያጋጠመን፣ አሁን እያጋጠመን ያለው ወይም ወደፊት የሚያጋጥመን ምንም ይሁን ምን፣
ይሖዋ ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳየን እርግጠኞች ነን።
ከእነዚህ ጥቂት ጥቅሶች ብዙ ትምህርት አግኝተናል።
ይሖዋ ቃል ስለገባቸው ተስፋዎች ማጥናት አዎንታዊ ሆነን የወደፊቱን ጊዜ እንድንጠብቅ ይረዳናል።
ወደፊት በትንሣኤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እንቀበላለን።
እናንተስ መልሳችሁ ለማግኘት፣ እቅፍ ለማድረግ የምትጓጉት ሰው አለ?
ይህን ሰው በአእምሯችሁ ይዛችሁ <i>የተኙት</i><i> </i><i>ሲነቁ</i><i> </i>የሚል ርዕስ ያለውን ቀጣዩን የሙዚቃ ቪዲዮ አጣጥሙ።
አይሽር እንዲህ በዋዛ፤
ሰው ያጣ ሰው፣ ቁስሉን አይረሳ።
መጽናናት እምቢ ሲል ልቤ፣
እሥለዋለሁ ነገን በምናቤ።
ድምፁን ይሰማሉ ሰዓቱ ደርሶ፤
ከ’ንቅልፍ ይቀሰቅሳቸዋል አስታውሶ።
እንደኔ ናፍቀው፣ ቀን የሚጠብቁ፣
ይታየኛል ሲፈነድቁ፣ የተኙት ሲነቁ።
ሐዘኑ ሲያገረሽ አድሮ፣
ድቅን ሲል ትዝታው ኖሮ ኖሮ፣
ሕመሜን ስነግረው ለሱ
ያረጋጋኛል በመንፈሱ።
ድምፁን ይሰማሉ ሰዓቱ ደርሶ፤
ከ’ንቅልፍ ይቀሰቅሳቸዋል አስታውሶ።
እንደኔ ናፍቀው፣ ቀን የሚጠብቁ፣
ይታየኛል ሲፈነድቁ፣ የተኙት ሲነቁ።
አንድ ቀን፣ በቅርቡ በማለዳ
የናፈቀኝ ያ ፈገግታ፣
በሬን አንኳኩቶ ሲመጣ፤
ሕልሜ ነው ብዬ፣ ዓይኔን ሳሸው፣ ሳመነታ፤
ስዘል፣ ስቦርቅ በደስታ፤
የምሆነውን እስካጣ።
ድምፁን ይሰማሉ ሰዓቱ ደርሶ፤
ከ’ንቅልፍ ይቀሰቅሳቸዋል አስታውሶ።
እንደኔ ናፍቀው፣ ቀን የሚጠብቁ፣
ይታየኛል ሲፈነድቁ፣
የተኙት ሲነቁ።
የተኙት ሲነቁ።
ሞት የነጠቀንን መልሰን ለማግኘት ምን ያህል እንደምንጓጓ ይሖዋ ያውቃል።
እሱም እነሱን ለማስነሳት ይጓጓል።
ቃሉ እንደሚያረጋግጥልን በእሱ ፊት ሁሉም ሕያዋን ናቸው።
ይሖዋ በሰጠን ተስፋዎች ላይ ጠንካራ እምነት እንዲኖረን
የአምላክን ቃል በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ማግኘታችን ይጠቅመናል።
ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክልና በተቻለ መጠን በብዙ ቋንቋዎች ለመተርጎም ምን አድርገናል?
የክርስቲያን ግሪከኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በ1950 ሲወጣ
የተዘጋጀበትን ዓላማ በተመለከተ
ወንድም ናታ ኖር እንዲህ ብሎ ነበር፦
“ዓላማው እነዚህ መጻሕፍት በተጻፉበት ዘመን የነበሩት የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በቀላሉ ይረዱት እንደነበረው
ዛሬም ያሉ አንባቢዎች በቀላሉ የሚረዱት ትርጉም ማዘጋጀት ነው።”
በቀጣዮቹ ዓመታት ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተተረጎሙ።
ከዚያም በ1961 ሙሉ <i>አዲስ</i><i> </i><i>ዓለም</i><i> </i><i>ትርጉም</i><i> </i>በእንግሊዝኛ ወጣ።
ይህም ትክክለኛ፣ በቀላሉ የሚገባና የይሖዋ ስም ያለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲኖረን አስችሏል።
በተመሳሳይ ወቅት ይህን መጽሐፍ ቅዱስ በሌሎች ስድስት ቋንቋዎች ለማዘጋጀት ሥራ ተጀመረ።
ከዚያም በ1963 ሥራው ተጠናቅቆ በስድስት ቋንቋዎች ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ወጣ።
ያም ቢሆን የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ሥራ አዝጋሚ ነበር።
እንዲያውም አንዳንድ ቋንቋዎች ይህን ትርጉም ለማጠናቀቅ ከ20 ዓመት በላይ ፈጅቶባቸዋል።
በዚህ የተነሳ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ በእንግሊዝኛ ከወጣ ከ30 ዓመታት በኋላ እንኳ
አዲስ ዓለም ትርጉም የሚገኘው በ12 ቋንቋዎች ብቻ ነበር።
ስለዚህ የበላይ አካሉ የትርጉም ሥራውን ለማቀላጠፍ
በ1989 በዋናው መሥሪያ ቤት ሥር የትርጉም አገልግሎት ክፍል የሚባል አንድ ዲፓርትመንት አቋቋመ።
የዚህ ዲፓርትመንት ዓላማ ያኔም ሆነ ዛሬ ተመሳሳይ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን የመተርጎሙን ሥራ ማገዝ፣
ተርጓሚዎችን ማሠልጠን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ተርጓሚዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች መመለስ።
ደግሞም ተርጓሚዎች ሐሳቡን በትክክል ለማስተላለፍ በርካታ ጥያቄዎች እንደሚያነሱ የሚጠበቅ ነው።
ታዲያ የትርጉም አገልግሎት ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ቡድኖችን የሚያደራጀው እንዴት ነው?
ሥራው የሚጀመረው መሠረታዊ የትርጉም መመሪያዎችን በተመለከተ ለቡድኑ ሥልጠና በመስጠት ነው።
ምሳሌያዊ አባባሎች፣ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫዎች፣
እንዲሁም ምሥል ከሳች ቃላት እንዴት መተርጎም እንዳለባቸው ይሰለጥናሉ።
ተርጓሚዎቹ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን በትክክል መተርጎም እንዲችሉ
ሐሳቡን በቅድሚያ በሥዕል ማስረዳት የግድ አስፈላጊ ነበር።
ከዚያም የትርጉም ቡድኑ በዋናው ጽሑፍ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በትክክል የሚያስተላልፍ ቃል ይመርጣል።
የትርጉም ቡድኑ ጥያቄ ከተፈጠረበት ማብራሪያ ለማግኘት የትርጉም አገልግሎት ክፍሉን መጠየቅ ይችላል።
ለጥያቄው የተሰጠው መልስ በአንድ ለየት ያለ የኮምፒውተር ሶፍትዌር አማካኝነት በሰነድ መልክ ይቀመጣል።
እስከ ዛሬ ድረስ 140 ሺህ ጥያቄዎች በዚህ መልኩ ተቀምጠዋል።
እነዚህ ጥያቄዎች የትርጉም ሥራን ፍጥነትና ጥራትን የሚያሻሽል ተጨማሪ ሥልጠና ለመስጠት ያገለግላሉ።
የበላይ አካል አባል የነበረው ወንድም አልበርት ሽሮደር
“አዲስ ዓለም ትርጉምን በስንት ቋንቋዎች ማዘጋጀት ታስባላችሁ?” ተብሎ ሲጠየቅ
<i>“</i><i>የመጠበቂያ</i><i> </i><i>ግንብ</i> መጽሔት በሚተረጎምበት በእያንዳንዱ ቋንቋ” ሲል መልሷል።
ሰዎች እውነትን እንዲማሩ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሚያስፈልግ ተገንዝቦ ነበር።
በ1990ዎቹ አጋማሽ በተለያዩ ቋንቋዎች ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የማግኘት ፍላጎት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እየጨመረ መጣ።
አዲስ ዓለም ትርጉም በቋንቋቸው ያልነበራቸው ወንድሞች የሚጠቀሙት ሌሎች ትርጉሞችን ነበር።
ከፍተኛ ዕድገት በነበራቸው አንዳንድ ጉባኤዎች ውስጥ የሚኖረው አንድ ወይም ሁለት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።
በወቅቱ የነበሩት ሌሎች ትርጉሞች ደግሞ ትክክል ያልሆኑ ወይም የሐሰት ትምህርትን የሚደግፉ ነበሩ።
እንዲያውም አንዳንድ ትርጉሞች የይሖዋን ስም በባዕድ አምላክ ስም ተክተዋል።
የትርጉም መሣሪያዎች፣ ቴክኖሎጂዎችና ሥልጠናዎች እየተሻሻሉ መጡ።
በመሆኑም የበላይ አካሉ በ2004 መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት እንዲተረጎም መመሪያ አስተላለፈ።
አንድ የትርጉም ቡድን መጠበቂያ ግንብ መተርጎም ከጀመረ በኋላ ቀጣይ ግቡ መጽሐፍ ቅዱስ መተርጎም ሆነ።
ይህም የወንድም ሽሮደር ምኞት እንዲሳካ ጥሩ መንደርደሪያ ሆነ።
የትርጉም ቡድኖቹ ከፊታቸው አስደናቂ ሥራ ይጠብቃቸው ነበር።
ሥራው ግን አንዴ ተርጉሞ በመጨረስ ብቻ የሚያበቃ አይደለም።
ቋንቋ በየጊዜው እየተለወጠ ስለሚሄድ ትርጉሙም መገምገም ያስፈልገዋል።
ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት በትክክል እንዲተላለፍ ያደርጋል።
በአሁን ወቅት ወደ 700 የሚጠጉ ወንድሞችና እህቶች የአምላክን ቃል በመተርጎሙ ሥራ ሙሉ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ።
መጽሐፍ ቅዱስን ከኢንተርኔት ለማውረድ ጥቂት ሰከንዶች ብቻ ሊበቁ ይችላሉ።
ሆኖም መላውን መጽሐፍ ቅዱስ ለመተርጎም ከአምስት እስከ ሰባት ዓመታት ይፈጃል።
በአሁኑ ወቅት የይሖዋ በረከት ተጨምሮበት
የእሱን ስም የሚያስከብር የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ከ325 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛል።
ደግሞም ይህ ትርጉም ትክክለኛና በቀላሉ የሚገባ ነው።
ጥቂት አስፋፊዎች ያሏቸው ቡድኖችም እንኳ በራሳቸው ቋንቋ አዲስ ዓለም ትርጉምን ማግኘት ይችላሉ።
ለመሆኑ ትሑት ሰዎች የአምላክን ቃል ልባቸውን በሚነካ ቋንቋ ሲያገኙ ምን ይሰማቸዋል?
ይደሰታሉ!
በደስታ ይፈነድቃሉ!
የአምላክን ቃል በምድር ላይ ለሚኖር ብሔር፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ መተርጎም
ምሥራቹ የሰዎችን ልብ እንዲነካ የሚያስችል አንድ እርምጃ ብቻ ነው።
ወሳኙን እርምጃ የምትወስደው አንተ ነህ።
መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ ልብህን እንዲነካው ፍቀድ።
በውስጡ የሚገኘውን ሕይወት አድን መልእክትም
ለብዙዎች ለማዳረስ የምትችለውን ሁሉ አድርግ።
እናንተም እንደነዛ ወንድሞች በደስታ ጨፍራችሁ ነበር?
አዲስ ዓለም ትርጉምን በራሳችን ቋንቋ ማግኘት እጅግ ያስደስታል።
ከዚህ ወር ፕሮግራም ምን ትምህርት አገኘን?
ከአምላክ ቃል የምናገኘው ጠቃሚ ምክር
ቀላል ዓይንና ብሩሕ ሰውነት እንዲኖረን ያስችለናል።
አንዳንድ መሥዋዕቶች ቢያስከፍለንም
አገልግሎታችንን ለማስፋት ስንል ኑሯችንን ቀላል ማድረጋችን እውነተኛ ደስታ ያስገኝልናል።
በአቅራቢያችሁ ቅርንጫፍ ቢሮ የሚገኝ ከሆነ
በተመላላሽነት ማገልገል ትችሉ እንደሆነ ለምን አታስቡበትም?
የዘካርያስ መጽሐፍ ይሖዋ ምን ያህል ኃይል እንዳለውና
ልክ እንደ ይሖዋ ሌሎችን ማበረታታት የምንችለው እንዴት እንደሆነ አስተምሮናል።
ደስ የሚል የሙዚቃ ቪዲዮም አይተናል።
እኔ በጣም ወድጄዋለሁ፣ እናንተስ?
ሞት የነጠቀንን የምንወዳቸውን ሰዎች መልሰን ስናገኝ ምን ያህል እንደምንደሰት አስቡት!
በዚህ ወር ሰላም ታይዘንላችሁ የመጣነው
በሉክሰምበርግ ከሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ነው።
ሉክሰምበርግ በማዕከላዊ አውሮፓ የምትገኝ ትንሽ አገር ናት።
ስያሜዋ የተገኘው “ትንሽ ምሽግ” የሚል ትርጉም ካላቸው ቃላት ነው።
ይህ መሆኑ አያስገርምም።
በአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ከ70 የሚበልጡ ጥንታዊ የድንጋይ ግንቦች ይገኛሉ።
እዚህ ላይ የምታዩት የቦርሻይድ ግንብ ከሲውር ወንዝ ከፍ ብሎ ይገኛል።
ዙሪያውን 11 የድንጋይ ማማዎች አሉት።
በአቅራቢያው ከ700 ዓመት በላይ ያስቆጠረው የቪያንደን ግንብ ይገኛል።
የተገነባው ሮማውያን ከ1700 ዓመታት በፊት በገነቡት ሕንፃ መሠረት ላይ ነው።
ለብዙ መቶ ዓመታት ጸንተው እንደቆሙት እንደነዚህ ግንቦች
በዚያ የሚገኙ ታማኝ ምሥክሮችም በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ጸንቶ ቆመዋል።
ለምሳሌ ከአካባቢው ቀሳውስት ከባድ ተጽዕኖና ተቃውሞ ቢያጋጥመውም
ዩጂን ሮይተር ቤቱን ለመንግሥቱ ሥራ ክፍት አድርጓል።
በ1933 በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች ማስቀመጫና ማሰራጫ ሆኖ ያገለገለው የእሱ ቤት ነበር።
በሩ ላይ <i>የመጠበቂያ</i><i> </i><i>ግንብ</i><i> </i>ማኅበርን ምልክት ማንጠልጠሉ
የነበረውን እምነትና ድፍረት ያሳያል።
በ1940 የጀርመን ሰራዊት አገሪቱን ሲቆጣጠር
ሮዛሊ ፎንክ በቤቷ ጽሑፎች ስለተገኙ ታሰረች።
ባለሥልጣናቱ የእምነት አጋሮቿንና የመሪዋን ማንነት እንድትናገር ሊያስገድዷት ሞከሩ።
እሷ ግን “መሪዬ ይሖዋ አምላክ ነው” በማለት መለሰችላቸው።
በዚያው ጊዜ ቪክተር ብሮ ለጦርነቱ ድጋፍ ስላልሰጠ ታሰረ።
ወደ ቡኸንቫልድ የማጎሪያ ካምፕም ተላከ።
ባለሥልጣናቱ ወንድሞችን ለሰዓታት እንዲቆሙ፣ ለሊቱን ሙሉ እንዲሠሩና
የማይመች የእንጨት ጫማ አድርገው እንዲጓዙ ያስገድዷቸው ነበር።
ወንድሞች ግን እርስ በርስ ይበረታቱ ነበር።
በኋላም ቪክተር ወደ ኦሽዋቲዝ የማጎሪያ ካምፕ ቢወሰድም እምነቱ አልተዳከመም።
በዚያም ምሥራቹን መስበኩን ቀጥሏል።
ዛሬም ቢሆን በአገሪቱ የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ተመሳሳይ ፍቅርና እምነት እያሳዩ ነው።
በአሥር የተለያዩ ቋንቋዎች ምሥራቹን የሚሰብኩ ከ2,000 በላይ አስፋፊዎች ይገኛሉ።
ወንድሞችና እህቶች እርስ በርስ ይበረታታሉ።
የባቄላ ሾርባ፣ በጭስ የተጠበሰ የአሳማ ሥጋና ቦሎቄ የመሳሰሉ ጣፋጭ ምግቦች ይመገባሉ።
በስብሰባዎችም ላይ አንድ ላይ በደስታ ይዘምራሉ።
በአለማንድ ጉባኤ ውስጥ የሚገኙ 84 አስፋፊዎች ይሖዋን በመዝሙር ሲያወድሱ እናዳምጥ።
በሉክሰምበርግ የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ሞቅ ያለ ፍቅራቸውንና ሰላምታቸውን ልከዋል።
የእኛም ሰላምታ ይድረሳችሁ።
ይህ ከይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት የሚተላለፍላችሁ
JW ብሮድካስቲንግ ነው!
-