የ2026 የመታሰቢያው በዓል ዕለት የማለዳ አምልኮ—ማርክ ሳንደርሰን፦ በፍቅር አንድ የሆኑት “ትንሽ መንጋ” እና “ሌሎች በጎች” (ሉቃስ 12:32)
Video
Other languages
Share text
Share link
Show times
Hide times
00:00:01
በዓመት ውስጥ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው በዚህ ቀን 00:00:04
00:00:04
ሁላችንም አንድ ላይ በመገናኘታችን ደስ ብሎናል።00:00:07
00:00:07
ዛሬ የጌታችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን00:00:11
00:00:11
የሞቱን መታሰቢያ እናከብራለን።00:00:13
00:00:14
የምንኖረው የትም ይሁን የት00:00:16
00:00:16
ወይም ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን 00:00:18
00:00:18
ይሖዋ የሰጠንን ይህን ታላቅ ስጦታ 00:00:21
00:00:21
አስታውሰው ከሚያከብሩት ሰዎች መካከል በመሆናችን በጣም ደስተኞች ነን። 00:00:25
00:00:25
በዚህ ምሽት የመታሰቢያውን በዓል ስናከብር የሚቀብልን ንግግር 00:00:30
00:00:30
ስለተሰጠን ስጦታ በሚገባ የሚያብራራ ነው።00:00:33
00:00:33
አሁን ግን እስቲ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ሐሳብ ላይ እንወያይ።00:00:37
00:00:37
ጥቅሱን ወንድም ክርስቶፈር ሜቨር ያነብልናል።00:00:40
00:00:42
የመታሰቢያው በዓል፦ ሐሙስ፣ ሚያዝያ 2 00:00:45
00:00:45
“አንተ ትንሽ መንጋ አትፍራ፤ 00:00:48
00:00:48
አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗልና።”00:00:51
00:00:51
ሉቃስ 12:32 00:00:54
00:00:56
በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ የሚገኙት ቃላት ጥቂት ብቻ ቢሆኑም 00:01:00
00:01:00
ቃላቶቹ ጥልቅ ትርጉም የያዙ ናቸው።00:01:03
00:01:04
ኢየሱስ ይህንን ሐሳብ የተናገረው ለትንሹ መንጋ ነው።00:01:07
00:01:07
ስለዚህ በውይይታችን ላይ 00:01:09
00:01:09
ስለ ታናሹ መንጋ አምስት ጥያቄዎችን ትኩረት ሰጥተን እንመረምራለን። 00:01:14
00:01:14
አንደኛ ትንሹ መንጋ ማን ነው?00:01:18
00:01:18
ኢየሱስ ራሱ ሉቃስ 12:32 ላይ የዚህን ጥያቄ መልስ ሰጥቶናል።00:01:25
00:01:25
እንዲህ ብሏል፦ 00:01:26
00:01:27
“አንተ ትንሽ መንጋ አትፍራ፤ 00:01:29
00:01:29
አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗልና።”00:01:34
00:01:35
በግልጽ ማየት እንደሚቻለው 00:01:37
00:01:37
ኢየሱስ እየተናገረ የነበረው አብረውት ስለሚገዙ ሰዎች ነው።00:01:41
00:01:41
በሰማይ ባለው መንግሥቱ!00:01:43
00:01:43
ግን ትንሽ መንጋ ያላቸው ለምንድን ነው?00:01:46
00:01:46
ራእይ ምዕራፍ አምስት ላይ 00:01:50
00:01:50
ከክርስቶስ ጋር ስለሚገዙ ሰዎች የተጻፈውን እናነባለን።00:01:54
00:01:54
ቁጥር 9 እና 10ን አብረን እናንብብ፦ 00:01:57
00:01:59
“እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፦ 00:02:02
00:02:02
“‘ጥቅልሉን ልትወስድና ማኅተሞቹን ልትከፍት ይገባሃል፤ ታርደሃልና፤ 00:02:08
00:02:09
“‘በደምህም ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ 00:02:12
00:02:12
“‘ከየሕዝቡና ከየብሔሩ ሰዎችን ለአምላክ ዋጅተሃል፤ 00:02:17
00:02:18
“‘እንዲሁም ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤ 00:02:23
00:02:23
በምድርም ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።’” 00:02:26
00:02:28
ቁጥር 9 ላይ በግልጽ እንደሚናገረው 00:02:30
00:02:30
ኢየሱስ ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ 00:02:36
00:02:36
ለይሖዋ ሰዎችን ዋጅቷል።00:02:39
00:02:39
ቁጥር 10 ላይ እንደሚናገረው ደግሞ እነዚህ ሰዎች ካህናት ይሆናሉ።00:02:44
00:02:44
በተጨማሪም በምድር ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።00:02:48
00:02:48
ግን አሁንም ቢሆን ጥያቄያችን አልተመለሰም።00:02:52
00:02:52
ኢየሱስ ትንሽ መንጋ ያላቸው ለምንድን ነው?00:02:56
00:02:56
ራእይ ምዕራፍ 14 ላይም ስለዚሁ ቡድን ማለትም 00:03:01
00:03:01
ከኢየሱስ ጋር እንዲገዙ ከምድር ስለተዋጁ ሰዎች ይናገራል።00:03:05
00:03:05
ግን ራእይ ምዕራፍ 14 ላይ በጣም ወሳኝ የሆነ አንድ መረጃ እናገኛለን።00:03:11
00:03:11
መጽሐፍ ቅዱሳችሁን አውጡና ራእይ ምዕራፍ 14 ቁጥር 1 እና 3ን እናንብብ፦ 00:03:17
00:03:19
“ከዚያም አየሁ፤ እነሆ፣ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሟል፤ 00:03:24
00:03:24
“ከእሱም ጋር የእሱ ስምና የአባቱ ስም 00:03:29
00:03:29
በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው 144,000 ነበሩ።”00:03:33
00:03:34
“እነሱም በዙፋኑ ፊት እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና 00:03:39
00:03:39
“በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ የሚመስል መዝሙር እየዘመሩ ነበር፤ 00:03:44
00:03:44
“ከምድር ከተዋጁት ከ144,000ዎቹ በስተቀር 00:03:48
00:03:48
ማንም ይህን መዝሙር ጠንቅቆ ሊያውቀው አልቻለም።”00:03:52
00:03:53
ወሳኙ መረጃ ምን እንደሆነ ልብ አላችሁ?00:03:56
00:03:56
ይህ ጥቅስ ከምድር የሚዋጁት ሰዎች ቁጥር 00:03:59
00:03:59
ምን ያህል እንደሆነ ነግሮናል። 00:04:01
00:04:01
144,000 ሰዎች ናቸው።00:04:04
00:04:04
ስለዚህ ኢየሱስ ትንሽ መንጋ ያላቸው ለምንድን ነው?00:04:08
00:04:09
አሁን ምክንያቱ ግልጽ ሆነልን አይደል?00:04:11
00:04:12
በእርግጥም ዛሬ በምድር ላይ ከሚኖሩት ሰዎች አንጻር ሲታይ 00:04:16
00:04:16
144,000 በጣም ትንሽ ቁጥር ነው።00:04:19
00:04:19
በምድር ላይ ምን ያህል ሰዎች አሉ?00:04:21
00:04:21
ከ8 ቢልየን በላይ ሰዎች!00:04:24
00:04:24
ግን ይሖዋ ከልጁ ከኢየሱስ ጋር በምድር ላይ እንዲገዙ 00:04:29
00:04:29
ውስን ቁጥር ያላቸው ሰዎች ማለትም 144,000 ሰዎች ብቻ መምረጡ 00:04:34
00:04:34
ምክንያታዊ ነው እንድንል የሚያደርገን ነገር ምንድን ነው? 00:04:36
00:04:38
እስቲ ይህን ለማሰብ ሞክሩ፦00:04:40
00:04:40
ዛሬ ወደ 190 የሚያህሉ አገሮች ፓርላማ አላቸው።00:04:45
00:04:45
በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ጠቅላላ ሰዎች የሚወክሉ 00:04:47
00:04:47
የተወሰኑ ሰዎች ተመርጠው ፓርላማ ይገባሉ።00:04:50
00:04:52
ግን በእነዚህ 190 ፓርላማዎች ውስጥ 00:04:55
00:04:55
ምን ያህል የሕዝብ ተወካዮች ያሉ ይመስሏችኋል?00:04:58
00:04:59
46,000 የሚያህሉ ተወካዮች!00:05:02
00:05:02
ይህ የሚገርም አይደለም?00:05:04
00:05:04
እነዚህ ጥቂት ቁጥር ያላቸው ሰዎች 00:05:06
00:05:06
በእነዚህ አገራት ውስጥ የሚገኙትን 00:05:09
00:05:09
በቢልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ይወክላሉ።00:05:11
00:05:11
ስለዚህ ይሖዋ ከልጁ ጋር እንዲገዙ 00:05:15
00:05:14
ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ የተውጣጡ 00:05:19
00:05:19
ጥቂት ሰዎች መምረጡ ምክንያታዊ ነው።00:05:22
00:05:22
ደግሞም ይሖዋ ከእነዚህ ሰዎች ጋር በተያያዘ 00:05:24
00:05:25
ትክክለኛ ምርጫ እንደሚያደርግ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።00:05:30
00:05:32
ግን ይህ ደግሞ ስለ ትንሹ መንጋ ሌላ ጥያቄ ያነሳል።00:05:36
00:05:37
የትንሹ መንጋ አባላት የሚመረጡት እንዴት ነው?00:05:41
00:05:41
ኃያላን መሆናቸው፣ ሀብታቸው ወይም ቤተሰባቸው ታይቶ ነው?00:05:46
00:05:46
መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ በጣም ግልጽ ነው።00:05:51
00:05:51
እስቲ እባካችሁ ሐዋርያው ጳውሎስ 1 ቆሮንቶስ 00:05:55
00:05:55
ምዕራፍ 1 ከቁጥር 26 እስከ 29 ላይ ያለውን እናንብብ፦ 00:06:00
00:06:01
“ወንድሞች፣ ከራሳችሁ ሁኔታ መረዳት እንደምትችሉት 00:06:05
00:06:05
“በሰብዓዊ አመለካከት ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፣ 00:06:08
00:06:08
“ኃያላን የሆኑ ብዙዎች እንዲሁም ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙዎች አልተጠሩም፤ 00:06:13
00:06:14
“ከዚህ ይልቅ አምላክ ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ 00:06:19
00:06:19
“ብርቱውንም ነገር ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ 00:06:22
00:06:23
“አምላክ በሰዎች ዘንድ ትልቅ ግምት የሚሰጠውን ነገር ከንቱ ያደርግ ዘንድ 00:06:28
00:06:28
“በዚህ ዓለም ዝቅ ተደርጎ የሚታየውንና የተናቀውን ነገር 00:06:33
00:06:33
“ይኸውም ከንቱ መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ፤ 00:06:36
00:06:36
“ይህን ያደረገው ማንም ሰው በአምላክ ፊት እንዳይኩራራ ነው።” 00:06:40
00:06:41
ታዲያ ከዚህ ምን እንማራለን?00:06:43
00:06:43
የትንሹ መንጋ አባላት የተመረጡት ኃያል መሆናቸው፣ 00:06:48
00:06:48
ሀብታቸው ወይም ቤተሰባቸው ታይቶ አይደለም።00:06:51
00:06:52
ከዚህ ይልቅ እንደ ትሕትና፣ እምነት እንዲሁም ለማገልገል ፍቃደኛ መሆንን የመሳሰሉ 00:06:59
00:06:59
ይሖዋ የሚደሰትባቸውን ባሕርያት ስላፈሩ ነው።00:07:02
00:07:02
እንዲያውም የትንሹ መንጋ አባላት 00:07:05
00:07:05
በዓለም እይታ ተራና የተናቁ መሆናቸው 00:07:08
00:07:08
የይሖዋ ጥበብና ኃይል ጎልቶ እንዲታይ ያደርጋል።00:07:12
00:07:13
ይሖዋ ታማኝና ትሑት ግን ተራ የሆኑ ሰዎችን ተጠቅሞ 00:07:18
00:07:18
ታላቁ ዓላማው እንዲፈጸም ማድረግ ይችላል።00:07:21
00:07:21
ይህ እውነታ “አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ 00:07:26
00:07:26
ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው እውነት መሆኑን ያረጋግጣል።00:07:31
00:07:31
በተጨማሪም ይሖዋ ምርጫውን ያደረገበት መንገድ 00:07:35
00:07:35
የትንሹ መንጋ አባላት በራሳቸው ለመኩራራት የሚያበቃ 00:07:38
00:07:38
ምንም ምክንያት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ነው።00:07:41
00:07:42
ቀጣዩ ጥያቄ 00:07:43
00:07:44
‘ትንሹ መንጋ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ሁሉ
የሚጠቅመው እንዴት ነው?’ የሚል ነው። 00:07:50
00:07:51
ራእይ ምዕራፍ ሃያ አንድ 144,000ዎቹን 00:07:55
00:07:55
ሰማያዊ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በማለት ይጠራቸዋል።00:08:00
00:08:01
እንዲያውም ቁጥር ዘጠኝ ላይ “የበጉ ሚስት” ተብለዋል።00:08:04
00:08:05
ከቁጥር ሁለት እስከ አራት እንዲህ ይላል፦ 00:08:07
00:08:08
“ደግሞም ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም 00:08:12
00:08:12
“ከሰማይ ከአምላክ ዘንድ ስትወርድ አየሁ፤ 00:08:15
00:08:15
“እሷም ለባሏ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ ነበር። 00:08:20
00:08:20
“በዚህ ጊዜ ከዙፋኑ አንድ ታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ 00:08:24
00:08:24
“‘እነሆ፣ የአምላክ ድንኳን ከሰዎች ጋር ነው፤ 00:08:28
00:08:28
“‘እሱም ከእነሱ ጋር ይኖራል፤ እነሱም ሕዝቡ ይሆናሉ።00:08:33
00:08:33
“‘አምላክ ራሱም ከእነሱ ጋር ይሆናል። 00:08:36
00:08:36
“‘እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ 00:08:40
00:08:41
“‘ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ 00:08:43
00:08:43
“‘ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። 00:08:47
00:08:47
ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።’” 00:08:50
00:08:51
እነዚህ እጅግ አስደናቂ በረከቶች ናቸው።00:08:53
00:08:53
ከዚህ በኋላ እንባ የለም።00:08:56
00:08:56
ሐዘን የለም።00:08:57
00:08:57
ሥቃይ የለም።00:08:59
00:08:58
ሌላው ቀርቶ ሞት እንኳ አይኖርም።00:09:02
00:09:02
የትንሹ መንጋ አባላት፣ 00:09:04
00:09:04
ቤዛዊ መሥዋዕቱ የሚያስገኛቸውን በረከቶች 00:09:06
00:09:06
ለሰው ልጆች ሁሉ ለማዳረስ00:09:09
00:09:09
ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በመሥራት 00:09:11
00:09:11
በቃላት የማይገለጽ ደስታ ያገኛሉ።00:09:13
00:09:13
ይህ ምን ማለት እንደሆነ እስቲ አስቡት፦ 00:09:16
00:09:16
በውርስ የመጣው ኃጢአት ሙሉ በሙሉ፣ አንዳች ሳይቀር ይሰረዛል።00:09:22
00:09:22
በምድር ላይ ለሚኖሩ የሰው ልጆች በሙሉ!00:09:25
00:09:25
እያንዳንዱ ሰው ፍጹም ይሆናል።00:09:28
00:09:28
ከአምላካችን ከይሖዋ ጋር ሙሉ በሙሉ ይታረቃል።00:09:32
00:09:33
አምስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄያችን፣00:09:36
00:09:37
‘በዛሬው ጊዜ በሁለቱ መካከል ማለትም 00:09:40
00:09:40
በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ባላቸውና 00:09:43
00:09:43
በትንሹ መንጋ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?’ የሚል ነው።00:09:47
00:09:47
ኢየሱስ ዮሐንስ 10:16 ላይ እንዲህ ብሏል፦ 00:09:52
00:09:52
“ከዚህ ጉረኖ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ 00:09:56
00:09:56
“እነሱንም ማምጣት አለብኝ፤ ድምፄንም ይሰማሉ፤ 00:10:00
00:10:00
“ሁሉም አንድ መንጋ ይሆናሉ፤ 00:10:03
00:10:03
አንድ እረኛም ይኖራቸዋል።”00:10:06
00:10:07
መልሱን አስተዋላችሁ?00:10:09
00:10:09
ይሖዋ አምላክ በሰማይ ላይ የመኖር ተስፋ ያላቸውንና 00:10:14
00:10:14
በምድር ላይ የመኖር ተስፋ ያላቸውን አንድ መንጋ አድርጓቸዋል።00:10:18
00:10:18
በእረኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥር!00:10:22
00:10:22
ስለዚህ ዛሬ ምሽት የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ የምናከብረው 00:10:27
00:10:27
በሁለት የተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ሆነን አይደለም።00:10:31
00:10:31
እርግጥ ነው፣ ከቂጣውና ከወይኑ የሚካፈሉት 00:10:35
00:10:35
የትንሹ መንጋ አባላት ብቻ ናቸው።00:10:37
00:10:38
ግን ሁላችንም ይሖዋ በመካከላችን እንዲሰፍን ያደረገውን 00:10:43
00:10:43
አስደናቂ አንድነት እንመለከታለን። 00:10:45
00:10:45
በዛሬው ምሽት የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በምናከብርበት ወቅት 00:10:50
00:10:50
ከተለያየ ዘር፣ ከተለያየ ብሔርና 00:10:54
00:10:54
ከተለያየ ቋንቋ የተውጣጡ በርካታ ሰዎች 00:10:57
00:10:57
ይሖዋ አምላክና ልጁ ኢየሱስ ላደረጉላቸው ነገር 00:11:01
00:11:01
ያላቸውን አድናቆት ለማሳየት በአንድነት ይሰበሰባሉ። 00:11:05
00:11:07
ወንድም ሜቨር እባክህ የቡክሌቱን ሐሳብ አንብብልን።00:11:10
00:11:12
“በጌታ ራት ወቅት ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ቂጣ ከሰጣቸው በኋላ 00:11:16
00:11:16
“ሥጋውን እንደሚያመለክት ነገራቸው።00:11:19
00:11:19
“ከዚያም የወይን ጠጁን ሰጣቸውና 00:11:22
00:11:22
“‘የቃል ኪዳን ደሙን’ እንደሚያመለክት ተናገረ።00:11:25
00:11:25
“አዲሱ ቃል ኪዳን የተገባው 00:11:27
00:11:27
“በአምላክ መንግሥት ውስጥ ቦታ ከሚኖራቸው 00:11:30
00:11:30
“‘[ከመንፈሳዊ] እስራኤል ቤት ጋር’ ነው።00:11:32
00:11:32
“ኢየሱስ በጌታ ራት ላይ ትኩረት ያደረገው ‘በትንሹ መንጋ’ ላይ ነበር።00:11:37
00:11:37
“የዚህ አነስተኛ ቡድን የመጀመሪያ አባላት 00:11:39
00:11:39
“እዚያ ክፍል ውስጥ ከኢየሱስ ጋር አብረው የነበሩት ታማኝ ሐዋርያቱ ናቸው።00:11:43
00:11:43
ከኢየሱስ ጋር አብረው እንዲሆኑ በሰማይ ቦታ የሚያገኙት እነሱ ናቸው።”00:11:48
00:11:50
እናመሰግናለን።00:11:51
00:11:51
አሁን የዛሬውን የመታሰቢያ በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እንከታተል።00:11:56
00:11:56
የሚነበቡልን ከአራቱም ወንጌሎች ላይ የተወሰዱ ዘገባዎች ናቸው።00:12:01
00:12:06
“የቂጣ በዓል በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣ 00:12:09
00:12:09
“ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው 00:12:12
00:12:12
“‘ፋሲካን እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?’ አሉት። 00:12:16
00:12:16
“እሱም ‘ወደ ከተማ ሄዳችሁ እገሌ የተባለውን ሰው፣ 00:12:21
00:12:21
“‘“መምህሩ ‘የተወሰነው ጊዜዬ ደርሷል፤ 00:12:24
00:12:25
“‘“ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በቤትህ አከብራለሁ’00:12:27
00:12:27
“‘“ብሏል በሉት”’ አላቸው።00:12:30
00:12:30
ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።”00:12:36
00:12:43
“የቂጣ በዓል በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣ 00:12:46
00:12:47
“እንደተለመደው የፋሲካን መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ዕለት 00:12:51
00:12:51
“ደቀ መዛሙርቱ ‘ፋሲካን እንድትበላ የት ሄደን እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?’ አሉት።00:12:58
00:12:58
“እሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦ 00:13:03
00:13:03
“‘ወደ ከተማው ሂዱ፤ በዚያም የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ።00:13:08
00:13:08
“‘እሱንም ተከተሉት፤ ወደሚገባበት ቤት ሄዳችሁ የቤቱን ጌታ 00:13:13
00:13:13
“‘“መምህሩ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት
የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሏል በሉት።’00:13:19
00:13:19
እሱም የተነጠፈና የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል። እዚያ አዘጋጁልን።”00:13:26
00:13:28
“ደቀ መዛሙርቱም ሄዱ፤ ወደ ከተማውም ገቡ፤ 00:13:32
00:13:32
እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።”00:13:37
00:13:43
“የቂጣ በዓል የሚከበርበት ቀን ደረሰ፤ 00:13:46
00:13:46
“በዚህ ዕለት የፋሲካ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤ 00:13:49
00:13:49
“ስለዚህ ኢየሱስ ‘ሄዳችሁ ፋሲካን እንድንበላ አዘጋጁልን’ 00:13:54
00:13:54
“ብሎ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው።00:13:57
00:13:57
“እነሱም ‘የት እንድናዘጋጅ ትፈልጋለህ?’ አሉት።00:14:03
00:14:03
“እሱም እንዲህ አላቸው፦ 00:14:06
00:14:06
“‘ወደ ከተማው ስትገቡ የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ።00:14:10
00:14:10
“‘እሱን ተከትላችሁ ወደሚገባበት ቤት ሂዱ።00:14:14
00:14:14
“‘የቤቱንም ባለቤት “መምህሩ 00:14:17
00:14:17
“‘“ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?
ብሎሃል” በሉት።00:14:22
00:14:23
“‘ሰውየውም የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁ።’” 00:14:29
00:14:30
እነሱም ሄዱ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።”00:14:36
00:14:45
“የፋሲካ በዓል ተቃርቦ በነበረበት ወቅት ኢየሱስ 00:14:49
00:14:49
“ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደደረሰ ስላወቀ 00:14:53
00:14:53
“በዓለም የነበሩትንና የወደዳቸውን ተከታዮቹን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።00:14:59
00:14:59
“በዚህ ጊዜ ራት እየበሉ ነበር።00:15:03
00:15:02
“ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ውስጥ 00:15:07
00:15:07
“ኢየሱስን አሳልፎ የመስጠት ሐሳብ አሳድሮ ነበር።00:15:11
00:15:13
“ኢየሱስ፣ አብ ሁሉን ነገር በእጁ እንደሰጠው እንዲሁም 00:15:17
00:15:17
“ከአምላክ እንደመጣና ወደ አምላክ እንደሚሄድ ያውቅ ስለነበር00:15:21
00:15:21
“ከራት ተነስቶ መደረቢያውን አስቀመጠ።00:15:24
00:15:25
“ፎጣ ወስዶም ወገቡ ላይ አሸረጠ።00:15:27
00:15:29
“ከዚያም በመታጠቢያ ዕቃ ውስጥ ውኃ ጨምሮ 00:15:32
00:15:33
የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና ባሸረጠው ፎጣ ማድረቅ ጀመረ።”00:15:38
00:15:51
“ልባችሁ አይረበሽ።00:15:54
00:15:54
“በአምላክ እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ። 00:15:58
00:15:59
“በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ ቦታ አለ።00:16:02
00:16:03
“ይህ ባይሆን ኖሮ በግልጽ እነግራችሁ ነበር፤ 00:16:06
00:16:06
“ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት እሄዳለሁና።00:16:09
00:16:10
“ደግሞም ሄጄ ቦታ ባዘጋጀሁላችሁ ጊዜ 00:16:14
00:16:14
“እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ 00:16:16
00:16:16
እንደገና መጥቼ እኔ ወዳለሁበት እወስዳችኋለሁ።”00:16:20
00:16:35
በዓለም ዙሪያ ይህን ፕሮግራም በከታተል ላይ ያላችሁ በሙሉ 00:16:39
00:16:39
እባካችሁ ዛሬ ምሽት በአቅራቢያችሁ በሚከበረው 00:16:43
00:16:43
የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ ለመገኘት የቻላሁትን ሁሉ አድርጉ።00:16:48
00:16:49
በአሁኑ ወቅት የቀዘቀዛችሁ ብትሆኑም ወይም ደግሞ 00:16:53
00:16:53
ከክርስቲያን ጉባኤ የተወገዳችሁ ብትሆኑም እንኳ 00:16:57
00:16:57
በበዓሉ ላይ ለመገኘት ጥረት በማድረግ 00:16:59
00:17:00
ይሖዋ አምላክና ኢየሱስ ክርስቶስ ላደረጉላችሁ ነገር 00:17:04
00:17:04
ያላችሁን አድናቆት አሳዩ።00:17:06
00:17:07
ይህን ፕሮግራም የምትከታተሉ በሙሉ 00:17:09
00:17:09
የይሖዋ በረከት እንዳይለያችሁ እንመኛለን!00:17:12
00:17:12
እንዲሁም ሁላችሁንም 00:17:14
00:17:14
በጣም እንወዳችኋለን። 00:17:17
የ2026 የመታሰቢያው በዓል ዕለት የማለዳ አምልኮ—ማርክ ሳንደርሰን፦ በፍቅር አንድ የሆኑት “ትንሽ መንጋ” እና “ሌሎች በጎች” (ሉቃስ 12:32)
-
የ2026 የመታሰቢያው በዓል ዕለት የማለዳ አምልኮ—ማርክ ሳንደርሰን፦ በፍቅር አንድ የሆኑት “ትንሽ መንጋ” እና “ሌሎች በጎች” (ሉቃስ 12:32)
በዓመት ውስጥ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው በዚህ ቀን
ሁላችንም አንድ ላይ በመገናኘታችን ደስ ብሎናል።
ዛሬ የጌታችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን
የሞቱን መታሰቢያ እናከብራለን።
የምንኖረው የትም ይሁን የት
ወይም ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን
ይሖዋ የሰጠንን ይህን ታላቅ ስጦታ
አስታውሰው ከሚያከብሩት ሰዎች መካከል በመሆናችን በጣም ደስተኞች ነን።
በዚህ ምሽት የመታሰቢያውን በዓል ስናከብር የሚቀብልን ንግግር
ስለተሰጠን ስጦታ በሚገባ የሚያብራራ ነው።
አሁን ግን እስቲ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ሐሳብ ላይ እንወያይ።
ጥቅሱን ወንድም ክርስቶፈር ሜቨር ያነብልናል።
የመታሰቢያው በዓል፦ ሐሙስ፣ ሚያዝያ 2
“አንተ ትንሽ መንጋ አትፍራ፤
አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗልና።”
ሉቃስ 12:32
በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ የሚገኙት ቃላት ጥቂት ብቻ ቢሆኑም
ቃላቶቹ ጥልቅ ትርጉም የያዙ ናቸው።
ኢየሱስ ይህንን ሐሳብ የተናገረው ለትንሹ መንጋ ነው።
ስለዚህ በውይይታችን ላይ
ስለ ታናሹ መንጋ አምስት ጥያቄዎችን ትኩረት ሰጥተን እንመረምራለን።
አንደኛ ትንሹ መንጋ ማን ነው?
ኢየሱስ ራሱ ሉቃስ 12:32 ላይ የዚህን ጥያቄ መልስ ሰጥቶናል።
እንዲህ ብሏል፦
“አንተ ትንሽ መንጋ አትፍራ፤
አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗልና።”
በግልጽ ማየት እንደሚቻለው
ኢየሱስ እየተናገረ የነበረው አብረውት ስለሚገዙ ሰዎች ነው።
በሰማይ ባለው መንግሥቱ!
ግን ትንሽ መንጋ ያላቸው ለምንድን ነው?
ራእይ ምዕራፍ አምስት ላይ
ከክርስቶስ ጋር ስለሚገዙ ሰዎች የተጻፈውን እናነባለን።
ቁጥር 9 እና 10ን አብረን እናንብብ፦
“እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፦
“‘ጥቅልሉን ልትወስድና ማኅተሞቹን ልትከፍት ይገባሃል፤ ታርደሃልና፤
“‘በደምህም ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣
“‘ከየሕዝቡና ከየብሔሩ ሰዎችን ለአምላክ ዋጅተሃል፤
“‘እንዲሁም ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤
በምድርም ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።’”
ቁጥር 9 ላይ በግልጽ እንደሚናገረው
ኢየሱስ ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ
ለይሖዋ ሰዎችን ዋጅቷል።
ቁጥር 10 ላይ እንደሚናገረው ደግሞ እነዚህ ሰዎች ካህናት ይሆናሉ።
በተጨማሪም በምድር ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።
ግን አሁንም ቢሆን ጥያቄያችን አልተመለሰም።
ኢየሱስ ትንሽ መንጋ ያላቸው ለምንድን ነው?
ራእይ ምዕራፍ 14 ላይም ስለዚሁ ቡድን ማለትም
ከኢየሱስ ጋር እንዲገዙ ከምድር ስለተዋጁ ሰዎች ይናገራል።
ግን ራእይ ምዕራፍ 14 ላይ በጣም ወሳኝ የሆነ አንድ መረጃ እናገኛለን።
መጽሐፍ ቅዱሳችሁን አውጡና ራእይ ምዕራፍ 14 ቁጥር 1 እና 3ን እናንብብ፦
“ከዚያም አየሁ፤ እነሆ፣ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሟል፤
“ከእሱም ጋር የእሱ ስምና የአባቱ ስም
በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው 144,000 ነበሩ።”
“እነሱም በዙፋኑ ፊት እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና
“በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ የሚመስል መዝሙር እየዘመሩ ነበር፤
“ከምድር ከተዋጁት ከ144,000ዎቹ በስተቀር
ማንም ይህን መዝሙር ጠንቅቆ ሊያውቀው አልቻለም።”
ወሳኙ መረጃ ምን እንደሆነ ልብ አላችሁ?
ይህ ጥቅስ ከምድር የሚዋጁት ሰዎች ቁጥር
ምን ያህል እንደሆነ ነግሮናል።
144,000 ሰዎች ናቸው።
ስለዚህ ኢየሱስ ትንሽ መንጋ ያላቸው ለምንድን ነው?
አሁን ምክንያቱ ግልጽ ሆነልን አይደል?
በእርግጥም ዛሬ በምድር ላይ ከሚኖሩት ሰዎች አንጻር ሲታይ
144,000 በጣም ትንሽ ቁጥር ነው።
በምድር ላይ ምን ያህል ሰዎች አሉ?
ከ8 ቢልየን በላይ ሰዎች!
ግን ይሖዋ ከልጁ ከኢየሱስ ጋር በምድር ላይ እንዲገዙ
ውስን ቁጥር ያላቸው ሰዎች ማለትም 144,000 ሰዎች ብቻ መምረጡ
ምክንያታዊ ነው እንድንል የሚያደርገን ነገር ምንድን ነው?
እስቲ ይህን ለማሰብ ሞክሩ፦
ዛሬ ወደ 190 የሚያህሉ አገሮች ፓርላማ አላቸው።
በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ጠቅላላ ሰዎች የሚወክሉ
የተወሰኑ ሰዎች ተመርጠው ፓርላማ ይገባሉ።
ግን በእነዚህ 190 ፓርላማዎች ውስጥ
ምን ያህል የሕዝብ ተወካዮች ያሉ ይመስሏችኋል?
46,000 የሚያህሉ ተወካዮች!
ይህ የሚገርም አይደለም?
እነዚህ ጥቂት ቁጥር ያላቸው ሰዎች
በእነዚህ አገራት ውስጥ የሚገኙትን
በቢልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ይወክላሉ።
ስለዚህ ይሖዋ ከልጁ ጋር እንዲገዙ
ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ የተውጣጡ
ጥቂት ሰዎች መምረጡ ምክንያታዊ ነው።
ደግሞም ይሖዋ ከእነዚህ ሰዎች ጋር በተያያዘ
ትክክለኛ ምርጫ እንደሚያደርግ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።
ግን ይህ ደግሞ ስለ ትንሹ መንጋ ሌላ ጥያቄ ያነሳል።
የትንሹ መንጋ አባላት የሚመረጡት እንዴት ነው?
ኃያላን መሆናቸው፣ ሀብታቸው ወይም ቤተሰባቸው ታይቶ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ በጣም ግልጽ ነው።
እስቲ እባካችሁ ሐዋርያው ጳውሎስ 1 ቆሮንቶስ
ምዕራፍ 1 ከቁጥር 26 እስከ 29 ላይ ያለውን እናንብብ፦
“ወንድሞች፣ ከራሳችሁ ሁኔታ መረዳት እንደምትችሉት
“በሰብዓዊ አመለካከት ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፣
“ኃያላን የሆኑ ብዙዎች እንዲሁም ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙዎች አልተጠሩም፤
“ከዚህ ይልቅ አምላክ ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤
“ብርቱውንም ነገር ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤
“አምላክ በሰዎች ዘንድ ትልቅ ግምት የሚሰጠውን ነገር ከንቱ ያደርግ ዘንድ
“በዚህ ዓለም ዝቅ ተደርጎ የሚታየውንና የተናቀውን ነገር
“ይኸውም ከንቱ መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ፤
“ይህን ያደረገው ማንም ሰው በአምላክ ፊት እንዳይኩራራ ነው።”
ታዲያ ከዚህ ምን እንማራለን?
የትንሹ መንጋ አባላት የተመረጡት ኃያል መሆናቸው፣
ሀብታቸው ወይም ቤተሰባቸው ታይቶ አይደለም።
ከዚህ ይልቅ እንደ ትሕትና፣ እምነት እንዲሁም ለማገልገል ፍቃደኛ መሆንን የመሳሰሉ
ይሖዋ የሚደሰትባቸውን ባሕርያት ስላፈሩ ነው።
እንዲያውም የትንሹ መንጋ አባላት
በዓለም እይታ ተራና የተናቁ መሆናቸው
የይሖዋ ጥበብና ኃይል ጎልቶ እንዲታይ ያደርጋል።
ይሖዋ ታማኝና ትሑት ግን ተራ የሆኑ ሰዎችን ተጠቅሞ
ታላቁ ዓላማው እንዲፈጸም ማድረግ ይችላል።
ይህ እውነታ “አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤
ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው እውነት መሆኑን ያረጋግጣል።
በተጨማሪም ይሖዋ ምርጫውን ያደረገበት መንገድ
የትንሹ መንጋ አባላት በራሳቸው ለመኩራራት የሚያበቃ
ምንም ምክንያት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ነው።
ቀጣዩ ጥያቄ
‘ትንሹ መንጋ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ሁሉ
የሚጠቅመው እንዴት ነው?’ የሚል ነው።
ራእይ ምዕራፍ ሃያ አንድ 144,000ዎቹን
ሰማያዊ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በማለት ይጠራቸዋል።
እንዲያውም ቁጥር ዘጠኝ ላይ “የበጉ ሚስት” ተብለዋል።
ከቁጥር ሁለት እስከ አራት እንዲህ ይላል፦
“ደግሞም ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም
“ከሰማይ ከአምላክ ዘንድ ስትወርድ አየሁ፤
“እሷም ለባሏ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ ነበር።
“በዚህ ጊዜ ከዙፋኑ አንድ ታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦
“‘እነሆ፣ የአምላክ ድንኳን ከሰዎች ጋር ነው፤
“‘እሱም ከእነሱ ጋር ይኖራል፤ እነሱም ሕዝቡ ይሆናሉ።
“‘አምላክ ራሱም ከእነሱ ጋር ይሆናል።
“‘እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤
“‘ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤
“‘ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።
ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።’”
እነዚህ እጅግ አስደናቂ በረከቶች ናቸው።
ከዚህ በኋላ እንባ የለም።
ሐዘን የለም።
ሥቃይ የለም።
ሌላው ቀርቶ ሞት እንኳ አይኖርም።
የትንሹ መንጋ አባላት፣
ቤዛዊ መሥዋዕቱ የሚያስገኛቸውን በረከቶች
ለሰው ልጆች ሁሉ ለማዳረስ
ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በመሥራት
በቃላት የማይገለጽ ደስታ ያገኛሉ።
ይህ ምን ማለት እንደሆነ እስቲ አስቡት፦
በውርስ የመጣው ኃጢአት ሙሉ በሙሉ፣ አንዳች ሳይቀር ይሰረዛል።
በምድር ላይ ለሚኖሩ የሰው ልጆች በሙሉ!
እያንዳንዱ ሰው ፍጹም ይሆናል።
ከአምላካችን ከይሖዋ ጋር ሙሉ በሙሉ ይታረቃል።
አምስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄያችን፣
‘በዛሬው ጊዜ በሁለቱ መካከል ማለትም
በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ባላቸውና
በትንሹ መንጋ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?’ የሚል ነው።
ኢየሱስ ዮሐንስ 10:16 ላይ እንዲህ ብሏል፦
“ከዚህ ጉረኖ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤
“እነሱንም ማምጣት አለብኝ፤ ድምፄንም ይሰማሉ፤
“ሁሉም አንድ መንጋ ይሆናሉ፤
አንድ እረኛም ይኖራቸዋል።”
መልሱን አስተዋላችሁ?
ይሖዋ አምላክ በሰማይ ላይ የመኖር ተስፋ ያላቸውንና
በምድር ላይ የመኖር ተስፋ ያላቸውን አንድ መንጋ አድርጓቸዋል።
በእረኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥር!
ስለዚህ ዛሬ ምሽት የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ የምናከብረው
በሁለት የተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ሆነን አይደለም።
እርግጥ ነው፣ ከቂጣውና ከወይኑ የሚካፈሉት
የትንሹ መንጋ አባላት ብቻ ናቸው።
ግን ሁላችንም ይሖዋ በመካከላችን እንዲሰፍን ያደረገውን
አስደናቂ አንድነት እንመለከታለን።
በዛሬው ምሽት የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በምናከብርበት ወቅት
ከተለያየ ዘር፣ ከተለያየ ብሔርና
ከተለያየ ቋንቋ የተውጣጡ በርካታ ሰዎች
ይሖዋ አምላክና ልጁ ኢየሱስ ላደረጉላቸው ነገር
ያላቸውን አድናቆት ለማሳየት በአንድነት ይሰበሰባሉ።
ወንድም ሜቨር እባክህ የቡክሌቱን ሐሳብ አንብብልን።
“በጌታ ራት ወቅት ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ቂጣ ከሰጣቸው በኋላ
“ሥጋውን እንደሚያመለክት ነገራቸው።
“ከዚያም የወይን ጠጁን ሰጣቸውና
“‘የቃል ኪዳን ደሙን’ እንደሚያመለክት ተናገረ።
“አዲሱ ቃል ኪዳን የተገባው
“በአምላክ መንግሥት ውስጥ ቦታ ከሚኖራቸው
“‘[ከመንፈሳዊ] እስራኤል ቤት ጋር’ ነው።
“ኢየሱስ በጌታ ራት ላይ ትኩረት ያደረገው ‘በትንሹ መንጋ’ ላይ ነበር።
“የዚህ አነስተኛ ቡድን የመጀመሪያ አባላት
“እዚያ ክፍል ውስጥ ከኢየሱስ ጋር አብረው የነበሩት ታማኝ ሐዋርያቱ ናቸው።
ከኢየሱስ ጋር አብረው እንዲሆኑ በሰማይ ቦታ የሚያገኙት እነሱ ናቸው።”
እናመሰግናለን።
አሁን የዛሬውን የመታሰቢያ በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እንከታተል።
የሚነበቡልን ከአራቱም ወንጌሎች ላይ የተወሰዱ ዘገባዎች ናቸው።
“የቂጣ በዓል በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣
“ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው
“‘ፋሲካን እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?’ አሉት።
“እሱም ‘ወደ ከተማ ሄዳችሁ እገሌ የተባለውን ሰው፣
“‘“መምህሩ ‘የተወሰነው ጊዜዬ ደርሷል፤
“‘“ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በቤትህ አከብራለሁ’
“‘“ብሏል በሉት”’ አላቸው።
ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።”
“የቂጣ በዓል በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣
“እንደተለመደው የፋሲካን መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ዕለት
“ደቀ መዛሙርቱ ‘ፋሲካን እንድትበላ የት ሄደን እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?’ አሉት።
“እሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦
“‘ወደ ከተማው ሂዱ፤ በዚያም የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ።
“‘እሱንም ተከተሉት፤ ወደሚገባበት ቤት ሄዳችሁ የቤቱን ጌታ
“‘“መምህሩ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት
የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሏል በሉት።’
እሱም የተነጠፈና የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል። እዚያ አዘጋጁልን።”
“ደቀ መዛሙርቱም ሄዱ፤ ወደ ከተማውም ገቡ፤
እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።”
“የቂጣ በዓል የሚከበርበት ቀን ደረሰ፤
“በዚህ ዕለት የፋሲካ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤
“ስለዚህ ኢየሱስ ‘ሄዳችሁ ፋሲካን እንድንበላ አዘጋጁልን’
“ብሎ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው።
“እነሱም ‘የት እንድናዘጋጅ ትፈልጋለህ?’ አሉት።
“እሱም እንዲህ አላቸው፦
“‘ወደ ከተማው ስትገቡ የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ።
“‘እሱን ተከትላችሁ ወደሚገባበት ቤት ሂዱ።
“‘የቤቱንም ባለቤት “መምህሩ
“‘“ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?
ብሎሃል” በሉት።
“‘ሰውየውም የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁ።’”
እነሱም ሄዱ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።”
“የፋሲካ በዓል ተቃርቦ በነበረበት ወቅት ኢየሱስ
“ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደደረሰ ስላወቀ
“በዓለም የነበሩትንና የወደዳቸውን ተከታዮቹን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።
“በዚህ ጊዜ ራት እየበሉ ነበር።
“ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ውስጥ
“ኢየሱስን አሳልፎ የመስጠት ሐሳብ አሳድሮ ነበር።
“ኢየሱስ፣ አብ ሁሉን ነገር በእጁ እንደሰጠው እንዲሁም
“ከአምላክ እንደመጣና ወደ አምላክ እንደሚሄድ ያውቅ ስለነበር
“ከራት ተነስቶ መደረቢያውን አስቀመጠ።
“ፎጣ ወስዶም ወገቡ ላይ አሸረጠ።
“ከዚያም በመታጠቢያ ዕቃ ውስጥ ውኃ ጨምሮ
የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና ባሸረጠው ፎጣ ማድረቅ ጀመረ።”
“ልባችሁ አይረበሽ።
“በአምላክ እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።
“በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ ቦታ አለ።
“ይህ ባይሆን ኖሮ በግልጽ እነግራችሁ ነበር፤
“ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት እሄዳለሁና።
<b>“</b>ደግሞም ሄጄ ቦታ ባዘጋጀሁላችሁ ጊዜ
“እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ
እንደገና መጥቼ እኔ ወዳለሁበት እወስዳችኋለሁ።”
በዓለም ዙሪያ ይህን ፕሮግራም በከታተል ላይ ያላችሁ በሙሉ
እባካችሁ ዛሬ ምሽት በአቅራቢያችሁ በሚከበረው
የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ ለመገኘት የቻላሁትን ሁሉ አድርጉ።
በአሁኑ ወቅት የቀዘቀዛችሁ ብትሆኑም ወይም ደግሞ
ከክርስቲያን ጉባኤ የተወገዳችሁ ብትሆኑም እንኳ
በበዓሉ ላይ ለመገኘት ጥረት በማድረግ
ይሖዋ አምላክና ኢየሱስ ክርስቶስ ላደረጉላችሁ ነገር
ያላችሁን አድናቆት አሳዩ።
ይህን ፕሮግራም የምትከታተሉ በሙሉ
የይሖዋ በረከት እንዳይለያችሁ እንመኛለን!
እንዲሁም ሁላችሁንም
በጣም እንወዳችኋለን።
-