JW subtitle extractor

“የምርምር መርጃ” አጠቃቀም

Video Other languages Share text Share link Show times

እስቲ የምርምር መርጃውን ዋና ዋና ገጽታዎች እንመልከት።
መጀመሪያ ምርምር ልታደርጉበት የምትፈልጉትን ርዕስ ምረጡ ።
JW Library ላይ ቤተ መጻሕፍት የሚለውን ተጫኑ።
ከዚያ የፍለጋ ምልክቱን ተጫኑ።
ለምሳሌ በሳጥኑ ውስጥ ዳዊት ብላችሁ ጻፉ።
ከምርምር መርጃው ላይ የመጡላችሁን ርዕሶች ተመልከቱ።
ከእነዚያ መሃል ዳዊት የሚለውን ተጫኑ።
የምርምር መርጃውን መጠቀም የምትችሉበት ሌላም መንገድ አለ።
ቤተ መጻሕፍት የሚለው ጋ ሂዱ።
በዚያ ሥር ማውጫ የሚለውን ምረጡ።
ከዚያም የምርምር መርጃውን ክፈቱ።
ርዕሶቹ የተቀመጡት በፊደል ቅደም ተከተል ነው።
የፈለጋችሁትን ርዕስ ለማግኘት የቃሉን የመጀመሪያ ፊደል ምረጡ።
የምትፈልጉትን ቃል ካጣችሁት ተቀራራቢ ትርጉም ያለው ሌላ ቃል ተጠቅማችሁ ፈልጉ።
ዳዊት የሚለውን ቃል ተጫኑ።
በእሱ ሥር "አጠቃላይ መረጃ"፣ "የምናገኘው ትምህርት" እንደሚሉ ያሉ ንዑስ ርዕሶች አሉ።
ለምሳሌ "የምናገኘው ትምህርት" የሚለውን ንዑስ ርዕስ ተጫኑ።
በእሱ ሥር የጽሑፎችና የቪዲዮዎች ዝርዝር ታገኛላችሁ።
ጽሑፉን ለመክፈት ወይም ቪዲዮውን ለማጫወት ሊንኩን ተጫኑ።
ጽሑፍ ከሆነ የጥናት መስኮቱ ላይ ይከፈትላችኋል።
መስኮቱን ለመዝጋት ከሥር ያለችውን ቀስት ተጫኑ።
አሁን ደግሞ "ቤተሰቦች" የሚለውን ተጫኑ።
አንዳንድ ጊዜ ወደ ሌሎች ርዕሶች የሚያመሩ ሊንኮች ይመጡላችኋል።
ከእነዚህ ርዕሶች አንዱን በመምረጥ ተጨማሪ ጽሑፎችና ቪዲዮዎች ማግኘት ትችላላችሁ።
የምርምር መርጃውን ካወረዳችሁ "ጥቅሶች" ከሚለው የምርምር መርጃው ክፍል የተወሰዱ ማጣቀሻዎችን መጽሐፍ ቅዱሳችሁ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
ለምሳሌ አንድ ጥቅስ ምረጡ።
የዕንቁ ምልክቱን ስትጫኑ በጥናት መስኮቱ ውስጥ የምርምር መርጃ ማጣቀሻዎችን ታገኛላችሁ።
እነዚህ፣ የምርምር መርጃው ካሉት ገጽታዎች ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው።
ጥናታችሁን ለማበልጸግና ብዙ መንፈሳዊ ዕንቁዎችን ለማግኘት የምርምር መርጃውን በደንብ ተጠቀሙበት።