JW subtitle extractor

መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው?

Video Other languages Share text Share link Show times

የይሖዋ ምሥክሮች አሳታፊ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ ይሰጣሉ።
ኮርሱ መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ለማወቅ ያስችልሃል።
የምትማረው ሃይማኖታዊ ወጎችን አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው።
የይሖዋ ምሥክር የመሆን ግዴታም የለብህም።
ትምህርቱን የምንሰጠው በነፃ ነው።
ለመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ለምታጠናበት ጽሑፍ ክፍያ አትጠየቅም።
ጊዜውንና ቦታውን እንዲሁም በየስንት ጊዜው የሚለውን የምትወስነው አንተው ነህ።
መጽሐፍ ቅዱስን የምትማረው በርዕስ በርዕስ ነው።
አስተማሪህ በውይይታችሁ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ አጭር ጸሎት ሊያቀርብ ይችላል።
ለአሥር ደቂቃ ብቻ ማጥናት ትችላለህ፤ ከፈለግክ ደግሞ ከአንድ ሰዓት በላይ።
ትምህርቱ ፈተና የለውም።
ምዕራፎቹ ብዙ ሥዕሎች አሏቸው፤ ቪዲዮዎችም እንዲካተቱ ተደርጓል።
ይህም ጥናቱን ቀላልና አስደሳች ያደርገዋል።
ከአስተማሪህ ጋር ከመገናኘትህ በፊት የምትወያዩበትን ርዕስ አስቀድመህ መዘጋጀት ትችላለህ።
ጥናቱን በአካል፣
በስልክ
ወይም በቪዲዮ ኮንፍረንስ ማድረግ ይቻላል።
የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ደስተኛ ሕይወት መምራት የምትችለው እንዴት አንደሆነ ትማራለህ።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ አንድ የይሖዋ ምሥክር አነጋግር።
ወይም የjw.org መነሻ ገጽ ላይ ያለውን ሊንክ ተጠቅመህ የይሖዋ ምሥክሮች እንዲያነጋግሩህ ጠይቅ።